Friday, December 20, 2024
Friday, November 8, 2024
Saturday, October 19, 2024
Friday, October 18, 2024
Tuesday, October 15, 2024
Friday, September 6, 2024
*** ትንሣኤ ክርስቶስ በሊቃውንት አንደበት ***
*** እንኳን ለጌታችን እና መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሳኤ በሰላም አደረሰን !! ***
*** ትንሣኤ ክርስቶስ በሊቃውንት አንደበት ***
በየጊዜያቱና በየዘመናቱ የተነሡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ከዚህ ቀጥሎ የተገለጠውን ትምህርትና ምስክርነት ሰጥተዋል፤
“ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ሲኦልን ረግጦ፣ በሞቱ ሞትን አጠፋው፤ በሦስተኛው ቀንም ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ‹አባት ሆይ አመሰግንሃለሁ፥› ብሎ ሥግው ቃል አመሰገነ፤” (እልመስጦአግያ ዘሐዋርያት ፭፥፩)፡፡
“እንደ ሞተ እንዲሁ ተነሣ፤ ሙታንንም አስነሣ፡፡ እንደ ተነሣም እንዲሁ ሕያው ነው፤ አዳኝ ነው፡፡ በዚህ ዓለም እንደ ዘበቱበት፣ እንደ ሰደቡት እንዲሁ በሰማይ ያሉ ዂሉ ያከብሩታል፤ ያመሰግኑታል፡፡ ለሥጋ በሚስማማ ሕማም ተሰቀለ፤ በእግዚአብሔርነቱ ኃይል ተነሣ፡፡ ይኸውም መለኮቱ ነው፡፡ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ማረከ፤” (ቅዱስ ሄሬኔዎስ፣ ሃይ. አበ. ፯፥፳፰-፴፩)፡፡
“እንዲህ ሰው ኾኖም ሰውን ፈጽሞ ያድን ዘንድ ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፡፡ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤” (ዘሠለስቱ ምዕት ፲፱፥፳፬)፡፡
“ሞትን ያጠፋው፤ ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ የሞት ሥልጣን የነበረው ዲያብሎስን የሻረው እርሱ ነው፡፡ ሰው የኾነ፤ በሰው ባሕርይ የተገለጠ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያደረበት ዕሩቅ ብእሲ አይደለም፡፡ ሰው የኾነ አምላክ ነው እንጂ፡፡ ፈጽሞ ለዘለዓለሙ በእውነት ምስጋና ይገባዋል፤” (ቅዱስ አትናቴዎስ፣ ሃይ. አበ. ፳፭፥፵)፡፡
“ሥጋው በመቃብር ያሉ ሙታንን አስነሣ፤ ነፍሱም በሲኦል ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን ፈታች፡፡ በዚያም ሰዓት የጌታችን ሥጋው በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ መቃብራት ተከፈቱ፤ ገሃነምን የሚጠብቁ አጋንንትም ባዩት ጊዜ ሸሹ፡፡ የመዳብ ደጆች ተሰበሩ (ሊቃነ አጋንንት፣ ሠራዊተ አጋንንት ድል ተነሡ)፡፡ የብረት ቍልፎቿም ተቀጠቀጡ (ፍዳ መርገም ጠፋ)፡፡ ቅድስት ነፍሱ በሲኦል ተግዘው የነበሩ የጻድቃን ነፍሳትን ፈታች፤” (ዝኒ ከማሁ፣ ፳፮፥፳-፳፩)፡፡
“ሥጋ ከመለኮቱ ሳይለይ በመቃብር አደረ፡፡ ነፍሱም ከመለኮት ሳትለይ በገሃነም ተግዘው ለነበሩ ነፍሳት ደኅነትን ታበስር ዘንድ፤ ነጻም ታደርጋቸው ዘንድወደ ሲኦል ወረደች፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተናገረው ቃል ዐፅም ሥጋ ወደ መኾን ፈጽሞ እንደ ተለወጠ የሚናገሩ የመናፍቃንን የአእምሮአቸውን ጕድለት ፈጽመን በዚህ ዐወቅን፡፡ ይህስ እውነት ከኾነ ሥጋ በመቃብር ባልተቀበረም ነበር፡፡ በሲኦል ላሉ ነፍሳት ነጻነትን ያበሥር ዘንድ ወደ ሲኦል በወረደ ነበር እንጂ፡፡ ነገር ግን ከነፍስና ከሥጋ ጋር የተዋሐደ ቃል ነው፡፡ እርሱ የሥጋ ሕይወት በምትኾን በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ለነፍሳት ነጻነትን ሰበከ፡፡ ሥጋው ግን በበፍታ እየገነዙት በጎልጎታ በዮሴፍ በኒቆዲሞስ ዘንድ ነበረ፤ ቅዱስ ወንጌል እንደ ተናገረ፡፡ አባቶቻችን ‹ሥጋ በባሕርዩ ቃል አይደለም፤ ቃል የነሣው ሥጋ ነው እንጂ› ብለው አስተማሩን፡፡ ይህን ሥጋም ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ቶማስ ዳሠሠው፤ በሥጋው ሲቸነከር ቃል ታግሦ የተቀበለውን የችንካሩን እትራትም በእርሱ አየ፤” (ዝኒ ከማሁ፣ ፴፥፴፩-፴)፡፡
“አሁን እግዚአብሔር ‹ሞተ› ሲል ብትሰማ አትፍራ፤ ‹የማይሞተውን ሞተ ሊሉ አይገባም› ከሚሉ ዕውቀት ከሌላቸው፤ ሕማሙን፣ ሞቱን ከሚክዱ መናፍቃን የተነሣ አትደንግጥ፡፡ እኛ ግን በመለኮቱ ሞት እንደሌለበት፤ በሥጋ ቢሞትም በመለኮቱ ሥልጣን እንደ ተነሣ እናውቃለን፡፡ ሞት የሌለበት ባይኾንስ ኖሮ በሥጋ በሞተ ጊዜ ሥጋውን ባላስነሣም ነበር፤ ሥጋው እስከ ዓለም ፍጻሜ በመቃብር በኖረ ነበር እንጂ፤” (ቅዱስ ባስልዮስ፣ ሃይ. አበ. ፴፬፥፲፯-፲፰)፡፡
“ከመስቀሉ ወደ ሲኦል በመውረዱ አዳነን፤ በአባታቸው በአዳም በደል በሲኦል ተግዘው የነበሩ ጻድቃንን ፈታ፡፡ ከሙታን ተለይቶ አስቀድሞ በተነሣው በእውነተኛ ትንሣኤውም አስነሣን፤ የንስሐንም በር ከፈተልን፤” (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣፴፮፥፴)፡፡
“በአባታችን በአዳም በደል የተዘጋ የገነት ደጅን የከፈተልን፤ ዕፀ ሕይወትን የሚጠብቅ ኪሩብንም ያስወገደው፤ የእሳት ጦርን ከእጁ ያራቀ፤ ወደ ዕፀ ሕይወት ያደረሰን እርሱ ነው፡፡ ፍሬውንም (ሥጋውን፣ ደሙን) ተቀበልን፡፡ አባታችን አዳም ሊደርስበት ወዳልተቻለው፤ በራሱ ስሕተት ተከልክሎበት ወደ ነበረው መዓርግ ደረስን፡፡ ክፉዉንና በጎዉን ከሚያስታውቅ፤ ወደ ጥፋት ከሚወስድ፤ በአዳምና በልጆቹም ላይ ኃጢአት ከመጣበት ከዕፀ በለስ ፊታችንን መለስን፤” (ዝኒ ከማሁ ፴፮፥፴፰-፴፱)፡፡
“የሕይወታችን መገኛ የሚኾን የክርስቶስ ሞት የእኛን ሞት ወደ ትንሣኤ እንደ ለወጠ እናምናለን፡፡ ክርስቶስም ሞትን አጥፍቶ የማታልፍ ትንሣኤን ገለጠ፤ እንደ ተጻፈ፣ ከሰው ወገን ማንም ማን ሞትን ያጠፋ ዘንድ፣ ትንሣኤንም ይገልጣት ዘንድ አይችልም፡፡ ዳዊት ‹በሕያውነት የሚኖር፤ ሞትንም የማያያት ሰው ማነው? ነፍሱን ከሲኦል፤ ሥጋውን ከመቃብር የሚያድን ማን ነው?› ብሎ እንደ ተናገረ፤” (ቅዱስ አቡሊዲስ፣ ሃይ. አበ. ፵፪፥፮-፯)፡፡
“በመለኮትህ ሕማም፣ ሞት የሌለብህ አንተ ነህ፤ በሥጋ መከራ የተቀበልህ አንተ ነህ፤ ከአብ ጋር አንድ እንደ መኾንህ ሞት የሌለብህ አንተ ነህ፤ ከእኛም ጋር አንድ እንደ መኾንህ በፈቃድህ የሞትህ አንተ ነህ፡፡ በመቃብር ያደርህ አንተ ነህ፤ በኪሩቤል ላይ ያለህ አንተ ነህ፤ ከሙታን ጋር በመቃብር የነበርህ አንተ ነህ፡፡ በአንተ ሕማምና ሞትም ድኅነት ተሰጠ፡፡ ከሙታን ጋር የተቈጠርህ አንተ ነህ፤ ለሙታንም ትንሣኤን የምትሰጥ አንተ ነህ፤ ሦስት መዓልት፣ ሦስት ሌሊት በመቃብር ያደርህ አንተ ነህ፤ በዘመኑ ዂሉ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምትኖር አንተ ነህ፤ በመለኮት ሕማም ሳይኖርብህ በሥጋ የታመምክ አካላዊ እግዚአብሔር ቃል አንተ ነህ፤” (ቅዱስ ኤራቅሊስ፣ ፵፰፥፲፪-፲፫)፡፡
“እኛስ ኃጢአታችንን ለማስተስረይ በሥጋ እንደ ታመመ፤ እንደ ሞተ፤ ከነፍሱም በተለየ ጊዜ ሥጋውን እንደ ገነዙ፤ ከሙታንም ተለይቶ በእውነት እንደ ተነሣ፤ ከተነሣም በኋላ በእውነት ወደ ሰማይም እንደ ዐረገ እናምናለን፡፡ ኋላም እርሱ በሚመጣው ዓለም በሕያዋን፣ በሙታን ይፈርድ ዘንድ ይመጣል፡፡ የሰውን ወገኖች ዂሉ በሞቱበት፤ በተቀበሩበት ሥጋ ከሞት ያስነሣቸዋል፡፡ ከትንሣኤውም በኋላ ያለ መለወጥ ዂል ጊዜ ይኖራል፡፡ እርሱ በዚህ በሞተበት፤ በተገነዘበት ሥጋ ከሙታን አስቀድሞ እንደ ተነሣ፤” (ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም፣ ሃይ. አበ. ፶፪፥፲፩-፲፪)፡፡
“የሥጋን ሕማም ለመለኮት ገንዘብ በአደረገ ጊዜ የእግዚአብሔር አካል በባሕርዩ በግድ ሕማምን አልተቀበለም፤ ሕማም በሚስማማው ባሕርዩ ኃይል እንጂ፡፡ ሞትም በሥጋ ለእግዚአብሔር ቃል ገንዘብ በኾነ ጊዜ ሞትን አጠፋ፤ ከሞትም በኋላ ፈርሶ በስብሶ መቅረትን አጠፋ፤” (ቅዱስ ቴዎዶጦስ፣ ሃይ. አበ. ፶፫፥፳፯)፡፡
“መለኮት በሥጋ አካል በመቃብር ሳለ መለኮት የሥጋ ሕይወት በምትኾን በነፍስ አካል ወደ ሲኦል ወረደ፡፡ እንደዚህ ባለ ተዋሕዶ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ከትንሣኤ በኋላ አይያዝም፤ አይዳሰስም፤ በዝግ ቤት ገብቷልና፡፡ ነገር ግን ምትሐት እንዳይሉት ቶማስ ዳሠሠው፤ የተባለውን ከፈጸመ በኋላ ቶማስ አመነበት፤” (ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፣ ሃይ. አበ. ፶፮፥፴፯-፴፰)፡፡
“ክርስቶስ የሙታን በኵር እንደ ምን ተባለ? እነሆ በናይን ያለች የደሀይቱን ልጅ አስቀድሞ አስነሣው፤ ዳግመኛም አልዓዛርን በሞተ በአራተኛው ቀን አስነሣው፡፡ ኤልያስም አንድ ምውት አስነሣ፤ ደቀ መዝሙሩ ኤልሣዕም ሁለት ሙታንን አስነሣ፤ አንዱን ሳይቀበር፤ ሁለተኛውን ከተቀበረ በኋላ ሥጋውን አስነሣ፡፡ እነዚያ ሙታን ቢነሡ ኋላ እንደ ሞቱ፤ እነርሱ ኋላ አንድ ኾነው የሚነሡበትን ትንሣኤ ዛሬ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የሙታን ትንሣኤያቸው በኵር ነው፡፡ እንግዲህ ወዲህም ሞት የሌለበትን ትንሣኤ አስቀድሞ የተነሣ እርሱ ነው፡፡ ‹ዳግመኛም ሞት አያገኘውም› ተብሎ እንደ ተጻፈ፤” (ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፣ ፶፯፥፫-፮)፡፡
“ቃል ሥጋውን በመቃብር አልተወም፤ በሲኦልም ካለች ከነፍሱ አልተለየም፡፡ ከነፍስ ከሥጋ በአንድነት ነበረ እንጂ፤ ለዘለዓለም ክብር ምስጋና ይግባው፤” (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ሃይ. አበ. ፷፥፳፱)፡፡
“ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ በትንሣኤ ‹ከእናንተ ጋር እስከምመጣበት ቀን ድረስ ከዚያ ወይን ጭማቂ አልጠጣም፤ በሐዲስ ግብር በምነሣበት ጊዜ የምታዩኝ እናንት ምስክሮቼ ናችሁ› ያለውን የማቴዎስን ወንጌል በተረጐመበት አንቀጽ እንዲህ አለ፤ ሐዲስ ያለው ይህ ነገር ምንድነው? ይህ ነገር ድንቅ ነው! መዋቲ ሥጋ እንዳለኝ ታያላችሁ፤ ነገር ግን ከትንሣኤ በኋላ የማይሞት ነው፤ አይለወጥም፡፡ ሥጋዊ መብልንም መሻት የለበትም፤ ከትንሣኤ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቢበላም ቢጠጣም መብልን ሽቶ አይደለም፤ እርሱ ከሙታን ተለይቶ እንደ ተነሣ ያምኑ ዘንድ በላ ጠጣ እንጂ፡፡ ይህ ድንቅ ሥራ ነው! ያለ መለወጥ ሰው የኾነ ቃል የተቸነከረበትን ምልክት (እትራት) አላጠፋምና፡፡
በሚሞቱ ሰዎች እጅ እንዲዳሠሥ አድርጎታልና፤ አምላክ የሆነ ሥጋ የሚታይበት ጊዜ ነውና አላስፈራም፤ እርሱ በዝግ ደጅ ገባ፤ ግዙፉ ረቂቅ እንደሆነ ሥራውን አስረዳ፤ ነገር ግን በትንሣኤው ያምኑ ዘንድ የተሰቀለው እርሱ እንደሆነ የተነሣውም ሌላ እንዳይደለ ያውቁ ዘንድ ይህን ሠራ፡፡ ስለዚህም ተነሣ፤ በሥጋውም የችንካሩን ምልክት /እትራት/ አላጠፋም፤ ዳግመኛም ከትንሣኤው አስቀድሞ ደቀ መዛሙርቱ ጧት ማታ ከእርሱ ጋር ይበሉ እንደነበረ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በላ፤ ስለዚህም በዐራቱ መዓዝነ ዓለም ትንሣኤውን አስረዱ፤ ከትንሣኤውም በኋላ ያየነው ከእርሱም ጋር የበላን የጠጣንም እርሱ ነው ብለው አስረዱ፤” (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ሃይ. አበ. ፷፮፥፯-፲፪)፡፡
“በእርሱ ሞት ከብረናል፤ በመለኮቱ ሞት ሳይኖርበት በሥጋ ሞተ፤ ምንጊዜም ቢሆን እርሱ የሕይወት ልጅ ሕይወት ነው፤ ይኸውም ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ልደት ነው፡፡ ወደ ሕይወት ሥጋ ደፍሮ በመጣ ጊዜ ሞት እንዲህ ድል ተነሣ፤ መፍረስ መበስበስም በእርሱ /በክርስቶስ/ እንዲህ ጠፋ፤ ሞትም ድል ተነሣ፤” (ቅዱስ ቄርሎስ፣ ሃይ. አበ. ፸፪፥፲፪)፡፡
“ሕማምን፣ ሞትን ገንዘብ አደረገ፤ በሥጋው የሞተው ሞትም የእኛን ባሕርይ በመዋሐዱ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ተዋሕዶውን አስረዳ፤ ሞት ሰው የመኾን ሥራ ነውና፡፡ ከሙታን ተለይቶ መነሣትም አምላክ የመኾን ሥራ ነውና፤ እነዚህ ሁለት ሥራዎችን /ሞትንና ትንሣኤን/ እናውቃለን፤” (ቅዱስ ቄርሎስ፣ ሃይ. አበ. ፸፪፥፴፭)፡፡
“በሥጋ ሞተ እንዳልን ዳግመኛ በሥጋ ተነሣ እንላለን፤ ስለ ትንሣኤም የእርሱ ገንዘብ እንደ ኾነ፤ ሙስና መቃብርም እንዳላገኘው ይነገራል፡፡ ይህ ለመለኮት አይነገርም፤ የተነሣው ሥጋው ነው እንጂ፤” (ዝኒ ከማሁ ፸፱፥፱)፡፡
“የሞትን ሥልጣን አጠፋ፤ ዲያብሎስንና ኃይሉን (ኃጢአትን) ሻረ፡፡ የብረት መዝጊያዎችን ሰበረ (ፍዳ መርገምን አጠፋ)፡፡ ሲኦልን በዘበዘ፡፡ የጣዖት ቤቶችን አፈረሰ፡፡ የምሕረትን በር ከፈተ፤ ይህችውም በደሙ የከበረች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ለዂሉ የዘለዓለም ሕይወት መገኛ የሚኾን ልጅነት የተገኘበት ሥጋውን ደሙን ሰጠን፤” (ቅዱስ ቴዎዶስዮስ፣ ሃይ. አበ. ፹፫፥፮)፡፡
“ለእኛስ እግዚአብሔር ቃል በባሕርየ መለኮቱ እንደ ታመመ፤ እንደ ሞተ፤ እንደ ተቀበረ ልንናገር አይገባንም፡፡ ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ ሞት የሌለበት እንደ ኾነ፤ መድኀኒታችን በሚኾን በሞቱና በሦስተኛው ቀንም በመነሣቱ ትንሣኤን እንደ ሰጠን እናምናለን፡፡ የሞተ እርሱ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና፡፡ ዂሉን የሚችል እርሱ ካልተነሣ፣ የችሎታ ዂሉ ባለቤት እርሱ የሌለ ከኾነ፣ እንኪያስ ትንሣኤም ሐሰት ነዋ! ትንሣኤም ሐሰት ከኾነ ሃይማኖታችን ከንቱ ነው፡፡ እንኪያስ አይሁድንም እንመስላቸዋለን፡፡ ሰው እንደ መኾኑ በሥጋ ባይሞትስ በሞት ላይ ሥልጣን ያለው አምላክ እንደ መኾኑ ሞትን ባላጠፋ ነበር፡፡ የአዳም የዕዳ ደብዳቤም ከእግዚአብሔርና ከሰው መካከል ባልተደመሰሰም ነበር፤” (ቅዱስ ሳዊሮስ፣ ሃይ. አበ. ፹፬፥፲፰-፳)፡፡
“ፈጣሪያችን ክርስቶስ ለጌትነቱ እንደሚገባ ሥጋ መለወጥ የሌለበት እስኪኾን ድረስ ድንቅ በሚያሰኝ ትንሣኤ ሙስና መቃብርን አጥፍቷልና፡፡ በሥጋ በተቀበላቸው በሚያድኑ በእነዚህ ሕማማት ከጽኑ ሞት፣ ከዲያብሎስም ሥልጣን ያድነን ዘንድ ወደ ቀደመ ቦታችንም ያገባን ዘንድ፤” (ቅዱስ ዮሐንስ ዘአንጾኪያ፣ ሃይ. አበ. ፺፥፴፬)፡፡
“ይታመም ዘንድ በተገባው በሥጋው፣ ነውር የሌለበትን ሕማም በፈቃዱ በእውነት ተቀበለ እንጂ በምትሐት እንዳልታመመ እናገራለሁ፡፡ እንደ ሕማሙ ሞትንም በመስቀል ላይ ተቀበለ፡፡ ለአምላክነቱ በሚገባ፣ ድንቅ በሚያሰኝ ትንሣኤውም የጌትነቱን ሥልጣን ገለጠ፡፡ ሥጋውንም የማይሞት አደረገ፡፡ ከኃጢአት በራቀ በንጹሕ ማኅፀን በተዋሐደው ጊዜ ለመለኮት ገንዘብ ስለኾነ በሥራው ዂሉ አይለወጥም፤” (ቅዱስ ቴዎዶስዮስ፣ ሃይ. አበ. ፺፪፥፲፭)፡፡
“ሕማም የማይስማማው እርሱ በሥጋ ሞትን ታገሠ፤ ብረት ወደ እሳት በገባ ጊዜ ዂለንተናው እሳት እንደ ኾነ እስኪታሰብ ድረስ በእሳት ዋዕይ እንዲግል፤ በመዶሻ በተመታ ጊዜ በመስፍሕ (መቀጥቀጫ) ላይ እንዲሳብ (እንዲቀጠቀጥ)፤ እሳትም ከብረት ጋር ተዋሕዶ ሳለ ፈጽሞ እርሱ እንዳይመታ፤ ከብረቱም እንዳይለይ ግን የመዶሻ ኃይል ሳያገኘው እንዲመታ፤ ለመዶሻ እንዲሰጥ፤ የሚያድን የጌታ ሕማም እንዲህ እንደ ኾነ ዕወቅ፡፡
በዚህ ትንሽ ምሳሌ በእሳትና በብረት ተዋሕዶ ምልክትነት ፍጹም ተዋሕዶን እንወቅ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ይህ መከራና ሕማምን የሚቀበል ሥጋን ተዋሕዶ በሞተ ጊዜም ከሦስት ቀን በኋላ አምላክነቱ በተገለጠበት ትንሣኤው ሞትን አጠፋው፡፡ ሥጋው በመቃብር በመቀበሩም በመቃብር ውስጥ የነበረ መፍረስን መበስበስን አጠፋልን፤ ከሥሩም ነቀለው፡፡ ይህንም የሚያስረዳ ከቅዱሳን ወገን ብዙ ሰዎች ተነሡ፤” (ቅዱስ ባስልዮስ፣ ሃይ. አበ. ፺፮፥፶-፶፪)፡፡
“ዳግመኛ እርሱ እንደ ሞተ፣ በሦስተኛውም ቀን እንደ ተነሣ፣ ስለ ተነሣም ሥጋው የማይፈርስ የማይበሰብስ፣ የማይታመም፣ የማይሞት እንደ ኾነ እናምናለን፡፡ ሥጋውም ከእርሱ ጋር አንድ ኾኖ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአርያም በልዑል ዙፋኑ ተቀመጠ፡፡ ዳግመኛም በሙታንና በሕያዋን ይፈርድ ዘንድ ዂሉ አንድ ኾኖ በሚነሣበት ጊዜ እርሱ በጌትነት ይመጣል፤ ለዂሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል፡፡ እኛ በእነዚህ ቃላት ሳናወላውል ጸንተን እንኖራለን፤” (ቅዱስ ዲዮናስዮስ፣ ሃይ. አበ. ፺፱፥፴፪)፡፡
“በፈቃዱ በሥጋው የእኛን ሕማም ታመመ፤ በእውነት የእኛን ሞት ሞተ፡፡ ይኸውም የነፍስ ከሥጋ መለየት ነው፡፡ በፈቃዱ በተለየ አካሉ ሞትን ገንዘብ አደረገ፡፡ በሦስተኛውም ቀን በሥልጣኑ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱ ዕሪና ተቀመጠ፡፡ በኋለኛይቱ ቀንም በሙታን በሕያዋን ሊፈርድ ይመጣል፤” (ቅዱስ ፊላታዎስ፣ ሃይ. አበ. ፻፭፥፲፬)፡፡
“በሞቱ ሞትን ያጠፋው እርሱ ነው፤ በሦስተኛው ቀን በመነሣቱም ሲኦልን በዘበዘ፡፡ ለዂሉም ትንሣኤን ገለጠ፡፡ ፈጽሞ አልተለወጠም፡፡ ለዂሉ አምላክነቱን አስረዳ፡፡ ሙስና መቃብርን ከእኛ አጠፋ፡፡ በቀደመ ሰው በአባታችን በአዳም ትእዛዝ ማፍረስ ምክንያት ሠልጥኖብን ለነበረ ኃጢአት ከመገዛት አዳነን፤” (ቅዱስ ዲዮናስዮስ፣ ፻፲፩፥፲፫)፡፡
“እሑድ በመንፈቀ ሌሊት ነፍሱን ከሥጋው አዋሕዶ በመለኮታዊ ኃይል ተነሣ፡፡ እርሱ ራሱ ‹ነፍሴን በፈቃዴ አሳልፌ ልሰጥ፣ ሁለተኛም መልሼ ላዋሕዳት ሥልጣን አለኝ፤ ይህን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልኩ› እንዳለ፡፡ በነጋም ጊዜ ለማርያም መግደላዊት ታያት፤ እጅ ልትነሣው በወደደች ጊዜም ‹አትንኪኝ› አላት፡፡ ‹ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና›፤ ስለዚህም ሥጋዊ አካሉ ከዚያን አስቀድሞ በአብ ቀኝ እንዳልተቀመጠ ዐወቅን፤” (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ ምሥጢር ዘትንሣኤ)፡፡
“ሞትን በሥጋ በቀመሰ ጊዜ መለኮቱ በመቃብር ውስጥ ያለ ነፍሱ ከበድኑ ጋር ነበር፡፡ በሲኦልም ውስጥ ያለ ሥጋው ከነፍሱ ጋር ህልው ነበር፡፡ በአባቱም ቀኝ ያለ ነፍስና ያለ ሥጋ ህልው ነበር፡፡ በትንሣኤውም ጊዜ ነፍሱን ከሥጋው ጋር አዋሕዶ አስቀድሞ ለአይሁድ ‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ በሦስተኛው ቀን እሠራዋለሁ› ብሎ እንደ ተናገረ፡፡ አይሁድም ‹ይህ ቤተ መቅደስ ተሠርቶ ያለቀው በዐርባ ሰባት ዓመት ነው፤ አንተ ግን ‹በሦስት ቀን እሠራዋለሁ› ትላለህ› አሉት፤ ይህንም የተናገረው ስለ ራሱ ሰውነት ነው፡፡
በተነሣም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ነገር እንደ ተናገረ አሰቡ፡፡ በመጽሐፍና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም የተናገራቸውን ቃል አመኑ፡፡ ሁለተኛም ‹ነፍሴን በፈቃዴ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ልለያት መልሼም አዋሕጄ ላስነሣት ሥልጣን አለኝ፤ ይህንንም ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልኩ› ብሏል፡፡ ዳዊትም ‹አቤቱ የመቅደስህን ታቦት ይዘህ ተነሥ› ይላል፡፡ ነቢዩ ‹አቤቱ አንተ የመቅደስህን ታቦት ይዘህ ተነሥ› ለምን አለ? የመቅደሱ ታቦት ከኾነችው ከዳዊት ዘር ከነሣው ሥጋ ጋር በመለኮታዊ ኃይሉ ከሞት እንቅልፍ ከመንቃት በስተቀር የእግዚአብሔር መነሣት ምንድነው?” (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽ. ምሥጢር ዘትንሣኤ)፡፡
“ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ከጲላጦስ ተካሰው ከመስቀል አውርደው፣ በድርብ በፍታ ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት፡፡ በሦስተኛው ቀን መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበት በዝግ ቤት ገብቶ በጽርሐ ጽዮን ታያቸው፤” (ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ፣ ፩፥፱-፴፩)፡፡
“ሰውን ስለ መውደድህ ይህን ሁሉ አደረግህ፤ ከሙታን ተለይተህ ‹መቃብር ክፈቱልኝ፤ መግነዝ ፍቱልኝ› ሳትል ተነሣህ፡፡ ከእግረ መስቀል ሙታንን አስነሣህ ነፍሳትን ከሲኦል ማርከህ ለአባትህ አቀረብህ፤” (ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ ፩፥፳፬)፡፡
“በታወቀች በተረዳች በሦስተኛይቱ ቀን ‹መቃብር ክፈቱልኝ፤ መግነዝ ፍቱልኝ› ሳይል ተነሣ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበት በዝግ ቤት ገባ፡፡ የተወጋውን ጎኑን፣ የተቸነከረውን እጁን፣ እግሩን አሳያቸው፡፡ በዓለመ ነፍስ የኾነውን እያስተማራቸው ዐርባ ቀን ኖረ፤” (ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት፣ ፬፥፳፭)፡፡
“ሰማያት (ሰማያውያን መላእክት) የደስታ በዓልን ያደርጋሉ፤ ደመናት (ቅዱሳን) የደስታን በዓል ያደርጋሉ፡፡ ምድር (ምድራውያን ሰዎችም) በክርስቶስ ደም ታጥባ (ታጥበው) የፋሲካን በዓል ታደርጋለች (ያደርጋሉ)፡፡ ያከብራሉ (ታከብራለች)፡፡ ዛሬ በሰማያት (በመላእክት ዘንድ) ታላቅ ደስታ ኾነ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ የፋሲካን የነጻነት በዓል ታደርጋለች፡፡ የትንሣኤያችን በኵር ክርስቶስ ከሙታን ሰዎች ዂሉ ተለይቶ ቀድሞ ተነሣ፤” (ድጓ ዘፋሲካ)፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ See less
Comments
Roza Kasim
እልልልልልልልልል
6y
Reply
Asfaw Amare Ab
አሜን አሜን አሜን
6y
Reply
የማርያም ልጂ የማርያም ልጂ
አሜን አሜን አሜን
6y
Reply
Abez GMedhin
ለእርምት ያክል
++++መጥፋት ያለበት ማስታወቂያ!!!… See more
6y
Reply
Brkti Mulubrhan
Amen
Amen
Amen
6y
Reply
Asratemariam Shitaye
Amen Amen Amen.
