Wednesday, December 14, 2022

መቅድም ተአምረ ኢየሱስ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ ኢየሱስ

መቅድም ተአምረ ኢየሱስ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብስተ ሕይወት ለዘይበልዖ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ጽዋዕ መድኃኒት ለዘይጸምኦ፡ ከመ ይባርኩነ ይፈኑ አርዳኦ፡ ለጸባኢነ ይጽብኦ ወልታሁ ነሢኦ። ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑም ስምዩ ንዝጽውዖ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስተ ሕይወት’ዩ ንዝበልዖ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ መስተ መድኃኒት’ዩ ንዝጸምኦ፣ ንኽባርኹና ይፈንወልና ኣርዳኦ(ሓዋርያቱ)፣ ዋልታኡ ኣልዒሉ ንዝጻብኣና ይጻብኦ። ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአጽልእቲሁ ምስሌሁ፡ መስቀለ ሞቱ ቅድሜሁ፡ ዐዘቅተ ወይን ገቦሁ፡ ቊርባነ አምልኮ ሥጋሁ፡ ያብአነ ቤተ መርዓሁ ውስተ ደብተራሁ፡ አመ ይትጋብኡ ለምሳሕ ሥርግዋን ሐራሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ስምብራቱ ኩሉ ምስኡ፣ መስቀል ሞቱ ቅድሚኡ፣ ዒላ ወይኒ ኢዩ ገቦኡ፣ ቊርባን ኣምልኾ ሥጋኡ፣ የእትወና ናብ ኣዳራሽ መርዓኡ፣ ስሉማት ኣገልገልቱ ንምሳሕ ምስ ተጋብኡ። ለጥብሐ ሥጋከ ንሴስዮ፡ ወለነቅዐ ደምከ ንረውዮ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በግዕ ዘቀራንዮ፡ ለላህይከ ንትሜነይ ከመ ንርአዮ፡ ውስተ ስያሐ ሱራፈ ለስእለትነ ደዮ፡ ወበሕማመ ሞትከ አምላካዊ ለቍስልነ አጥዕዮ። ንጥብሓት ሥጋኻ ንሰስዮ፣ ንዝውሕዝ ደምካ ንሰትዮ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በጊዕ ናይ ቀራንዮ፣ ንውቃብ ገስካ ንምነ ንኽንርእዮ፣ ንልማኖና ናብ ምስጋና ሱራፈ ወደዮ፣ ብሕማም ሞትካ ኣምላኻዊ ንቊስልና ኣጥዕዮ። ለጥብሐ ሥጋከ ንጸግቦ፡ ወለነቅዐ ደምከ ንሰርቦ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በግዕ ርጉዝ ገቦ፡ አይሁዳዊ ከሐዲ አሚነ ሥላሴ ዘአልቦ፡ ኢተወልደ እማርያም ዘይቤለከ እመቦ፡ እህጉራተ ዓለም ለይዑድ ከመ ከልብ ርኂቦ። ንጥብሓት ሥጋኻ ንሰግቦ፣ ንምንጪ ደምካ ንሠርቦ (ንሰትዮ)፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በጊዕ ርጉዝ ገቦ፣ ኣይሁዳዊ ከሓዲ እምነተ-ሥላሴ ዘኣልቦ፣ ካብ ማርያም ኣይተወልደን ዝብለካ እንተሎ ኣህጉራት ዓለም ይኲለል ከም ከልቢ ርሂቦ(ጠምዩ)። 1 ድህሪ ንባብ ተአምረ ኢየሱስ አመ ትመጽእ ለኰንኖ ምስለ ደመ ገቦ ወአእጋር፡ አማኅፀንኩ ነፍስየ ውስተ እዴከ ክቡር፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአ ሰማያት ወምድር፡ ይትዋቀሱ በእንቲአየ ተኰርዖትከ በበትር፡ ወተሰይጦትከ ከመገብር ለኅዳጥ ብሩር። ንፍርዲ ክትመጽእ ከሎኻ ምስ ደም ገቦ ወኣእጋር፣ ነፍሰይ ኣማሕጺነ ኣሎኹ ናብ ኢድካ ክቡር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጐይታ ሰማያት ወምድር፣ ምእንታይ ይባኣሱ ምቕጥቃጥካ ብበትር፣ ምሻጥካውን ከም ባርያ ንቊሩብ ብሩር። ሃሌ ሉያ በሣህልከ ምህረትከ ኢየሱስ አድህነነ እም መከራ ስጋ ወነፍስ። ሃሌ ሉያ ብይቕሬታ ምሕረትካ ኢየሱስ ኣድሕነና ካብ መከራ ሥጋ ወነፍስ። ስብሐት ለከ ኢየሱስ በአፈ ኩሉ ውዱስ፡ ስብሐት ለከ ኢየሱስ ለዕሩቃን ልብስ፡ ስብሐት ለከ ኢየሱስ ዘኢትሠዓር ንጉሥ፡ ስብሐት ለከ ኢየሱስ ለዓለመ ዓለም ንጉሥ፡ ስብሐት ለከ ኢየሱስ ቃለ አብ ቅዱስ። ምስጋና ንዓኻ ኢየሱስ ብኣፍ ኩሉ ውዱስ፣ ምስጋና ንዓኻ ኢየሱስ ንዕሩቓን ልብስ፡ ምስጋና ንዓኻ ኢየሱስ ዘይትሠዓር ንጉሥ፡ ምስጋና ንዓኻ ኢየሱስ ንዘለዓለም ንጉሥ፥ ምስጋና ንዓኻ ኢየሱስ ቃል ኣብ ቅዱስ። 1

