Wednesday, February 28, 2024

https://www.facebook.com/groups/370086873800791/permalink/1316396815836454/

Thursday, February 8, 2024

#መጽሐፍ_ቅዱስ_81_ወይስ_66 ? መጽሐፍ ቅዱስ ማን ጻፈው? - - - - - - - መጽሐፍ ቅዱስ ባለቤቱ እግዚአብሔር ሲሆን ጸሐፊዎቹ ግን ከእርሱ የተላኩ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ ጸሐፊዎቹ ብዛታቸውም ከአርባ በላይ ሲሆን አንዳቸውም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ አልጻፉም፡፡ “በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” 2ጴጥ 1፡20 - - - - - - - -+- መጽሐፍ ቅዱስ አሁን በእጃችን ላይ እንዳለው በአንድ የተጠረዘ መጽሐፍ ነበር? - መጽሀፍ ቅዱስ በአንድ ወቅት በአንድ ጊዜ ተጠርዞ የተሰጠ ወይም ከሰማይ የወረደ ሳይሆን የተለያዩ ክፍሎች በተለያዩ ጸሐፍት እና ዘመናት የተጻፉ ናቸው፡፡ በጥንት ዘመን መጸሀፍት በጥቅል ተጠቅልልው ይቀመጡ እንደነበር ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡- ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ ያነበበው የነቢዩ ኢሳያስን ጥቅልል መጽሐፍ ነበረ፡- “የነቢዩን የኢሳያስን መጽሀፍ ሰጡት መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው …….. ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ፡፡ መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፡፡” ሉቃ 4፡17-20 ከዚህ ክፍል እንደምንረዳው ቅዱሳት መጻህፍት ለየብቻቸው በአንድነት ሳይጠረዙ እንደነበሩ ነው፡፡ - - - - - - - -+- ቅዱሳት መጻህፍት አሰባሰብ? -ቅዱሳት ሐዋርያት ስለ ስርዓተ ቤተክርስትያን የተለያዩ ቀኖናትን ደንግገዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ስለ ቅዱሳት መጻህፍት ነው፡፡ በ325 እ.ኤ.አ በኒቂያ በተካሄደው ጉባኤ ላይ እውነተኖቹን ቅዱሳት መጻህፍት ለመሰብሰብ በተወሰነው መሰረት ቅዱስ አትናቲዎስ በ367 ዓ.ም በ39ኛው የትንሳኤ ምልዕክቱ ላይ የቅዱሳትን መጽሐፍትን እና አይነት በአብዛኛው አስታውቋል፡፡ ከዚያም በሎዶቅያ በተካሄደ ጉባኤ እና በ393፣399 እና 419 እ.ኤ.አ በሰሜን አፍሪካ ትገኝ በነበረችው ቅርጣግና /ካርቲጅ/ በተካሄዱት ጉባኤዎች ቅዱሳት መጽሐፍትን ለይቶ ለማወቅ ጥረት ተደርጓል፡፡ የካርቴጁ ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን በአንድ ላይ መጠረዝ እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት መድብል/ጥራዝ/ ተብሎ መጠራት ተጀመረ:: - - - - - - - -+- ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳት መጻሕፍት ብዛት ሰማንያ አንድ መሆኑን ትናገራለች፡፡ ዳሩ ግን በዓለም ላይ በብዛት ተሰራጭቶ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ስልሣ ስድስት ነው፡፡ - በስልሣ ስድስቱ ውስጥ የሌሉት መጻሕፍት:- ሀ. ከ ብ ሉ ይ (2ኛ የቀኖና መጻሕፍት):- 1.መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል 2.መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ 3.መጽሐፈ ጦቢት 4.መጽሐፈ ዮዲት 5.መጽሐፈ አስቴር 6.መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ 7.መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ 8.መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ 9. መጽሐፈ ሲራክ 10.ጸሎተ ምናሴ 11. ተረፈ ኤርሚያስ 12. ሶስና. 13. መጽሐፈ ባሮክ 14. መጽሐፈ ጥበብ 15. መዝሙረ ሰልስቱ ደቂቅ 16. ተረፈ ዳንኤል 17. መጽሐፈ ኩፋሌ 18. መጽሐፈ ሄኖክ - - - - - - - ለ. ከሐዲስ ኪዳን:- 1. ትዕዛዘ ሲኖዶስ 2. ግስው ሲኖዶስ 3. አብጥሎ ሲኖዶስ 4. ሥርዓተ ጽዮን ሲኖዶስ 5. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ 6. መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ 7. ቀለሚንጦስ 8. ዲዲስቅሊያ (እነዚህ የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት አሁን በእጃችን በሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ ይህም የሆነው እያንዳንዳቸው በጣም ትልቅ መጻሕፍት በመሆናቸው ለማካተት አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ ግን ከ81 መጻሀፍት መድበን ነው የምንቆጥራቸው፡፡ ሁሉም መጻህፍት በቤተክርስትያኖች ቤተ-መጻሀፍት ውስጥ ይገኛሉ እንዲሁም ገዝቶ ማንበብ ይቻላል፡፡ - - - - - - - -+- እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መጽሕፍት ሳታጓድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትቀበላለች፡፡ ዘመናዊ ነን የሚሉ እምነቶች ግን ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌላ የለም ሲሉ ይሰማሉ፣ ለዚህም የሚጠቀሱት ዩሐንስ ራዕይ መጨረሻው ላይ ያለውን ቃል ነው። ‹‹ማን በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል››፡፡ ራእይ 22‹18 - ይህን አባባል በጥሞና ስናጤነው የዩሐንስ ራዕይን ብቻ የሚመለከት ሆኖ አናገኘዋለን፡፡ “በዚህ በትንቢት መጽሐፍ” አለ እንጂ ከዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አላለም፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “የትንቢት መጽሐፍ” ብቻ ሳይሆን የ”ወንጌል” ፣የመዝሙር፣ የመልዕክታት እና የመሳሰሉት መጽሐፍ ነው፡፡ - በተጨማሪ የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ጠፍቶ ስለነበር እንደገና ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር ገልጾለት ስለጻፈው " በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር" ብሎ የጻፈው ወጌላዊው ዮሐንስ ሳይሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው። - ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ ከመነሻው እንደዚሁ አንድ ላይ እንደተጠረዘ ሆኖ የተገኘ አይደለም፡፡ ጻሕፍቱ በተለያየ ዘመን የነበሩ እንደሆነ ሁሉ ፣መጻሕፍቱም በተለያዩ ዘመናት የተጻፉና በአንድ ወቅት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጸሐፍ ተጽፈው አልቀው በጥራዝ መልክ እንደወጡ አድርጎ በመውሰድ የዩሐንስ ራዕይን ማጠቃለያ ለሁሉም መጻሕፍት አድርጎ መውሰድ አለማወቅ ወይንም ተንኮል ነው፡፡ - - - - - - - -+- መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ፡- - ብሉይ ኪዳን በሐገራችን ቋንቋ በግዕዝ የተተረጎመው ከክርስቶስ ልደት በፊት አንድ ሺህ ዓመት ቀደም ብሎ ሲሆን ይኸውም በንግሥተ ሳባ ዘመነ መንግሥት ጊዜ ነው፡፡ - ኢትዮጵያ ከዚህን ጊዜ ጀምሮ መጻሕፍትን ጠብቃ አቆይታለች፡፡ አባቶች ምንም አይነት ጦርነት ቢነሳ ህይወታቸውን በማስቀደም መጻሕፍትን ጠብቀው አቆይተውልናል፡፡ - ከምዕራባውያን በፊት ክርስትናን ሆነ የአይሁድ እምነትን የተቀበለችው ሀገራችን በምዕራባውያን የሌሉ መጻሐፍት መገኛ ብቸኛ ሀገር ናት፡፡ ለዚህም ነው በአይሁድ ዘንድ ሆነ በሮማውያን ዘንድ በነበረው ጦርነት የጠፉ መጻህፍት ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የሚገኙት፡፡ ለዚህም መጽሐፈ ሄኖክ እና መጽሐፈ ኩፋሌ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የመጽሐፈ ሄኖክ ጥቅልል አሁን በቅርቡ በቁምራን ዋሻ ተገኝቷል፡፡ የተገኘው ጥቅልልም ሀገራችን ጠብቃ ካቆየችው መጽሐፈ ሄኖክ ጋር አንድ አይነት ሆኖ በመገኘቱ ምዕራባውያን ተርጉመው መጠቀም ጀምረዋል፡፡ - - - - - - - -+- የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት:- - የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁለት አይነት የቀኖና ክፍሎችን ያካትታል እነሱም ፕሮቶካኒካል እና ዲዩትሮካኖኒካል ይባላሉ፡፡ - (የመጀመሪያ)፡- እነዚህ መጻሕፍት የተሰበሰቡት በካህኑ እዝራ ሲሆን መጀመሪያ በቀኖና መጻሕፍትነት የተመዘገቡ ናቸው፡፡ 1ኛ. መቃብያን 2፡10 “ነህምያም የነገስትን መጻሕፍት የያዘ ቤተ መጻሕፍት አቋቁሞ ነበር“ እነዚህም መጻሕፍት በ ሶስት ይከፈላሉ እነሱም ቶራህ (አምስቱ ብሔረ ኦሪት) ፣ ነበኢም (ቀደምት ነብያት እና ደኃርት ነብያት) እና ከተቢም (ታላላቅ የታሪክ መጽሐፍትና ታናናሽ የታሪክ መጽሐፍትን ያካትታል) ተብለው ይጠራሉ፡፡ እንዲሁም - ዲዩትሮካኖኒካል የምንላቸው አይሁድ እንደ ቀኖና መጻሕፍት የማይቀበሉዋቸው ግን እንደ አዋልድ መጻህፍት የሚቀበሉዋቸው ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ -> አይሁዶች 24 የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን ብቻ ሲቀበሉ (የመጽሐፋቸው አቆጣጠር ከእኛ አቆጣጠር ይለያል) -> ፕሮቴስታንቶች 39 የብሉይ ኪዳን እንዲሁም 27 የሐዲስ ኪዳን ይቀበላሉ፡፡ -> ካቶሊኮች 46 የብሉይ ኪዳን መጻህፍት እና 27 የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት ሲቀበሉ እኛ -> ኦርቶዶክስ ተዋህዶዎች ግን 46 የብሉይ ኪዳን እና 35 የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንቀበላለን፡፡ (ከካቶሊኮች ጋር በብሉይ ኪዳን የምንቀበላቸው መጻሕፍት ላይ የአቆጣጠር እና የመጻሕፍት ልዩነት አለ፡፡) - እዚህ ላይ ከላይ በግልጽ እንደምንረዳው 81 የነበረው የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ ብዛት ቀስ በቀስ በሰዎች እየተቀነሰ እንዲሁም በነበሩት ጦርነቶች መጻሐፍቱ እየጠፉ በመምጣታቸው፣ መጀመሪያ 73 እንዲሆን በመቀጠልም ማርቲን ሉተር ሲያምንበት ከነበረው የካቶሊክ እምነት ፣ከካቶሊክ መነኮሳት ጋር በነበረው የግል ጸብ እና የፖለቲካ ጸብ (የጀርመን ዜጋ ስለነበር የአይሁዶች ጥላቻ ስለነበረው) በነበረው ቅራኔ ምክንያት 7 መጻህፍትን በገዛ ፈቃዱ ቀንሶ ዛሬ በምዕራብውያን ዘንድ በስፋት የተስፋፋውን እና የእኛን ሐገር ጨምሮ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ሀይል የሌላቸውን ሀገራት የተቆጣጠረውን የ66 መጻሐፍት ሊያስፋፋ ችሏል፡፡ - - - - - - - ።--> መናፍቃን 81 /ሰማንያ አሃዱ/ መጽሐፍ ቅዱስን የማይቀበሉባቸው ምክንያቶች እና እንዲቀበሉ የሚያስገድዳቸው ምክንያቶች እንዲሁም ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት የሉም እንዳይሉ ማስረጃዎች፡- -> ተቃዋሚዎች ከ66 ውጭ መጽሐፍ የለም ቢሉም ሐዋርያት ሆኑ ጌታ ከ81 መጻሐፍት እየጠቀሱ አስተምረዋል፡፡ ይህን እስቲ በማስረጃ እንመልከተው፡፡ _ _ _ _ _ _ _ _ማስረጃ 1. - ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር ይለናል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (ሉቃ.3፡3) - እንግዲህ ጌታችን አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ30 ዓመቱ በፊት የት ነበረ? ምን እየሰራ ነበረ? ብልን ስንጠይቅ መልሱን በ66 መጻሕፍት ውስጥ ሳይሆን በቤተክርስቲያናችን የትውፊት መጻህፍት ውስጥ እድገቱምን እንደሚመስል በዝርዝር ተጽፎ እናገኛለን፡፡ _ _ _ _ _ _ _ _ማስረጃ 2. - በማቴዎስ ወንጌል 27፡3-10 (በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን። እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ። ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ። የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው። የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ። ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት። ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ። በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው። ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ።) በዚያን ጊዜ የነቢዩ የኤርሚያስ ቃል ተፈጸመ ይለናል ይሁዳ… እንዲህ ያለው ‹‹የእስራኤል ልጆች የተስማሙበትን የክቡርን ዋጋ ሠላሳውን ብር ወሰዱ›› ይህን ቃል የምናገኘው በስድሳ ስድስቱ ውስጥ ሳይሆን በተረፈ ኤርሚስ 7፡ 2-4 ባለው ላይ ነው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ትንቢተ ኤርሚያስን ጠቅሶ ሲጽፍልን 'በነብዩ ኤርሚያስ የተባለው ብሎን ነው፡፡' ምን ተባለ ስንል ማቴዎስ ''የተባለውን'' እና ''ተፈጸመ'' ያለንን የምናገኘው መናፍቃኑ አንቀበለውም በሚሉት በ81 መጽሐፍት ውስጥ ነው፡፡ _ _ _ _ _ _ _ _ማስረጃ 3. - ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፡፡ ‹‹እንፍጠር›› ሲል ከአንድ በላይ ብዛትን ሲያመለክት 2 ወይም 4 ወይም 10 ሳይሆኑ ስላሴን /ሶስትነት/ ስስት መሆናቸውን የሚነግረን በሲራክ 2፤22 ሄኖክ 5፤38 ሄኖክ 6፤24 ሄኖክ 13፤14 እዝራ ስቱኤል 4፤56 እዝራ ስቱኤል 12፤48 ሲራክ 44፤10 በግልጽ ሥላሴ እያለ በማሳየት ነው፡፡ ክብር ለቅድስት ሥላሴ ይሁን! _ _ _ _ _ _ _ ማስረጃ 4. በሉቃስ 14:13-14 “ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ” የሚለውን ኃይለ ቃል ከጦቢት 4፡7፡10 የተገኘ ነው ‹‹ከገንዘብህም ምጽዋት ስጥ ምጽዋትም በመጸወትህ ጊዜ በገንዘብህ አትዘን፣ ከድሃም ፊትህን አትመልስ፤ እግዚአብሔርም ገጸ በረከቱን ካንተ አይመልስም፡፡›› _ _ _ _ _ _ _ማስረጃ 5. 