6y
Reply
6 of 31
Monday, August 26, 2024
Sunday, July 28, 2024
Thursday, July 25, 2024
Tuesday, July 2, 2024
Wednesday, June 26, 2024
https://youtu.be/Eb84MBV13IY?si=bAFJYz9jPhyZhiq4Could have, should have, would have: Past Tense Modals (+Negative)
https://youtu.be/Eb84MBV13IY?si=bAFJYz9jPhyZhiq4Could have, should have, would have: Past Tense Modals (+Negative)
https://youtu.be/GJiZnG-o5FQ?si=b08JhB-6wIXZiD9x Correct Use of COULD, SHOULD and WOULD - Modal Verbs in English Grammar
https://youtu.be/GJiZnG-o5FQ?si=b08JhB-6wIXZiD9x
Tuesday, June 25, 2024
Follow These Simple Instructions for Gmail: 1. In your inbox, locate an email from jennifer@jforrestenglish.com
Follow These Simple Instructions for Gmail:
1. In your inbox, locate an email from jennifer@jforrestenglish.com
P.P.S - If you missed my last email with the link to download your free speaking guide, here's the link again: jforrestenglish.com/free-guide (jennifer@jforrestenglish.com) to your contacts to make sure my e-mails are getting delivered to the right inbox! I don't want you to miss out on your premium resources! (Click here for instructions)
Wednesday, June 19, 2024
🤳 ለልጅ ምክር - ለአባት መታሰቢያ
🤳 ለልጅ ምክር - ለአባት መታሰቢያ
☀️ ልጄ ሆይ! ጠላትህ ሲሞት ወይም ሌላ መከራና ጭንቀት ሲያገኘው ደስ አይበልህ። እርሱ ሞቶ አንተ በዚህ ዓለም አትቀርምና አንተ ደግሞ በሠራኸው ሥራ እንደ እርሱ መከራና ጭንቀት ሳያገኝህ አይቀርም፤ በመከራና በሞትም የሰው ሁሉ ድርሻው ትክክል እንደ ሆነ እወቅ፥
☀️ ልጄ ሆይ! ነውርህን ለብቻህ የሚነግርህን ሰው አትጥላው፤ አንተም በወዳጅህ ላይ ነውር የሚሆን ነገር ያየህበት እንደ ሆነ ለብቻው አድርገህ ንገረው። ለሌላ ሰው ግን አትንገርበት፥
☀️ ልጄ ሆይ! በየጊዜው በሰውነትህ ውስጥ የሚነሣውን አሳብ ደግና ክፉ መሆኑን ሳትመረምር ያሰብኸውን ሁሉ ለመፈፀም አትቸኩል፥
☀️ ልጄ ሆይ! አንተ ራስህ የምትጠቀምበት ወይም ወዳጅህ የሚጠቀምበት ነገር ካልሆነ በቀር "ሰው እንዲያመሰግነኝ" ብለህ ሰውነትህን አታድክም። ሰውም በከንቱ ቢያመሰግንህ ደስ አይበልህ። አመስጋኙም ሁለቱም ይሞታሉና ደስ አይበልህ፥
☀️ ልጄ ሆይ! በነገርህ ሁሉ የታመንህ ሁን። ባነጋገርህም ደማም ሁን። ሰውን የሚያስፈራና ሰውን የሚያሳዝን ነገር ለመናገር አትድፈር። በልዝብ ምላስ ሰውን አታታል። ሰውንም ከሚየሙ ሰዎች ጋር አትደባለቅ፥
☀️ ልጄ ሆይ! ንብረትህ በልክ ይሁን። ቤተ ሰዎችም አታብዛ የቀንድ ከብትና የጋማ ከብትም በብዙ አታርባ። ላንተ የማይገባህን ነገር ከማንም ቢሆን አትቀበል። አንተም ለማንም ቢሆን የማይገባውን ነገር አትስጥ፥
☀️ የማታገኘውን ነገር አትመኝ። ባይንህ ካላየህና እርግጥ መሆኑን ካልተረዳኸው በቀር በማንም ሰው ላይ የሚወራውን ወሬ እውነት ነው ብለህ አትቀበል፥
☀️ ለሰውነትህ የሚያስፈልገውን ነገር ለማግኘት አስብ እንጂ ሰው የሚጠፋበትን፤ ሰው የሚጨነቅበትን ነገር አታስብ።
«ወደጄ ልቤና ሌሎችም - ብላቴን ጌታ ኀሩይ ወ/ስላሴ»
ምንጭ፦ ነቢል እንድሪስ
#ብላቴን ጌታ ሕሩይ ወልደ ስላሴ "ለልጅ ምክር ለአባት መታሰቢያ" በተሰኘው ድርሳናቸው ልጄ ሆይ እያሉ እንዲህ ይመክሩናል።
ልጄ ሆይ፤ የአንበሳና የነብር የሌሎቹንም አራዊት ግርማ ከመፍራት ይልቅ እግዚአብሄርን የማይፈሩ የክፉ ሰዎችን ፊት ፍራ። የዱር አራዊት ለመግደል ካልፈለጓቸው እነርሱ ፈልገው አይመጡም። #ክፉ ሰዎች ግን ሰውን ፈልገው ካላጠፉ እንቅልፍ አይወስዳቸውም
ማለፍያ ብዕራቸው ሞገስ ይሁንላቸውና አንጋፋው የብዕር አለቃ ብላቴ ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ ለልጅ ምክር አባት መታሰብያ በሚለው መጽሐፋቸው ያሉትን ብንጠቅስ መልካም መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም እንዲህ ይነበባል ልጄ ሆይ ሰው ምንም ብልህና አዋቂ ቢሆን በራሱ ሥራ ብቻ ራሱን ችሎ እንደማይኖር እወቅ ነገር ግን ሁሉም በየሥራው ጸንቶ እርስ በእርሱ ይፈላለጋል ሰውን ሁሉ አክብረህ ኑር ሰውን ሁሉ በሥራው አትናቅ ሥራውንም አትንቀፍ ካሉ በኋላ የሚከተለውን አክለውበታል ገበሬውን አትንቀፍ ከነቀፍከውም እህሉን አትክልቱን ከእርሱ አትፈልግ ወታደሩን አትንቀፍ ከነቀፍከውም ሀገር የሚያጠፋ ነፍስን የሚገድል ጠላት ሲመጣ ተዋጋልኝ አትበል እረኛውን አትንቀፍ ከነቀፍከውም ከብት ጠብቅልኝ ወተት እለብልኝ አትበል ሸክላ ሰሪውን አትንቀፍ ከነቀፍከውም የሸክላ እቃውን አትፈልግ በማለት ይደመድሙታል
እንግዲህ ይህ የብላቴ ጌታ ህሩይ መጽሐፍ አደባባይ የዋለው ምንአልባት ከዛሬ ሰማንያ ዓመት በፊት ነው እኛ ግን እነዚያን እርሳቸው አትንቀፍ ያሏቸውን ዛሬም እየነቀፍን እንታያለን ነቅፈንም ለሌላ ነቃፊ እየሰጠን የስድብ ባላደራዎች ሆነን ለወገን የሚበጀውን እየተውን ለወገን የማይበጀውን ኢትዮጵያችንን የሚያለማትን እየተቃወምን ኢትዮጵያችንን የሚያጠፋትን እየደገፍን እንገኛለን ይህን ታድያ ምን ይሉታል ሲሉ መጽሐፉን ያነበቡ አስተያየት ሰጪ አክለው ተናገሩ
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ “ጎሀ ጽባሕ” በተሰኘ መጽሐፍ ምን እያሉን ነው?
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ “ጎሀ ጽባሕ” በተሰኘ መጽሐፍ ምን እያሉን ነው?
-ለአማርኛ ሥነ ጽሑፍ እድገትና ለኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት ምንጭ ሁነው ሊጠቀሱ የሚችሉ መጻሕፍትን በማበርከት ትልቅ አስተዋጽዖ ያደረጉት ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ (1871-1931 ዓ.ም.) ከብዙ መጻሕፍቶቻቸው መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ 1917 ዓ.ም. የታተመ “ጎሀ ጽባሕ” የተሰኘ መጽሐፍ ነበራቸው፡፡ በቅርቡ በ2014 ዓ.ም. በድጋሚ ታትሟል፡፡ መጽሐፉ በአብዛኛው ሃይማኖታዊ ሥነ ምግባርና ታሪክ ላይ ትኩረት በማድረግ ማብራሪያ የሚሰጥ መጽሐፍ ነው፡፡ ምናልባት ካላነበቡት በጥንቃቄ ቢያነቡት መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት አንጻር ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ በ“ጎሀ ጽባሕ” መጽሐፍ ምን እያሉን ነው? በማለት ሐሳባቸውን ሙሉ በሙሉ ለመቀበል ጽነት ያላቸውና ከበድ የሚሉ ሐሳቦች አሉበት፡፡ ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን ልጥቀስ
1.) “አዋልድ መጻሕፍት በዓለም ሁሉ በብዙ ተጽፈዋል ከነዚህም የሚበዛው ልብ ወለድ ከቅዱሳት መጻሕፍት ቃል ጋር የማይሰማማ ነው፡፡ አዋልድ መጻሕፍት ማለት በመንፈሳዊ ስለ መላእክትና ስለ ቅዱሳን፣ ስለ ሰማዕታትና መነኮሳት፣ ስለ ሊቃውንትና ስለ ጳጳሳት፣ የተጻፉ የድርሳንና የገድል የክርክርም መጻሕፍት ናቸው፡፡” ( ጎሀ ጽባሕ፣ገጽ 24፣ 2014 ዓ.ም.)
-እውነት አብዛኛው አዋልድ መጻሕፍት ልብ ወለድ የሆነ ከቅዱሳት መጻሕፍት ቃል ጋር የማይሰማማ ነው?
2.) “የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍት ምሥጢራቸው ባይገለጥልን እንኳን በግድ መቀበል ይገባናል ብለን ከዚህ ቀድሞ አስረድተናል፡፡ የአዋልድን መጻሕፍት ግን የመንፈሳዊም የሥጋዊም ቢሆኑ ወግና ታሪክ ለማወቅ የደራሲውን ደግነትና ክፋት ለመመርመር አንዳንድ ጊዜ ልናነባቸው ይገባል እንጅ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት በግድ ልንቀበላቸው አልታዘዝንም፡፡” (ገጽ 27)
-አዋልድን መጻሕፍት በግድ ልንቀበላቸው አይገባንም? አልታዘዝንም?
3.) “ሚስት አግብቶ ልጆች ወልዶ በሥርዐት የሚኖር ከእግዚአብሔር የታዘዘ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ ነውና ሚስት ያላገቡ መነኮሳት ሚስት ታገቡ ሰዎች ይልቅ የበለጠ ክብር ያገኛሉ ብለን በልባችን አናስብም በቃላችንም አንናገርም፡፡” (ገጽ 181)
-በክብር በድንግልና የሚኖሩ መነኮሳት በጋብቻ ከሚኖሩት ጋር አይበልጡም? በልባችን ማሰብና በቃላችንም መናገር አይገባንም?
4.) “በእውነተኛ አእምሮ ብንፈርደው ግን ከመነኮሳት ይልቅ ሚስት ያገቡ ሰዎች ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡፡ እነሆ አሁን በጦርነት ጊዜ መመስገን የሚገባው በሰልፉ ጸንቶ የተዋጋ ወታደር ነው እንጅ ሸሽቶ የሄደ ወታደር አይመሰገንም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ መንኩሶ በገዳም መኖር ከዚህ ዓለም መከራና ፈተና ሸሽቶ እንደመሄድ ነው፡፡ ሚስት አግብቶ ልጆች ወልዶ በሕገ እግዚአብሔር ጸንቶ የእዚህን ዓለም መከራና ፈተና ታግሦ የሚኖር ሰው ግን በሠይፍ ጸንቶ እንደመዋጋት ነው፡፡” (ገጽ 182)
-እውነት ከመነኮሳት ይልቅ ሚስት ያገቡ ሰዎች ሊመሰገኑ ይገባቸዋል?
-ምንኩስና በጦርነት ጊዜ ሸሽቶ የሄደ ወታደርን ይመስላል?
-ጋብቻን አመስግነው ምንኩስናን ማመስገን ያልፈለጉበትና ያቀረቡት ምሳሌ አግባብነት አለው?
5.) ልብ ብለን ከተመለከትነው በተራ ቁጥር 3 እና 4 ያሉት የብላቴን ሐሳቦች ይጋጫሉ፡፡ ጋብቻና ምንኩስና በክብር አይበላለጡም ካሉ በኋላ እንደገና “የእዚህን ዓለም መከራና ፈተና ታግሦ የሚኖር ሰው ግን በሠይፍ ጸንቶ እንደመዋጋት ነው” በማለት ጋብቻን ከምንኩስና ጋር በማነጻጸር በተራ ቁጥር 4 ላይ ያስበልጡታል፡፡ በጋብቻ የሚኖሩ ሰዎች ከመነኮሳት ይልቅ ሊመሰገኑ ይገባል ይላሉ፡፡ በዚህም ጋብቻን ማስበለጣው ይታወቃል፡፡
6.) ስለ ሊቃነ ጳጳሳት በሚያብራሩበት የመጽሐፋቸው ክፍል ላይ የሚከተለውን ይላሉ “ኤጲስ ቆጶሳትን … የሚገባቸውን ክብር ልናከብራቸው ይገባል እንጅ ከውኃና ከመንፈስ በጥምቀት የወለዱን አባቶቻችንና አምላኮቻችን ናቸው ለማለት አይገባንም፡፡” (ገጽ 140 ) በገጽ 141 ሐሳባቸውን ለማስረዳት “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ …በምድር ላይ ማንንም አባታችን ብላችሁ አትጥሩ፡፡ አባታችሁ አንዱ በሰማይ ያለው ነውና፡፡ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ ጌቶችም ብላችሁ አትጠሩ፡፡ ጌታችሁም አንዱ ክርስቶስ ነው፡፡” በማለት መንደርደሪያ በማድረግ ያስረዳሉ፡፡
-እውነት ጳጳሳትን አባቶች ማለት አይገባም?
-በመጽሐፍ ቅዱስ በሐዋርያት በጻፋት ወንጌልና መልእክታት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውጭ አባት፣ ጌታ ያሉት አልነበረም?
- እርስዎ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ሐሳቦች ላይ ምን ይላሉ? ይወያዩበት፡፡
@Yosef Fish
Tuesday, June 18, 2024
አለቃ መሠረት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
“መድሎተ ጽድቅ” በመድሎተ ጽድቅ ሲመዘን - ክፍል አንድ
ጮራ
http://www.chorra.net › blog-post
·
Translate this page
Aug 16, 2015 — ” (መሠረት 1988፣ የአቶ መሠረት ስብሐት ለአብ ዐጭር የሕይወት ታሪክ)። ይህም የሚያሳየው አለቃ መሠረት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ...
ከአባ እስጢፋኖስ በኋላ የተነሱ ተሃድሶአውያን
ይህ የነ አባ እስጢፋኖስ እንቅሥቃሴ በጊዜው በነበረው የፖለቲካ የበላይነት ተዳፍኖ ቢቆይም ውስጥ ውስጡን ግን ሲሄድ እና ቀስ ብሎ ሲጓዝ የኖረ እንቅሥቃሴ ነው። ይህን ውስጣዊ እንቅሥቃሴ በርካታ ሊቃውንት በሥዉር ሲሳተፉበት ኖረዋል። ለምሳሌ ከነዚህ ሊቃውንት ውስጥ ጥቂቶች ከመጻሕፍቶቻቸው መረዳት እንደሚቻለው አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ አለቃ ታዬ፤ አለቃ ብላቴን ጌታ ሕሩይ፤ ፤ አለቃ ገብሩ ደስታ፤ ዘመንፈስ፤ የሚባሉ ሊቃውንት ሲሆኑ በደንብ ወደ አደባባይ ካወጡት እና ከቤተ ክርስቲያን ከተገለሉት የቅርብ ሊቃውንት ውስጥ አለቃ መሠረት ስብሐት ለአብ እና ጓደኞቻቸው ይገኙባቸዋል። የአለቃ መሠረት ስብሐት ለአብ ጓደኞች አሁንም በሕይወት ስለአሉ ስማቸውን መጽሐፍ አልፈለግሁም። እነርሱም ስማቸው እንዲወጣ አይፈልጉም። ዛሬም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በተለያዩ ሥራዎች ተመድበው ይገኛሉ። ከላይ ስማቸውን የጠቅስኋቸው ሰዎች የአባ እስጢፋኖስ ሐሳብ ነበራቸው። ይህን ለማለት ያስቻለኝ አሁን ያሉት ቤተ ክርስቲያን መታደስ አለባት የሚሉት ወገኖች ከሚያራምዱት አላማ ጋር መጻሕፍቶቻቸውን በማስታያየት እና የሕይወት ታሪካቸውን በማገናዘብ ነው።
የተሐድሶዎች ዓላማ ምንድን ነው?
ተሐድሶዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሻሻል አለባት ይላሉ። ራእያቸውም ቤተ ክርስቲያኒቱ በሐዋርያት እምነት ላይ የተመሠረተች በመሆኗ፤ የሐዋርያትን ትምህርት መከተል አለባት። አሁን የሚታዩት የሕዝብ ልማዶች እንደ ሃይማኖት ሆነው የሚታዩት ከዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ጀምረው በኃይል እና በፖለቲካ የበላይነት የተጫኑብን እንጂ እውነተኛው እና ጥንታዊው የኦርቶዶክስ እምነት አይደለም ባይ ናቸው። እውነተኛውን ኦርቶዶክሳዊ ትውፊትንም ሆነ እምነትን የሸፈነ ልማድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለ። ይህን ቀስ በቀስ ሕዝብን በማስተማር መሰረቱን ሳያፈርሱ ውሸት የሆነውን ሁሉ እናስወግዳለን የሚል ራእይ አላቸው።
ተሐድሶ እንዲደረግ የሚፈልጉትም፦
1ኛ በአምልኮው ላይ 2ኛ በመጻሕፍቱ ላይ 3ኛ በአስተዳደሩ ላይ ተሐድሶ እንዲደረግ ይፈልጋሉ። ለዚህም መጻሕፍቶቻቸውን ማንበብ ይቻላል በርካታ መጻሕፍት አሏቸው። በገድላት፣ በድርሳነ ሚካኤል እና በድርሳነ ገብርኤል በድርሳነ ኡራኤልም ላይ በጠቅላላ በድርሳናቱ እና በገድላቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ትችታቸውን ጽፈዋል ወደ ፊት እናቀርበዋለን።
በአስተዳደር ላይ የሚያነሱት ጥያቄ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ተመሳሳይ ነው።ልዩነቱ ማኅበረ ቅዱሳን አስተዳደሩ በራሱ ሰዎች እንዲያዝ የሚፈልግ ሲሆን ተሐድሶዎች ግን ለእውነት በቆሙ ሰዎች መያዝ አለበት በሚለው ነው።አስተዳደሩ መንፈሳዊ ካልሆኑ ሰዎች ተላቆ በተማሩ እና ፈሪሃ እግዚአብሔር ባላቸው ሰዎች ይመራ ባይ ናቸው። በአስተዳደሩ የሚፈጸሙ የዘረኝነት እና የሙስና አሠራርን አጥብቀው የሚቃወሙ ሲሆን በየቤተ ክርስቲያኑ በበዓል ቀን መንፈሳዊ ያልሆነ አሠራር እየተስፋፋ ነው። ይህም የንግድ ሥራ እንጂ የእምነት ሥራ አይደለም በማለት አጥብቀው ይቃወማሉ። ጠንቋዮች በቤተ ክርስቲያኒቱ መታቀፍ የለባቸውም። ጠንቋይ የሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ባዕድ አምልኮን በማስፋፋት ትልቁን ሚና እየተጫወቱ ስለሚገኙ ይወገዱልን ባይ ናቸው። በዚህ እረገድ ማህበረ ቅዱሳንም ጠንካራ አቋም አለው። የቀረውን የእንቅሥቃሴያቸውን ታሪክ በሚቀጥለው አቀርባለሁ። ከኔ የቀረውን አንባቢ ቢያስተካክለው ደስ ይለኛል።
Monday, June 17, 2024
Tuesday, June 11, 2024
የመጽሀፍ ቅኝት፡ የነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ሥራዎች
የመጽሀፍ ቅኝት፡ የነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ሥራዎች
Rukya Hassen Shibeshi, #OPEN_TO_WORK
Rukya Hassen Shibeshi
Associate Professor at Kotebe University of Education
July 29, 2020
በዶ/ር ሩቅያ ሀሰን
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ
የስነልሳንና ስነተግባቦት ተባባሪ ፕሮፌሰር
የነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝን ሁለት መጽሀፎች በአንድ ጥራዝ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ በ2003 ዓ.ም. አሳትሞታል፡፡ የነባር ምርጥ መጻህፍት ሕትመት በሚል ርእስ እያሳተማቸው ካለው መጽሀፎች ውስጥ ይህ ድንቅ ስራ በመካከቱ ፕሬሱ ሊመሰገን ይገባል፡፡ በዚህ መጽሀፍ በአንድ ጥራዝ የወጡት የነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ ስራዎች “አጤ ምኒልክና ኢትዮጵያ”ና “መንግስትና የህዝብ አስተዳደር” የተሰኙ ናቸው፡፡ ስራዎቹ እንዲታተሙ ሀሳብ ያቀረቡት የወቅቱ የፕሬሱ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ እንደሆኑ የየነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ የልጅ ልጅ የሆኑት ወ/ሮ ዓይናለም አሸብር ገብረ ሕይወት ገልጸዋል፡፡
ለመጽሀፉ መግቢያ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ እንዲሁም ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጽፈዋል፡፡ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ በመጽሀፉ ጀርባ ላይም እንደታተመው ስለደራሲው ሁለት አስገራሚ ነገሮችን ሲጠቅሱ አንደኛው ገብረ ሕይወት ይህን የመሰለ እስካሁን ድረስ የሚያስተጋባ ጥልቅ የኢኮኖሚና ፖለቲካ ጉዳዮችን በሰላሳዎቹ እድሜ መጻፍ መቻላቸውና ሁለተኛው የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ባልሆነው በአማርኛ ውብና አጥንት የሚሰረስር ስራ ጽፈው ማለፋቸው ነው፡፡ የሞቱት በ33 ወይም በ37 አመት እድሜያቸው በ1911 ከአውሮፓ በመጣው የንፋስ (ግሪፕ) የወረርሽኝ በሽታ እንደሆነ በመጽሀፉ ተገልጧል፡፡ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ በሁለተኛው መጽሀፍ ላይ ሰፋ ያለ አድናቆት ያስቀመጡ ሲሆን የብዙ ኢኮኖሚክስ ሀሳቦች ባለቤት እንደነበሩና ከሳቸው ከ50ና 60 አመት በኋላ የመጡ ምእራባውያን ኢኮኖሚስቶች የሳቸውን ሀሳብ በባለቤትነት ወስደው እንደሚታወቁበት ነገር ግን አሁንም የነጋድራስ ሞዴል እያሉ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ የሚጠሯቸው አዳዲስ የኢኮኖሚክስ ሀሳቦች እንዳሏቸው በከፍተኛ አድናቆት ጽፈዋል፡፡
“አጤ ምኒሊክና ኢትዮጵያ”
ነጋድራስ ለመንግስትና ለህዝባቸው በርካታ ምክሮችን በመጀመሪያው “አጤ ምኒሊክና ኢትዮጵያ” በተሰኘው መጽሀፍ ላይ ያሰፈሩ ሲሆን በመጀመሪያ ምክሮቹ ለአጤ ምንሊክ የታቀዱ የነበሩ ቢሆንም በኋላ ግን ምክሮቹ ለልጅ እያሱ እንዲሆኑ በሚል ጽፈዋቸዋል፡፡ መጽሀፉ አጭር ሲሆን ትልልቅና ቁልፍ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ ነጋድራስ ካነሷቸው ቁልፍ ምክሮች ውስጥ ጥቂቶቹን እናነሳለን፡፡
ታላቁ ምሁር ነጋድራስ ገብረህይወት ከመቶ አመት በፊት በጻፉት በዚህ አስደናቂ መጽሀፋቸው ለአንድ ህዝብ ስርአት ወይም ሲስተም እንደሚያስፈልግ ሲገልጹ “የሀይል ምንጭ ሥርአት ነው እንጅ የሰራዊት ብዛት አይደለም” ብለዋል፡፡ ላለመሰልጠናችንና ላለማደጋችንም በአስተሳሰብ ባለመብሰላችን መሆኑን ሲገልጹ ደግሞ እንዳሉት “እኛ ኢትዮጵያውያን ካለመስማማታችን የተነሳ ሌሎች ህዝቦች በአእምሮና በጥበብ እየበረቱ ሲሄዱ እኛ ወደ ኋላ ቀረን” ነበር (ነጋድራስ ገ/ሕይወት 2003፣ 19)፡፡
በሚገርም ሁኔታ ነጋድራስ ገብረህይወት ከመቶ አመት በፊት የጠቀሱት ጉዳይ ነገር ግን እኛን አሁን በደንብ የሚገልጸን የሚከተለው ገለጻቸው ነው፡፡
በመላው አለም ላይ ሰላም ሲሰፋ አእምሮም ስትበራ እኛ በጨለማ እንኖራለን፡፡ እርስ በርሳችን መጠራጠራችንንም አልተውንም፡፡ ህዝቦቹም ሁሉ እርስ በርሳቸው በፍቅር ተቃቅፈው ስለልማታቸው ባንድነት ሆነው ሲደክሙ እኛ ግን ዘርና ወንድማማች መሆናችንን ገና አልተገለጸልንም፡፡ እርስ በርሳችን መፋጀትም እስከ ዛሬ ድረስ ጀግንነት ይመስለናል፡፡ ስለዚህ እግዚያብሄር ለብርታት የሚሆነውን ስጦታ ሁሉ ሰጥቶን ሳለ ባለቤቶቹ ሰነፍነ፡፡ ለሌሎቹም ነገስታት እንደ ሰነፎች ይቆጥሩናል፣ ይንቁናልም (ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ 2003፣ 19-20)፡፡
ነጋድራስ ገብረህይወት የድህነታችንን ምክንያት ሲገልጹ የሚከተለውን አስቀምጠዋል፡፡
ህዝቡም ሀብታም የሆነ መንግስት ብርቱ ነው፡፡ ህዝቡ የደኸየ እንደሆነ ግን ደካማ፡፡ እኛ ግን ስርአት የለንም፡፡ ስለዚህ ሰነፍን፡፡ በመሬታችን ውስጥ የተሸሸገውም ሀብት ፈላጊ አጣ፤ ስለዚህም ደኸየነ… ምነው የኢትዮጵያ ህዝብ ከእንቅልፍህ መቸ ትነሳለህ? (ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ 2003፣ 22)፡፡
ጽሁፍ ለማህበረሰብ እድገት መሰረታዊ መሆኑን ሲገልጹ እንዳሉት “የተጻፈ ስርአት የሌለው መንግስት ብዙ እድሜ የለውም” (ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ 2003፣ 25)፡፡
ከሁሉም በላይ ለዚህ ዘመን ነዋሪ እጅት በጣም የሚያስገርመው የነጋድራስ ገብረህይወት ሀሳቦች ውስጥ የሚጠቀሰው ስለሃይማኖት የጻፉት ነው፡፡ የሀይማኖት ነጻነት መኖር እንዳለበትና ሀይማኖት ከልብ የሆነ መሆኑንና ዳኛውም ፈጣሪ መሆኑን የገለጹበት መንገድ አስገራሚ ነው፡፡
ደግሞም ባገራችን አንድ የድንቁርና ነገር አለ፡፡ ሃይማኖቱ ተዋህዶ ያልሆነ ሁሉ እንደ ርኩስ ይቆጠራል፡፡ ይህም እጅግ ያስቃል፡፡ አእምሮ የሌለው ህዝብ ሁሉ የእግዚያብሄርን ቃል ሳያውቅ የእግዚያብሄር ጠበቃ ሊሆን ይወዳል፡፡ … ሀይማኖት የልብ ነው፡፡ ስለዚህ ሰማያዊው ንጉስ አንጅ የዚህ አለም ንጉስ አይቆጣጠረውም (ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ 2003፣ 28)፡፡
ስለርእዮተ አለም ሲመክሩ ነጋድራስ ይህንን ብለው ነበር “ኢትዮጵያችን የኤሮጳን አእምሮ የተቀበለች እንደሆነ የሚደፍራት ጠላት የለም፡፡ ያልተቀበለች እንደሆነ ግን ትፈርሳለች፤ ወደ ባርነትም ትገባለች” (ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ 2003፣ 28)፡፡
በስተመጨረሻ የመጀመሪያውን መጽሀፍ ያገባደዱት “መንግስታችንም እንድትቀና የሚከተሉት አሥር ነገሮች በቶሎ ቢፈጸሙ ማለፊያ ነበር” (ነጋድራስ ገብረህይወት፣ 2003፡ 23-27) ያሉትን በማቅረብ ነበር፡፡
1. ለመንግስት የሚሆን ገንዘብና ለንጉሱ የሚሆነውን ገንዘብ በሥርአት ይለይ፡፡ ሹሞቹም በደሞዝ ይደሩ፡፡ ካገር የሚወጣውም ግብር ለመንግስት ይግባ፡፡
2. ሕዝቡ ለመንግስት የሚከፍለው ግብር እንደየሀብቱ መጠን ቁርጥ ሁኖ ይታወቅለት፡፡ የሕዝቡም ቁጥር በመዝገብ ይግባ፡፡ እንዲሁም በየአመቱ የሚወለደውና የሚሞተውም የሚጋባውና የሚፋታውም በመዝገብ ይታወቅ፡፡
3. ሕዝቡም የሚከፍለው ግብር በብር እንጅ በእህል በማርም በፍሪዳም አይሁን፡፡ የመንግስት ስራ ሁሉም በባላገር አይስራ፤ በባለ ደሞዝ እንጅ፡፡
4. ያማርኛ ቋንቋ ገና ሰዋሰው አልተበጀለትም፡፡ ስለዚህ መንግስታችን ከያገሩ ሰዋሰው የሚያዉቁትን ሊቃውንት ሰብስቦ ያማርኛን ቋንቋ ሰዋሰው ቢያስወጣ ደግ ነው፡፡… ያገራችን ሰው ፊደልን ለመማ ቢተጋ አገራችን ቶሎ በቀናች፡፡ ፊደልንም መማር እጅግ ቀላል ነገር ነው፡፡
5. ፍትሐ ነገሥታችን (ህጋችን) ከዛሬው ያደባባይ ሥርአት ጋር አይስማማም፡፡ ስለዚህ መንግስት የሥርአት አዋቆችን ሰብስቦ ከኤሮጳ ሥርአት ጋር የተስማማ ፍትሐ ነገስት ያውጣ፡፡
6. ያገራችን ሰራዊት ስርአት የለውም፡፡ ስለዚህ የኤሮጳን መኳንንት አምጥተው ሰልፍን ቢማር ማለፊያ ነበር፡፡ እንዲሁም የኤሮጳን መምህራን አምጥተው ባዲስ አበባ ላይ የጦር ትምህርት ቤት ይበጅ፡፡
7. የዛሬው የመንግስታችን ብር የተበላሸ ነው፡፡ ሥርአት ውል የለውም፡፡ ስለዚህ መንግስት ለመላው ኢትዮጵያ የሚሆን የገንዘብ ሥርአት በቶሎ ያላወጣ እንደሆነ ንግድ ሊለማ አይችልም፡፡
8. ላገራችን ነጋዴ ሥርአት እስኪወጣለት ድረስ መንግስታችን አይቀናም፡፡ በሩና (ኬላው) ቀራጩ ብዙ ነው፡፡ በአንድ መንግስት ውስጥ አንድ ነጋዴ በየበሩ መቀረጥ የለበትም፡፡
9. ህዝቡ ባንድ መንግስት ውስጥ መሆኑን አጥብቆ እንዲታወቀው አገሩን የሚዞሩ ተቆጣጣሪዎች ይሾሙበት፡፡
10. የሀይማኖት አርነት ይታወጅ፡፡ የሃይማኖት አርነት ቢታወጅ ሃይማኖት ይታወቃል እንጅ አያጠፋም፡፡ ሃይማኖት የልብ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ሰማያዊው ንጉስ እንጅ የዚህ ዓለም ንጉስ አይቆጣጠረውም፡፡
“መንግስትና የህዝብ አስተዳደር”
ሁለተኛው መጽሀፍ “መንግስትና የህዝብ አስተዳደር” ሰፋ ያለ ሲሆን ደራሲው በርካታ ቁልፍ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ ይህ መጽሀፍ ኢኮኖሚክስ፣ ገንዘብ፣ ንግድና የመሳሰሉ ሱዳዮችን ይዳስሳል፡፡ ለሁሉም ነገር ቁልፉ ትምህርት እንደሆነ ሲገልጹ ይህንን ብለዋል “መንግስት ሀይል ለማግኘት የፈለገ እንደሆነ ህዝቡ እንዲበለጽግና እንዲማር መጣር ያስፈልገዋል” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 36)፡፡
ስለዋጋ ሲናገሩ “ዋጋ ማለት የስራ መለኪያ ማለት ነው” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 68)፡፡ የኑሮውድነትና ጫናን ለመቀነስ እውቀት ቁልፍ እንደሆነ ነጋድራስ እኛን የመከሩን ከመቶ አመት በፊት እንደዚህ ብለው ነው “እውቀት ሲበዛ ለኑሮ የሚያስፈልገውን ማናቸውንም ነገር ለማግኘት መሰናክሉ ያንሳልና የማናቸውም ዋጋ ሁሉ ዝቅ ይላል” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 71)፡፡ ትምህርት ለአንድ ህዝብ የጀርባ አጥንት መሆኑን ሲገልጹ “ህዝቡ እንዳይጎዳ የሚፈልግ መንግስት ሁሉ አውራ ጥረቱ ትምህርት እንዲበዛ ነው” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 75)፡፡
ነጻነት በእውቀትና በትምህርት የሚገኝ መሆኑን ሲገልጹ “ሰው በአለም ላይ ጌታ የሆነው ግን በእውቀቱ ብቻ ነው፡፡… እውቀት የሌለው ህዝብ ሁሉ ለብቻው መንግስት ቢኖረውም ባይኖረውም እውቀት ላቸው ህዝቦች ይገዙታል” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 75)፡፡ እውቀት ለሰው ልጅ መበልጸጊያና ማደጊያ መሰረታዊ መሳሪያ መሆኑን ሲያሰምሩ “እውቀት አለምን እንዲገዛ የማይነቃነቅ ዘላለማዊ ደንብ ነው” ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ደራሲው የሰው ልጅ ሲፈጠር ጌታና ሎሌ እንዲሆን እንዳልነበረ አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል፡፡ ፈጣሪ የሰውን ልጅ በምድር ሲያስቀምጥ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ አሟልቶለት እንደሆነም በሚመስጥ አገላለጽ ገልጸውታል “ለሰው የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ምድር በሆዷ ይዛለች፡፡… ማናቸውንም ነገር ሲፈልግ አንቀሳቅሶ ማጋጠም ብቻ ነው ያለበት፡፡ ማንቀሳቀስና ማጋጠም የሚሆነው በስራ ነው፡፡ ስለዚህ የሰው እውቀቱና ገንዘቡ ስራ ብቻ ነው” ይሉናል (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 80)፡፡
በእውቀት፣ በስራና በጥረት ላይ የተመሰረተ ለውጥን የሚያቀነቅኑት አስገራሚው ነጋድራስ ገብረህይወት “ሰውም ምድርን የሚገዛበት ምክንያት በእውቀት ነው እንጅ በጉልበት አይደለም” ያሉን ከ100 አመት መሆኑ ነገር ግን እና እስካሁን አዲስ ነገር እየሆነብን መሆኑ ይገርማል፡፡ እሳቸው ግን አበክረው “እውቀት የሌለው ህዝብ ሀብታም ሊሆን አይችልም” ብለውናል (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 83)፡፡
የሰው ልጅ ምድርን ለመግዛት እንጅ በምድር ለመገዛትና የምድር ሎሌ ለመሆን እንዳልተፈጠረ ያስረዳሉ፡፡ ነገር ግን ደሀ ከሆንን ሌላ አማራጭ አይኖረንም፡፡ ይህንንም በአሳማኝ ሁኔታ ሲያቀርቡት እንደዚህ በማለት ነው “ድሀ የሆነ ህዝብ የምድር ሎሌ ነው፡፡ በረሀብና በበሽታ በሞት ስታንገላታው ትኖራለች፡፡ ሀብታም ህዝብ ግን የምድር ጌታ ነውና ምድር ሎሌ ሆኖ ታገለግለዋለች” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 84)፡፡
ሌላው አስገራሚው የገብረሂወት ገለጻ ስለሀብት የሰጡት ነው፡፡ “ሀብት ማለት የተከማቸ ስራ ማለት ነው፡፡… እውቀት የሌለው ህዝብ ግን ሥራው አይከማችለትም፡፡ የፊት የፊቱ ወዲያው ያልቃል፡፡ ከድካሙም ፍሬ የሚያገኘው ጥቅም ጥቂት ነው፡፡ ስለዚህ እውቀት የሌለው ህዝብ ድሀና የሰው ሎሌ ነው” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 94)፡፡
ከውጭ ስለሚመጡና ስለምንገዛቸው ቁሶች ሲገልጹ “እውቀት ያነሳቸው ህዝቦች እውቀታቸው ከፍ ካለ ህዝቦች ላይ እቃ ሲገዙ እየተበደሩ ነው፡፡ የሚበደሩትም ብድር እኩሌታው ከጉልበታቸው እኩሌታው ከምድራቸው ነው” ይሉናል፡፡ ነጻነት ስላለው ህዝብ የሚከተለውን ማብራሪያ በመግለጽ ስለሀገራችን ነጻ መሆን ይጠይቃሉ
እስቲ አሁን እኛ የኢትዮጵያ ህዝብ አርነት አለን ነው? አርነት ያለው ህዝብ ማለት እውነተኛ ትርጉሙ ለብቻው መንግስት ያለው ህዝብ ማለት ብቻ አይደለም፤ ራሱን የቻለ ህዝብ ማለት ነው እንጅ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እስከ ዛር ድረስ ገና ራሱን አልቻለም፡፡ እስቲ የለበስነውን እንይ፤ ከወዴት የተሰራና ማን ያመጣው ነው? የቤታችንስ እቃ ራሱ ከወዴት የመጣ ነው? የምንለብሰውስ ልብስ የምንጠጣውስ የምንበላበት ምግባችንን የምናበስልበት እቃና መስሪያ ሁሉ ፈጽሞ ከውጭ አገር የመጣ አይደለምን?” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 102)፡፡
የሀገር ሀብት የሚያንሰው ከሰሪው ይልቅ በላተኛው ሲበዛ መሆኑን ገልጸው ለሀገር ብልጽግና ሲባል እውቀት ብቻ ሳይሆን ሀብትም እንደሚያስፈልግ አበክረው እንደሚከተለው ይመክራሉ “የዚህ አለም ህዝቦች የለውጥ መሳሪያዎቻቸው ብርና ወርቅ ብቻ ስለሆኑ ብርና ወርቅ ያነሰበት ህዝብ ከፍ ወዳለው የእውቀት ደረጃ ደርሶ ሀብታም ሊሆን አይችልም” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 131)፡፡ በተጨማሪም መሰረታዊ ፍላጎቱን ያላሟላ ህዝብ የሀገር ፍቅር እንደማይኖረው በማሳሰብ የህዝብን ፍላጎት ማሟላት ለሀገር ደህንነት ቁልፍ ሚና እንዳለው በዚህ መልኩ ይነግሩናል “የሚበላውና የሚለብሰውንም ያጣ ድሀ የተወለደበትን አገር የሚወድበትን ምክንያት ያጣልና ያገሩ መንግስት ቢበረታ ወይም ቢጠፋ ግድ የለውም፤ ስለዚህ መንግስት የሚጠቁም ያገሩ ሀብት በጥቂቶች ሰዎች እጅ ቢሰበሰብ አይደለም፡፡ ያገሩን ሀብት በመላው ህዝቡ ሊከፋፈል ነው አንጅ” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 142)፡፡
ስርአት ወይም ሲስተም ከህዝብ ፍላጎት መመንጨት እንዳለበት ሲያብራሩ እንዳሉት “ስርአት የሚመች ይሆናል ተብሎ በብልሆች ሰዎች ልብ ውስጥ ተፈጥሮ አይጻፍም፤ ከህዝብ ልብ ቀዳል እንጅ፡፡ ንጉስ ወይም ሹም በኋለኞች ትውልዶች የሚመሰገንም በልቡ ፈልስፎ ደንብ ሲያወጣ አይደለም፡፡ የህዝቡን አሳብ ተርጉሞ በትርጉሙ ሲሄድ ነው እንጅ” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 147)፡፡