Mekdem teamere Iyesus መቅደም ተአምረ ኢየሱስ

ኢየሱስ ክርስቶስ፤ኢየሱስ ክርስቶስ መአዛዉ ያማረ ሽቶ ነዉ"።/ኤፌ ፭-፪/አንድም ኢየሱስ ክርስቶስ ምዑዘ ባህሪይ ነዉ።"ንዑ ንስግድ ሎቱ፤እንሰግድለት ዘንድ"/ፊል ፪- ፲/ "ወንዕቀብ ትዕዛዛቲሁ፤ትዕዛዙን እንጠብቅ ዘንድ ኑ"።"ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣዉኢነ፤ኃጢአታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ" ኑ /መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜዉ

“መኑ ይመስለከ”/መዝ ፹፰-፮/ "ዕፍረት ምዑዝ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ኢየሱስ ክርስቶስ መአዛዉ ያማረ ሽቶ ነዉ"።/ኤፌ ፭-፪/አንድም ኢየሱስ ክርስቶስ ምዑዘ ባህሪይ ነዉ።"ንዑ ንስግድ ሎቱ፤እንሰግድለት ዘንድ"/ፊል ፪- ፲/ "ወንዕቀብ ትዕዛዛቲሁ፤ትዕዛዙን እንጠብቅ ዘንድ ኑ"።"ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣዉኢነ፤ኃጢአታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ" ኑ /መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜዉ ገጽ ፹፪//ሉቃ ፭-፳፬/ ።ክፉ መአዛችንን በበጎ መአዛህ የለወጥህ። በመልዕልተ መስቀል ተሰቅለህ በወርቀ ደምህ ፈሳሽነት ወደ ገነት መንግሥተ ሰማያት ያቀረብኸን መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነህ። ውሉደ አዳም ደቂቀ አዳም የወደቀበትን የሞት የኃጢአት ዕዳ ከላዩ ለማንሳት አቅም አልነበረውም።የሰዉ ልጅ ሞቱን በሕይወት ለመለወጥ ችሎታ አልነበረውም።በባሕሪህ ምዑዝ የሆንህ አምላክ ወልደ አምላክ አንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ሁሉን ማድረግ ተችላለህ።ስለዚህም በሥልጣንህ ለአዳም ዘር የሚበጀውን ሁሉ አደረግህ። በዚህና በሌላም ቁጥር በሌለው ምክንያት ነዉ "መኑ ይመስለከ" የምንልህ::"መኑ ይመስለከ እምነ አማልክት እግዚኦ"አቤቱ አማልክት ከተባሉ በአማልክት ከተመሰሉ በመፍጠር በማሳለፍ አንተን የሚመስልህ ማነው?"/መዝ ፹፰-፮/አንተ ውእቱ ዘትገብር መንክረ፤አቤቱ ተአምራት የምታደርግ አንተ ነህ"/ሁል ጊዜ የሚያደርግውን ተአምራት ነው።አንድም ሥጋውን ደሙን መለወጡን ነው/።"አርአይኮሙ ለሕዝብከ ኃይለከ ወአድኃንኮሙ ለሕዝብከ በመዝራዕትከ''ኃይልህን ለሕዝብህ አሳየሃቸዉ በፅኑ ሥልጣንም ሕዝብህን አዳንህ። "ሖርከ ዉስተ ሲኦል ወአዕረገ ጼዋ" ወደ ሲኦል በአካለ ነፍስ ወርደህ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣህ/፩ኛ ጴጥ ፫-፲፱/።"ወጸጎከነ ምዕረ ዳግመ ግዕዛነ"ዳግመኛም ግዕዛነ ንፍስን/የነፍስን ነጻነት/ ሰጠኸን።"እስመ መጻእከ ወአድኀንከነ"ከወዲያ ዓለም ወደዚህ ዓለም መጥተህ አንድም ሰው ሆነህ አድነኸናልና።"በእንተ ዝንቱ ንሴብሐከ ወንጸርሕ ኀቤከ እንዘ ንብል ቡሩክ አንተ እግዚኦ ኢየሲስ ክርስቶስ" ሰዉ ሆነህ ስላዳንኸን አሰምተን ኢየሱስ ክርስቶስ የባህሪይ አምላክ ነህ እያልን እናመሰግንሃለን።/መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜዉ ገጽ ፺፮/ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በመዝራዕትህ ከሲኦል ግዞት ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ ያወጣኸን አንተ ነህ።አምስት ሺህ ከአምስት መቶ ዘመን በባርነት የማቀቁ ነፍሳትን ከሲኦል ሞት ነጻ ያደረግህ አንተ ነህ።ደጅ የተጠኑ ዕጣን የታጠኑ፣ወይፈን አሰዉተው፣እጅ መንሻ ሽተው፣ግብር ያስገበሩ፣አማልክት ነን ያሉ ብዙዎች አልፈዋል።ለሰዉ ልጅ ግን የበጁት አንድም ነገር የለም።"መኑ ይመስለከ"አንተን ግን ማን ይመስልሃል?የሞት ወጥመድን በመስበር የሚመስልህ ማን አለ?እዉነተኛ አምላክ የፍጥረታት ሁሉ ጌታ አንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ነህ። "ፈቀደ እግዚእ ያግዕዞ ለአዳም ሕዙነ ወትኩዘ ልብ" አምስት ሺህ ከአምስት መቶ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው ዘንድ ወደደ።/አትብላ ያለኝን ዕፀ በለስ በልቼ ከፈጣሪ ትእዛዝ ወጣሁ ብሎ ያዘነ አዳምን ነጻ ያደርገው ዘንድ ወደደ/::"ወያገብኦ ኀበ ዘትካት መንበሩ" ወደ ቀደመ ቦታዉ ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰዉ ዘንድ ወደደ።/ ክብር ቢሉ ልጅነት ቦታ ቢሉ ገነት ነዉ//የሰኞ ዉዳሴ ማርያም/።ትዕዛዝህን አፍርሶ ሕግህን ጥሶ የወደቀ አዳምን በዓይነ ምኅረት ተመለከትኸዉ።ሀዘኑን መከራውን ሞቱን አይተህ አዘንህለት።ወደ ቀደመ ርስቱ ልትመልሰው ወደድህ።