Thursday, December 31, 2020
Monday, December 28, 2020
Sunday, December 27, 2020
Thursday, December 24, 2020
Wednesday, December 23, 2020
«ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም»መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4፡7 በማለት ጠቢቡ ሰሎሞን ከመዝሙራት ሁሉ በሚበልጥ መዝሙሩ የዘመረላትን እመቤታችንን «ጥንተ አብሶ» /የቀደመ በደል/ እንዳልደረሰባት ቤተክርስቲያናችን መፅሐፍ ቅዱስን እና የጥንታውያን አባቶችን ትምህርት መሰረት አድርጋ ታምናለች ፡፡
«እመቤታችን አዳም በጥንተ ተፈጥሮው ሳለ /ከመበደሉ በፊት/ የተቀዳች ዘር ናት፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ...»ኢሳ 1፡9 እንዲል፡፡ ጌታችንም ይህን ንጹሕ ሥጋ ነው የተዋሐደው፡፡ የተአምረ ማርያም መቅድም «እመቤታችን አስቀድማ በአምላክ ሕሊና ትታሰብ ነበረ» ማለቱም ምክንያተ ድኂን ያደረጋት ንጹሕ ዘር መሆኗን ነው የሚገልጠው፡፡
አነጻት፣ ቀደሳት የሚሉት ቃላት የሚገልጡት አሳብ አንድ ነው፡፡ አስቀድሞ ያዘጋጃት የመረጣት እናት መሆኗን ብቻ፡፡ ቅዱስ ያሬድ «ማርያምሰ ተሃቱ እምትካት ውስተ ከርሡ ለአዳም ከመባሕርይ ፀዐዳ፤ ማርያም አስቀድሞ በአዳም አካል /ባሕርይ/ ውስጥ እንደ ዕንቁ ታበራለች፡፡» እንዲል፡፡ አዳምና ሔዋን በጥንተ ተፈጥሮ ሳሉ ካልበደለ ዘር የተቀዳች ንጹሕ መሆኗን በነጭ እንቁ መስሎ ተናግሮላታል፡፡
ሊቁ ቅዱስ ሳዊሮስ ደግሞ በሃይማኖተ አበው «መንፈስ ቅዱስ አቀባ እም ከርሠ እማ፤ መንፈስ ቅዱስ በእናቷ ማኅፀን ጠበቃት» ነው የሚለው፡፡ ሊቃውንቱ አንድ ትምህርት ያላቸው ናቸው፡፡ ቅዱስ ያሬድ «አንጺሖ ሥጋሃ ሃደረ ላእሌሃ» ያለውን ትርጉም ለመስጠት የቅዱሳን አባቶችን ትምህርትና እምነት መረዳት ያሻል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከላይ በዕንቁ መስሎ በአዳም ባሕርይ ውስጥ ታበራለች ያላትን እናት ደርሶ ሌላ ይላታል ማለት አይቻልም፡፡ ብዙዎቹን ወደ ስህተት የከተተው የቋንቋ ችግር ነው፡፡ ቋንቋ ንባብ እንጂ ምስጢር አይደለም፡፡ ፊደል ይገድላልና፣ ትርጓሜ /ምስጢር/ ግን ሕይወትን ይሰጣል፡፡ «አንጺሖ ሥጋሃ ሀደረ ላእሌሃ» መረጠ፣ አከበረ፣ ቀደሰ፣ ለየ እና አደረባት የሚል ነው፡፡ ሊቁ ስለ ሰንበተ ክርስቲያን ክብር የተናገረው ለዚህ አስረጅ ይሆናል፡፡ «ቀደሳ ወአክበራ ወዐልዓላ እምኩሎን መዋእል» ምን ማለት ነው፡፡ ሰንበተ ክርስቲያንን ለያት፣ አከበራት ማለት ነው፡፡ «ንጹሕ አነ እምደሙ ለዝ ብእሲ፤ እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ» ስንልስ ልዩነኝ አይመለከተኝም ማለታችን ነው፡፡ ስለዚህ ሊቁ «አንጺሖ ሥጋሐ» ያለው «ሥጋዋን ከአዳም ለይቶ አነጻ ቀደሰ ለየ» ማለት እንደሆነ ቤተክርስቲያናችን ታምናለች፡፡
በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው መጽሐፍ የእመቤታችንን ንጽሕናና ቅድስና አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያናችን ያላትን አስተምህሮና አቋም እንዲህ ያስረዳል፡፡ «አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጢአት /ጥንተ አብሶ/ ያላገኛት፤ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት፤ ገና ከመውለዷ አስቀድሞ በአምላክ ሕሊና ታስባ ትኖር የነበረች፤ በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ አሳብና ፈቃድ ሁሉ የተጠበቀች፤ ከተለዩ የተለየች ንጽሕት ቅድስተ ቅዱሳን ናት ይላል፡፡ /መሐል. 4፥7/፡፡» /የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና የውጪ ግንኙነት፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ድርጅት፣ 1988 ዓ. ም./፡፡