የህዝብና መንግስት መሰረት ትምህርት ቤት መሆኑን ያሰመሩበት ነጋድራስ ገብረህይወት “ትምህርት የሌለበት አገር አዲስ ደንብ ቢያወጣ ከሚጠቅመው የሚጎዳው ይበልጣል” ብለዋል (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 148)፡፡
ስራን በመስራት ሀብት ለማካበት በምንጥርበት ወቅት መተማመን ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ብር የለውጥ መሳሪያ እንጅ ሌላ ፋይዳ ያለው ነገር እንዳልሆነ አስገንዝበዋል፡፡ የሰው ልጅም መልካምና መጥፎ ባህሪ እንዳለው ሲገልጹልን “የሰው ባህሪው ሁለት ነው፡፡ አንዱ መለኮታዊ፤ ሁለተኛው ግን እንስሳዊ ይባላል፡፡ ቀስቃሽ ካላገኘ ግን ሰው መልአካዊ ባህሪውን አይከተልም፡፡ ወደ እንስሳዊ ባህሪው ያደላል፡፡ ለሰው አውራ ቀስቃሽ ግን ባላንጣ ነው” (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 164)፡፡
አንድ መንግስት አማካሪ እንደሚያስፈልገው የሚያመለክት አንድ ተጨባጭ ምክር በባንክ ዙሪያ የሚከተለው ተገልጧል
ዛሬ በኢትዮጵያ የቆመው ባንክ ኦፍ አቢሲን ከቆመበት ቀን ዠምሮ እስከ ሀምሳ አመት ድረስ በኢትዮጵያ ሌላ ባንክ እንዳይቆም ውል ተቀብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም እንደተረዳነው ግን ማናቸውም ነገር የጥቂቶች ሰዎች እጅ ገብቶ ሞኖፖል ሲሆን ለህዝብም ለመንግስትም ጉዳት ው፡፡ ለአጼ ምኒሊክ አንድ ሰው መጥቶ ባገርዎ ከኔ በቀር ሌላ ሰው እንዳያርስ ወይም በቅሎ ገዝቶ እያከራየ እንዳይነግድ ወይም እኔን ሳይጠይቅ በየቤቱ ማንም ወጥ እየሰራ እንዳይበላ ፈቃድ ይስጡኝ ብሎ ለምኗቸው ቢሆን የሚያናግራቸው ቃል ምንም ቢያምር የሰጣቸው ተስፋ ምን ትልቅቢሆን ያለጥርጥር ይቆጡት ነበር (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፣ 163)፡፡
መንግስትና የህዝብ አስተዳደርን በተመለከተ ሀሳባቸውን በሚከተሉት በአስር ነጥቦች አጠቃለው አስቀምጠዋል (ነጋድራስ ገብረህይወት 2003፡ 124-126)፡፡
1. ሰው የተፈጠረ የምድር ጌታ ለመሆን ነበር፡፡ ነገር ግን በመዠመሪያ ጥቂት እራሱን ስለ ሆነ የሚበቃ መሳሪያ የለውምና የምድር ተገዥ ሆነ፡፡
2. በኋላ ግን እውቀት ስላገኘ ተባዛ ተባበረም
3. በዝቶ ከተባበረም ዘንድ ሥራውን ተከፋፍሎ የሰራውን ሥራ እንደየስራው መጠን መለዋወጥ ዠመረ፣ ዋጋ ማለት የስራ መለኪያ ነው እንዳልነው ሁሉ፡፡
4. ሀብት ማለት የአለም ጌትነት መለኪያ ነው፡፡ ማንቀሳቀስና ማጋጠም የሚሆነው በስራ ብቻ ነውና ሀብት ማለት የተከማቸ ስራ ማለት ነው፡፡
5. ማንኛውም የተሰራ ስራ ከኋላ የሚከተለውን ስራ ያቀላል፡፡ ማንኛውንም ሀብት የበለጠ ሀብት ይከተለዋል፡፡
6. የህዝብ ሀብት የሚሰፋው ህዝቡ የሚያስፈልገውን ሁሉ ለመስራት ስራውን በብዙ ተካፍሎ የተለዋወጠ እንደሆነ ነው፡፡
7. የድካማቸውን ፍሬ የሚለዋወጡ ሰራተኞች እንዲቃረቡ መንገስት መጣር ይገባዋል፡፡
8. መንገድና የምድር ባቡርም ጥቅም ሚሆነው የስራ ማሰልጠኛ የትምህርት ቤቶች በያይነቱ ሲሰራና ማናቸውም እቃ ሁሉ እንደሚቻል መጠን ባገሩ ውስጥ እንዲበጅ መንግስትም ሲጥርበት ነው፡፡
9. መሬቱ በጥቂቶች ሰዎች እጅ የገባ ህዝብ በጣም ይደኸያል፡፡ የባላገሩ ጥቅም እያነሰ ይሄዳል፣ መሬትም ይረክሳል፡፡
10. የመንግስት መሰረት እርሻ ነው፡፡ ባለእርሻ የሚያገኘው ጥቅም ሲያንስ የመንግስት መሰረት አይጠናም፡፡ ባለእርሻ ሺፀቀም ግን መንግስትም ይጠነክራልና ይበረታል፡፡
ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ ከመቶ አመታት በፊት ያስቀመጧቸው እነዚህ ቁልፍ ቁልፍ ሀሳቦች በአሁኑ ሰአት ብንተገብራቸው ራሱ ብዙ እናተርፋለን፡፡ በጣም መነበብ ያለበት ምርጥ መጽሀፍ ነው፡፡
Report this article
Comments
like
12
Photo of Yonas Asfaw
Like
Comment
Share
Add a comment…
Open Emoji Keyboard
Rukya Hassen Shibeshi
አለቃ ታየ
የአለቃ ታየ ገብረማርያም ልደት በዘመነ ወንጌላዊ ሉቃስ፣ ኅዳር ፳፩ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ/ም። ይህም አፄ ቴዎድሮስ በነገሡ በሰባተኛው ዓመት መሆኑ ነው።
በጣና ሐይቅ በስተምስራቅ በምትገኘው ልዩ ስሟ ይፋግ ተብላ በምትታወቀው መንደር የተወለዱት አለቃ ታየ በልጅነታቸው ወራት ወላጆቻቸውን በማጣታቸው፣ የእናታቸው ወንድም ትግራይ ይኖሩ ስለነበር አጎታቸውን ፍለጋ ወደ ትግራይ ያመራሉ። እዚያም እንደደረሱ አጎታቸውን ስላጡዋቸው ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ አቅደው ምፅዋ ደረሱ። ምፅዋ ይገኝ በነበረው የስዊድናውያን ሚሲዮን ትምህርት ቤት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት የጀመሩትም ያኔ ነበር።
በዚያው ትምህርት ቤት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ኦሮምኛ የተረጎሙት ኦኔሲሞስም ይማሩ ነበር። እምኩሉ በተባለው በዚህ ትምህርት ቤት ለብዙ ዓመታት የወንጌልን ቃል ከተማሩ በኋላ ወደ ትውልድ አገራቸው ጎጃም ተመለሱና የግዕዝ ቅኔ ትምህርት ቤት ገቡ። ቅኔውን ከሙሉ አገባቡ ጋር አሳምረው ከዘረፉ በኋላ አለቃ የሚለውን ከፍተኛ ማዕረግ አግኝተው እንደገና ምፅዋ በመመለስ በተማሩበት እምኩሉ ትምህርት ቤት በመምህርነት አገለገሉ ።
በዚህ ጊዜም "መጽሐፈ ሰዋሰው " የተሰኘውን የመጀመርያ መፅሐፋቸውን ፅፈዋል። አለቃ በሕይወት ዘመናቸው ከደረሷቸው መፅሐፍቶቻቸው ዋና ዋናዎቹ እስካሁን ድረስ የሚገኘው በስዊድንኛ ቋንቋ የጻፉት en Teologisk strid infor Ras Mengescha" ( A theological debate before Ras Mengesha....ወይም ነገረ መለኮታዊ ክርክር በራስ መንገሻ ችሎት ) እና በእጅ ፅሑፋቸው የተዘጋጀውና አብዛኛው ማጣቀሻው በግዕዝ የሆነው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ወይም የፅንሰ-ሐሣብ መዝገብ ናቸው ።
እንደገና ወደ ትውልድ መንደራቸው የተመለሱት አለቃ ታዬ በወቅቱ ቤጌምድርን ይገዙ በነበሩት በራስ መንገሻ አቲከም ዘንድ ሞገስ በማግኘታቸው በ፲፰፻፺፩ ዓ/ም ወደ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ላኩዋቸው ። ለንጉሠ ነገሥቱም የበኩር ሥራቸው የሆነውን መፅሐፈ ሰዋሰውን በገጠ በረከትነት ሰጡ። ንጉሠ ነገሥቱም የግል ፀሐፌያቸውን ፀሐፌ-ትዕዛዝ ገብረሥላሴን ባልደረባ አድርገው ሰጡዋቸው። በንጉሠ ነገሥቱ እና በመኳንንቱ ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ በማግኘታቸው የቀኑ አንዳንድ የቤተ ክህነት ሰዎች «አለቃ ታዬ ትምህርቱን የቀሰመው ከሚስዮናውያን ነው» በሚል ሰበብ ብቻ ክስ ያበዙባቸው ስለነበር ይህኑኑ ጉዳይ ለአፄ ምኒልክ አመልክተው የሚከተለውን ደብዳቤ ተቀበሉ፦
«ሞዐ አንበሳ ዘዕምነገደ ይሁዳ፣ ዳግማዊ ምኒልክ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ። አለቃ ታየ ገብረማርያም የሚባል ምጥዋ የነበረ ሀይማኖቱን እኛ መርምረነዋልና ማንም አንዳች አይበለው በሀይማኖት ነገር ። በኅዳር ወር በስድስተኛው ቀን ፲፰፻፺፩ ዓ/ም በወረኢሉ ከተማ ተፃፈ ።»
ከዚህ በኋላ ወደ ቤጌምድር ተመልሰው ሥራቸውን ቀጠሉ። ዳሩ ግን አሁንም «የታዬ ሀይማኖት የፈረንጅ ነው። ንጉሡ ሳያውቁ ነው ማህተም የሰጡት።» የሚሉ ከሳሾች በመነሳታቸው እንደገና ተከሰው ግብፃዊው ሊቀ-ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ፊት ቀረቡ። አቡነ ማቴዎስም ጉባዔ ከተው አለቃ ታዬን ካስጠሩ በኋላ «አንት አህያ ! ሀይማኖትህ ምንድነው?» በማለት ሲጠየቁዋቸው፤ አለቃም «እኛን አህያ የሚያስብለን እናንተን በመሾማችን ነው።» ብለው ስለመለሱ፣ ነገሩ እየከረረ መጥቶ ንጉሠ ነገሥቱ ፊት ድረስ ደረሰ። ዳግማዊ ምኒልክም አለቃንም ሊቀ-ጳጳሱንም ገስጸው ነገሩን ካበረዱት በኋላ ወደ ቤጌምድር መልሰው ላኩዋቸው። ወድያውኑም እንዲህ የሚል ደብዳቤ ደረሳቸው፦
«ሞዐ አንበሳ ዘዕምነገደ ይሁዳ ዳግማዊ ምኒልክ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ። ይድረስ ከአለቃ ታዬ፣ እንደምን ሰንብተሀል? ከንምሳ መንግሥት ተልከው የመጡ ሰዎች ወደ ሀገራቸው ለመሄድ በጎጃም በኩል ወጥተዋል። ነገር ግን በኢትዮጵያ ቋንቋ የተፃፉ የጥንት መፅሐፍት በአገራችን አሉ ያንን የሚያውቅ ብልህ ሰው ይሂድና እንዲመለከት ይሁን ብለውኛል። አንተ የዚያን ሀገር ባህል ለምደኸዋልና እናንተ ዘንድ በደረሱ ጊዜ አንተም ከነሱ ጋር አብረህ ሂድ። መጋቢት ፱ ቀን ፲፰፻፺፯ ዓ/ም አዲስ አበባ ከተማ ተፃፈ።
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ 'የሕይወት ታሪኬ' በሚለው መፅሐፋቸው ይህኑኑ ሁኔታ እንዲህ ገልጠውታል፦ «የጀርመን መንግሥት የግዕዝ ቋንቋ የሚያስተምር አንድ ሊቅ ይሰጠኝ ብሎ ዓፄ ምኒልክን በለመነ ጊዜ ስመ-ጥሩውን ሊቅ አለቃ ታዬን መርጠው ሰደዱዋቸው። በጀርመን መንግሥት ሦስት ዓመት ሙሉ የግዕዝ ቋንቋ አስተምረው ኒሻን ተሸልመው ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ፣ ዓፄ ምኒልክም ኒሻን ሸልመው የአባታቸውን አገር ሰጥተው ወደ ቤጌምድር ሰደዱዋቸው።
አለቃ ታዬ በአውሮፓ አኅጉር በቆዩበት ጊዜ ብዙ ሀገራትን ጎብኝተዋል። የሚከተለው ከግል ማስታዋሻ ደብተራቸው የተገኘ ነው።
ማክሰኞ ግንቦት ፳፪ ቀን ፲፰፻፺፯ ዓ/ም
በዚህ ቀን ሌሊቱን ስንሄድ አድረን ማለዳ ሲቂልያ በ፮ ሰዓት ደረስን። ስንሄድ ውለን ማታ በ፯ ሰዓት ኒያፓል ገብተን አደርን። ሲቂልያ የኢጣልያ ክፍል ናት እርስዋም ቃሮዳን የምታህል ታላቅ ደሴት ናት። ከተሞቿም በባሕር ዳር ተሠርተው እጅግ የሚያምሩ ናቸው። ኒያፓልም በባሕር ዳር የተሠራ የጥንት የጣልያን ነገሥታት ከተማ ነው። ዛሬ ግን ራሱ ከተማው ሮማ ነው።
ቅዳሜ ግንቦት ፳፮ ቀን ፲፰፻፺፯ ዓ/ም
በዚህ ቀን በማርሴል ዋልን። ባቡሪቱ ዕቃ ስታወርድ ዕቃ ስትቀበል ዋለች። እኔና ዮሴፍ ሱማሊ በ፰ ሰዓት ከባቡር ወጥተን በሰረገላ ከተማ ለከተማ እኩል ሰዓት ሄድነ። ወርደን በእግራችን ደግሞ እየዞርን ብዙ ነገር አየነ። በዚያም እጅግ ሀፍረት የሌላቸው ደፋሮች ጋለሞቶች አየነ። በ፭ ሰዓት ወደ ማታ ባቡራችን ገብተን አደርነ።
አለቃ በጀርመን ቆይታቸው ከዓፄ ምኒልክ ጋር እየተፃፃፉ በግዕዝ የተፃፉትን መፅሐፍት ከመሰብሰብና ከመመርመር በተጨማሪ አማርኛንና ግዕዝን በበርሊን ዩኒቨርሲቲ አስተምረዋል።
ጳጉሜ ፫ ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ/ም ለንጉሠ ነገሥቱ የፃፉት ደብዳቤ እንዲህ ይነበባል፦
«.....እኔ ያስተማርኩዋቸው አማርኛና ግዕዝ ያነባሉ ይፅፋሉ። ...ደህና ሰዎች ናቸው ....የጃንሆይ መልክተኛ ብለው አክብረውና አፍቅረው ይዘውኛል ...ከአገር ናፍቆት በቀር የጎደለብኝ ነገር የለም ......ለጥበባቸው ፍፃሜ የለውም ....በየዕለቱ አዲስ ነገር አያለሁ .....አዲስ ነገር እሰማለሁ።»
«ጃንሆይ ከአገርዎ ልጆች ወደ አውሮፓ ሰደው ቢያስተምሩ መልካም በሆነ ....የያጆንና የሞሮኮ መንግሥት ሰው እየሰደዱ አስተማሩ ....ይህን አይቼ ለአገሬ መንግሥት ቅንአት እንደ እሳት በላኝ ....ምንኮ አደርጋለሁ ? አዝኘ ወደ መቃብር እወርዳለሁ .....የጃንሆይ ብር እንዲሰለጥን (እንዲለመድ ማለታቸው ነው) የፊተኛውን ብርና አሞሌ ያጥፉ .....»
በማከታተልም በግንቦት ወር ፲፰፻፺፱ ዓ/ም እንዲህ የሚል ደብዳቤ ለንጉሠ ነገሥቱ ፃፉ፦
«...እኛ ሀበሾች በመንፈሳዊና በሥጋዊ ጥበብ ወደፊት የማንገፋበት ምክንያት ምን ይሆን? ብሎ ለሚጠይቅ ሕዝቡ ሁሉ ባይማርና የወንጌልን ስብከት በብዙው ባይሰማ እውነተኛ እውቀትና አፍቅሮ-ቢጽ፣ ትህትና ቢጠፋ ነው .....ባገራችን ጥቂት ዕውቀት ያላቸው ሰዎች በመከበር ፈንታ ስለሚሰደቡና ስለሚዋረዱ ስለሚጠቁም የሚያውቁትን ጠቃሚ የጥበብ ሥራ ትተው በቦዘን መኖርን መረጡ።»
«የአዳምን ልጆች ሁሉ የፈጠረ አድልዎ የሌለበት አንድ ልዑል እግዚአብሔር ነው። ላንዱ ወገን ሕዝብ ሙሉ ላንዱ ጎደሎ ልብ አልፈጠረም .....እንዲህ ከሆነ ስለምን ያውሮፓና የእስያ ልጆች ካፍሪካ ክፍልም ጥቂቶች ብልሀተኞች ሲሆኑ ....እኛ ሀበሾች መፅሐፍ ቢማሩ፣ 'ኮቸሮ ለቃሚ'፤ ብር እና ወርቅ ቢሠሩ፣ 'ቀጥቃጭ፣ ቡዳ'፤ እንጨት ቢሠራ፣ 'አናጢ፣ እንጨት ቆርቋሪ'፤ ቆዳ ቢፍቅ 'ጥንበ-በላ፣ ፋቂ' እየተባለ ስም እየተሰጠው ስለሚሰደብ የጥበብ ሥራ ጠፋ። ስለዚህ ጉዳይ ጃንሆይ አስበው እንዲህ ያለው ነገር በአዋጅ እንዲከለከል፣ ሰዎች እንዲከበሩ ቢያደርጉ በሌላ መንግሥት ስምና መልክ በተቀረጸ ገንዘብ (የማሪያ ተሬዛ ብር ማለታቸው ነው) ከመገበያየት በጃንሆይ መልክና ስም ገንዘብ እንዲወጣ ቢያደርጉ ነፃ መንግሥትም ራሱን የቻለና የተምዋላም ይሆናል።»
ይህ ደብዳቤ ከተፃፈ ከአራት ወር በኋላ ጥር ፲፯ ቀን ፲፱፻ ዓ/ም ዓፄ ምኒልክ የትምህርትን አስፈላጊነትና የሥራን ክቡርነት ያካተተውን፤ «ሠራተኛን በሥራው የምትሰድብ ተወኝ» የሚለውን አስደንጋጭና ብርቱ አዋጅ አወጁ። [1]
ከጀርመን አገር ሲመለሱ የኢትዮጵያን ሦስተኛ ደረጃ የክብር ኮኮብ ኒሻን የተሸለሙት አለቃ ታዬ፣ በቤጌምድር እንደገና ታላቅ ተቃውሞ ተነሳባቸው። የአገሩ ገዢ የነበሩት ራስ ወልደጊዮርጊስ አቦዬም (በኋላ ንጉሥ) የሚከተለውን ደብዳቤ ሰደዱላቸው፦
«የተላከ ከራስ ወልደጊዮርጊስ፤ ይድረስ ከአለቃ ታዬ እንዴት ሰንብተሀል? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። ዝም ብለህ ተቀመጥ ስንልህ እንደዚህ ያል ትምህርት ከየት ነው ያመጣኸው? በምን ተጣላኝ እንዳትል! በ ፲፱፻፫ ዓ/ም ኅዳር ፳፬ ቀን ተፃፈ።»
አለቃም ሀይማኖታቸው ተዋሕዶ መሆኑንና የተፈጠመባቸውም ግፍ መሆኑን በመግለፅ ደብዳቤ ፅፈው ላጼ ምኒልክ መልስ ላኩ። ንጉሠ ነገሥቱም የተወሰደባቸው መሬት እንዲመለስላቸው ትዕዛዝ ሰጡ። ሁኔታው ያልተዋጠላቸው የቤተ ክህነት ሰዎች ታዬ ፀረ ማርያም ነውና አገር መግዛት አይገባውም የሚል ሌላ ክስ አመጡ። ነገሩ የሀይማኖት ጉዳይ በመሆኑ ወደ ግብፃዊው ሊቀ-ጳጳስ ዘንድ ነገር ተመራና ጥር ፳፬ ቀን ፲፱፻፫ ዓ/ም በዋለው ጉባዔ አለቃ ፈለቀ የተባሉ የቤተ-ክህነት ወኪል ከሳሽ ሆነው በመቅረብ፣ «አለቃ ታዬ ለስዕልና ለመስቀል አይሰግድም፤ በሞቱ ቅዱሳን አማላጅነት አያምንም፤ ዝክርና ምፅዋት የሞተ ሰውን ሊያፀድቅ እንደማይችል ይናገራል፤ የልማድ ፆም ዋጋ እንደሌለው ይናገራል፤ ቀናትን አያከብርም» ሲሉ የክሱን ጭብጥ አስረዱ።
በቀረቡት ክሶች ላይ ከፍተኛ ክርክር ተደርጎ ሊቀ-ጳጳሱ ከመሳፍንቱና ከባልደረቦቻቸው ጋርዔ በመሆን አለቃ ታዬን ከገሰፁ በኋላ በነፃ ቢለቁዋቸውም፤ በነፃ መለቀቃቸው ያበሳጫቸው ካህናት የንጉሠ ነገሥቱ ባለ ሙሉ ሥልጣን እንደራሴ ለነበሩት ለራስ ተሰማ ናደው አቤት በማለታቸው ያለ ሕግ ወደ ታላቁ ወህኒ ቤት እንዲገቡ ተደረገ።
ከጥቂት ጊዜ እሥራት በኃላ ተፈተው በቁም እሥር እንዲቆዩ ተደርገው፣ በ፲፱፻፲፪ ዓ/ም ለመንግሥት አማካሪነት ተመርጠው መሥራት ጀምረው ነበር። ምሁሩ አለቃ ታዬ ነሐሴ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
በቀብራቸው ወቅት እህታቸው ወይዘሮ ላቀች አምነህ እንዲህ ሲሉ ተቀኙላቸው
ከወህኒ ቤት አስረው የዘጉበት ሳንቃ
ብሎ ተናግሮ ነው የወንጌል ቃል ይብቃ
የወንጌልን ስራት ተማሩ ቢላቸው
ትልቁም ትንሹም ሁሉም ደደብ ናቸው
አሉት ጸረ ማርያም መልስ ቢሳናቸው
እውቀትና ምግባር ጉድጓድ ተከተተ
አራት ነው እንጂ መች አንድ ሰው ሞተ
ወዝውዘው ወዝውዘው ጣሉት እንደ ዝሆን
ያው ወደቀላቸው ይበሉት እንደሆን
ከጨለማ መሀል ቢወጣ ብርሀን
ኣጥፉት አጥፉት አሉ እንዳይታየን
የግርጌ ማስታወሻ
[2]
ዋቢ ጽሑፍ
^ ጳውሎስ ኞኞ፣ አጤ ምኒልክ (፲፱፻፹፬ ዓ/ም)፣ ገጽ ፪፻፴፰ - ፪፻፴፱
^ ኃይሉ ከበደ የአለቃ ታዬ ገብረማርያም የሕይወት ታሪክ ቀ .ኃ . ሥ . ዩኒቨርሲቲ 1963 ኅሩይ ወልደሥላሴ (ብላቴን ጌታ) የሕይወት ታሪኬ አ .አ . 1951 ገብረሕይወት ባይከዳኝ ...አፄ ምኒልክና ኢትዮጵያ ብርሀን ይሁን ማተሚያ ቤት አስመራ 1912 ባህሩ ዘውዴ pioneers of change in Ethiopa....the reformist intellectualls at the early twentineeth century,Oxford 2002 Getachew Hayle......Aasulv Land, Samuel Robinson (eds-) the missionary factor in ethiopia........Lund university August 1996 Prouty,Chris..... Empress Taytu and Minilik 2nd Ethiopia....1883-1910 London
መደብ: አለቃ ታየ
ይህ ገጽ መጨረሻ የተቀየረው እ.ኣ.አ በ03:51፣ 1 ዲሴምበር 2020 ዓ.ም. ነበር።
እኛ ኢትዮጵያዊያን የአባይን ጉዳይ አሸንፈናል፤ አሁን የቀረን ራሳችንን ማሸነፍ ነው
እኛ ኢትዮጵያዊያን የአባይን ጉዳይ አሸንፈናል፤ አሁን የቀረን ራሳችንን ማሸነፍ ነው
ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት በአባይ ወንዝ ላይ ያለንን ቁጭት በብዙ መልኩ ስንገልጽ ኖረናል፤ አዝማሪው በድምጹ፤ ጸሐፍት በብዕራቸው፤ ተዋንያን በመድረክ ቴአትሮችና ፊልሞች እንዲሁም ምሁሩ በጥናትና ምርምሮቹ ስለአባይ ተክዘው ኖረዋል፤ እንደመታደል ሆኖ ይህ ትውልድ ከዚህ ትካዜ ለመላቀቅ የሚስችለውን አኩሪ ገድል ችግሮች ሳበግሩት አባይን በአገሩ አስሮ ለሃይል ማመንጫነት፣ ለአሳ ሃብት ልማት እንዲሁም ለቱሪዝም ወዘተ አውሎታል
አሁን የበረታብን ትልቁ ተግዳሮት ከራሳችን ጋር ያላቆምነው ጦርነት ነው፤ የዘመናችን የኢትዮጵያ ችግር እኛ ህዝቦቻ ራሳችንን ማሸነፍ አለመቻላችን ነው! ራስን ለማሸነፍ እንቅፋት ከሆኑብን ነገሮች ዋናው ስለጉዳዩ ያለን የተሳሳተ ግንዛቤ/አተያይ ነው፤ ለብዙዎቻችን ራስን ማሸነፍ መሸነፍ ነው፤ ራስን ማሸነፍ ደካማነት ነው፤ ነገር ግን ራስን ማሸነፍ ጀግንነት ነው፤ ሽንፈት ሳይሆን ድል ነው፤ ራሱን ያሸነፈ ከራሱ አልፎ በዙሪያው ላሉ ሁሉ መፍትሄ ይሆናል እኛ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ያለንበትን ሁኔታ ከመረመርነው የችግሮቻችን ሁሉ መሰረት የሚሆነው ከራሳችን ጋር ጦርነት ውስጥ መግባታችን ነው፤ ራሳችንን አለማሸነፋችን ነው
ሁላችንም ደረጃው ወይም ፈርጁ ይለያይ እንጂ ከራሳችን ጋር ጦርነት ላይ ከከረምን ውለን አድረናል፤ በመሬት ላይ የምናየው የህዝብ ምስቅልቅል የፖለቲከኞች ቁማር እና/ወይም ዳፋ ብቻ አይደለም፤ እያንዳንዳችን ዛሬ ላለንበት አስከፊ ሁኔታ ድርሻ አለን
ይህ አጭር መጣጥፍ በሚከተሉት ነጥቦች ዙሪያ ዳሰሳ ያቀርባል፡-
• ለመሆኑ ራስን ማሸነፍ ምን ማለት ነው?
• ራሱን ያላሸነፈ ሰው ባህሪያት መገለጫዎች ምንድናቸው?
Download
51 Views
አለቃ ታዬ ማን ናቸው? Short Biography of Aleqa Taye Gebremariam
ይህ መጣጥፍ የስነ ጽሁፍ ሰዎች እና ስራዎቻቸው፡ ልቦለድ፣ የተውኔት ድርስት እና ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ (1850-1960 ዎቹ) ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ ነው፡፡ መጽሐፉ በ2011 መስከረም ወር ለህትመት የበቃ ነው፡፡ አለቃ ታዬ ገብረ ማርያም በዘመናዊ የኢትዮጵያ አገረ ግዛት ግንባታ መባቻ ወቅት በተራማጅ አስተሳሰባቸውና በሀይማኖታዊ አስተምህሮታቸው ጎልተው የሚነሱ የስነ ሃይማኖት (theology) ምሁርና የታሪክ ጸሃፊ ነበሩ፡፡ በዚህች አጭር መጣጥፍ የእኚህን አንጋፋ ሰው የህይወት ታሪክ በአጭሩ ለማስቃኘት እሞክራለሁ፡፡ በህይወት ጉዛቸው ትርክት የወቅቱን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ከፍታና ዝቅታ ለማስቃኘት እሞክራለሁ፡፡
ይህ መጣጥፍ የስነ ጽሁፍ ሰዎች እና ስራዎቻቸው ሌቦሇዴ፣ የተውኔት ዴርስት እና ጋዛጠኝነት በኢትዮጵያ (1850-1960 ዎቹ) ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰዯ ነው መጽሐፉ በ2011 መስከረም ወር ሇህትመት የበቃ ነው አሇቃ ታዬ ገብረ ማርያም በመናዊ የኢትዮጵያ አገረ ግዚት ግንባታ መባቻ ወቅት በተራማጅ አስተሳሰባቸውና በሀይማኖታዊ አስተምህሮታቸው ጎሌተው የሚነሱ የስነ ሃይማኖት (theology) ምሁርና የታሪክ ጸሃፊ ነበሩ በዙህች አጭር መጣጥፍ የእኚህን አንጋፋ ሰው የህይወት ታሪክ በአጭሩ ሇማስቃኘት እሞክራሇሁ በህይወት ጉዚቸው ትርክት የወቅቱን የኢትዮጵያ የፖሇቲካ ከፍታና ዜቅታ ሇማስቃኘት እሞክራሇሁ
1. አሇቃ ታዬ ገብረ ማርያም (1853 - 1916 ዓ.ም) ከቀዯምት ኢትዮጵያዊያን ምሁራን አንደ የሆኑት አሇቃ ታዬ ገብረ ማርያም ህዲር 21 ቀን 1853 ዓ.ም በወቅቱ አጠራር በጌ ምዴር አገረ ግዚት፣ ከምከም ቃሮዲ፣ ይፋግ በሚባሌ ቦታ ተወሇደ በግብርና ስራ የሚተዲዯሩት አባታቸው የትምህርትን ጥቅም ጠንቅቀው የተረደ ነበሩና ሌጃቸው ገና አፍ መፍታት ሲጀምር ከፊዯሌ ገበታ እንዱተዋወቅ ወዯ ትምህርት ቤት አስገቡት፤ የወሊጆቻቸው እንክብካቤ ግን ብዘም የሇቀ አሌነበረም፤ እናታቸውን በህጻንታቸው ያጡት አሇቃ ታዬ አባታቸው ጥሇዋቸው ወዯ ሸዋ ክፍሇ አገር በመሰዯዲቸው አጎታቸው ይኖሩበት ከነበረው ትግራይ እንዱሄደ ሆነ እዙያ ሲዯርሱ ግን አጎታቸው ወዯ ህንዴ አገር እንዯሄደ ስሇተነገራቸው ወዯዙያው መሄዴ አሇብኝ ብሇው ጉዞቸውን በመርከብ ሇመጀመር ወዯ ቀይ ባህር ዲርቻዋ ምጽዋ ከተማ አመሩ፤ ነገር ግን ውጥናቸው እንዲሰቡት ሳይሆን የህይወት ጉዞቸውን በላሊ አቅጣጫ የቀየረ ሆነ። በምጽዋ ምንም መዴም ሆነ የሚያውቁት ሰው ያሌነበራቸው አሇቃ ታዬ እንዯ ቤተሰብ ሰብስቦ ሉያስተምራቸው የስዊዴሽ ሚሽነሪ ት/ቤት ፈቀዯ። የስዊዴን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በአሇቃ ታዬ ህይወት ውስጥ ትሌቅ ቦታ አሇው፤ በትምህርት አቀባበሊቸው ፈጣን እና አይነግቡ ነበሩና የትምህርት ቤቱ ዱሪክተር የነበሩት ሉንዲሃሌ የቅርብ ረዲታቸው እንዱሆኑ አቀረቧቸው፤ በዙህም ቅደሳን ጥንታዊ መጻህፍትን በመተርጎሙ ስራ ሊይ የያኔው ወጣት ታዬ በትጋት ተሳትፈዋሌ
አሇቃ ታዬ መንኩለ ከሚባሇው የሚሽነሪ ትምህርት ቤት ሳለ ሇሀገረኛ መጽሃፍትና ሇኦርቶድክስ ተዋህድ ቤተ ክርስቲያን የትምህርት ስርዓት የተሇየ ፍቅር ነበራቸው ጥንታዊ መጻህፍትንም እያዯኑ አብዜተው ይመራመሩ ነበር፤ ነገር ግን መጻህፍቱ በግእዜ ቋንቋ የተጻፉ በመሆናቸው የግዕዜ ቋንቋን ማወቅ ይጠበቅባቸዋሌ፤ እናም በ1875 ዓ.ም ወዯ ትውሌዴ መንዯራቸው ተመሌሰው ግዕዜ ትምህርት ቤት ገቡ፤ ከሁሇት ዓመታት በኋሊ ትምህርታቸውን እንዲጠናቀቁ በጌ ምዴርን ሇቀው ወዯ ምጽዋ አቅንተው በመምህርነት፣ በአስተርጓሚነትና በወንጌሌ ሰባኪነት አገሌግሇዋሌ። የምእራቡን ክርስትና አስተምህሮ እና የአውሮፓን ባህሌ መሰረት አዴርጎ የተቀረጸውን መንፈሳዊ የትምህርት ስርዓት በአንዴ በኩሌ፣ እንዱሁም ከታሊሊቅ የኦርቶድክስ ተዋህድ አዴባራትና ገዲማት የምስራቁን የክርስትና አስተምህሮ በጠሇቀ ሁኔታ መርምረዋሌ፤ ያገኙትን መንፈሳዊ ዕውቀት ሇህዜብ ሇማስተሊሇፍም ‹መጽሀፈ ሰዋሰው› የሚሇውን መጽሃፋቸውን አዯራጅተው ነበር። አሇቃ ታዬ ከአስራ ሶስት ዓመታት በኋሊ በ1890 ዓ.ም ወዯ ትውሌዴ አገራቸው በጌምዴር ተመሌሰው ወንጌሌን ሉሰብኩ፣ በዙያውም የቅኔ ትምህርታቸውንም በበጌ ምዴር ዘሪያ በሚገኙ ታሊሊቅ ገዲማት ሉከታተለ መጡ
አስተምህሯቸው ግን የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋህድ ቀኖናን የሚቃረን ነው በሚሌ ከህዜብ ውግትን አስነስቶባቸው ነበር። ማህበራዊ መገሇሌ፣ ብልም አካሊዊ ጥቃት ተዯጋግሞ ዯርሶባቸዋሌ የበጌምዴር አውራጃ ኦርቶድክስ ሀይማኖት አባቶችና ካህናት ከሰዋቸውም ነበር፤ በዙህም የአውራጃው ገዢ ከነበሩት ከራስ መንገሻ አቲከም ንዴ ቀርበው ሀይማኖታዊ አቋማቸውን እንዱገሌጹ ተዯረገ በሸንጎው ሊይ አሇቃ ታዬ ባንዴ ጎን፣ ከሳሾቻቸው ዯግሞ በላሊ ሆነው ሇረጅም ሰዓታት ተከራከሩ፤ ራስ መንገሻ አቲከምም የአሇቃ ታዬን ሀሳብ ይበሌጥ ገዢ ሆኖ ስሊገኙት የሙግቱን የአሸናፊነት ፍርዴ ሰጧቸው። ይህ የአሇቃ ታዬ አሸናፊነት ሙግቱን ከመርታትም ባሇፈ ትርጉም ነበረው፤ አጋጣሚው ከኦርቶድክስ ቤተ ክርቲያን ሉቃውንት ጫና ሇጊዛውም ቢሆን እፎይታን ሇማግኘታቸው ምክንያት ሆናሌ። እንዳት? በክሱ ሰበብ ራስ መንገሻ አቲከምን አግኝተዋሌ፤ በአጭር ጊዛም ጥሩ ግንኙነት መስርተው ነበርና አሇቃ ታዬ የሚዯርስባቸው መገሇሌና መዴሌዖ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት እንዱያውቀው ሆኗሌ። ራስ መንገሻ አቲከም አሇቃ ታዬን ዯብዲቤ አስይውና አሽከራቸውን እንዱያጅቧቸው አዴርገው ወዯ ዲግማዊ ምኒሌክ ሰዯዶቸው። በጊዛው የአጼ ዮሐንስ የሌጅ ሌጅ የሆኑት ራስ ስዩም መንገሻ በአጼ ምኒሌክ መንግስት ሊይ ሸፍተው ነበርና በራስ መኮንን የተመራ ጦር ወዯ ሰሜን ምቶ ነበር፤ ምኒሌክም የጦሩን ሁኔታ ሇመከታተሌ ዯነባ አካባቢ ተገኝተው ነበርና አሇቃ ታዬን ያገኟቸው በዙያው ነበር፤ አመሇካከታቸውን በተመሇከተም እንዱገሌጹሊቸው አዴርገው ነበር፤ ዲግማዊ ምኒሌክ መጽሀፈhttps://www.researchgate.net/publication/336367643_Short_Biography_of_Aleqa_Taye_Gebremariam
https://www.researchgate.net/publication/336367643_Short_Biography_of_Aleqa_Taye_Gebremariam
https://www.researchgate.net/publication/336367643_Short_Biography_of_Aleqa_Taye_Gebremariam
Wednesday, June 5, 2024
ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ! (የቤተክርስቲያን ሀኪም)
ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ!
(የቤተክርስቲያን ሀኪም)
📖ቅዱስ አትናቴዎስ ማን ነው?
ቅዱስ አትናቴዎስ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዘመነ ሰማዕታት መጠናቀቂያ በ296/300 ዓ.ም አከባቢ እስክንድርያ ግብፅ ውስጥ ነው የተወለደው:: ወላጆቹ አረማውያን በመሆናቸው ክርስትናን አልተማረም ነበር:: አሞጽን ከእረኝነት ሐዋርያትን ከአሳ አጥማጅነት የጠራ እግዚአብሔር አምላክ አትናቴዎስን ከጨዋታ ሜዳ ጠርቶ የቤተክርስቲያን ወርቃማ ልጅ አድርጎታል፡፡ ሕጻን እያለ ለጫዋታ ከቤቱ ሲወጣ የክርስቲያን ልጆች ሃይማኖታዊ ጨዋታ ሲጫወቱ ተመለከተ:: ሊቀላቀላቸው ቢፈልግም ክርስቲያን ባለመሆኑ ከለከሉት:: አትናቴዎስም ክርስቲያን ልሁንና አጫውቱኝ ቢላቸው እሺ ስላሉት ሕጻናቱ ዕጣ ተጣጣሉ:: ላንዱ ቄስ: ላንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያሪክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕጻናት ይሰግዱለት ጀመር:: በአጋጣሚ ሕጻናቱ ይሕንን ሁሉ ሲያደርጉ የወቅቱ ፓትርያሪክ ቅዱስ እለ እስክንድሮስ በመገረም ያያቸው ነበርና ለሕጻኑ አትናቴዎስ ትንቢት ተናገረለት:: ከዚያም የአትናቴዎስ አባቱ ሲሞት ሊቀ ዻዻሱ ከእናቱ ወስዶ አጥምቆ የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ሁሉ በልቡናው ላይ ቀረጸበት:: ከዚህ በኋላ ዲቁናን ሹሞ አስተምር አለው:: ምንም ሕጻን ቢሆንም ከሊቅነቱ: ከአመላለሱና ከአንደበቱ ጣፋጭነት የተነሳ የሰማው ሁሉ ይደነቅ ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ አድራለችና::ቅዱስ አትናቴዎስ ሊቀ ዲቁና በተሾመ ወራት አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን በመረበሹ ኒቅያ ላይ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡ ጸሐፊ አድርገው ሾሙት:: በጊዜውም በዕድሜ የስንት ጊዜ ትልቁ የሚሆነውን አርዮስን ተከራክሮ ምላሽ አሳጣው::
ቅዱስ አትናቴዎስ ከሊቃውንቱ ጋር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: እግዚአብሔር መሆኑን በአደባባይ መሠከረ:: ጸሎተ ሃይማኖትንም ያረቀቀው እርሱ ነው::
ፓትሪያሪክ አለ እስክንድሮስ ባረፈ ጊዜ በመንበሩ አትናትዮስን ይሾሙት ዘንድ አሳስቧቸዉ ነበር ህዝቡም ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት እንደሆነ ስለ ተረዱ ሊሾሙት ወሰኑ ቅዱሱ ግን እኔ ምናምንቴ ነኝ ለዚህ ክብር የምገባ አይደለሁም ሲል እራሱን በተራራዎች ስር ደበቀ፤ ህዝቡ ግን ፈልገዉ አመጡት፤ ከዚህ በኃላ በ33 ዓመቱ በ328 ዓ/ም የእስክንድርያ (የግብፅ) 20ኛ ፓትርያሪክ ሆኖ ተሾመ:: ከቅዱስ እንጦንስ ምንኩስናን የተቀበለ የመጀመሪዉ ፓትርያሪክ ነዉ፡፡ የምንኩስና ልብሱንም የጳጳሳት ዩኒፎርም እንዲሆን አድርጓል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በመልካም እረኝነት ለ48 ዓመታት ሲመግብ ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል::
📚ቅዱስ አትናቴዎስ ለኢትዮጵያ
በ328 ዓ.ም. ቅዱስ ፍሬምናጦስ በእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪክን ለኢትዮጵያ ለማሾም በመጠባበቅ ላይ እያለ 19ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ አለ እስክንድሮስ አርፎ በምትኩ በእስክንድርያ መንበር ቅዱስ አትናቴዎስ ተተካ፡፡በዚህ ጊዜ ፍሬምናጦስ የተላከበትን ጉዳይ ለቅዱስ አትናቴዎስ አቀረበ ፓትርያሪክ አትናቴዎስም በጉዳዩ ተደስቶ ለኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ቋንቋቸውንና ባህላቸውን የሚያውቅ ሌላ ባለመገኘቱ ራሱን ቅዱስ ፍሬምናጦስን ‹‹ጳጳስ ዘአክሱም ወዘኩሉ ኢትዮጵያ›› ብሎ የመጀመሪያዉን ጳጳሳችንን በቅብአትና በአንብሮተ እድ ሹሞ ላከው፡፡
📚መከራዉና ስደቱ
የቅዱስ አትናቴዎስን መከራዉንና የስደት ሕይወቱን ማወቅና መረዳት በተለይ የአራተኛውን መቶ ዓመት፣ በአጠቃላይ ደግሞ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የተመሠረተችውን የቤተ ክርስቲያንን የዚህ ዓለም የመስቀል ጉዞ መረዳት ነው፡፡ ይህ አራተኛው መቶ ዓመት ደግሞ ምንም እንኳን ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር እጅ ቢሆንም እንደ ሰው ስንመለከተው ግን የቤተ ክርስቲያንን መሠረታዊ አቅጣጫ ሊያስለውጡ የደረሱ ከባድ ኑፋቄያዊ ፈተናዎች የተነሡበት ዘመን ነበር፡፡
ቤተ ክርስቲያን ከግማሽ ምዕተ ዓመት ለሚበልጥ ዘመን ከአርዮሳውያን ጋር ላደረገችው እልህ አስጨራሽ ትግል መለያ ግርማና ወካይ መገለጫው ቅዱስ አትናቴዎስ ነው፡፡ ዘመን ገጠሙ የነበረው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ የቅዱስ አትናቴዎስን ተጋድሎ በተመለከተ ሲናገር‹‹ አትናቴዎስን ሳመሰግን የማመሰግነው የመልካም ተጋድሎ ሕይወትን ነው፤ ስለ እርሱ መናገርና ስለ መልካም ተጋድሎ ሕይወት መናገር አንድ ናቸውና፣ ምክንያቱም እርሱ የመልካም ተጋድሎ ሕይወትን በምልዓት ገንዘብ አድርጓልና ›› ያለው ለዚህ ነበር፡፡
ቅዱስ አትናቴዎስ በዘመኑ ለ5 ጊዜ ከመንበሩ አፈናቅለው ወደ በርሃ እንዲጋዝ አድርገዉታል፡፡ (በስደት ከ15/16 ዓመታት በላይ አሳልፏል)፡፡ ቅዱሱ በተሰደደባቸው ቦታዎች መከራን እየተቀበለ ያላመኑትን አሳምኗል:: በጎቹ እንዳይባዝኑበት ደግሞ በጦማር (በደብዳቤ) ይጠብቃቸው ነበር:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናገኘው ቃለ ሃይማኖት በዚህ ዘመን የተጻፈ ነው::
· የቅዱሱ የመጀመሪያ ስደቱ መንስኤ የአርዮሳዊያን መናፍቃን የሐሰት ክሶች ነበሩ አትናቴዎስም በጉባኤ መዓል ሐሰተኝነታቸዉን አጋልጦ ንጽሕናዉን አስመስክሩዋል፡፡ በዘመኑ የነበረዉ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ንጽህናዉን ቢረዳም እነዚህ መናፍቃን እርሱን ለማጥፋት ቆርጠዉ እንደተነሱ ስለተረዳ ከነሱ ሊሰዉረዉ ሲል ወደ ትሬቬሬ እንዲጋዝ አደረገዉ::
· ሁለተኛ እና ሶስተኛ ስደቱ ደግሞ (ትንሹ ቆስጠንጢኖስ) የአባቱን (ታላቁ ቆስጠንጢኖስን) ዕረፍት ተከትሎ ነገሠ:: ወዲያውም አርዮሳዊ መናፍቅ ሆነ:: ሃይማኖታቸው የቀና አባቶችንም ያሳድድ ገባ:: ከአበው ቅዱሳን መካከል ግን የዚህ መከራ ቀዳሚው ገፈት ቀማሽ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ ነበር:: ከ መንበሩም ሁለት ጊዜ አፈናቅሎታል፡፡ በተለይ አንድ ጊዜ ቅዱሱን ወደ በርሃ አግዞ: መናፍቅ ዻዻስ በግብጽ ሹሞ: ብዙ ክርስቲያኖችን በግፍ ሲያስገድል: ቅዱሱን ለ6 ዓመታት አሰቃየው:: የወገኖቹ (የልጆቹን) ስቃይ የሰማው ቅዱስ አትናቴዎስ ግን በድፍረት ወደ ቤተ መንግስት ገብቶ ተናገረው:: ሁለት አማራጭን አቅርቦ "ወይ ግደለኝና እንደ አባቶቼ ሰማዕት ልሁን: ካልሆነ ግን ወደ መንጐቼ (ምዕመናን) መልሰኝ" አለው:: መናፍቁ ንጉሥም ቢገድለው ብጥብጥ እንደሚነሳ ስለሚያውቅ በስልት ሊያጠፋው ወሰነ:: ቀዛፊ መቅዘፊያ ምግብና ውሃ በሌላት ጀልባ ውስጥ ከቶም ሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ ጣለው:: ድንገት ግን ከሰማይ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ ወረደ:: ሚካኤልና ገብርኤል ባሕሩን እየቀዘፍ: ሌሎች መላእክት እየመገቡት እስክንድርያ (ግብጽ) አድርሰውት ተሠውረዋል:: ሕዝቡም በታላቅ ሐሴት እየዘመሩ አባታቸውን ተቀብለውታል::
· ቀጥሎም ንጉሡ አረማዊዉ ዮልዮስ ሲነግስ ቅዱሱ ጣኦት አምላኪዎችን እያሳመነ ያጠምቅ ነበርና በዚህ ስራዉ ተናዶ ሊያሲዘዉ ትእዛዝ አዘዘ በዚህም ንጉሱ እስኪሞት ድረስ በስደት ቆየ፡፡
· በመጨረሻም ንጉስ ጁቪያን ሲነግስ አሪዮስያዊ ነበርና 30 ጳጳሳትን አስገደለ አትናትዮስም በመቃብር ቤት ተሸሸገ ነገር ግን ንጉሱ የሕዝቡንና የጳጳሱን ጽናት ሲመለከት አትናትዮስን ወደ መንበሩ መለሰዉ፡፡ አትናትዮስ በዚህ ጊዜ 72 ዓመት ሞልቶት ነበር በብዙ እንግልትም ደክሞ ነበር ቢሆንም ግን ለሕግ የቆመ ጠንካራ የቤ/ክ ታላቅ ጠበቃ ነበር፡፡
· ቅዱሱ ብቻዉን የሮማዉያን ቄሳሮችን ዛቻና ኃይል ያለ ምንም ፍርሃት የተጋፈጠ ልዩ ጀግና ነዉ፡፡ በዚያ ዘመን የነበረዉ በቅዱስ አትናትዮስና በ አሪዮስያዊያን መካከል የተካሄደዉ ተጋድሎ ‹‹አትናቴዎስ ከዓለሙ ጋር፤ ዓለሙም በአትናቴዎስ ላይ›› "Athanasius against the world." ብለዉ ገልጸዉታል፡፡
📚አትናቴዎስ ለቤተክርስቲያን
1. በስሙ የሚጠራ ቅዳሴን ደርሷል ‹‹ቅዳሴ አትናቴዎስ››
2. ጸሎተ ሃይማኖትን አርቆ ጽፏል
3. የመጽሐፍ ቅዱስን ቁጥር ለይቶ ገልጿል
4. ለኑፋቄ ትምህርት መልስ ሰጥቷል
5. ብዙ መልእክታትን ጽፎ ለአብያተ ቤተክርስቲያናት አስተላልፏል
6. ስለ ነገረ ሥጋዌ ጽፏል
📚እረፍቱ ለ ቅዱስ አትናቴዎስ
አትናቴዎስ በዘመኑ ሁሉ በቤተ ክርስቲያን የተቃጣዉን ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ዘመቻ ሲዋጋ የኖረ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን አርበኛ ነዉ፡፡ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ አትናቴዎስን ‹‹ የቤተክርስቲያን ምሶሶ›› ይለዉ ነበር፡፡ አትናትዮስ ሃይማኖተኛ፤ ጀግና፤ ዘዴኛ፤ ታላቅ የትህትና አባት እና የሚያስደሰት ጥበብን አሙዋልቶ የያዘ ነበር፡፡ ቅድሱ በሕይወት ዘመኑ ብዙ ሃይማኖታዊ ሥራዎችን ሠርቶ አልፏል፡፡ ሐዋርያዊው ቅዱስ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋግቶ: ብዙ ስቃይንም ተቀብሎ በ 75 ዓመቱ ግንቦት 7 ቀን በ373 ዓ/ም አካባቢ አርፏል:: ቤተ ክስርቲያን "ሊቀ ሊቃውንት፤ ርዕሰ ሊቃውንት፤ የቤተ ክርስቲያን (የምዕመናን) ሐኪም (Doctor of the Church)፤ ሐዋርያዊ፤ የሕይወት ምንጭ" ብላ ትጠራዋለች::
+"+ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዐን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩ ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና:: +"+ (ማቴ. 5:10)
ምንጭ፡-
ቅዱስ አትናቴዎስ ሕይወቱ እና ትምሕርቱ
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቁጥር 1 See less
የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 1) ክፍል አራት
የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 1) ክፍል አራት
DECEMBER 4, 2019
ጸአተ ግብጽ ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ተሃድሶ
LEAVE A COMMENT
EDIT
የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 1)
ክፍል አራት
የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን የዛሬው ትምህርት ደግሞ ትውልድ የተሰጠውን የእግዚአብሔር እውነት የሚፈልግበትና ጌታ በሰጠው እውነት ላይም እስከ መጨረሻው ቆሞ የሚታገልበት በመሆኑ ይህንንና እነዚህን በመሣሠሉ ትምህርቶች እየተጠቀመ ሊነቃ ሊመረምር በብዙ ሊረዳና ሊገነዘብ ይገባል እላለሁኝ በሐዋርያዊው ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተመሠረተች የመጀመርያዋ ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን ያቋቋማት ሐዋርያው ሰላማ ከሞተ በኋላ ጥሩ ሁኔታ አላጋጠማትም ከእርሱ በኋላ የተነሱት ሰዎች ጤናማዋን የወንጌል ቤተክርስቲያን ማን ማንን ሊመራ ይችላል በሚል ፉክክር የማን ቤት ጠፍቶ የማን ይበጅ ቀረርቶ ሲሉ ተርተውና በተረታቸውም እርስ በእርሳቸው ሳይቀር ተደባድበው ባለመስማማት ከሣቴ ብርሃን ሰላማን የሾሙት ግብጻውያን ስለሆኑ ግብጻውያን ይምሩን ሲሉ ለግብጻውያን አሳልፈው ሰጧት ግብጻውያንም ለ1600 ዓመታት በጨለማና በባርነት ገዟት ታድያ ሰላማ የመሰረታት ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን ውድቀቷ የጀመረው ያኔ ነው በዚህም ውስጥ ዘመን መምጣቱ አይቀርምና ዘመን ስለመጣልኝ ነጻነቴን አውጄ ከዚህ ባርነት ወጣሁ ብትልም ነገር ግን አሁንም በዚሁ በባርነቱ ምክንያት ለዓመታት የጣለችውን ወንጌል እንደሚገባ ልታነሳው ያልቻለች በመሆንዋ ዘርዓ ያዕቆብ የተባለው ንጉሥ በ15 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ተነስቶ ይህቺን ያላገገመችና ከቁስልዋም ፈጽሞ ያልተፈወሰችን ቤተክርስቲያን ወደማትፈልገው አቅጣቻ በመምራት ይባስ ብሎ ከአዳኝዋ ከኢየሱስ ለይቶ አፋታት በጅማሬዋና በቅድምና ዘመንዋ በተቀበለችው ጌታ አማካኝነት ወደላይ መውጣት የሚገባትን ይህቺኑ ቤተክርስቲያንም ወደታች አውርዶ የቁልቁለቱን መንገድ እንድትመርጥና በዚያው መንገድ ላይ እየተንደረደረች እንድትወድቅ እንድትንከባለልም አደረጋት
የተወደዳችሁ ወገኖች በቪዲዮ የተለቀቀው ትምህርት እንግዲህ ይህንኑ አስመልክቶ የተነገረ ነው በመሆኑም ትምህርቱ ታድያ ቤተክርስቲያንዋ በተመሠረተችበት በቅድምና ዘመንዋ ያመነችው መጽሐፍቅዱሳዊ እውነት ምን እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን ይሄ መጽሐፍቅዱሳዊው እውነት ደግሞ በመጽሐፍቅዱሱ ላይ ሠፍሮ ያለ እውነት ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እስከ ዛሬ ድረስ በምትጠቀምባቸው የቅዳሴ ፣ የሰዓታት ፣ የዚቅ ፣ የድጓ እንዲሁም የሃይማኖተ አበው እና የመሣሠሉት መጻሕፍት ውስጥ በትክክል ተጽፎና ሰፍሮ የሚገኝ ነው ይሁን እንጂ እነዚህን የመሠሉ የቃሉ እውነቶች በበተክርስቲያን መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈውና ሰፍረው ቢገኙም ደፋሩ ዘርዓያዕቆብ ግን ለእነዚህ ተጽፈው ላሉ እውነቶች ቦታ ባለመስጠት ሥልጣኑን ተገን አድርጎ እንደ ተአምረ ማርያም ያሉ የወንጌሉን እውነት የሸፈኑ የጨለማ መጻሕፍትን በመጻፍ ከዚህም ሌላ መጻሕፍትን በማያውቁ ፣ ቅዠት ናላቸውን ባዞረውና በተወናበዱ የዋሻ ፣ የገድል ነዋሪ ባሕታውያን የተጻፉ ገድላትና ድርሳናትን በመሰብሰብ ምን የመሰለችዋን ኦርቶዶክሳዊት የወንጌል ቤተክርስቲያን እስከዛሬ ድረስ የአሮጊቶች ተረት መከማቻና መጠራቀምያ አደረጋት