መድኅን ዓለም ክርስቶስ ሆይ በሱራፊ የእሳት ሰይፍ የታጠረ ርስቱን አንተ ባትከፍትለት ማን ይመልስለት ነበር? ትዕዛዝህን በስህተቱ ለጣሰ፣በራሱ ላይ የሞት ድግስ ለደገሰ ለአባታችን ለአዳም ስትራራ ለሁላችንም ራርተሃል።የወገቡ ፍሬዎች ነንና ሁላችንን በእርሱ ዉስጥ አይተኸናል።ለዚህ ርህራሄ ለዚህ ደግነት ለዚህ ቸርነት ምሥጋና ይገባል።ለአዳም ብቻም ያይደል ለሁላችን ገነት ርስታችንን አንተ ባትመልስልን ከወዴት እናገኛት ነበር?ወደ ቀደመ ርስታችን አንተ ባትመልሰን ፍጻሜያችን እንዴት መራራ በሆነ ነበር። ሊቁ ቅዱስ አትናቴዎስ አዳም አባቱን ይጠይቃል።"ኦ አዳም ምንተኑ ለሰይናከ ዘአምጻእከ ፍትሐ ሞት ላዕሌነ" አዳም ሆይ የሞትን ፍርድ ያመጣህብን ምን አደረግንህ ምን በደልንህ።/ ቢነደዉ ቢቊጨዉያማርራል/።"ኦ አዳም ምንተኑ ረሰይናከ ዘኢኃደገነ ንትፈጋዕ በገነተ ፍግዕ በአብያተ እግዚእ"።ተድላ ደስታ በሚደረግበት በጌታ ማደሪያ በገነት ደስ ይለን ዘንድ ያልተዉኸን ምን አደረግንህ።"ኦ ሔዋን ምንተኑ ረሰይናኪ" ሔዋን ሆይ ምን አደረግንሽ ምን በደልንሽ።"ናሁ ጸልመ ሥጋነ በብዝኃ ኃጣዉዕ"።ከኃጢአት ብዛት የተነሣ አንድም በኃጢአት ብዛት ሰውነታችን በሐዘን ጠቆረ።"ኦ ሔዋን ምንተኑ ረሰይናኪ" ሔዋን ምን አደረግንሽ ምን በደልንሽ። ሊቁ አዳምና ሔዋንን ከጠየቀ በኋላ መልሶ እናንተን መክሰስ አይቻለንም እናንተ እኛን ናችሁ እኛም እናንተን ይላል።አስከትሎም "ኦ አዳም ወሔዋን አንትሙሰ ነሳህያን በተግሳጸ እግዚእ መሐሪ" ፈጽመንም እንዳንነቅፋችሁም ይቅር ባይ የሚሆን ጌታ በመጣባችሁ መከራ ንሰሐ ገብታችኋል።"ኦ አዳም ወሔዋን አንተሙሰ በአማን ድኁኃን" እናንተስ በእዉነት ድናችኋል ያለመከልከል ወደ ነበራችሁበት ወደ ቀደመ ረስታችሁ ወደ ገነት ገብታችኋል።"በደመ ዚአሁ ለዘተቤዘወክሙ" ቤዛ ሆኖ ባዳናችሁ በጌታ ደም ድናችኋል ይላል/መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው ገጽ ፫፻፲፪/። አዳምና ሔዋን ወደ ቀደመ ርስታቸዉ የገቡት ሚጠተ ነፍስ ያገኙት በአንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ነዉ።መራራው የሰዉ ልጅ የመከራ ሕይወት የጣፈጠዉ በአንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ።በተደረገልን ታላቅ የቸርነት ሥራ ምክንያት የሀዘን የመከራ እንጉርጉሯችን ወደ ምሥጋና ተለዉጧል። አንደበታችን ስለአንተ ተናጋሪ ድንቅ ሥራህን ሌትና ቀን መስካሪ ሆኗል። ለሰው ልጆች ያለህን ፅኑ ፍቅር በመሰቀል ሞት ስለገለጥኸልን በመዐልት ወበሌሊት እናመሰግንሃለን። ጌታችን ሆይ"ያብአነ ቤተ መርዓሁ ውስተ ደብተራሁ አመ ይትጋብኡ ለምሳሕ ሥርግዋን ሐራሁ"እንዳለ/መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ ፪፻፵/ የተመረጡ እድምተኞች በማዕድህ ዙሪያ በተሰበሰቡ ጊዜ እኛንም ወደ ሠርጉ አዳራሽ አግባን።ለአዳም ያደረግኸውን ምሕረት ቸርነት ለእኛም አድርግልን።ፀአዳ የለበሱ ንጽሕናቸውን በኃጢአት ያላሳደፉ ቅዱሳን በፊትህ ሲታደሙ እኛንም ይቅር እንድትለን እንማጸናለን።"ኲናኔ ሥጋ ወነፍስ" በነፍስና በሥጋ የሚፈርድ ለማዳንም ለመግደልም ሥልጣን ያለው እንዳንተ ማን አለ?መኑ ይመስለከ የሚተካከለዉ በሌለ በዚህ መለኮታዊ ሥልጣንህስ አንተን ማን ይመስልሃል? ክርስቶስ ሆይ "ሰራዬ ኃጢአት ወደምሳሴ አበሳ" ነህ ስለ ሥጋ ፣ስለ ነፍስ ስለ ጊዜዉ፣ስለ ዘላለሙ፤በውስጥ በአፍአ፣በነፍስ በሥጋ ኃጢአታችንን የምታሥተሰርይልን ነህ።"ሥርግዋን ሐራሁ"የተመረጡ የሰማያዊው ሠርግ እድምተኞችን ስናስብ እኛ ማን ነን? እንላለን።በሠርግህ አዳራሽ በዚያ ልዕልት፣ወክብርት፣መልዕልተ ፍጡራን፣መትሕተ ፈጣሪ፣ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን አለች።አማላጅነቷ ከሲኦል ሞት ያድነንና ድንግል የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ በየማንህ ትቆማለች።ወጽአ ነገሮሙ የተባሉ ደቀ ማዛሙርትህ ሐዋርያት ከጻድቃን ከሰማዕታት ሁሉ ጋር አስበ ፃማቸዉን ልትከፍላቸዉ በሠርግህ አዳራሽ ይታደማሉ።ስለ ስምህ በአላውያን ነገሥታት በመናፍቃን ጳጳሳት መከራ የተቀበሉ ሁሉ እድምተኞች ናቸዉ።"ንኡስ አነ እም አኀዉየ"ከወንድሞች ሁሉ የማንስ እኔ ባሪያህ ስለሠርግህ ሳስብ እጅግ እፈራለሁ።""አመ ትመጽእ ለኮንኖ ምስለ ደመ ገቦ አእጋር አማኅፀንኩ ነፍስየ ውስተ እዴከ ክቡር"/መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ ፪፻፵፩/በዳግመኛ ምጽአትህ ጎንህ በጦር እንደተወጋ እጆችህና እግሮችህም እንደተቸነከሩ ሆነህ ለፍርድ ስትመጣ ነፍሴ በከበረ የእጅህ መዳፍ እረፍት እንድታገኝ አደራ እልሃለሁ/እማፀንሃለሁ/ማቴ ፳፭-፴፩/።ስለ ግርፋትህ፣ሞትህ፣መራብ፣መጠማትህ ሁሉ ብለህ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ። ይቆየን See less