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡2 በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ የሚለውን ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ከጦቢት 4፡12 ጠቅሶ ነው ያስተማረው የተገኘ ነው፡፡ _ _ _ _ _ _ _ _ማስረጃ 6. በዮሐንስ ወንጌል 10፡22 በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤ … ‹‹የመቅደስ መታደስ በዓል›› በሌሎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አናገኘውም ግን ቅዱስ ዮሐንስ ከመጽሐፈ መቃብያን 4 ላይ ጠቅሶ ተናገረ፡፡ _ _ _ _ _ _ _ማስረጃ 7. በ ሮሜ 13፡1 ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። የሚለው ኃይለ ቃል ከሲራክ 17፡14 የተወሰደ ነው፡፡ _ _ _ _ _ _ _ _ማስረጃ 8. አዳምና ሔዋን አቤልና ቃየልን ወለዱ፡፡ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ይላል ዘፍጥረት 4፡17 በ66ቱ መጽሐፍት ላይ ስለ አቤልና ቃየል መወለድ እንጂ ሌላ የሰው ዘር በምድር ላይ ሰለመኖራቸው ምንም አያወራም፡፡ ታድያ ይህቺ የቃየል ሚስት ከየት መጣች? ስለስዋ ምንም አይናገርም በአለም ላይ የነበሩ ሰዎች አራት ብቻ እንደነበሩ ነበር የምናነበው፡፡ የዚህን መልስ የምናገኘው በኩፋሌ 5፡8-17 ላይ ነው፡፡ _ _ _ _ _ _ _ _ማስረጃ 9. - ይሁዳ በመልዕክቱ ‹‹የሄኖክን ትንቢት ከመጽሐፈ ሄኖክ ጠቅሶ›› ጽፎታል (ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል (ይሁዳ 1፡14-15) መጽሐፈ ሄኖክ ደግሞ በስልሣ ስድስቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፡፡ ሄኖክ ትንቢት ተናገረ ብሎ ከትንቢቱ ጠቅሱ ይሁዳ በመልዕክቱ ጽፎልናል ይህም ትንቢት በሄኖክ 1፡9 ላይ በግልጹ ተቀምጦ እናገኘዋለን፡፡ እንግዲህ ይሁዳ ሄኖክ ትንቢት መናገሩን እየነገረን ተቃዋሚዎች ሄኖክ ትንቢት አልተናገረም ይሉናል፡፡እኛስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የጻፈወን ይሁዳን እናምናለን፡፡ እሱ የተቀበለውን እንቀበላለን ጥበብ አይኮረጅም (መጽሐፍ ቅዱስ ትውፊታዊ የአምላክ ቃል) - - - - - - - -+- በመጀመሪያ እስኪ መጽሐፍ ቅዱስ ትውፊታዊ መረጃ መሆኑን እንተማመን፡፡ ትውፊት ማለት ቅብብል፣ ርክክብ ወይም ውርስ ማለት ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ ውርስ ከቀደሙት አበው ለእኛ በርክክብ ደርሶናል፡፡ አንዱ ከሌላው የተቀበለውን ለሌላው አሳልፎ በመስጠት እስከ ዘመናችን የደረሰ እውነታ ነው፡፡ ትውፊት መጽሐፍ ቅዱስ ከመጻፉ በፊት ያለ የነበረ ነው፡፡ እንደውም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚሐብሔር ቃል መሆኑን አምነን የተቀበልነው የቀደሙት አባቶቻችን የእግዚሐብሔር ቃል መሆኑን በትውፊት ስላስረዱን ነው፡፡ -ለምሳሌ፡- 1-ዓለም ከተፈጠረ ሺህ 486 ዘምን መጽሐፈ ሄኖክ ተጻፈ 2- እስራሄል በግብጽ ሳሉ በፈርሆን ዘመን የኢዮብ መጽሐፍ ተጻፈ 3- 3643 ዓ.ዓ. እስራሄል ከግብጽ ወጡ በዚህ ጊዜ ኦሪት ተጻፈ፣ ወዘተ. . . . . እንግዲህ ከ1486 ዘመን በፊት የተጻፈ ህግ አልነበረም፤ በዚያ ጊዜ የነበሩ አበው ይመሩ የነበሩት ሙሉ በሙሉ በትውፊት ወይም በህገ ልቡና ነበር ማለት ነው፡፡ ከስልሳ ስድስቱ (66) መጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትየለም የምትሉ ወይም ትውፊታዊ መረጃ አንቀበልም ለምትሉ እስኪ የሚከተለውን ጥያቄ ላቅርብ _ _ _ _ _ _ _ 1- በኦሪት ዘፍጥረት አገላለጥ ቃየንም ሆነ አቤል ሁለቱም ለእግዚሐብሔር ከስራቸው ውጤት መስዋዕት አቅርዋል፡፡ ዳሩ ግን የተቀበለው የአቤልን መስዋዕት ብቻ ነው፡፡ የቃየንን መስዋዕት ያልተቀበለው ለምንድን ነው? መቼም ለአቤል አድልቶ ነው የሚል መልስ እንደማይሰጥ እርግጣኛ ነኝ ምክንያቱም እግዚሐብሔር ለሰው ፊት አያዳላም፡፡ 2- አቤል ከበጎቹ በኩራትና ከሰቡ እግዚሐብሔር መስዋእት አቅርቧል፤ ከበጎቹ መካከል በኩራትና ስቡን ማቅረብ እንደሚገባ እንዴት አወቀ? ምክንያቱም የጽሁፍ ህግና ትዕዛዝ በዘመኑ አልነበረም 3- ‹ቃየንም ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ሄኖህንምም ወለደች› ይላል፡፡ እግዚሐብሔርወንድና ሴት አድርጎ የፈጠረው አዳምንና ሄዋንን ብቻ ነው፡፡ አዳምና ሄዋን ደግሞ የወለዱአቸው አቤልና ቃየንን እንደሆነ በምዕራፍ 4 ተገልጽዋል ፤ታዲያ የቃየን ሚስት ማንነች? ከየትስ መጣች? ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከ66 መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑትን ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትንና ትውፍታዊ መረጃ መሰረት ማድረግ ይገባል ያለበለዚያ ጥያቄዎቹ የማይፈቱ እንቆቅልሽ ሆነው መቅረታቸው ነው? _ _ _ _ _ _ _ - እስኪ ደግሞ ወደ ሐዲስ ኪዳን እንሂድ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ቢያንስ ቢያንስ ለ20 ዓመታት ያህል ስለ ጌታ ይማሩ የነበሩት በቃል ነበር ምክያቱም ሐዲስ ኪዳን ገና በጽሁፍ አልተቀረጸም ነበርና በቅብብል ወይም በሰሚ ያገኙትንም እነርሱ ራሳቸው ከጌታ እደተቀበሉት አድርገው ያስተምሩ ነበር ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ጳውሎስ ነው (1 ቆሮ. 11፥23-24)፡፡ ጳውሎስ ከሐዋርያት ቃል የተማረውን ለሌሎች ደግሞ አስተላለፈ፡፡ ስለዚህም ወንጌል የሚያሰኘው በጽሁፍ መስፈሩ ብቻ ሳይሆን የሕያው የእግዚሐብሔር ቃልና የህይወት መንገድ መሆኑነው፡፡ በጌታ ጊዜ ወንጌል ገና አልተጻፈም ነበር፣ “ለሐዋርያቱም ወደ ዓለም ሒዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ”(ማር.16፥1) ይህም ሲል የሰሙት ተማሩት እንጂ በጽሁፍ ቀርጾ የሰጣቸው ወንጌል አልነበረም፡፡ _ በተጨማሪም በማርቆስ ወንጌል ም.1፥21-22 ‹ወደ ቅፍራንሆም ገቡ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማረ እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጸፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ›፡፡ ይህ የክርስቶስን ተቃዋሚዎች ራሱ ያስገረማቸው ትምህርት ምን አይነት ነበር ‹ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለእርሱ በመጻህፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጎመላቸው› ሉቃ 24-27 _ ከትንሳሄው በኋላ ለሁለቱ ደቀ መዝሙር ተረጎመላቸው የመጻህፍት ትርጓሜ በየትኛው ሀዲስ ኪዳን ላይ ይገኛል? “በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ. . . ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ” ማቴ 2፥23 ይህን የተናገረው ነቢይ ማነው? በየትኛው የትንቢት መጽሐፍ ይገኛል? ማቴ 27፥9 ‹በዚያን ጊዜ በነቢዩ ኤርምያስ የተባለው ከእስራሄል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን የተገመተውን ዋጋ ሰላሳ ብር ያዙ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሰሪ መሬት ሰጡት የሚል ተፈጸመ› ይህስ ከየት ተገኘ? በተጨማሪም ሉቃ 2፥25-32፣ 2ኛ ጢሞ 2፥ 8፣ ዕብ 12፥ 21 ፣ ራዕይ 2 ፥14፣ ዮሐ 20፥ 30 ፣ ዮሐ 21 ፥25፣ ይሁዳ 9 እንዲሁም ዮሐ 1 ፥48 ሌሎች ማሳያዎች ናቸው፡፡ _ በአጠቃላይ እነዚህ መረጃዎች ከ66ቱ መጻህፍት የማናገኛቸውና ነገር ግን ተዋህዶ እምነት በምትጠቀምበት ሰማንያ አህዱ ውስጥ ፍንትው ብለው የተጠቀሱ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህን የመሳሰሉ ፍሬ ሃሳቦች ስለተቀመጡበት ነው ሰማንያ አሃዱን ከሌላው ጋር ይጋጫል የሚባለው? _ ብርሃን ዓለም ጳውሎስ ‹እንግዲያስ ወንድሞች ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ› ያለው (2ተኛ ተሰሎንቄ 2 15)፡፡ በቃላችንም በመልእክታችንም የተማራችሁትን ‹ወግ› ያዙ ሲል ትውፊትን ማለቱ ነው፡፡ _ ፊልጵ 4፥9 ‹ከህኔ የተማራችሁትና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም እና ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል›፡፡ የቅዱስ ጳውሎሰ መልዕክት ግልጽ ነው፡፡ በፊልጵስዮስ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ከእርሱ ከአንደበቱ የተማሩትንና በጽሁፍ የተቀበሉትንም