ቀደም ባሉት ዓመታት በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሊቃውንት ጉባኤ አባል እና ጸሐፊ በመሆን ያገለግሉ የነበሩት መምህር ሀብተ ማርያም ተድላ፤ የወላዲተ አምላክን ቅድስና እና ንጽሕና የበርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ጠቅሰው ባስረዱበት መጽሐፋቸው እንዲህ ብለዋል፡ «አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኀጢአት /ጥንተ አብሶ/ ያላገኛት ለመሆኗ በቅዱሳት መጻሕፍት የተረጋገጠ ነው፡፡ «መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው፣ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት...» /ሉቃ. 1፥28-38/ ይህ አባባል፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እርሷ ከመላኩ በፊት ጸጋን የተሞላችና የተባረከች መሆኗን በማያጠራጥር ሁኔታ ነው የሚገልጸው፣ ምክንያቱም መልአኩ ሰላምታውን በኃላፊ እንጂ በትንቢታዊ ግሥ አላቀረበምና፤ ወደፊት ጸጋ ይመላብሻል ከሴቶችም ሁሉ የተባረክሽ ትሆኛለሽ አላላትም፡፡ እንደገና መልአኩ በሰላምታ መደንገጧን አይቶ... «ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን /ባለሟልነትን/ አግኝተሻልና አትፍሪ...» አላት፡፡ አሁንም የመልአኩ ማረጋጊያ ዐረፍተ ነገር እንደ ኃላፊ እንደ ትንቢት አይደለም፤አግኝተሻል አላት እንጂ ወደ ፊት ታገኛለሽ አላላትም፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየው እመቤታችን ከመፀነሷ በፊት ወይም ወደዚህ ዓለም ከመምጣቷ በፊት ጀምሮ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያልነበረባት መሆኑን ነው፡፡» /ነጭ ዕንቁ በአዳም ገላ፤ በመምህር ሀብተ ማርያም ተድላ፤ አዲስ አበባ 2002 ዓ.ም፤ ገጽ. 43/፡፡
ልበ ብርሃኑ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ /ሊቀ ጠበብት/ «ምልጃ እርቅና ሰላም» በተሰኘው መጽሐፋቸው፤ «ለእናትነት የመረጣትን ማደሪያውን ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ ከኀጢአት ከርኩሰት ከእድፈት ሁሉ ጠብቋታል፡፡ የሰው ልጆች በተያዙበት በአዳም በደል ወይም በራሳቸው በደል ምክንያት የረከሱበት የኀጢአት ቅሪት መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የለባትም፣ አላገኛትም፤ ምክንያቱም እርሱ ራሱ ማደሪያ አድርጎ ስለመረጣት» በማለት አብራርተዋል፡፡ /ምልጃ እርቅና ሰላም፤ አለቃ አያሌው ታምሩ፤ አዲስ አበባ፤ ገጽ 49/፡፡
ወላዲተ አምላክ የውርስ ኃጢአት አለባት ማለት ጽርፈት ሆኖ ሳለ፤ ጥንተ አብሶ /መርገመ ሥጋ ወነፍስ/ በመልአክ ብሥራት ራቀላት ማለትም ከፍተኛ የሆነ የነገረ ሃይማኖት ስሕተት ውስጥ የሚጨምር ነው፡፡ የመልአክ ብሥራት የቀደመ በደልን /ጥንተ አብሶን/ የሚያርቅ ከሆነ በብሥራተ መልአክ የፀነሱ እመው /እናቶች/ የሶምሶን እናት፣ የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ... ምነው ከጥንተ አብሶ ያልነጹ ? በዚያውስ ላይ የወልደ እግዚአብሔርን ሞት ከንቱ አያደረገውምን ? የኑፋቄ ትምህርቶች መሠረታዊ ችግር አንዱን ጥቅስ ብቻ መዞ መነሣት ብቻ አይደልም፡፡ አንዱ ስሕተት ማለቂያ ወደ ሌለው ክህደት የሚጨምር መሆኑ ነውና ራሳችንን በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ጠብቀን ልናቆይ ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ አባል የሆኑት መልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን የወላዲተ አምላክን ንጽሕና በመሰከሩበት ቃል፡- «... ከዚህ ዓለም ቅዱሳንና ቅዱሳት መካከል እንደ እመቤታችን ያለ፤ በእርሷ መጠን ጸጋን የተመላ፤ በንጽሕናና በቅድስና የተዋበ፤ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነና በልዑል ኃይልም የተጠበቀ ሰውነት ያለው /ሉቃ. 1፥28-36/ የለም፡፡ ይኸውም እመቤታችን ለአምላክ እናትነት የተመረጠች ድንግል በመሆንዋና እንዲሁም የአምላክ እናት እንደ መሆንዋ መጠን በሐልዮ፤ በነቢብና በገቢር ሁሉ ንጽሐ ጠባይዕ ያላደፈባት ቅድስትና ቡርክት በመሆንዋ ነው፡፡ ስለዚህ ራስዋ አስቀድማ በወንጌል ቃል እንደተናገረችው፤ ትውልድ ሁሉ «ቅድስት ወብፅዕት» እያለ ሲያመሰግናት ይኖራል፡፡ ሉቃ. 1፥48፡፡»/ ሰአሊ ለነ ቅድስት የነገረ ማርያም ትምህርት፤ ክፍል አንድና ሁለት፤ የማእዶት መጽሔት ልዩ እትም፤ 1993 ዓ. ም. 2ኛ እትም፤ ገጽ 48/፡፡
«ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌል ቢሰበክላችሁ የተረገመ ይሁን፡፡» እንደተባለ፡፡ /ገላ.1፥8 እና 9/፡፡ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲ ያናችን ካስተማረችን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትምህርት ውጪ አዲስ /የተለየ፣ የኑፋቄ/ ትምህርት የሚያስተምሩ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ለይተን በማወቅ የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርት ጠንቅቀን ልንጠብቅ ያስፈልጋል፡፡ የተለየ የኑፋቄ ትምህርትን ከሚዘሩ መስሕታን /አሳቾች/ ርቀን በሃይማኖት ጸንተን ምግባር ትሩፋት ሠርተን መንግሥቱን ለመውረስ ስሙን ለመቀደስ የእግዚአብሔር ቸርነት የወላዲተ አምላክ አማላጅነት አይለየን፡፡
ይቆየን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Monday, December 21, 2020
Saturday, December 19, 2020
ጸሎተ ሃይማኖት (የሃይማኖት ጸሎት)
Thursday, December 17, 2020
Monday, December 14, 2020
Sunday, December 13, 2020
Useful Bible Studies > 1 Corinthians Commentary > chapter 15
Be careful about your friends
1 Corinthians 15:33-34
We have seen that the Christians in Corinth were doing many wrong things. Let us think about the cause of this wrong behaviour.
Clearly, the basic cause was wrong attitudes. Those Christians cared too much about their own desires, their own feelings, and their own gifts. That is, they cared too much about themselves. That was why they were not showing love towards each other. The result was that they were not obeying God.
Clearly, those wrong ideas did not come from their knowledge of God. The Bible did not teach them to do such things. There had to be another cause, and in 1 Corinthians 15:33, Paul mentions that cause. Those Christians had chosen friends who were evil.
We may ask whether Paul has mentioned this problem earlier. Perhaps he has. In 1 Corinthians 8:10, he said that they were joining people from evil religions, to eat together. In 1 Corinthians 1:18-23, he urged them not to care whether other people approved of them.
However, perhaps these wrong friends were other church members, who belonged to the powerful groups in their church (1:11-13). These groups were causing the Christians to argue fiercely, and even to take other Christians to the judges (3:3; 6:6).
The people who had no knowledge of God in 1 Corinthians 15:34 were church members. Otherwise, there would be no reason for the Christians to be ashamed. Perhaps those people knew about God, but they knew nothing about his character. They had not learned from him how they should live.
It is not wrong to have friends who do not know God (10:27). However, it is very wrong and foolish for a Christian to copy their evil behaviour.
Next part: How can a dead body live again? (1 Corinthians 15:35-36)
Please use the links at the top of the page to find our other articles in this series. You can download all our articles if you go to the download page for our free 450 page course book.
© 2014, Keith Simons.