Thursday, November 17, 2022

ኦርቶዶክስ ኢየሱስ በቂ አይደለም ትላለች ወይ? የተሐዲሶች ትልቁ ስሕተታቸው አንድ አካል የማይለውን ብሏል ማለታቸው ብቻ ሳይሆን በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮዋን በምትፈጽምባቸው መጻሕፍት፣ የምትቀበለው የክርስቶስን ሥጋና ደም ብቻ፣ የምትጠመቀውም በወልድ ያመነ ተጠመቀ ይድናል ብላ መሆኑንና በሥርዓቶቿ ሁሉ ክርስቶስን እንደምትሰብክ መካዳቸው ነው። በኦርቶዶክስ ቤተ ክርሰቲያን የድኅነት መሠረቶችስ ምንድናቸው? አንድ ተሐዲሶ፣ አንድ ፕሮቴስታንት ስለኢየሱስ ለኦርቶዶክስ ያስተምራል? አያፍሩም?

Tuesday, September 13, 2022

Schedule a post

Schedule a post Sign in to YouTube. At the top of the page, select Create. Create post. In the box at the top: ... Click the down arrow next to Post and select Schedule Post. Choose a date, time, and time zone to publish the post. Select Schedule.

Saturday, August 27, 2022

ወንድሞችና እህቶች የአርዮሳውያኑን የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ታዘቡልኝ!!! ምንጭ <<ክብረ መላእክት በዘመናት>> አዘጋጅ ሊ/ኅ ተግባሩ አዳነ 2ተኛ እትም 2006ዓ.ም ገጽ 66 ኢያሱ 5:13-15 ቃሉ እንዲህ ይላል!!! << እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ። ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን? አለው። እርሱም፦ አይደለሁም፤ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና። ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው? አለው። የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን። አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።
Facebook ሃይማኖተ አበው የ አበው ሃይማኖት - Posts | Facebook Consulter Les images peuvent

Thursday, July 21, 2022

ጮራ: ዕቅበተ እምነት

ጮራ: ዕቅበተ እምነት: READ PDF መድሎተ ጽድቅ በመድሎተ ጽድቅ ሲመዘን ክፍል ዐምስት “መድሎተ ጽድቅ” ለተሰኘውና እንደ ስሙ ኾኖ ላልተገኘው መጽሐፍ ባለፉት አራት ተከታታይ ዕትሞች ምላሽ እየሰጠን መቈየታችን ይታወቃል። በዚህ ...