የሰሙትንም ያዩትንም ሁሉ እንዲይዙ እንደያደርጉ እንጂ የተጻፈውን ብቻ እንዲይዙና እንዲጠብቅ አልነበረም፡፡ ዛሬም እኛ በትውፊት የደረሰንን ሁሉ ልንጠብቅ መንፈሳዊ ግዴታችን ነው ፡፡ _ 2ኛ ጢሞ ‹የእግዚሐብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚሐብሔር መንፈስ ያለበትን መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ይጠቅማል›፡፡ ምክሩም ጠቃሚና አስፈላጊ መሆኑን ተዋህዶዋውያን እናምናለን፡፡ ስለዚህም በቤተክርስቲያናችን ያሉትን የእግዚሐብሔር መንፈስ ያለባቸውን ቅዱሳት መጻህፍት ሁሉ ለክርስቲያናዊ ህይወታችን እንገለገልባቸዋለን፡፡ --> በመጨረሻም ኦርቶዶክሳዊያን በቤታችን ያለን መጽሐፍ ቅዱስ:- 81: የኦርቶዶክስ 73: የካቶሊክ 66: የፕሮቴስታንት 24: የአይሁድ በሆኑንና አለመሆኑን ለይተን ተረድተን የረሳችንን የሆነውን ትክክለኛውን 81 አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስን እንጠቀም። ♥ ♥ ♥ ♥ ♥ 21 21 21 ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን አትታደስም! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር) የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!! †† † † †† ለአባ ሕርያቆስ ፤ ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለአባ ይስሀቅ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!! †† † † †† ከዋክብት የሚያመሰግኑት በስማቸውም የሚጠራቸው: የፀጋው ብዛት የማይታወቅ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!! †† † † †† ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር ( #Zerihun_Eshetu 's post in #እግዝእትነ_ማርያም_OUR_LADY_MARY #ይህች_ለዘላለም_ማረፊያዬ_ናት_መርጫታለሁና_በዚህች_አድራለሁ።መዝ-13:14 #የእግዚአብሔር_እናት_Mother_of_God እነዚህን ግሩፕ እና ፔጅ Like ያድርጉና ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ አስተምህሮዎችን ይማሩ: የነፍስ ምግብን እግዚአብሔር ያዘጋጅል። ♥ ♥ ♥ ♥ ♥ See less — with Abesha WeddingPhoto.

Friday, February 2, 2024

Biblical Truth – The Centrality of Jesus Christ DATE: 09/07/22 CATEGORY: DEVOTIONALGENERAL TAGS: BIBLICAL TRUTHDISCIPLEMAKERSDISCIPLESHIPGOOD NEWS The Bible is the story of God’s redeeming work in human history. The main focus is God’s plan of salvation through Jesus Christ, designed to redeem us and all of creation. In fact, the life and teachings of Jesus are central to shaping our interpretation of passages that are difficult or not easily understood. So, biblical truth convicts us of sin, leads us to salvation, and teaches us how to follow Jesus in daily life. We can explore biblical truth by understanding: The power and authority of the Word of God Biblical Interpretation The discipline of studying the Word of God The Centrality of Jesus Christ The Whole Bible is the Word of God. It is helpful to allow the words of Jesus to guide our understanding of the rest of the story. In fact, the life and teachings of Jesus can shape our interpretation of passages that are difficult or not easily understood. For instance, after the resurrection, two disciples were walking on the Road to Emmaus. Jesus joined them and gave them a lesson on how to interpret His own death and resurrection. He told them that the entire Old Testament had pointed to Him. Christ revealed that His teachings will help us interpret both the Old Testament and New Testament more accurately. He said to them, ‘How foolish you are, and how slow to believe all that the prophets have spoken! Did not the Messiah have to suffer these things and then enter his glory?’ And beginning with Moses and all the Prophets, he explained to them what was said in all the Scriptures concerning himself”. – Luke 24:25-27 Biblical Truth and Interpretation Centered on Jesus Here are some steps to follow as we attempt to interpret the Scriptures correctly through Christ: Allow Biblical narrative and the teachings of Jesus to carry more weight in the development of doctrine and theology. In the interpretation of any Biblical passage, check to see if Jesus made reference to that passage or Biblical issue elsewhere, and allow Jesus’ teachings to improve your understanding. Allow the clear teachings of scripture, especially the teachings of Jesus, to help you interpret the passages which are more difficult to understand. Be careful to avoid making strong theological statements based on one Biblical text which is obscure or difficult to understand. Reading and studying the Bible in Christian community will help us to interpret Scripture. He promises to be with us—“Where two or three are gathered in my name, there am I with them” (Matthew 18:20). Be obedient to the Scriptures that are clear and the truths you already know. There is no need for more if you are not willing to obey what you already understand. Growing In Understanding One of the ways we can grow in our ability to interpret the Bible Is simple. Ask your self how did Jesus interpreted passages from the Old Testament? You’ll find that many of His teachings are quotes from various Old Testament books. Many of these are taken from the books of the Torah, the Psalms, and Isaiah. Here are some good examples: When Jesus was tested in the wilderness (Matthew 4:1-11), He quoted passages from Deuteronomy 8:3, Psalm 91:11-12, Deuteronomy 6:16, and Deuteronomy 6:13. In Jesus’ first sermon (Luke 4:14-30), He quoted a section from Isaiah 61:1-2. In the Sermon on the Mount (Matthew 5-7), Jesus quoted passages from Exodus, Leviticus, and Deuteronomy Preaching Jesus from the Word of God It is clear from the Book of Acts, that the apostles had a very high regard for God’s Word. It was their conviction that if they preached the “Word of God” their message would be used by the Holy Spirit and it would have the power to convict and transform. This belief suggests that as the Word of God is preached, it extends the power and presence of the Kingdom of God. In this