ቅዱሳን ወገኖቼ ትምህርቱ በስፋት የሚጠቁመን አሁንም ይህንኑ እውነት ነው ታድያ ተጨባጭ የሆነውን ይህን እውነት ለሕዝባችን ለመስጠት እያንዳንዱን ሃሳብ በጥልቀት በተናጠልና በዝርዝር የምናይበት ትምህርት ስለሆነ ሰፊ ትንታኔ ለመስጠት በዚህ አርዕስት ዙርያ ለተወሰኑ ጊዜያቶች እንቆያለንና በማስተዋል እንድትከታተሉ ጥሪዬን ለእናንተ ለወገኖች በፍቅር ማስተላለፍ እወዳለሁ ግንዛቤያችሁ ይበልጥ እንዲጨምር ግን ይህንኑ የተለቀቀውን ቪዲዮ ደግማችሁ ስሙት ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ
ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 1) ክፍል አራት
የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 1) ክፍል አራት
DECEMBER 4, 2019
ጸአተ ግብጽ ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ተሃድሶ
LEAVE A COMMENT
EDIT
የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 1)
ክፍል አራት
የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን የዛሬው ትምህርት ደግሞ ትውልድ የተሰጠውን የእግዚአብሔር እውነት የሚፈልግበትና ጌታ በሰጠው እውነት ላይም እስከ መጨረሻው ቆሞ የሚታገልበት በመሆኑ ይህንንና እነዚህን በመሣሠሉ ትምህርቶች እየተጠቀመ ሊነቃ ሊመረምር በብዙ ሊረዳና ሊገነዘብ ይገባል እላለሁኝ በሐዋርያዊው ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተመሠረተች የመጀመርያዋ ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን ያቋቋማት ሐዋርያው ሰላማ ከሞተ በኋላ ጥሩ ሁኔታ አላጋጠማትም ከእርሱ በኋላ የተነሱት ሰዎች ጤናማዋን የወንጌል ቤተክርስቲያን ማን ማንን ሊመራ ይችላል በሚል ፉክክር የማን ቤት ጠፍቶ የማን ይበጅ ቀረርቶ ሲሉ ተርተውና በተረታቸውም እርስ በእርሳቸው ሳይቀር ተደባድበው ባለመስማማት ከሣቴ ብርሃን ሰላማን የሾሙት ግብጻውያን ስለሆኑ ግብጻውያን ይምሩን ሲሉ ለግብጻውያን አሳልፈው ሰጧት ግብጻውያንም ለ1600 ዓመታት በጨለማና በባርነት ገዟት ታድያ ሰላማ የመሰረታት ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን ውድቀቷ የጀመረው ያኔ ነው በዚህም ውስጥ ዘመን መምጣቱ አይቀርምና ዘመን ስለመጣልኝ ነጻነቴን አውጄ ከዚህ ባርነት ወጣሁ ብትልም ነገር ግን አሁንም በዚሁ በባርነቱ ምክንያት ለዓመታት የጣለችውን ወንጌል እንደሚገባ ልታነሳው ያልቻለች በመሆንዋ ዘርዓ ያዕቆብ የተባለው ንጉሥ በ15 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ተነስቶ ይህቺን ያላገገመችና ከቁስልዋም ፈጽሞ ያልተፈወሰችን ቤተክርስቲያን ወደማትፈልገው አቅጣቻ በመምራት ይባስ ብሎ ከአዳኝዋ ከኢየሱስ ለይቶ አፋታት በጅማሬዋና በቅድምና ዘመንዋ በተቀበለችው ጌታ አማካኝነት ወደላይ መውጣት የሚገባትን ይህቺኑ ቤተክርስቲያንም ወደታች አውርዶ የቁልቁለቱን መንገድ እንድትመርጥና በዚያው መንገድ ላይ እየተንደረደረች እንድትወድቅ እንድትንከባለልም አደረጋት
የተወደዳችሁ ወገኖች በቪዲዮ የተለቀቀው ትምህርት እንግዲህ ይህንኑ አስመልክቶ የተነገረ ነው በመሆኑም ትምህርቱ ታድያ ቤተክርስቲያንዋ በተመሠረተችበት በቅድምና ዘመንዋ ያመነችው መጽሐፍቅዱሳዊ እውነት ምን እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን ይሄ መጽሐፍቅዱሳዊው እውነት ደግሞ በመጽሐፍቅዱሱ ላይ ሠፍሮ ያለ እውነት ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እስከ ዛሬ ድረስ በምትጠቀምባቸው የቅዳሴ ፣ የሰዓታት ፣ የዚቅ ፣ የድጓ እንዲሁም የሃይማኖተ አበው እና የመሣሠሉት መጻሕፍት ውስጥ በትክክል ተጽፎና ሰፍሮ የሚገኝ ነው ይሁን እንጂ እነዚህን የመሠሉ የቃሉ እውነቶች በበተክርስቲያን መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈውና ሰፍረው ቢገኙም ደፋሩ ዘርዓያዕቆብ ግን ለእነዚህ ተጽፈው ላሉ እውነቶች ቦታ ባለመስጠት ሥልጣኑን ተገን አድርጎ እንደ ተአምረ ማርያም ያሉ የወንጌሉን እውነት የሸፈኑ የጨለማ መጻሕፍትን በመጻፍ ከዚህም ሌላ መጻሕፍትን በማያውቁ ፣ ቅዠት ናላቸውን ባዞረውና በተወናበዱ የዋሻ ፣ የገድል ነዋሪ ባሕታውያን የተጻፉ ገድላትና ድርሳናትን በመሰብሰብ ምን የመሰለችዋን ኦርቶዶክሳዊት የወንጌል ቤተክርስቲያን እስከዛሬ ድረስ የአሮጊቶች ተረት መከማቻና መጠራቀምያ አደረጋት
ቅዱሳን ወገኖቼ ትምህርቱ በስፋት የሚጠቁመን አሁንም ይህንኑ እውነት ነው ታድያ ተጨባጭ የሆነውን ይህን እውነት ለሕዝባችን ለመስጠት እያንዳንዱን ሃሳብ በጥልቀት በተናጠልና በዝርዝር የምናይበት ትምህርት ስለሆነ ሰፊ ትንታኔ ለመስጠት በዚህ አርዕስት ዙርያ ለተወሰኑ ጊዜያቶች እንቆያለንና በማስተዋል እንድትከታተሉ ጥሪዬን ለእናንተ ለወገኖች በፍቅር ማስተላለፍ እወዳለሁ ግንዛቤያችሁ ይበልጥ እንዲጨምር ግን ይህንኑ የተለቀቀውን ቪዲዮ ደግማችሁ ስሙት ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ
ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
በከሣቴ ብርሃን አባ ሰላማ የተቋቋመችው የመጀመርያዋ ኦርቶዶክሳዊት ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኅብረት ያለፈችባቸው መንገዶች ክፍል ሁለት
በከሣቴ ብርሃን አባ ሰላማ የተቋቋመችው የመጀመርያዋ ኦርቶዶክሳዊት ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኅብረት ያለፈችባቸው መንገዶች ክፍል ሁለት
DECEMBER 4, 2019
ጸአተ ግብጽ ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ተሃድሶ
LEAVE A COMMENT
EDIT
በከሣቴ ብርሃን አባ ሰላማ የተቋቋመችው የመጀመርያዋ ኦርቶዶክሳዊት ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኅብረት ያለፈችባቸው መንገዶች
ክፍል ሁለት
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን ትምህርቱ በእግዚአብሔር ጸጋና እርዳታ በእናንተም በቅዱሳኑ ጸሎትና እገዛ ቀጥሎ ዛሬ የክፍል ሁለትን ትምህርት ይዤ ቀርቤያለሁ ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ በክርስቶስ ላይ የተመሠረተች በምትሆንበት ጊዜ ለሁል ጊዜም ትፈተናለች ይሁን እንጂ የተመሠረተችበት ዓለቱ ጽኑ ስለሆነ አትወድቅም እንደገናም የገሃነም ደጆች አይችሏትም በሰላማ ከሣቴ ብርሃንም ጊዜ የተመሠረተችው ቤተክርስቲያን በሐዋርያዊው አባ ሰላማ የተቋቋመች ቤተክርስቲያን ብትሆንም የተመሠረተችው በክርስቶስ ላይ እንጂ በሐዋርያዊው አባ ሰላማ ላይ ባለመሆኑ ባለፈችባቸው መንገዶች ሁሉ መሠረትዋ የሆነው ጌታ በሌላ አነጋገር በራሱ ላይ የመሠረታት ኢየሱስ ባለ ድል አድርጎአታል ( የማቴዎስ ወንጌል 16 ፥ 15 _ 19 ) ትምህርቱን በሰፊው በተለቀቀው ቪድዮ በኩል ስለምትከታተሉት ታሪኩን መድገም አያስፈልገኝም ነገር ግን የታሪኩን ዳራና ጠቅለል ያለውን መልዕክት በአጭሩ ለማስታወስ ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ክርስቲያኖች በነበሩት ነገሥታት ብርታትና በሕዝብዋም ጠንካራ ከሆነው መጽሐፍቅዱሳዊ እውቀት የተነሣ ከቄሣር ቁንስጣ የተላከውን መልዕክት ያልተቀበለችና በፍሬምናጦስ አባ ሰላም ምትክ መንፈሳዊ መሪዋ ሊሆን ተልኮ የመጣውን አርዮሳዊ እና ሕንዳዊ ቴዎፍሎስን አሳፍራ የመለሰች ነበረች ይህንንም ያደረገችው ከቃሉ የመረዳት ጉልበት ጭምር ብቻ ሳይሆን ከሮማ ቄሣሮች ተጽዕኖ ሳይቀር ነጻ በሆነ ጥላ ሥር ስለነበረች ጭምር ነው
ታድያ ይህንን የአርዮስ ትምህርት ተቀብላ ቢሆን ኖሮ እንደገና ዘመን መጥቶ በእስክንድርያው መሪ በቴዎዶስዮስ ዘመነ መንግሥት ፈጽሞ የተወገዘውን ኑፋቄ አርዮስን ከአዕምሮዋ አስወጥቶ በምትኩ ታድሶ የጸናውን የኒቅያን የእምነት መግለጫ ( ጸሎተ ሃይማኖትን ) ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት እንድትቀበል የማድረግ ዕድሉ የመነመነ በሆነ ነበር
ስለዚህ በደገኛው ሐዋርያዋና መሪዋ ፍሬምናጦስ በተሰኘው አባ ሰላማ ብርታትና አርቆ አስተዋይነት ቀደም ብላ የኒቅያን የእምነት መግለጫ እንደ እግዚአብሔር ቃል በሆነ መረዳት ድቅቅ አድርጋ በመማርዋና በመገንዘብዋ በኋላ ላይ በለሰለሰ መንገድ በአታላይነት ሊገባ የሞከረውን አርዮሳዊ ኑፋቄና መልዕክተኛውን ቴዎፍሎስን በመጡበት አኳኋን መመለስ እንድትችል አድርጓታል ይህ ብቻ አይደለም ለወደፊቱም ትምህርተ መለኮትዋን በመልካም ጐዳና ለመምራት ያስቻላትን ዕድልና ጸጋ በቸርነቱ እንደሰጣት ያረጋግጥልናል
እኔም ታድያ ከዚህ ትምህርት የተነሳ ሳላመሰግናቸው የማላልፋቸው አንድ እውነተኛ አባቴና መንፈሳዊ መሪዬ የነበሩ ስላሉ በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት አባ ሃብተ ማርያም ሊቀ ጵጵስናን ከተቀበሉ በኋላ ደግሞ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የተባሉትን አባት ሳላመሰግን አላልፍም እኚህ አባት እኔ በነበርኩበት ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የትምህርት ቤታችን ዲን ነበሩ በጣም ተራማጅና መጽሐፍቅዱሳዊ አስተሳሰብ የነበራቸው በመሆኑ ያደረጉብን ብዙ የብዙ ብዙ በጎ ተጽእኖዎች ነበሩ እያንዳንዱን አሁን ዘርዝሬ አልጨርሰውም ነገር ግን ዋናውና ትልቁ በጎ ተጽዕኖ የእምነት መግለጫችሁንና ማብራርያውን ከነ ጥሬ ንባቡ እንዲሁም የቃሉ ትርጉም ጋር በቃላችሁ አጥኑ ይሉን ነበር ፈተናውም የሚመጣው ከዚሁ የእምነት መግለጫ ነበረና ይህንን ፈተና ያላለፈ ከበድ ያለ እርምጃ ይወሰድበት ስለነበር እኛም ታድያ እርሳቸውንም ሆነ የሚወስዱብንን እርምጃ ስለምንፈራ አልጋችንን ለቀን የምንማርበት የክፍል ወለል ላይ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ቁጭ ብለን እናጠና ነበር በጊዜው የነበረው የአባታችን ጭካኔ ያማረረንና የክፍል ወለል ላይ ያሳደረን ቢሆንም አሁን አሁን ላይ ሳስበው ለአባታችን ዕድሜ ዘመን ይጨመርልዎ እርስዎ የሚያውቁት ምስጢር ስላለ ነው እንዲህ ጠንክረን የእምነት መግለጫችንን እንድናጠናና እንድናውቅ ያደረጉን በማለት ልባርካቸው ወደድኩ አባታችን ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ እውነተኛ አባታችንና የወንጌል መምህራችን ኖት ትላንት ለማጥናት በከፈልነው ዋጋ ብንከፋም ዛሬ ላይ ጠንክረው በወሰዱት እርምጃ ያስጠኑን የእምነት መግለጫ የትም ሳንሄድ በእምነታችን መሠረት ላይ እንድንተከልና ሌላውንም እንድንተክል ያስቻለን በመሆኑ ዕድሜና ዘመንን ይጨምርልዎ ብድራትዎትንም በላይ በሰማይ እግዚአብሔር ይክፈልዎት ተባረኩልኝ በማለት ላመሰግንዎት እወዳለሁ
የተወደዳችሁ ወገኖች ለዚህ ነው እንግዲህ እንዴት እንደተቀበልክና እንደ ሰማህ አስብ ጠብቀውም ንስሐም ግባ በማለት በትምህርቴ ማጠቃለያ ላይ የገለጽኩት ( ራዕይ 3 ፥ 3 ) እንዴት እንደተቀበለና እንደ ሰማ ያወቀ ሰው የተቀበለውንም እንዴት እንደሚጠብቅ ያውቃልና በቀላሉ ለስሕተት ትምህርት የተጋለጠ አይሆንም ከዚህም ሌላ ለሚጠይቁት ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጀ ነው 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3 : 15 ታድያ ለዛሬዋም ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ያለኝ መልዕክት የተቀበለችውና እየተቀበለች ያለው መልዕክት ከማን መሆኑን እንድትረዳ እንዴት እንደተቀበለች ማወቅ ይኖርባታል የሚል ነው ጌታ ያልሰጣትን ይዛ ወይም ተቀብላ ከሆነ ደግሞ ብትጠለው ፈውሷ ይበዛል እንጂ አትጎዳም የሚል መልዕክት አስተላልፋለሁ ከዚህ በመለስ ደግሞ ቪዲዮውን ደግማችሁ ስሙት ትባረኩበታላችሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
በመልካም ሁኔታ ተመሥርታ መልካም ጐን የነበራት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በግብጻውያን ጳጳሳት መሪዎች ምክንያት ውድቀቷ የጀመረበት ጊዜ ክፍል ሦስት
በመልካም ሁኔታ ተመሥርታ መልካም ጐን የነበራት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በግብጻውያን ጳጳሳት መሪዎች ምክንያት ውድቀቷ የጀመረበት ጊዜ ክፍል ሦስት
በመልካም ሁኔታ ተመሥርታ መልካም ጐን የነበራት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በግብጻውያን ጳጳሳት መሪዎች ምክንያት ውድቀቷ የጀመረበት ጊዜ
ክፍል ሦስት
ሰላም ሰላም የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንዴት ናችሁ ተባረኩ የዛሬው ትምህርት እንዲያመልጣችሁ አያስፈልግምና የተለቀቀውን ቪዲዮ ከፍታችሁ ደጋግማችሁ ስሙ ይህ ትምህርት ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን በዋናነት የሚመለከት ቢሆንም ከዚያ መልስ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ተጠርተው ላሉ አማኞች የምሥራቹን ቃል ለሚሰብኩ ለሚያስተምሩና ለሚመሩ አብያተክርስቲያናት መሪዎች እንዲሁም አገልጋዮቻቸው ጭምር ጥሩ ማስገንዘቢያና ማስተዋልን የሚሰጥ ወቅታዊ ፣ አስፈላጊም የሆነ ትምህርት ነው
በደገኛው መሪ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ተቋቁማ ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት የሚል ስያሜ ይዛ በነገሥታቱ ፈቃድ ብሔራዊነትን አግኝታ አገር አቀፍ እንቅስቃሴ የጀመረችው ቤተክርስቲያን መልካም በሆኑ ተግባሮችዋ እና በጥሩ ጐንዋ ያስደመመችን ቢሆንም ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ሥራውን በክብር አጠናቆ ካረፈ በኋላ ከእርሱ በመቀጠል የተነሱት ሰዎች ማንም ከማንም አይበልጥም አያንስምም ማን ማንን ሊመራ ይችላል ? የማን ቤት ጠፍቶ የማን ይበጅ ቀረርቶ በሚል ተረታዊ ባሕልና እኔነት ፣ የእበልጥ ባይነትና የውድድር አተካሮ ውስጥ ገብተው ግብጾች ይምሩን ፍሬምናጦስን የሾሙ እነርሱ ናቸውና በሚል ደካማ ሃሳብ የዝሆን ጥርስ ፣ ወርቅ ፣ አልማዝ ፣ ብርና የመሣሠሉትን ይዘው በመሄድ ቤተክርስቲያኒቱን አሳልፈው ለግብጻውያን ሰጡ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ የቤተክርስቲያኒቱ ውድቀት የጀመረው ግብጻውያኑ መልካም አባቶችና እውነተኛም መንፈሳዊ መሪዎች ሆነው የክርስቶስ ኢየሱስን ወንጌል በመስበክ ቤተክርስቲያኒቱን ለተሻለ ክብር ቢያበቁ እንዴት መልካም በሆነ ነበር ነገር ግን ያ ሳይሆን ቀርቶ መንፈሳዊነቱ በሥጋዊ ጥቅም ተቀየረ ግብጻውያኑም ከተረከቡት ሃላፊነትና ሥልጣን ይልቅ በኢትዮጵያውያኑ በኩል በየጊዜው የሚገበርላቸው ወርቅና ብር እንዲሁም የዝሆን ጥርስ በልጦባቸው ለአንድ ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት ያክል ቤተክርስቲያኒቱን ለከፋ ውድቀት ዳረጓት ይህ ብቻ አይደለም በፍትሐ ነገሥት መጽሐፍ ላይ ኢይሲሙ ጳጳሳተ እማዕምራኒሆሙ በማለት በስርዋጽ አስገብተው ትርጉሙም ከሊቃውንቶቻቸው መካከል ጳጳሳትን አይሹሙ ማለት ነውና ከላይ ከሐዋርያት በመለኮታዊ ኃይል የወረደ ድንጋጌ በማስመሰል አኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ሹመቱን ቢጠይቁም ለዚህ ነገር የማይበቁና መጠየቃቸው እንኩዋ ሳይቀር ትልቅ ኃጢአትን የሚያወርድና መቅሰፍትንም ጭምር የሚያመጣብን መሆኑን በመንገር የኢትዮጵያው ንጉሣችን የግብጽን ቤተክህነት ይቅርታ እንዲጠይቅ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንቱም ጥፋተኞች ነን ሲሉ እንዲሸማቀቁ ዝቅ ብለውም እንዲያደገድጉም ሆነ እንዲያጎበድዱ አድርገዋቸዋል ይህንና የመሣሠሉትን ሁሉ ማድረጋቸው ኢትዮጵያውያን የነቁብን እንደሆነ ዓባይን ይገድቡብናል ቤተክርስቲያኒቱንም ከእኛ እጅ አውጥተው የራሳቸው በማድረግ የለመድነውን ወርቅ ብር አልማዝና የመሣሠሉትን ሁሉ ያስቀሩብናል በማለት አስበው ነው ቤተክርስቲያናችንንም እንደራሳቸው አጥቢያ አድርገው ይመለከቷት ነበርና እነዚህን ነገሮች ሁሉ ቢያስቡና ቢያደርጉ አይደንቅም ነገር ግን በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እገዛና በመምህራኖቻችን እልህ አስጨራሽ ትግል ቤተክርስቲያናችን ከግብጻውያን እጅ ወጥታ የራስዋን ሥልጣን የራስዋ ማድረግ ቻለች በገዛ ልጆችዋም መመራት ጀመረች ይሁን እንጂ በእነዚህ አስከፊ የጨለማና የባርነት ዓመታት ውስጥ እነዚህ ደበሎ ለባሽ የኮፕቲክ መነኮሳት ድሪንቶአቸውንና አቧራቸውን ያራገፉብን በመሆናቸው ቤተክርስቲያናችን እስከ ዛሬ ድረስ ከወንጌሉ እውነት ወጥታ ወደ ተመሠረተችበት የእግዚአብሔር ቃል መሠረትና የእምነት መግለጫዋ እንዳትመለስ ዓይነተኛ የጥፋት ምክንያት ሆኑ ከዚህ የተነሣ እስካሁንዋ ሰዓት እስከ እኛ ዘመን ድረስ እነዚሁ ግብጻውያን የታሪክ ተወቃሽ ሆነው ይኖራሉ በፍጻሜውም ዘመናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ከተጠያቂነት አያመልጡም
የተወደዳችሁ ወገኖች መሪነት ምሳሌነት ነው ለዚህም ነው በ2ኛ ጢሞቴዎስ 3: 10 ላይ አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ ያለው ስለዚህ አንድ ሰው በሃላፊነት ተመድቦ ከመሥራቱና ይህንንም ሃላፊነት ከመውሰዱ በፊት ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ማየት አለበት መሪ የምንሆነው እንደ ኮፕቲክ መነኮሳት ባለ አፍቅሮ ንዋይ ውስጥ ተዘፍቀንና ተጠምደን ፣ ሥልጣናችንን በመጠቀም ወርቅና ብር ለማጋበስ ከሆነ ወርቅና ብሩ አልቆ ወይንም ቀርቶብን በምትኩ ሌላ ነገር ሲመጣ መቆም ያቅተንና ጥለን እንፈረጥጣለን ግብጻውያኑ ደበሎ ለባሽ መነኮሳት ያደረጉት ይህንኑ ነበር የጣሊያን ወረራ ሲመጣ ወንበራቸውን እስከ ጊዜውም ድረስ ቢሆን ሊጠብቅላቸውና ሊያስጠብቅላቸው የሚችለውን ጊዜያዊና ተጠባባቂ ሰው መድበው ጥለውን ፈረጠጡ ዛሬም ታድያ በኦርቶዶክሳዊቷ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በወንጌላውያኑም አብያተክርስቲያናት ጭምር ይሄ ስሕተት እንዳይደገም ሥጋቴ ነው ለምን ብትሉኝ ዛሬ ላይ ከእኔ ወዲያ ሲል አላስይዝ ብሎ መድረኩን የሞላው ፓስተር ሁሉ በነገው የመከራ ዘመን አሳማኝ በሚላቸው ልዩ ልዩ ምክንያታዊ ጥቅሶቹ የየራሱን የምቾት ቀጠና በማዘጋጀትና በማደላደል መንጋውንም በትኖ ለአውሬ በመስጠት እግሬ አውጪኝ ሲል ሲኮበልልም እንዳይገኝ ይልቁንም እንደ ሐዋርያው እንደ ጳውሎስ በመከራም ጭምር ጸንቶ በመቆም ምሳሌ የሆነውን የተፈተነ ሕይወቱን ለሕዝቡ እንዲያሳይ ጽኑ የሆነውን ምክሬን ለማስተላለፍ እወዳለሁ 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2 : 15 እንደገናም ግብጻውያን መነኮሳት ከጣልያን ወራራ መልስ ተመልሰው መጥተው ወንበራቸውን በመያዝ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የባጣ ቆዪኝ ቤት ሊያደርጓት እንደ ሞከሩት ሁሉ ዛሬም ኦርቶዶክሳዊት ብቻ ሳትሆን ማንኛዋም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የባጣ ቆዪኝ ቤት አይደለችምና ቤተክርስቲያንን የባጣ ቆዪኝ ቤት ሊያደርጉ እንዲህ ዓይነቱን አስነዋሪ ተግባር ለሚፈጽሙ አሁንም ቤተክርስቲያን የራስዋ የሆነን ፈጣን የዲሲፒሊን እርምጃ ልትወስድ ይገባታል እንጂ ጉዳዩን እንዲሁ በቸልታ ልታየውና ልታልፈው አያስፈልግም የሚል መልዕክት አለኝ ቤተክርስቲያንን ደግሞ እኛ አገልጋዮችዋና መሪዎቿ ብንተዋት የሞተላት ኢየሱስ ግን ፈጽሞ አይተዋትም የራሱ የሆኑ ታማኝ ሎሌዎቹን በማስነሳት እስከ ፍጻሜው ድረስ ይጠብቃታል በመጨረሻም ቤተክርስቲያን ለሌላ ላትሆን አንዴ ለእርሱና ለራሱ ስለሆነች ከራሱ ጋር ለዘላለም ሊያኖራት እርሱ ራሱ መጥቶ ይወስዳታል ወገኖች ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን ተከታተሉ በተረፈ በክፍል አራት ትምህርታችን እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑ የምላችሁ
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
Advertisements
Occasionally, some of your visitors may see an advertisement here,
as well as a Privacy & Cookies banner at the bottom of the page.
You can hide ads completely by upgrading to one of our paid plans.