Wednesday, March 16, 2022

ቤተ-ክርስቲያን ምንድን ናት? መልስ፤ ብዙ ሰዎች ዛሬ ቤተ-ክርስቲያንን የሚረዱት እንደ ሕንፃ ነው።ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የቤተ-ክርስቲያን መረዳት አይደለም። “ቤተ-ክርስቲያን” የሚለው ቃል የመጣው ekklesia (ኢክሌሲያ) ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን፣ ትርጓሜውም “ጉባኤ” ወይም “የተጠሩ” ማለት ነው። የቤተ-ክርስቲያን ሥረ-ፍቺ ስለ ሕንፃው አይደለም፣ ስለ ሰዎች እንጂ። እሱ ውስጠ-ወይራ ነው፣ ማለትም ሰዎችን የትኛውን ቤተ-ክርስቲያን እንደሚካፈሉ ስትጠይቋቸው፣ አዘውትረው የሚገልጹት ሕንፃውን ነው። ሮሜ 16፡5 ይላል “…በቤታቸው ላለች ቤተ-ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።” ጳውሎስ የሚጠቅሰው በቤታቸው ያለችን ቤተ-ክርስቲያን ነው— የቤተ-ክርስቲያንን ሕንፃ ሳይሆን፣ የአማኞችን አካል እንጂ። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ነች፣ እሱም ራስ የሆነባት። ኤፌሶን 1:22-23፣ “ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።” የክርስቶስ አካል በሁሉም የኢየሱስ ክርስቶስ አማኞች የተሠራ ነው፣ ከጰንጠቆስጤ ቀን አንሥቶ (ሐዋርያት ሥራ 2) ክርስቶስ እስከሚመለስ ድረስ። የክርስቶስ አካል ከሁለት ገጽታዎች ነው የተሠራችው፡ 1) ሁለንተናዊቷ ቤተ-ክርስቲያን፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የግል ግንኙነት ያላቸውን ሁሉ የያዘችዋ። “አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።” (1 ቆሮንቶስ 12፡13)። ይህ ቁጥር የሚለው ማናቸውም የሚያምን ሰው የክርስቶስ አካል ብልት መሆኑን እና የክርስቶስን መንፈስ እንደማስረጃ መቀበሉን ነው። ሁለንተናዊቷ የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ደኅንነትን የተቀበሉ ሁሉ ናቸው። 2) የአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ገላትያ 1፡1-2 ላይ ተገልጻለች፡ “ጳውሎስ፣ ሐዋርያ… እና ከእኔ ጋር ያሉ ወንድሞች፣ በገላትያ ላሉት አብያተ-ክርስቲያናት።” እዚህ የምናየው በገላትያ አውራጃ በርካታ አብያተ-ክርስቲያናት እንደነበሩ ነው— አጥቢያ አብያተ-ክርስቲያናት ብለን የምንጠራቸው። ባፕቲስት ቤተ-ክርስቲያን፣ ሉተራን ቤተ-ክርስቲያን፣ ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን፣ ወዘተ…ቤተ-ክርስቲያን አይደለም፣ እንደ ሁለንተናዊቷ ቤተ-ክርስቲያን— ነገር ግን አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ነው፣ አጥቢያዊ የአማኞች አካል። ሁለንተናዊቷ ቤተ-ክርስቲያን የተሠራችው ከእነዚህ የክርስቶስ ከሆኑት እና ለደኅንነት እሱን ከሚያምኑት ነው። እነዚህ የሁለንተናዊቷ ቤተ-ክርስቲያን አባላት ከአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ኅብረት ማድረግና መንጻት ይጠበቅባቸዋል። በማጠቃለያም፣ ቤተ-ክርስቲያን ሕንፃ ወይም ክፍለ ሃይማኖት አይደለችም። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ቤተ-ክርስቲያን የክርስቶስ አካሉ ነች— ለደኅንነት በኢየሱስ ክርስቶስ እምነታቸውን ያኖሩ እነሱ (ዮሐንስ 3:16፤ 1 ቆሮንቶስ 12:13)። አጥቢያ አብያተ-ክርስቲያናት የሁለንተናዊዋ ቤተ-ክርስቲያን አባላት ስብስቦች ናቸው። አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን የሁለንተናዊቷ ቤተ-ክርስቲያን አባላት በሙላት “የአካሉን” መርሖዎች የሚተገብሩበት ነው፣ 1ቆሮንቶስ ምዕራፍ 12 ላይ ያለውን፡ ማበረታታት፣ ማስተማር፣ እና እርስ በርስ መገነባባት፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እውቀትና ጸጋ።