way, the Gospel gains power in new regions of the world. Note the following passages: (Acts 8:25) They “proclaimed the word of the Lord and testified about Jesus.” (Acts 13:33) On the Sabbath, “the whole city gathered to hear the word of the Lord.” (Acts 13:48-49) “When the Gentiles heard this, they were glad and honored the word of the Lord” and “the word of the Lord spread through the whole region.” (Acts 15:35) In Antioch, they “taught and preached the word of the Lord.” (Acts 15:36) Later, Paul said to Barnabas, “Let us go back and visit the believers in all the towns where we preached the word of the Lord and see how they are doing.” (Acts 16:32) “They spoke the word of the Lord to him and to all the others in his house.” (Acts 19:20) “In this way the word of the Lord spread widely and grew in power.” Biblical Truth When You Preach When we preach, it is possible for us to draw attention to ourselves rather than to the word of God? The goal of preaching is to testify about Jesus and for God to be glorified. Does your preaching focus on Jesus, and does it allow the power of the Word of God to be released? Global Disciples Canada is a Christian mission organization that trains local leaders living near least-reached communities to multiply disciples for Christ. One-third of our world hasn’t heard the Good News of Jesus. Yet. Global Disciples refers to these as “least-reached” people, and fewer than 10% of all missionaries work among these groups. We live in a time where many of these people are within reach of a local church. Through our simple and effective strategy of training and coaching, believers share the Gospel in their own nations and cultures. Jesus said, “Go and make disciples of all nations,” and we’re committed to doing just that. If you are looking for a Christian mission organization to partner with to become a better disciple and help make disciples, connect with us today! Centrality of Jesus Share Recent Posts New Year Bible Verses: Empowering Words for a Fresh Start Inspiring Discipleship Quotes: Gateway to a Life of Faith This collection brings together profound insights from renowned spiritual leaders, thinkers, and philosophers. For Unto Us A Child Is Born: Discover What It Really Means Get God Stories Every Month. - blog page Ordinary men and women are bringing the message of Jesus Christ to those who have never heard the name of Jesus. And they are experiencing extraordinary encounters. Sign up now and receive a monthly reminder of how God is working in the least-reached areas across the world. NAME* First Name First Last Name Last EMAIL* Enter Email Enter Email Confirm Email Confirm Email Subscribe