UPGRADE NOW DISMISS MESSAGE
በፍሬምናጦስ የተመሠረተች ማህበረጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን
በፍሬምናጦስ የተመሠረተች ማህበረጽዮን ሰማያዊት ቤተክርስቲያን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አመሠራረት ( ክፍል አንድ )
የተወደዳችሁ ወገኖቻችን እንዴት ናችሁ ተባረኩ ይህንን ትምህርት ዛሬ ለእናንተ አንድ ብለን ጀምረነዋል የምንወዳት አንጋፋዋ ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያናችን በ325 ዓመተ ምሕረት የመጀመርያው ሐዋርያችን በሆነው ፍሬምናጦስ ተብሎ በቀዳሚነት በተጠራውና አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በተባለው ሰው ነው የተቋቋመችው ይህ ሰው ክርስትናን ከእስክንድርያ ይዞልን ሲመጣ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት ያደረገ ክርስትናና የእምነት መግለጫንም ጭምር ይዞልን የመጣና በዚሁ መሠረትም ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት የምትለዋን ማኅበር ወይንም ቤተክርስቲያን ያቋቋመ ነው ታድያ ቤተክርስቲያንም ሆነ የቤተክርስቲያንን የእምነት አቋም የሚገልጸው የእምነት መግለጫ መሠረቱ የእግዚአብሔር ቃል ሲሆን ቤተክርስቲያን የገሃነም ደጆች የማይችሏት ጠንካራ ትሆናለችና ሥራው ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሰው በጣም አስደሳች ነው የሚሆነው የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የእምነት ሐዋርያችን አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ያደረገው እንግዲህ ይህንን ነው እንደ ዛሬው ዘመን አገልጋዮች ደርሶ ቤተክርስቲያንን የተከለና ስምም ያወጣ አይደለም ቅድሚያውን ይዞ ከዓለም አቀፍዋ ቤተክርስቲያን መሪ ከ20ኛው ፓትርያርክ ከሐዋርያው አትናቴዎስ የኤጲስቆጶስነትንና የሐዋርያነትን ሥልጣን ብቻ ሳይሆን ይኸው አትናቴዎስ 27 የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሲል በቃለ ቡራኬ የደነገገበትን ውሳኔ በመቀበል 27ቱን የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትና 39ኙን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በአንድ ላይ አስተባብሮ ይዞ በመምጣት በዚህ በእግዚአብሔር መንፈስ በተጻፉ 66 ቱ ቅዱሳት መጻሕፍት አማካኝነት ወንጌልን ነገሥታት ጓዳ ድረስ በመግባትና በመስበክ ማኅበሩን ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት በማለት የመሠረተ ብቻ ሳይሆን እምነቱንም በመንግሥት ደረጃ ሳይቀር ታውጆና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆና በመንግሥት ሰነድም ጸድቆ የደርግ መንግሥት እስከ ተሻረበት ዘመን ድረስ ምድሪቱ የክርስቶስ እንድትሆን ያደረገ ታላቅ የቤተክርስቲያን ባለ ውለታና ለእኛም ምሳሌ የሆነን የእምነት ሐዋርያ ነው
ይህ ሰው ሰው ይህንን ሁሉ ወደ ማድረግ የመጣው ትክክለኛውን 66 ቱን ቅዱስ መጽሐፍ ማለት መጽሐፍቅዱስን አምኖና ተቀብሎ የአገልግሎቱም መሠረት አድርጎ ስለተነሳ ነው ለዚህም ነው በዚህ በተሃድሶ አገልግሎት ከ50 ዓመት በላይ በአገልግሎት የገፉና ዛሬ በመካከላችን በሕይወት የሌሉ መጻሕፍቶቻቸውና ሥራዎቻቸው ግን ዛሬም ድረስ ሕያው ሆኖ ማንነታቸውን እየገለጸ ያለ ታላቁ ሊቅ አለቃ መሠረት ስብሐት ለአብ በስምዓ ጽድቅ ብሔራዊ መጽሐፋቸው ላይ ከዓለም አቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን ሐዋርያና ከእስክንድርያው ፓትርያርክ አትናቴዎስ በሐዋርያችን አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን አማካኝነት ሲያያዝ መጥቶ እኛ ጋር የደረሰው ይሄ እምነት መሠረቱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ጠንቅቀው ያወቁና የተረዱ በመሆናቸው እንደገናም ቤተክርስቲያኒቱን ዛሬም ላይ ቢሆን ወደ መሠረቷ ሊመልሳት የሚችለው ይኸው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ስለተገነዘቡ ፦ በሃይማኖተ አበው ያለ የዮሐንስ አፈወርቅን ሃሳብ በማንሳት ይደልወነ ናጽምዕ ቃላተ መለኮት ከመ ኢይባዕ ውስተ አልባቢነ ቃል ነኪር አሉን ትርጉም ባዕድ ቃል ወደ ልባችን እንዳይገባ ቃላተ መለኮትን ማድመጥ ይገባናል ሲሉ ሃይማኖተ አበው ላይ በሠፈረው የአባቶች መጽሐፍ ከመከሩን በኋላ ባዕድ ቃል ያሉበትን ሃሳብ ሊያብራሩልን ስለፈለጉ ደግሞ እንዲህ አሉን ያለንን በመገንዘብ በእግዚአብሔር ቃል ብቻ ተወስነን ከቊርዓንና እነርሱንም ከሚመሳስሉ ልዩ ልዩ የልብ ወለድ መጻሕፍት እምነት እንርቃለን በማለት ተናገሩ ( ምንጭ ስምዓ ጽድቅ ብሔራዊ ገጽ 48 ) መልዕክቴን ስጠቀልለው በእምነታችን ተመሥርተንና ጸንተንና እስከ መጨረሻውም በፊቱ ለመቆም አሁንም አለቃ መሠረት በመጽሐፋቸው ላይ አሁን ድረስ እንደነገሩን ቃላተ መለኮትን በማድመጥ መኖር ይሁንልን
ታቦቱም በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠበት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፥ ሀያ ዓመትም ሆነ፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግዚአብሔርን ተከተለ
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 7 : 1
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፦ በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ …..ሳሙኤልም የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ንጉሥን ለፈለጉ ሕዝብ ነገራቸው ( ሳሙኤል ቀዳማዊ 8 : 7 ,10 )
ሕዝቡ ግን የሳሙኤልን ነገር ይሰማ ዘንድ እንቢ አለ። እንዲህ አይሁን፥ ነገር ግን ንጉሥ ይሁንልን እኛም ደግሞ እንደ አሕዛብ ሁሉ እንሆናለን፤ ንጉሣችንም ይፈርድልናል፥ በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ይዋጋል አሉት ሳሙኤልም የሕዝቡን ቃል ሁሉ ሰማ፥ ለእግዚአብሔርም ተናገረ
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፦ ቃላቸውን ስማ፥ ንጉሥም አንግሥላቸው አለው
( መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 8 : 10 , 19 – 22 )
ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፦ ንጉሥ በመለመናችን በኃጢአታችን ሁሉ ላይ ይህን ክፋት ጨምረናልና እንዳንሞት ስለ ባሪያዎችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 12 : 19
ሳሙኤልም ሕዝቡን አለ፦ አትፍሩ በእውነት ይህን ክፋት ሁሉ አደረጋችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ እግዚአብሔርን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ
ምናምንቴ ነውና የማይረባንና የማያድን ከንቱን ነገር ለመከተል ፈቀቅ አትበሉ መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 12 : 23
ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች አለ የሐዋርያት ሥራ 3 : 23
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
Advertisements
Sunday, June 2, 2024
Saturday, May 18, 2024
Sunday, April 28, 2024
Thursday, March 21, 2024
Tuesday, March 19, 2024
Sunday, March 17, 2024
Tuesday, March 12, 2024
Sunday, March 10, 2024
Saturday, March 9, 2024
Friday, March 8, 2024
Wednesday, March 6, 2024
Monday, March 4, 2024
Sunday, March 3, 2024
Thursday, February 29, 2024
Wednesday, February 28, 2024
Wednesday, February 21, 2024
Monday, February 19, 2024
Sunday, February 18, 2024
Friday, February 16, 2024
Tuesday, February 13, 2024
Friday, February 9, 2024
Thursday, February 8, 2024
#መጽሐፍ_ቅዱስ_81_ወይስ_66 ?
መጽሐፍ ቅዱስ ማን ጻፈው?
- - - - - - -
መጽሐፍ ቅዱስ ባለቤቱ እግዚአብሔር ሲሆን ጸሐፊዎቹ ግን ከእርሱ የተላኩ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ ጸሐፊዎቹ ብዛታቸውም ከአርባ በላይ ሲሆን አንዳቸውም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ አልጻፉም፡፡ “በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” 2ጴጥ 1፡20
- - - - - - -
-+- መጽሐፍ ቅዱስ አሁን በእጃችን ላይ እንዳለው በአንድ የተጠረዘ መጽሐፍ ነበር?
- መጽሀፍ ቅዱስ በአንድ ወቅት በአንድ ጊዜ ተጠርዞ የተሰጠ ወይም ከሰማይ የወረደ ሳይሆን የተለያዩ ክፍሎች በተለያዩ ጸሐፍት እና ዘመናት የተጻፉ ናቸው፡፡ በጥንት ዘመን መጸሀፍት በጥቅል ተጠቅልልው ይቀመጡ እንደነበር ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡- ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ ያነበበው የነቢዩ ኢሳያስን ጥቅልል መጽሐፍ ነበረ፡- “የነቢዩን የኢሳያስን መጽሀፍ ሰጡት መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው …….. ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ፡፡ መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፡፡” ሉቃ 4፡17-20 ከዚህ ክፍል እንደምንረዳው ቅዱሳት መጻህፍት ለየብቻቸው በአንድነት ሳይጠረዙ እንደነበሩ ነው፡፡
- - - - - - -
-+- ቅዱሳት መጻህፍት አሰባሰብ?
-ቅዱሳት ሐዋርያት ስለ ስርዓተ ቤተክርስትያን የተለያዩ ቀኖናትን ደንግገዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ስለ ቅዱሳት መጻህፍት ነው፡፡ በ325 እ.ኤ.አ በኒቂያ በተካሄደው ጉባኤ ላይ እውነተኖቹን ቅዱሳት መጻህፍት ለመሰብሰብ በተወሰነው መሰረት ቅዱስ አትናቲዎስ በ367 ዓ.ም በ39ኛው የትንሳኤ ምልዕክቱ ላይ የቅዱሳትን መጽሐፍትን እና አይነት በአብዛኛው አስታውቋል፡፡ ከዚያም በሎዶቅያ በተካሄደ ጉባኤ እና በ393፣399 እና 419 እ.ኤ.አ በሰሜን አፍሪካ ትገኝ በነበረችው ቅርጣግና /ካርቲጅ/ በተካሄዱት ጉባኤዎች ቅዱሳት መጽሐፍትን ለይቶ ለማወቅ ጥረት ተደርጓል፡፡ የካርቴጁ ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን በአንድ ላይ መጠረዝ እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት መድብል/ጥራዝ/ ተብሎ መጠራት ተጀመረ::
- - - - - - -
-+- ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳት መጻሕፍት ብዛት ሰማንያ አንድ መሆኑን ትናገራለች፡፡ ዳሩ ግን በዓለም ላይ በብዛት ተሰራጭቶ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ስልሣ ስድስት ነው፡፡
- በስልሣ ስድስቱ ውስጥ የሌሉት መጻሕፍት:-
ሀ. ከ ብ ሉ ይ (2ኛ የቀኖና መጻሕፍት):-
1.መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል
2.መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ
3.መጽሐፈ ጦቢት
4.መጽሐፈ ዮዲት
5.መጽሐፈ አስቴር
6.መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ
7.መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ
8.መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ
9. መጽሐፈ ሲራክ
10.ጸሎተ ምናሴ
11. ተረፈ ኤርሚያስ
12. ሶስና.
13. መጽሐፈ ባሮክ
14. መጽሐፈ ጥበብ
15. መዝሙረ ሰልስቱ ደቂቅ
16. ተረፈ ዳንኤል
17. መጽሐፈ ኩፋሌ
18. መጽሐፈ ሄኖክ
- - - - - - -
ለ. ከሐዲስ ኪዳን:-
1. ትዕዛዘ ሲኖዶስ
2. ግስው ሲኖዶስ
3. አብጥሎ ሲኖዶስ
4. ሥርዓተ ጽዮን ሲኖዶስ
5. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ
6. መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ
7. ቀለሚንጦስ
8. ዲዲስቅሊያ (እነዚህ የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት አሁን በእጃችን በሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ ይህም የሆነው እያንዳንዳቸው በጣም ትልቅ መጻሕፍት በመሆናቸው ለማካተት አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ ግን ከ81 መጻሀፍት መድበን ነው የምንቆጥራቸው፡፡ ሁሉም መጻህፍት በቤተክርስትያኖች ቤተ-መጻሀፍት ውስጥ ይገኛሉ እንዲሁም ገዝቶ ማንበብ ይቻላል፡፡
- - - - - - -
-+- እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መጽሕፍት ሳታጓድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትቀበላለች፡፡ ዘመናዊ ነን የሚሉ እምነቶች ግን ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌላ የለም ሲሉ ይሰማሉ፣ ለዚህም የሚጠቀሱት ዩሐንስ ራዕይ መጨረሻው ላይ ያለውን ቃል ነው።
‹‹ማን በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል››፡፡ ራእይ 22‹18
- ይህን አባባል በጥሞና ስናጤነው የዩሐንስ ራዕይን ብቻ የሚመለከት ሆኖ አናገኘዋለን፡፡ “በዚህ በትንቢት መጽሐፍ” አለ እንጂ ከዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አላለም፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “የትንቢት መጽሐፍ” ብቻ ሳይሆን የ”ወንጌል” ፣የመዝሙር፣ የመልዕክታት እና የመሳሰሉት መጽሐፍ ነው፡፡
- በተጨማሪ የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ጠፍቶ ስለነበር እንደገና ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር ገልጾለት ስለጻፈው " በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር" ብሎ የጻፈው ወጌላዊው ዮሐንስ ሳይሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው።
- ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ ከመነሻው እንደዚሁ አንድ ላይ እንደተጠረዘ ሆኖ የተገኘ አይደለም፡፡ ጻሕፍቱ በተለያየ ዘመን የነበሩ እንደሆነ ሁሉ ፣መጻሕፍቱም በተለያዩ ዘመናት የተጻፉና በአንድ ወቅት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጸሐፍ ተጽፈው አልቀው በጥራዝ መልክ እንደወጡ አድርጎ በመውሰድ የዩሐንስ ራዕይን ማጠቃለያ ለሁሉም መጻሕፍት አድርጎ መውሰድ አለማወቅ ወይንም ተንኮል ነው፡፡
- - - - - - -
-+- መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ፡-
- ብሉይ ኪዳን በሐገራችን ቋንቋ በግዕዝ የተተረጎመው ከክርስቶስ ልደት በፊት አንድ ሺህ ዓመት ቀደም ብሎ ሲሆን ይኸውም በንግሥተ ሳባ ዘመነ መንግሥት ጊዜ ነው፡፡
- ኢትዮጵያ ከዚህን ጊዜ ጀምሮ መጻሕፍትን ጠብቃ አቆይታለች፡፡ አባቶች ምንም አይነት ጦርነት ቢነሳ ህይወታቸውን በማስቀደም መጻሕፍትን ጠብቀው አቆይተውልናል፡፡
- ከምዕራባውያን በፊት ክርስትናን ሆነ የአይሁድ እምነትን የተቀበለችው ሀገራችን በምዕራባውያን የሌሉ መጻሐፍት መገኛ ብቸኛ ሀገር ናት፡፡ ለዚህም ነው በአይሁድ ዘንድ ሆነ በሮማውያን ዘንድ በነበረው ጦርነት የጠፉ መጻህፍት ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የሚገኙት፡፡ ለዚህም መጽሐፈ ሄኖክ እና መጽሐፈ ኩፋሌ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የመጽሐፈ ሄኖክ ጥቅልል አሁን በቅርቡ በቁምራን ዋሻ ተገኝቷል፡፡ የተገኘው ጥቅልልም ሀገራችን ጠብቃ ካቆየችው መጽሐፈ ሄኖክ ጋር አንድ አይነት ሆኖ በመገኘቱ ምዕራባውያን ተርጉመው መጠቀም ጀምረዋል፡፡
- - - - - - -
-+- የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት:-
- የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁለት አይነት የቀኖና ክፍሎችን ያካትታል እነሱም ፕሮቶካኒካል እና ዲዩትሮካኖኒካል ይባላሉ፡፡
- (የመጀመሪያ)፡- እነዚህ መጻሕፍት የተሰበሰቡት በካህኑ እዝራ ሲሆን መጀመሪያ በቀኖና መጻሕፍትነት የተመዘገቡ ናቸው፡፡ 1ኛ. መቃብያን 2፡10 “ነህምያም የነገስትን መጻሕፍት የያዘ ቤተ መጻሕፍት አቋቁሞ ነበር“ እነዚህም መጻሕፍት በ ሶስት ይከፈላሉ እነሱም ቶራህ (አምስቱ ብሔረ ኦሪት) ፣ ነበኢም (ቀደምት ነብያት እና ደኃርት ነብያት) እና ከተቢም (ታላላቅ የታሪክ መጽሐፍትና ታናናሽ የታሪክ መጽሐፍትን ያካትታል) ተብለው ይጠራሉ፡፡ እንዲሁም
- ዲዩትሮካኖኒካል የምንላቸው አይሁድ እንደ ቀኖና መጻሕፍት የማይቀበሉዋቸው ግን እንደ አዋልድ መጻህፍት የሚቀበሉዋቸው ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ
-> አይሁዶች 24 የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን ብቻ ሲቀበሉ (የመጽሐፋቸው አቆጣጠር ከእኛ አቆጣጠር ይለያል)
-> ፕሮቴስታንቶች 39 የብሉይ ኪዳን እንዲሁም 27 የሐዲስ ኪዳን ይቀበላሉ፡፡
-> ካቶሊኮች 46 የብሉይ ኪዳን መጻህፍት እና 27 የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት ሲቀበሉ እኛ
-> ኦርቶዶክስ ተዋህዶዎች ግን 46 የብሉይ ኪዳን እና 35 የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንቀበላለን፡፡ (ከካቶሊኮች ጋር በብሉይ ኪዳን የምንቀበላቸው መጻሕፍት ላይ የአቆጣጠር እና የመጻሕፍት ልዩነት አለ፡፡)
- እዚህ ላይ ከላይ በግልጽ እንደምንረዳው 81 የነበረው የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ ብዛት ቀስ በቀስ በሰዎች እየተቀነሰ እንዲሁም በነበሩት ጦርነቶች መጻሐፍቱ እየጠፉ በመምጣታቸው፣ መጀመሪያ 73 እንዲሆን በመቀጠልም ማርቲን ሉተር ሲያምንበት ከነበረው የካቶሊክ እምነት ፣ከካቶሊክ መነኮሳት ጋር በነበረው የግል ጸብ እና የፖለቲካ ጸብ (የጀርመን ዜጋ ስለነበር የአይሁዶች ጥላቻ ስለነበረው) በነበረው ቅራኔ ምክንያት 7 መጻህፍትን በገዛ ፈቃዱ ቀንሶ ዛሬ በምዕራብውያን ዘንድ በስፋት የተስፋፋውን እና የእኛን ሐገር ጨምሮ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ሀይል የሌላቸውን ሀገራት የተቆጣጠረውን የ66 መጻሐፍት ሊያስፋፋ ችሏል፡፡
- - - - - - -
።--> መናፍቃን 81 /ሰማንያ አሃዱ/ መጽሐፍ ቅዱስን የማይቀበሉባቸው ምክንያቶች እና እንዲቀበሉ የሚያስገድዳቸው ምክንያቶች እንዲሁም ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት የሉም እንዳይሉ ማስረጃዎች፡-
-> ተቃዋሚዎች ከ66 ውጭ መጽሐፍ የለም ቢሉም ሐዋርያት ሆኑ ጌታ ከ81 መጻሐፍት እየጠቀሱ አስተምረዋል፡፡ ይህን እስቲ በማስረጃ እንመልከተው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 1. - ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር ይለናል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (ሉቃ.3፡3) - እንግዲህ ጌታችን አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ30 ዓመቱ በፊት የት ነበረ? ምን እየሰራ ነበረ? ብልን ስንጠይቅ መልሱን በ66 መጻሕፍት ውስጥ ሳይሆን በቤተክርስቲያናችን የትውፊት መጻህፍት ውስጥ እድገቱምን እንደሚመስል በዝርዝር ተጽፎ እናገኛለን፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 2. - በማቴዎስ ወንጌል 27፡3-10 (በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን። እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ። ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ። የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው። የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ። ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት። ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ። በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው። ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ።) በዚያን ጊዜ የነቢዩ የኤርሚያስ ቃል ተፈጸመ ይለናል ይሁዳ… እንዲህ ያለው ‹‹የእስራኤል ልጆች የተስማሙበትን የክቡርን ዋጋ ሠላሳውን ብር ወሰዱ›› ይህን ቃል የምናገኘው በስድሳ ስድስቱ ውስጥ ሳይሆን በተረፈ ኤርሚስ 7፡ 2-4 ባለው ላይ ነው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ትንቢተ ኤርሚያስን ጠቅሶ ሲጽፍልን 'በነብዩ ኤርሚያስ የተባለው ብሎን ነው፡፡' ምን ተባለ ስንል ማቴዎስ ''የተባለውን'' እና ''ተፈጸመ'' ያለንን የምናገኘው መናፍቃኑ አንቀበለውም በሚሉት በ81 መጽሐፍት ውስጥ ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 3. - ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፡፡ ‹‹እንፍጠር›› ሲል ከአንድ በላይ ብዛትን ሲያመለክት 2 ወይም 4 ወይም 10 ሳይሆኑ ስላሴን /ሶስትነት/ ስስት መሆናቸውን የሚነግረን በሲራክ 2፤22 ሄኖክ 5፤38 ሄኖክ 6፤24 ሄኖክ 13፤14 እዝራ ስቱኤል 4፤56 እዝራ ስቱኤል 12፤48 ሲራክ 44፤10 በግልጽ ሥላሴ እያለ በማሳየት ነው፡፡ ክብር ለቅድስት ሥላሴ ይሁን!
_ _ _ _ _ _ _
ማስረጃ 4. በሉቃስ 14:13-14 “ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ” የሚለውን ኃይለ ቃል ከጦቢት 4፡7፡10 የተገኘ ነው ‹‹ከገንዘብህም ምጽዋት ስጥ ምጽዋትም በመጸወትህ ጊዜ በገንዘብህ አትዘን፣ ከድሃም ፊትህን አትመልስ፤ እግዚአብሔርም ገጸ በረከቱን ካንተ አይመልስም፡፡››
_ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 5. 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡2 በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ የሚለውን ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ከጦቢት 4፡12 ጠቅሶ ነው ያስተማረው የተገኘ ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 6. በዮሐንስ ወንጌል 10፡22 በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤ … ‹‹የመቅደስ መታደስ በዓል›› በሌሎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አናገኘውም ግን ቅዱስ ዮሐንስ ከመጽሐፈ መቃብያን 4 ላይ ጠቅሶ ተናገረ፡፡
_ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 7. በ ሮሜ 13፡1 ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። የሚለው ኃይለ ቃል ከሲራክ 17፡14 የተወሰደ ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 8. አዳምና ሔዋን አቤልና ቃየልን ወለዱ፡፡ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ይላል ዘፍጥረት 4፡17 በ66ቱ መጽሐፍት ላይ ስለ አቤልና ቃየል መወለድ እንጂ ሌላ የሰው ዘር በምድር ላይ ሰለመኖራቸው ምንም አያወራም፡፡ ታድያ ይህቺ የቃየል ሚስት ከየት መጣች? ስለስዋ ምንም አይናገርም በአለም ላይ የነበሩ ሰዎች አራት ብቻ እንደነበሩ ነበር የምናነበው፡፡ የዚህን መልስ የምናገኘው በኩፋሌ 5፡8-17 ላይ ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 9. - ይሁዳ በመልዕክቱ ‹‹የሄኖክን ትንቢት ከመጽሐፈ ሄኖክ ጠቅሶ›› ጽፎታል (ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል (ይሁዳ 1፡14-15) መጽሐፈ ሄኖክ ደግሞ በስልሣ ስድስቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፡፡ ሄኖክ ትንቢት ተናገረ ብሎ ከትንቢቱ ጠቅሱ ይሁዳ በመልዕክቱ ጽፎልናል ይህም ትንቢት በሄኖክ 1፡9 ላይ በግልጹ ተቀምጦ እናገኘዋለን፡፡ እንግዲህ ይሁዳ ሄኖክ ትንቢት መናገሩን እየነገረን ተቃዋሚዎች ሄኖክ ትንቢት አልተናገረም ይሉናል፡፡እኛስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የጻፈወን ይሁዳን እናምናለን፡፡ እሱ የተቀበለውን እንቀበላለን ጥበብ አይኮረጅም (መጽሐፍ ቅዱስ ትውፊታዊ የአምላክ ቃል)
- - - - - - -
-+- በመጀመሪያ እስኪ መጽሐፍ ቅዱስ ትውፊታዊ መረጃ መሆኑን እንተማመን፡፡ ትውፊት ማለት ቅብብል፣ ርክክብ ወይም ውርስ ማለት ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ ውርስ ከቀደሙት አበው ለእኛ በርክክብ ደርሶናል፡፡ አንዱ ከሌላው የተቀበለውን ለሌላው አሳልፎ በመስጠት እስከ ዘመናችን የደረሰ እውነታ ነው፡፡ ትውፊት መጽሐፍ ቅዱስ ከመጻፉ በፊት ያለ የነበረ ነው፡፡ እንደውም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚሐብሔር ቃል መሆኑን አምነን የተቀበልነው የቀደሙት አባቶቻችን የእግዚሐብሔር ቃል መሆኑን በትውፊት ስላስረዱን ነው፡፡
-ለምሳሌ፡-
1-ዓለም ከተፈጠረ ሺህ 486 ዘምን መጽሐፈ ሄኖክ ተጻፈ
2- እስራሄል በግብጽ ሳሉ በፈርሆን ዘመን የኢዮብ መጽሐፍ ተጻፈ
3- 3643 ዓ.ዓ. እስራሄል ከግብጽ ወጡ በዚህ ጊዜ ኦሪት ተጻፈ፣ ወዘተ. . . . . እንግዲህ ከ1486 ዘመን በፊት የተጻፈ ህግ አልነበረም፤ በዚያ ጊዜ የነበሩ አበው ይመሩ የነበሩት ሙሉ በሙሉ በትውፊት ወይም በህገ ልቡና ነበር ማለት ነው፡፡ ከስልሳ ስድስቱ (66) መጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትየለም የምትሉ ወይም ትውፊታዊ መረጃ አንቀበልም ለምትሉ እስኪ የሚከተለውን ጥያቄ ላቅርብ
_ _ _ _ _ _ _
1- በኦሪት ዘፍጥረት አገላለጥ ቃየንም ሆነ አቤል ሁለቱም ለእግዚሐብሔር ከስራቸው ውጤት መስዋዕት አቅርዋል፡፡ ዳሩ ግን የተቀበለው የአቤልን መስዋዕት ብቻ ነው፡፡ የቃየንን መስዋዕት ያልተቀበለው ለምንድን ነው? መቼም ለአቤል አድልቶ ነው የሚል መልስ እንደማይሰጥ እርግጣኛ ነኝ ምክንያቱም እግዚሐብሔር ለሰው ፊት አያዳላም፡፡
2- አቤል ከበጎቹ በኩራትና ከሰቡ እግዚሐብሔር መስዋእት አቅርቧል፤ ከበጎቹ መካከል በኩራትና ስቡን ማቅረብ እንደሚገባ እንዴት አወቀ? ምክንያቱም የጽሁፍ ህግና ትዕዛዝ በዘመኑ አልነበረም
3- ‹ቃየንም ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ሄኖህንምም ወለደች› ይላል፡፡ እግዚሐብሔርወንድና ሴት አድርጎ የፈጠረው አዳምንና ሄዋንን ብቻ ነው፡፡ አዳምና ሄዋን ደግሞ የወለዱአቸው አቤልና ቃየንን እንደሆነ በምዕራፍ 4 ተገልጽዋል ፤ታዲያ የቃየን ሚስት ማንነች? ከየትስ መጣች? ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከ66 መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑትን ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትንና ትውፍታዊ መረጃ መሰረት ማድረግ ይገባል ያለበለዚያ ጥያቄዎቹ የማይፈቱ እንቆቅልሽ ሆነው መቅረታቸው ነው?