በዳኑ አገልጋዮችና ክርስቲያኖች ልማድ ሲገባ ( ክፍል ዘጠኝ )አገልጋዮችን አገልጋዮች ናቸው ብሎ ማመን

Wednesday, March 9, 2022

#Felegetbeb #ዓቢይ #ጾም #Eritrean orthodox tewahdo church #ፈለገጥበብ / ዓቢይ ጾም /

+++ምሥጢረ ሃይማኖት+++ ምሥጢር ማለት በዓይን የማይታይ በቃላት የማይገለፅ ከአእምሮ በላይ የሆነ ማለት ነው፣ሃይማኖት ማለትም ማመን ማለት ነው ፣ ምሥጢረ ሃይማኖት ማለት የሃይማኖት ወይም የማመን ምሥጢር ማለት ነው፣ ይህም ምሥጢር ምሥጢረ ሥላሴ ወይም የሦስትነት ምሥጢር ነው። ምንም እንኳን በቤተ ክርስቲያን ትምህርት አምስት አዕማደ ምሥጢራት፣ ሰባት ምሥጢራተ ቤተ ክር ስቲያን ቢኖሩም ቅሉ መነሻቸውና መድረሻቸው ግን ምሥጢረ ሥላሴ ነው፣ ምሥጢረ ሥላሴ ሲተነተን ሲዘረዘር ሲብራራና ሲገለጥ ሌሎቹ ምሥጢራት ይወለዳሉ ፣ ስለዚህም ሌሎቹ ምሥጢራት የምሥጢረ ሥላሴ ውላጆች ናቸው። ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ከድንግል መወለዱ ነው፣ እርሱ በሥጋ በምድራችን ሲወለድ፣ በእኛ ቋንቋ ሲናገር እንደኛ ሲበላ ሲጠጣ ሲታይ፣ ሲደክም ሲራብ ሲጠማ ሲጎሳቈል ስናየው ምሥጢራትን አየን፣ የሰማዩን ተረከልን፣የአባቱን ክብር የባህርይ ሕይወቱን የመንፈስ ቅዱስን ክብር አየንበት ፣ በመጠናችን አንጸባረቀልን፣ "ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ?" እንዳለ ዮሐ14 : 9። ቅዱስ ጳውሎስም፦ "እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ" ብሏል፣ ዕብ 1÷3 የተሰወረውን እንደዓቅማችን ገለጠልን።"ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው። የተገለጠው ግን ለዘላለሙ ለእኛና ለልጆቻችንም ነው" ዘዳ 29÷29፣ሐዋ 2÷38፣ ሉቃ 10÷21፣1ኛ ዮሐ 1÷2፣ኤፌ 3÷3 ፣3÷8፣ 1ኛ ጴጥ 1÷19—21 ምሥጢረ ሥጋዌን ስንመረምር ደግሞ ሌሎቹ ምሥጢራት ተገለጡልን፣ ምሥጢረ ጥምቀትን ሰው ሆኖ ሥጋ ለብሶ በመስቀል ተሰቅሎ ከጎኑ ባፈሰሰው ቅዱስ ውሃ አየነው፣ ምሥጢረ ቊርባንን በዕለተ ሐሙስ ሠርቶ አሳየን፣ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በርሠ መቃብር አድሮ በሦስተኛው ቀን ተነስቶ አሳየን። ሌሎቹ የአገልግሎት ምሥጢራት ደግሞ ከምሥጢረ ጥምቀት ተወለዱ(ክህነት፣ ተክሊል፣ ንስሐ፣ሜሮን፣ቀንዲል)። ይህንንም ምሥጢር ራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ አስተምሯቸዋል፣ ለሊቁ ለኒቆዲሞስም በስፋትና በጥልቀት ለብቻው በረቀቀ አገላለጥ ያስተማረውን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቦታል ዮሐ 3÷1—22፡፡ በነዚህ መሠረትነት ምሥጢረ ሥላሴን እንመረምራለን፣ እንማራለን፣ እንደ ዓቅማችን ሀልዎተ እግዚአብሔርን እንናገራለን ይህም ምሥጢረ ሃይማኖት በመባል ይጠራል። ሃይማኖት እግዚአብሔርን ከምንመረምርበት በተጨማሪ መንፈሳዊነታችንን የምናዳብርበት እንደመላእክት መኖርን የምንለማመድበት ሥርዓተ አምልኮ ነው። መሠረታዊ የቃሉ ትርጉም እምነት ከሚለው ቃል የተሻገረና ያለፈ ትርጉም የሚሰጠውም በዚህ ምክንያት ነው፣ ሃይማኖት የማይታየውን እግዚአብሔርን እንዳየነው እንደሰማነው እንደደዳሰስነውና እንደጨበጥነው አድርገን የምንናገርበት ትልቅ መሳሪያችን ነው፣ ከዚህም በላይ ሰዎች ሁሉ ልንግባባበት የሚገባን የነፍስ ቋንቋ ነው። ቅኝቶቹም፦ • ለባዊነት • ነባቢነትና • ሕያውነት ናቸው፡፡ በዚህ ቋንቋ ነው ከመላእክት ጋር የምናወራው የምንግባባውም፣ ዓለማችን ይህን ቋንቋ አያውቅም አይረዳም ፣ በዚህ ምክንያት ሃይማኖታውያን ስንሆን ዓለም ታሳድደናለች ትገፋናለች ትገርፈናለች ታሰቃየናለች ። ከጥንት ጀምሮ በዚህች ሃይማኖት ብዙዎች ደማቸውን አፍሰውባታል፣ አጥንታቸውን ከስክሰውባታል፣ ሕይወታቸውን ከፍለውባታል ይህ የሃይማኖት ምሥጢር ነው። ሃይማኖት አንዲት ናት የምንልበት ምሥጢርም ከዚህ በመነሣት ነው፡፡ "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ኤፌ 4 : 5 ። የሰማያውያን ሁሉ ቋንቋ ፣ የመላእክትና የሰዎች (የክርስቲያኖች) ኅብረት (ጉባኤ) መግባቢያ ይህች አንዲቷ የእኛ ሃይማኖት ብቻ ናት፣ ይህችም አንድ ጌታ(አንድ እግዚአብሔር) ያላት ናት ፣ ከመላእክት ጋር የተግባባነው፣ ዓለም ከጠላቸውና ካሰደዳቸው ቅዱሳን ጋር አውርተን የምንግባባውም ለዚህ ነው፣ ይህች ሃይማኖት ስላለችን፣ ሦስት መቶ አስራ ስምንቱ ሊቃውንትም ይህችን ሃይማኖት "ኦርቶዶክስ" (ርትዕት ሃይማኖት—የቀናች የተስተካከለች ሃይማኖት) ብለው መሰየማቸው በዚህ ምክንያት ነው፣ ከሰማይ የተሰጠችን ወደሰማያት የምንሄድባት ማለፊያ መሻገሪያ መንገድ፣ መግባቢያ፣ ማመስገኛ ለዘለዓለም መኖሪያ መናገሪያ ቋንቋችን ስለሆነች ነው፣ ይህችውም ጠባብ ናት ጥቂቶች ብቻ ይገቡባታል፣ ዓለመ ሥጋን ፈቃደ ሥጋን አሸንፈው ይገቡባታል፣ማቴ 7:13 የዚህች ቋንቋ ጥግ ምሥጢር ምሥጢረ ሥላሴ ነው። ሥላሴን ለማድነቅ፣ ለማመስገን ፣ ለማምለክ ፣ በዓቅም ለመመርመር ፣ ስለ ሥላሴ ለሌሎች ለመናገር ሃይማኖት ያስፈልጋል፣ ራሱ ምሥጢሩ በሃይማኖት ቋንቋነት ካልሆነ አይገለጽም ፣ ሃይማኖት ሌላ ቀመር የለውም፣ ቀመሩ ማመን ነው!!! እውነተኛነቱ የሚረጋገጠውም በማመን ነው! ሃይማኖት እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ያሰቀመጠው ኃይል ነው ፣ ይሄን ስንረዳ ዓለማችን ነዳጅ ቆፍራ ለማውጣት ከምታደርገው ጥረት በላይ እኛ እግዚአብሔርን ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን፣ እንተጋለን፣ ይህ በውስጣችን ያለው ኃይል ሲቀጣጠል በዓለም የሚቀጣጠለውን እሳት ፣ በጋን ውስጥ እንደ ክረምት ነጎድጓድ የሚፈላውን ውሃ እንረሳለን፣ ስለሃይማኖታችን ወደመከራው ለመግባት እንቸኩላለን፣ ምክንያቱም በውጪ ከሚቃጠለው ኃይል በላይ እኛ ውስጥ የሚቃጠለው(ሃይማኖት) ስለሚበልጥ። አባቶቻችን ነቢያት ከዚህ ዓለም ስላልሆኑና በውስጣቸው ያለው አግዚአብሔርን የማምለክ ዓቅም ከዓለም ረብኅ ስለበለጠባቸው ከዓለም ወጥተው ተቅበዝብዘዋል " ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ" ዕብራውያን 11 : 38፡፡ ሐዋርያትም እንዲሁ በእሳትና በስለት አልፈዋል፣ ይህም በውስጣቸው በሚነደውና በሚቀጣጠለው አምልኮተ እግዚአብሔር ምክንያት ነው፣ይህም ሕይወትን እስከማስከፈል ዓቅም ያለው የኃይል ቋንቋ ነው። በዚህ ምክንያት ሃይማኖት ራሱ ምሥጢር ተብሎ ይጠራል። የምሥጢርነቱ ማብቂያውና ጥጉ፣ መድረሻውና መጨረሻውም ምሥጢረ ሥላሴ ነው። ይህንንም ይዞ ሊቁ እንዲህ አለ:—"ሃይማኖት እንተ እምኀበ አብ ተወጥነት ወኀበ ወልድ ታበጽሕ ወበኀበ መንፈስ ቅዱስ ትትፌጸም" "ሃይማኖት በአብ ተጀምራ ወደ ወልድ ታደርሳለች፣ በመንፈስ ቅዱስም ትፈጸማለች" ሃይ አበው። ይህ የሊቁ አነጋገር ብዙ ምሥጢራትን ያቀፈ ከሀገር ከዓለም የሚሰፋ ቃል ነው፣ አብ ማለት አባት፣ ወልድ ማለት ልጅ፣ መንፈስ ቅዱስ ማለት ቅዱስ እስትንፋስ(ሕይወት) ማለት ነው ፣ ሃይማኖት የሚጀምረው አብን አባት በማለት ሲሆን አባትነቱ ለማን ነው? በሚለው ጥያቄ ደግሞ ለ"ወልድ" ወደሚለው እንደርሳለን ፣ አባት(አብ) እና ልጅ(ወልድ) እንዴት ይኖራሉ? የሚለው ጥያቄ ደግሞ መልሱ ወደ መንፈስ ቅዱስ ይወስደናል ፣ ይህም ማለት እስትንፋሳቸው መንፈስ ቅዱስ ነው የሚል የመጨረሻ መልስ እናገኛለን፣ ይህ አኳዃን እነሱ የሚገለጡበት አኗኗር ነው! ይህ ደግሞ ለእኛ ምን ጥቅም አለው ወደሚለው እንምጣ! የእኛ ተፈጥሮ ሱታፌ—ሥላሴ ያለው ነው፣ በባህርይ ሳይሆን በጸጋ ከሥላሴ ጋር አንድነት እንዲኖረን የተፈጠርን ነን። ሊቁ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ፦ "ወንበርህ በአስማተ ቅድስት ሥላሴ ዘውእቱ እምነትነ" (የሦስቱን ስም በመጥራት አዋቂዎች እንሆናለን፣ ይኸውም እምነታችን ነው) እንዳለ። አብ አካላዊ ልብ ነው፣ ወልድ አካላዊ ቃል ነው፣ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ሕይወት ነው። በእኛ በሰዎች ውስጥ በአካላዊነት ሳይሆን በዝርውነት የሚገኙ ለባዊነት፣ነባቢነትና ሕያውነት የነፍሳችን ባህርያት ናቸው ፣ እነዚህም ከሥላሴ ያለንን ሱታፌ ያሳያሉ።በለባዊነታችን አብን፣ በነባቢነታችን ወልድን፣ በሕያውነታችን መንፈስ ቅዱስን እንመስላለን! "እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።