Saturday, December 12, 2020
Friday, December 11, 2020
Thursday, December 10, 2020
Wednesday, December 9, 2020
Tuesday, December 8, 2020
ግሩም ምክር ነው እባካቹ አንብቡት ትጠቀሙበታላቹ
Monday, December 7, 2020
Sunday, December 6, 2020
Friday, December 4, 2020
Thursday, December 3, 2020
Tuesday, December 1, 2020
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለመልአኩ ዜና ብስራት በሰጠችው ቃለ ተአምንሮ ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር ከጥንት ያሰበውና የፈቀደው ያድህነተ ዓለም ሥራ እንዲፈጸምና አማናዊ እንዲሆን አድርጋለች :: ይህም ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ታላቅ ሱታፌ በጉልህ ያሳያል :: ይህንን ምሥጢር በተመለከተ ኢትዮጵያዊው ሊቅ በድርሰቱ "" ዘበቃለ ጉሕሎቱ ለሰይጣን መልአክ ስሕተት ተሰፍሐ ግላ ጽልመት ውስተ ኩሉ ዓለም :ወበቃለ ብሥራቱ ለገብርኤል መልአክ ጽድቅ ተሰፍሐ ብርሀነ ሕይወት ውስተ ኩሉ ዓለም : የስሕተት አለቃ በሆነው በሰይጣን የክፋትና የጥፋት ቃል ምክንያት የጨለማ መጋረጃ በዓለም ሁሉ እንደተዘረጋ : የእውነት መልአክ በሆነው በቅዱስ ገብርኤል የምሥራች ቃል ደግሞ የሕይወት ብርሀን በዓለም ሁሉ ተዘረጋ በማለት መስክሯል :: ኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም እመቤታችን በነገረ ድህነት ውስጥ ያላትን ልዩ ሥፍራ ሲናገር "" በእንተ ተሠግዎቱ ለወልደ አምላክ እምኔኪ ቀሩባነ ኮነ እምድር ውስተ አርያም :ብኪ ወበከመ ወልድኪ "" ብሏል :: የዚህ ኃይለ ቃል ትርጉዋሜ ምሥጢርም ቃለ እግዚአብሔር ወልድ ከሥጋሽ ሥጋ :ከነፍሥሽ ነፍስን ነሥቶ ካንቺ ሰው በመሆኑ ከምድር ወደ ሰማይ :ከሞት ወደ ሕይወት : ከመርገም ወደ በረከት : ከኃሳር ወደ ክብር : ከሲኦል ወደ ገነት የተሸጋገርንብሽ ማለት ነው :: ከላይ የተጠቀሰውን በቃዲምት ሔዋንና በዳግሚተ ሔዋን መካከል ያለውን ምሥጢራዊ ንጽጽር አስመልክቶ
'' ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ ""በመባል የሚታወቀው ሊቁ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲገልጽ "" ለእመ ኃሠሥላ ለሔዋን ትረክባ በህየ እንዘ ትትፌሣሕ በወለታ ዘእምጽአት ፈውሰ ለቁስሊሀ : ለእመ ኃሠሦኮ ለአዳም ረክቦ በህየ እንዘ ይትፌሣሕ ወይገብር በዓለ ምስለ ዳግማዊ አዳም "" በማለት በንጽጽሩ ውስጥ ያለውን ጥልቅና ረቂቅ ምሥጢረ ድህነት አስተምሯል :: እንደ ሊቁ አገላለጽ ዳግሚት ሔዋን የተባለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍሬ ሕይወት ወመድኃኒት የሆነው ጌታ የተገኘባት አማናዊት ዕጸ ሕይወት በመሆኗ የዕጸ በለስን ፍሬ በልታ ሞትን ላመጣችብን ለቀዳሚቷ ሔዋን ካሣ ናት :: ምክንያቱም ከዳግሚት ሔዋን ከድንግል ማርያም የተወለደው የማኅጸኗ ፍሬ ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሚያርቅ :በረከተ ሥጋ :በረከተ ነፍስን የሚያድል ሕይወተ ሥጋን ሕይወተ ነፍስን የሚሰጥ : ቀዳሴ ሥጋ ወነፍስ ወመንፈስ የሆነ ቡሩክ አምላክ ነውና ::
ሥርዓተ ማሕሌት ዘልደት
Print Emailረከብኪ ሞገሰ መንፈሰ ቅዱሰ ወኃይለ ሰአሊ አስተምህሪ ለነ ማርያም ወልድኪ ሳህሎ ይክፍለነ ።
ኀበ ተርህወ ገነት ወሃበ ተነጽፈ እረፍት ይክፍለነ ነሃሉ ውስተ በአቶሙ ለቅዱሳን (ሦስት ጊዜ በአራራይ በል) ።