:" በማለት ሙሴ የጻፈውም ይህንን ምሥጢር ነው፣ ዘፍ1 : 26። አዳም ሲፈጠር እነዚህን አሟልቶ ፣ መልኩና አካሉ ምሉእነት ሳይኖረው ውሱን ሆኖ ተፈጠረ ፣ ይህንን መልክና አካል ፣ ጠባዕይና ባህርይ ምሳሌ ግን በኃጢአት አበላሸው ፣የተበላሸውን ለማደስ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ(ቃል) ሰው ሆነ፣ ሥጋ ለበሰ። በእርሱ ሞት በሦስቱ አካላትና(በሥላሴ) በሰው ልጆች መካከል ዕርቅ ተደረገ። ዕርቁም ሦስት ትልልቅ ነገሮችን አስገኘ፦ 1. ልጅነትን 2. ምስጋናን 3. ዘለዓለማዊነትን 1. ልጅነት:—አብን አባት ብሎ መጥራት፣ ለወልድ የባህርይ አባቱ ሲሆን ፣ወልድ የእኛን ሥጋ በመልበሱ ለእኛ የጸጋ አባታችን እንዲሆን አደረገ ፣ዮሐ1÷12፣20÷17 2. ምስጋና:—የነበረብን የጥል ግድግዳ ፈርሶ "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ………) ብሎ ከመላእክት ጋር ማመስገን፣ ቃል ወልድ ሰው ስለሆነልን በኢመዋቲ ልሳን ማመስገን። 3. ዘለዓለማዊነት:—የማንሞት ፣የማንፈርስ የማንበሰብስ ሆነን መነሣት እነዚህ ሁሉ ከሦስቱ አካላት ጋር በጸጋ ያገኘናቸው ሱታፌዎች ሲሆኑ "አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ" (አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ) ዘፍ 3÷22 ብሎ ራሱ ባለቤቱ የተናገረው በባህርይ ሳይሆን በጸጋ እንደተፈጸመልን ያጠይቃል፣ሃይማኖታችን ከአብ ጀምሮ (በመወለድ) በመንፈስ ቅዱስ (በዘለዓለማዊ ሕይወት) ይታተማል!!! ይህ ምሥጢረ ሃይማኖት ይባላል፡፡፡ ሊቁ ይህን ሲያይ "በመንፈስ ቅዱስ ትፈጸማለች አለ!" ለዚህም ነው ሃይማኖት ሰማያዊ ዘለዓለማዊ ቋንቋ ነው ያልነው፣ ሁሉ ሲያልፍ ፣ ጠፈርና ምድር ድራሻቸው ሲጠፋ ሃይማኖት የሰውና የመላእክት የልጅነት፣የምስጋና የዘለዓለማዊ ሕይወት ቋንቋ ሆኖ ይቀጥላል ፣ ጌታም እንዲህ አለ:—"ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም" ማቴ 24÷35 "ቃሌ" ያለው ሃይማኖት መሆኑን ልብ ይሏል፣ ለኒቆዲሞስ ያስተማረው ራሱ ነውና፣ ዮሐ 3÷1—12። ይህን ቀጥተኛና ዘለዓለማዊ ሕይወት የምታስተምረን ይህች "ሐዋርያዊት፣ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን" ናት ፣ ዛሬ በዓለም ብዙ ነገሮች እየተሰሙ ነው፣ ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች እንጂ ሃይማኖት አይደሉም ፣ ሃይማኖት በህዝብ ቁጥር ልክ ሳይሆን በሰው ልክ ነው፣ ሰው ደግሞ አንድ ነው!! ሃይማኖትም አንድ ነው! ሃይማኖት ዘመንአመጣሽ አይደለም፣ ሥላሴ ዘመን አመጣሽ ስላልሆኑ! ምሥጢረ ሥላሴ በዘመን ስለማይለካ! ትውልድ ሃይማኖቱን ሊከተለው ይገባል እንጂ ሃይማኖቱ ትውልድን አይከተለውም፣ እንዲያ ከሆነ ሰው የሥላሴ ተከታይ መሆኑ ቀርቶ ሥላሴ የሰው ተከታይ ሆኑ እንደማለት ይሆናል፣ ለዚህም ነው ሰው ሃይማኖቱን መለወጥ የሌለበት፣ ሃይማኖት ማንነታችን ስለሆነ! ሃይማኖት አንድ ጊዜ የተሰጠ መሆኑንንም ሐዋርያው ይሁዳ ሲመሰክር እንዲህ ብሏል " ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ" ይሁዳ 1 : 3 ሃይማኖት ምን ማለት እንደሆነ ስንረዳ ስናውቅ ፣ ማንነታችንና በውስጣችን እየተቀጣጠለ ፣እየተብላላ የሚኖር ተፈጥሯዊ ኃይል መሆኑን ስናውቅ ለእግዚአብሔር እናድራለን፣ ክርስተያናዊ ሥራም እንሰራለን ፣ መንግሥቱንና ጽድቁን እንወርሳለን። ሃይማኖት በቃል የሚጠና ብቻ ሳይሆን በተግባር እስከሞት ድረስ በሚከፈል ዋጋ የሚገለጥ በመሆኑ ብቻውን ጥቅም እንደሌለው ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክት ነግሮናል ፣ " እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።" የያዕቆብ መልእክት 2 : 17፡፡ (ተሻሽሎ በድጋሚ የተለጠፈ) አምላካችን እግዚአብሔር በሃይማኖት ፀንተን ምግባር ትሩፋት ሠርተን የመንግሥቱ ወራሾች አንድንሆን ይርዳን! የሞቱትን ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር!!! መዋዕለ ጾሙን በሰላም ያስፈጽመን አሜን!!! ነቅዐ-ጥበብ ከፍያለው ዘመካኒሳ ሚካኤል See less