_ _ _ _ _ _ _
- እስኪ ደግሞ ወደ ሐዲስ ኪዳን እንሂድ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ቢያንስ ቢያንስ ለ20 ዓመታት ያህል ስለ ጌታ ይማሩ የነበሩት በቃል ነበር ምክያቱም ሐዲስ ኪዳን ገና በጽሁፍ አልተቀረጸም ነበርና በቅብብል ወይም በሰሚ ያገኙትንም እነርሱ ራሳቸው ከጌታ እደተቀበሉት አድርገው ያስተምሩ ነበር ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ጳውሎስ ነው (1 ቆሮ. 11፥23-24)፡፡ ጳውሎስ ከሐዋርያት ቃል የተማረውን ለሌሎች ደግሞ አስተላለፈ፡፡ ስለዚህም ወንጌል የሚያሰኘው በጽሁፍ መስፈሩ ብቻ ሳይሆን የሕያው የእግዚሐብሔር ቃልና የህይወት መንገድ መሆኑነው፡፡ በጌታ ጊዜ ወንጌል ገና አልተጻፈም ነበር፣ “ለሐዋርያቱም ወደ ዓለም ሒዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ”(ማር.16፥1) ይህም ሲል የሰሙት ተማሩት እንጂ በጽሁፍ ቀርጾ የሰጣቸው ወንጌል አልነበረም፡፡
_ በተጨማሪም በማርቆስ ወንጌል ም.1፥21-22 ‹ወደ ቅፍራንሆም ገቡ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማረ እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጸፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ›፡፡ ይህ የክርስቶስን ተቃዋሚዎች ራሱ ያስገረማቸው ትምህርት ምን አይነት ነበር ‹ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለእርሱ በመጻህፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጎመላቸው› ሉቃ 24-27
_ ከትንሳሄው በኋላ ለሁለቱ ደቀ መዝሙር ተረጎመላቸው የመጻህፍት ትርጓሜ በየትኛው ሀዲስ ኪዳን ላይ ይገኛል? “በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ. . . ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ” ማቴ 2፥23 ይህን የተናገረው ነቢይ ማነው? በየትኛው የትንቢት መጽሐፍ ይገኛል? ማቴ 27፥9 ‹በዚያን ጊዜ በነቢዩ ኤርምያስ የተባለው ከእስራሄል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን የተገመተውን ዋጋ ሰላሳ ብር ያዙ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሰሪ መሬት ሰጡት የሚል ተፈጸመ› ይህስ ከየት ተገኘ? በተጨማሪም ሉቃ 2፥25-32፣ 2ኛ ጢሞ 2፥ 8፣ ዕብ 12፥ 21 ፣ ራዕይ 2 ፥14፣ ዮሐ 20፥ 30 ፣ ዮሐ 21 ፥25፣ ይሁዳ 9 እንዲሁም ዮሐ 1 ፥48 ሌሎች ማሳያዎች ናቸው፡፡
_ በአጠቃላይ እነዚህ መረጃዎች ከ66ቱ መጻህፍት የማናገኛቸውና ነገር ግን ተዋህዶ እምነት በምትጠቀምበት ሰማንያ አህዱ ውስጥ ፍንትው ብለው የተጠቀሱ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህን የመሳሰሉ ፍሬ ሃሳቦች ስለተቀመጡበት ነው ሰማንያ አሃዱን ከሌላው ጋር ይጋጫል የሚባለው?
_ ብርሃን ዓለም ጳውሎስ ‹እንግዲያስ ወንድሞች ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ› ያለው (2ተኛ ተሰሎንቄ 2 15)፡፡ በቃላችንም በመልእክታችንም የተማራችሁትን ‹ወግ› ያዙ ሲል ትውፊትን ማለቱ ነው፡፡
_ ፊልጵ 4፥9 ‹ከህኔ የተማራችሁትና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም እና ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል›፡፡ የቅዱስ ጳውሎሰ መልዕክት ግልጽ ነው፡፡ በፊልጵስዮስ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ከእርሱ ከአንደበቱ የተማሩትንና በጽሁፍ የተቀበሉትንም የሰሙትንም ያዩትንም ሁሉ እንዲይዙ እንደያደርጉ እንጂ የተጻፈውን ብቻ እንዲይዙና እንዲጠብቅ አልነበረም፡፡ ዛሬም እኛ በትውፊት የደረሰንን ሁሉ ልንጠብቅ መንፈሳዊ ግዴታችን ነው ፡፡
_ 2ኛ ጢሞ ‹የእግዚሐብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚሐብሔር መንፈስ ያለበትን መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ይጠቅማል›፡፡ ምክሩም ጠቃሚና አስፈላጊ መሆኑን ተዋህዶዋውያን እናምናለን፡፡ ስለዚህም በቤተክርስቲያናችን ያሉትን የእግዚሐብሔር መንፈስ ያለባቸውን ቅዱሳት መጻህፍት ሁሉ ለክርስቲያናዊ ህይወታችን እንገለገልባቸዋለን፡፡
--> በመጨረሻም ኦርቶዶክሳዊያን በቤታችን ያለን መጽሐፍ ቅዱስ:-
81: የኦርቶዶክስ
73: የካቶሊክ
66: የፕሮቴስታንት
24: የአይሁድ
በሆኑንና አለመሆኑን ለይተን ተረድተን የረሳችንን የሆነውን ትክክለኛውን 81 አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስን እንጠቀም።
♥ ♥ ♥ ♥ ♥
21 21 21
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም
ቤተክርስቲያን አትታደስም!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም
እንማልዳለን!
(መጽሐፈ ሚስጢር)
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን
መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣
የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ
ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
†† † † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት
እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም
ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
†† † † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
( #Zerihun_Eshetu 's post in #እግዝእትነ_ማርያም_OUR_LADY_MARY
#ይህች_ለዘላለም_ማረፊያዬ_ናት_መርጫታለሁና_በዚህች_አድራለሁ።መዝ-13:14 #የእግዚአብሔር_እናት_Mother_of_God
እነዚህን ግሩፕ እና ፔጅ Like ያድርጉና ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ አስተምህሮዎችን ይማሩ: የነፍስ ምግብን እግዚአብሔር ያዘጋጅል።
♥ ♥ ♥ ♥ ♥ See less
— with Abesha WeddingPhoto.
Wednesday, February 7, 2024
Friday, February 2, 2024
Biblical Truth – The Centrality of Jesus Christ
DATE: 09/07/22
CATEGORY: DEVOTIONALGENERAL
TAGS: BIBLICAL TRUTHDISCIPLEMAKERSDISCIPLESHIPGOOD NEWS
The Bible is the story of God’s redeeming work in human history. The main focus is God’s plan of salvation through Jesus Christ, designed to redeem us and all of creation. In fact, the life and teachings of Jesus are central to shaping our interpretation of passages that are difficult or not easily understood. So, biblical truth convicts us of sin, leads us to salvation, and teaches us how to follow Jesus in daily life.
We can explore biblical truth by understanding:
The power and authority of the Word of God
Biblical Interpretation
The discipline of studying the Word of God
The Centrality of Jesus Christ
The Whole Bible is the Word of God.
It is helpful to allow the words of Jesus to guide our understanding of the rest of the story. In fact, the life and teachings of Jesus can shape our interpretation of passages that are difficult or not easily understood. For instance, after the resurrection, two disciples were walking on the Road to Emmaus. Jesus joined them and gave them a lesson on how to interpret His own death and resurrection. He told them that the entire Old Testament had pointed to Him. Christ revealed that His teachings will help us interpret both the Old Testament and New Testament more accurately.
He said to them, ‘How foolish you are, and how slow to believe all that the prophets have spoken! Did not the Messiah have to suffer these things and then enter his glory?’ And beginning with Moses and all the Prophets, he explained to them what was said in all the Scriptures concerning himself”. – Luke 24:25-27
Biblical Truth and Interpretation Centered on Jesus
Here are some steps to follow as we attempt to interpret the Scriptures correctly through Christ:
Allow Biblical narrative and the teachings of Jesus to carry more weight in the development of doctrine and theology.
In the interpretation of any Biblical passage, check to see if Jesus made reference to that passage or Biblical issue elsewhere, and allow Jesus’ teachings to improve your understanding.
Allow the clear teachings of scripture, especially the teachings of Jesus, to help you interpret the passages which are more difficult to understand.
Be careful to avoid making strong theological statements based on one Biblical text which is obscure or difficult to understand.
Reading and studying the Bible in Christian community will help us to interpret Scripture. He promises to be with us—“Where two or three are gathered in my name, there am I with them” (Matthew 18:20).
Be obedient to the Scriptures that are clear and the truths you already know. There is no need for more if you are not willing to obey what you already understand.
Growing In Understanding
One of the ways we can grow in our ability to interpret the Bible Is simple. Ask your self how did Jesus interpreted passages from the Old Testament? You’ll find that many of His teachings are quotes from various Old Testament books. Many of these are taken from the books of the Torah, the Psalms, and Isaiah. Here are some good examples:
When Jesus was tested in the wilderness (Matthew 4:1-11), He quoted passages from Deuteronomy 8:3, Psalm 91:11-12, Deuteronomy 6:16, and Deuteronomy 6:13.
In Jesus’ first sermon (Luke 4:14-30), He quoted a section from Isaiah 61:1-2.
In the Sermon on the Mount (Matthew 5-7), Jesus quoted passages from Exodus, Leviticus, and Deuteronomy
Preaching Jesus from the Word of God
It is clear from the Book of Acts, that the apostles had a very high regard for God’s Word. It was their conviction that if they preached the “Word of God” their message would be used by the Holy Spirit and it would have the power to convict and transform. This belief suggests that as the Word of God is preached, it extends the power and presence of the Kingdom of God. In this way, the Gospel gains power in new regions of the world. Note the following passages:
(Acts 8:25) They “proclaimed the word of the Lord and testified about Jesus.”
(Acts 13:33) On the Sabbath, “the whole city gathered to hear the word of the Lord.”
(Acts 13:48-49) “When the Gentiles heard this, they were glad and honored the word of the Lord” and “the word of the Lord spread through the whole region.”
(Acts 15:35) In Antioch, they “taught and preached the word of the Lord.”
(Acts 15:36) Later, Paul said to Barnabas, “Let us go back and visit the believers in all the towns where we preached the word of the Lord and see how they are doing.”
(Acts 16:32) “They spoke the word of the Lord to him and to all the others in his house.”
(Acts 19:20) “In this way the word of the Lord spread widely and grew in power.”
Biblical Truth When You Preach
When we preach, it is possible for us to draw attention to ourselves rather than to the word of God? The goal of preaching is to testify about Jesus and for God to be glorified.
Does your preaching focus on Jesus, and does it allow the power of the Word of God to be released?
Global Disciples Canada is a Christian mission organization that trains local leaders living near least-reached communities to multiply disciples for Christ. One-third of our world hasn’t heard the Good News of Jesus. Yet. Global Disciples refers to these as “least-reached” people, and fewer than 10% of all missionaries work among these groups. We live in a time where many of these people are within reach of a local church. Through our simple and effective strategy of training and coaching, believers share the Gospel in their own nations and cultures. Jesus said, “Go and make disciples of all nations,” and we’re committed to doing just that. If you are looking for a Christian mission organization to partner with to become a better disciple and help make disciples, connect with us today!
Centrality of Jesus
Share
Recent Posts
New Year Bible Verses: Empowering Words for a Fresh Start
Inspiring Discipleship Quotes: Gateway to a Life of Faith
This collection brings together profound insights from renowned spiritual leaders, thinkers, and philosophers.
For Unto Us A Child Is Born: Discover What It Really Means
Get God Stories Every Month. - blog page
Ordinary men and women are bringing the message of Jesus Christ to those who have never heard the name of Jesus. And they are experiencing extraordinary encounters.
Sign up now and receive a monthly reminder of how God is working in the least-reached areas across the world.
NAME*
First Name
First
Last Name
Last
EMAIL*
Enter Email
Enter Email
Confirm Email
Confirm Email
Subscribe
Thursday, February 1, 2024
Wednesday, January 31, 2024
Tuesday, January 30, 2024
Saturday, January 27, 2024
የሀገራችን ታቦት ለአስማትና ለጥንቆላ ሥራ የዋለ ስለመሆኑ
የሀገራችን ታቦት ለአስማትና ለጥንቆላ ሥራ የዋለ ስለመሆኑ
በመሪጌታ ጽጌ ስጦታው የተጻፈ የወጋገን መጽሐፍ እንዲህ ይለናል ተከታተሉ
እመሂ ዘረገሙ ሰማየ ነጺሮሙ ምድረ ጒድጓዶሙ ታቦተ ገሲሶሙ ዕጣነ ወጊሮሙ ባሕረ በጽቢጾሙ ቆጽለ መቲሮሙ ጾመ ነቂሎሙ አስማተ ገቢሮሙ ይሠአር ሥራያቲሆሙ ለመሠርያን ኩሎሙ ዮፍታሄ በስምከ ሆልናዝር ሆልናዝር ሆልናዝር ሥራዬ ዘርዝር እምላዕለ ገብርከ ( ዓመትከ )
ትርጒም ፦ ሰማይን ተመልክተው ቢሆን ምድርንም ቆፍረው ቢሆን ታቦትን ዳሰውም ቢሆን ዕጣን አጢሰውም ቢሆን ውሃ በጥብጠውም ቢሆን ቅጠል በጥሰውም ቢሆን ቆርጠውም ቢሆን አስማት አድርገውም ቢሆን በእኔ ላይ ያደረጉት ማናቸውም ድግምት ቢሆን ሆልናዝር ሆልናዝር ሆልናዝር በተባለው ስምህ ከባርያህ ከእከሌ ላይ ብትንትን አድርግ ( መጽሐፈ ቆጵርያኖስ የዘወትር ገጽ 6 )
ልብ እንበል የመቅደሱ አገልጋዮች የሆኑት የኦርቶዶክስ ካህናት ከምንና ከምን የተዘጋጀ ድግምት እንደሚደግሙ እንመልከት :: ሰማይን በመመልከት ከዋክብትን በመቁጠር ምድርን ቆፍረው የሰው ወይንም የእንስሳትን አጥንት በማውጣት ታቦት በመዳሰስ ዕጣን በማጤስ ቅጠል በመበጠስ ሥር በመማስ የሚደረገውን አጋንንታዊ ድግምት ተመልከቱ:: እንዲሁ ብንናገረው የቤተክርስቲያን ጠላት ተደርገን በተቆጠርን ነበር :: ከራሳችን ልብ ያወጣነው ወይንም እኛ የፈጠርነው እንዳልሆነ ግን አሁን በግልጥ እየታየ ነው :: ስለ ታቦት ስለ መቅደሱ አገልግሎት ምን ያህል ክፋትም በውስጡ እንደሚደረግ የእከሌ ታቦታ ያለ መምሬ እከሌ አይያዝም ፣ አይንቀሳቀስም :: የእከሌ ታቦት እንደወጣች አልመለስም አለች የሚባለው ከምን መንፈስ እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል ::
የዚህ መጽሐፍ ደራሲና አዘጋጅ ማለትም የቆጵርያኖስ መጽሐፍ አዘጋጅ የመቅደስ ሰው እንደሆነ ደጋሚዎችም በዚሁ አገልግሎት ውስጥ የተጠመዱ መሆናቸው የመጽሐፉ ይዘት በግልጥ ያሳያል :: የሚገርመው ድግምታቸው እንዲበጣጠስ ደጋሚ ሟርተኞች ደግሞ ታቦት ዳሰው ዕጣን አጢሰው ሥር ምሰው ቅጠል በጥሰው በሰው ላይ የሚደግሙት ራሳቸው ከታቦቱ ጋር ቅርበት ያላቸውና ታቦቱን ለመዳሰስ ዕድልና ሥልጣን ያላቸው ቀሳውስት መሆናቸው ነው :: ምን ይህ ብቻ በቅዱስ ቊርባን ማለትም በሥጋ ወደሙ ላይ ደግመው መድኃኒት አድርገው ለሴት ወይም ለወንድ መስተፋቅር የሚሰጡትስ እነርሱ አይደሉምን ?
ቄሱ ቅዳሴውን እንደጨረሰ አንድ የሚለው ነገር አለው እርሱም ፦። አናምንም አንመራመርም አንማርም ያሉትን መናፍቃንን ዕጣኑን እያሸ ዕጣኑ እንደታሸ ይሻቸው አውዱ እንደተደፋ ይድፋቸው:: አውድ የተባለው ኅብስቱን የያዘው ትሪ ነው :: ታድያ ቄሱ ትሪውን እየደፋ እንዲሁ ይላል ማለት ነው :: መብራቱ እንደጠፋ ያጥፋቸው ( መብራቱ እያጠፋ ) ይላል :: ይህን ከማለት ይልቅና ምናምንቴ ድጋም ደግሞ በአጋንንታዊ ትብታብ ከማሰር ማስተማሩ መምከሩ ይበልጥ የተሻለ አይሆንምን ? ለነገሩ ሳይማሩ ምኑን ያስተምሩታል :: እንዳይማሩ እነ ደጉ ዓለም ካሣ ከተማረ ሰው ጋር አትዋል ብለዋል ሲል መሪጌታ ጽጌ ይህንን የደረሰበትን እውነት አካፍሎናል ::
ሌሎችንም መረጃዎች ከአውደ ነገስት የጥንቆላ መጽሐፍ እና ከመሳሰሉት አምጥቶ ማካፈል ይቻላል :: ታድያ ታቦት ለእስራኤል ሕዝብ ብቻ ተሰጥቶ ሳለ የሌላውን ኪዳን የራስ ለማድረግ በሰሎሞን ዘመን ታቦተ ጽዮን ወደ እኛ መጣች ብሎ ይህን አሉታዊ ትርክት አሜን ብሎ መቀበል ትልቅ ስሕተት ነው :: ከዚህም ሌላ ማርያም በሰሎሞን ጊዜ ነበረችን ? ገና መች ተወለደችና ነው ታቦት የሚቀረጽላት ? ለበሬ ወለደዎች በሰጠነው መልስ መሰረት ታቦቱ በሰለሞን ዘመን መጣ ከተባለ ከሰለሞን በኋላ 16ኛ ሆኖ በነገሠው በኢዮስያስ ዘመን ታቦቱ እዚያው ኢየሩሳሌም እንደነበረ መጽሐፍቅዱሳችን ይናገራል 2ኛ ዜና 35 ፥ 3 :: ይህንን ሃሳብ በጥልቀት ስላስተማርኩበት ብዙ አልሄድበትም :: ያነሳሁበት ጉዳይ ግን በቲዎሎጂ ማስተርሱን የሰራው ዶክተር ወዳጄነህ የበሬ ወለደ ታሪክ ተናጋሪዎችን ወሬ ሰምቶ ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መጥታለች በዓይኔ በብረቱ አይቻለሁ አስራቴንም ለእርስዋ መስጠት ጀምሬያለሁ ተቀላቀሉኝ አንድ ላይ እንሁን በማለት ጠቅላይ ሚኒስቴርያችንን ሳይቀር አክሱም ጽዮን ሄደው ቢባረኩ በመንግስትዎ ውጤታማ ይሆናሉ ድል ይቀናዎታል ማለቱ ከእርሱ እውቀትና የትምህርት ደረጃ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ጉዳዩ ገርሞኝና ድንቅ ብሎኝ ነው :: ይህ የዶክተር ወዳጄነህ አካሄዱ ደግሞ አሁን ላይ ባለ ነገሩ አቋሜና መብቴ ነው ተጠምቄ የኦርቶዶክስ አባል ብሆንስ ማን ይከለክለኛል ? ሲል ዘርዘር አድርጎ በተናገረው ጉዳይ ላይ አላዋቂ አሰኝቶታል :: ሰዎችም በብዙ ታዝበውታል :: የኦርቶዶክስ አባል መሆን ከፈለገ ጥንቱኑስ ማን ከለከለው ? ሲጀመርስ የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሰባኪና የእምነቱ አካል ማን ሁንልኝ አለው ? እኔ ሲገባኝ የግዴታ እምነትም ሆነ አገልግሎት የሰጠን የለም :: ስናምን ወደን ገብቶናል ብለን ነው ያመነው :: ስናገለግልም ወደን እና ገብቶናል ብለን ነው የምናገለግለው :: ከዚህ ውጪ ከጀርባችን የቆመ አስገዳጅ ኃይል ለማናችንም የለንም :: ወዳነሳነው መሠረታዊው ጉዳይ ስመለስ እኛ ኢትዮጵያውያን አሕዛባውያን ስለሆንን ታቦት የለንም :: ታድያ ይሕንን ያወቁ ብልጥና ነጋዴ ጠንቋይ ካህናቶች ናቸው ታቦቱ በሰለሞን ዘመን ወደ እኛ መጥቶአል የሚለውን የውሸት ትርክት ይዘው ታቦቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለ በመቁጠርና አውደ ነገሥታቸውንም በመድገም ጥንቆላቸውን የሚያጧጡፉት :: ታድያ ታቦቱ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ሳይሆን እንዳልመጣ ወይም እንደሌለ ያመኑ ጠንቋይ ካህናት ናቸው እነዚህ ካህናት :: ስለዚህ ታቦቱ በአሁኑ ሰዓት ለእነርሱ የመክተፍያ ያህል ስለሆነ ይህን ተላላና ምስኪን ሕዝብ ታቦት በሰለሞን ጊዜ የመጣልህ ክብርህ ነው በማለት በታቦቱ ጀርባ ይህንኑ ከላይ የዘረዘርኩትን ጥንቆላ ያስፋፋሉ:: አያይዘውም የእንጀራቸው ጉዳይ ነውና ታቦትን አክብር ባታከብር የኦዛ ስብራት ያገኝሃል ፣ ትቀሰፋለህ በማለት ሕዝብን ማስፈራራታቸው ሳያንሳቸው ፣ በታቦቱ ስም ደግሞ ሆዳቸውን ሊሞሉ ለታቦቱ ክብርና ታቦቱ ሄዶ ወደ ማደርያው እንዲገባ ደም ይፍሰስለት በግ ፣ በሬ ይታረድለት እያሉ ታቦት ወጥቶአለ በተባለበት ቦታ ሁሉ ይወተውታሉ :: ይህንን የሚያደርጉት ግን ጥቅማቸው እንዳይቀርባቸውና የስዕለት ገንዘብ ለመብላት ሲሉ ፣ ለሆዳቸውም ጭምር ነው :: ደም ሲፈስለት ደግሞ ይህንኑ የጠንቋይ ቀሳውስቱን አጀንዳ ለማስፈጸም በዚያው ልክ በታቦቱ ላይ ያለው የጥንቆላ መንፈስና አደራረግ እግረ መንገዱን ይገለጣል :: ታድያ ታቦቱን እንዳይቀርቡት የኦዛ ስብራት ሕዝቡን የሚያገኝ ከሆነ ታቦቱን እየዳሰሱ የሚጠነቁሉትን እነዚሁኑ ጠንቋዮች ለምን ቀድሞ አላገኛቸውም ? እነርሱ ላይ ሲሆን ታቦቱ ይደክማል ማለት ነውን ? መልሱን ለእናንተ ለአንባቢዎች እተዋለሁ :: ስለዚህ ከዚህ በኋላ መወሻሸትም ሆነ የውሸት ማስፈራራት አያስፈልግም :: ታቦትን ለአስማትና ለጥንቆላ ሥራ መጠቀምያ እናድርግ ካላልን በስተቀር ታቦት እኛ ኢትዮጵያውያን ጋር የለም :: አይኖረንምም :: አሁን ላይ ያለ ታቦት በመጎናጸፍያ ተሸፍኖ ነገሠ እልል በሉለት ተብሎ በሬና በግ ቢታረድለት ፣ አልፎም ደግም የጠንቋዮች መጠቀምያ ሊሆን እየተዳሰሰና እጣን እየተጬሰ ቢጠነቆልበትም ምናልባትም አጋንንቱ የሚሳብበት ታቦት በኢየሱስ ብቸኛ አዳኝነት ያላመኑትን ሰዎች ይዋጋ ካልሆነ በስተቀር ክብሩ በኢየሱስ ክርስቶስ የተተካ በመሆኑ እኛ ላይ የኦዛ ስብራት አያመጣም:: ተሸክሞ ወጥቶም ለሆድ መሙያ የሚሆን የበሬና የበግ እርድ ከሚያስገኝ በቀር ፍጹም በሬ ወለደ ነውና ስለተሸከምነው ብቻ የጦርነት ድል አይሰጠንም :: ይሄ ሁሉ የነ ምሕረተ አብና የነዘበነ ለጥቅምና ለእንጀራ መብያ የሆነ የውሸት ዲስኩር ነው :: አሁን ደግም አስራት ሰጪውና ታቦተ ጽዮንን ተሳለሚው ዶክተር ወዳጀነህ ተጨምሮበታል ፣ እግዚአብሔር ይራራላቸው ፣ ይድረስላቸውም ነው የሚባለው :: ይሁን እንጂ አሁን ላይ ተነስቶ ዶክተር ወዳጄነህ እንዳደረገው ሰዎችን ወደ ታቦት መምራት ወዴት መምራት እንደሆነ ለሁላችሁም ግልጽ የሆነ ይመስለኛል :: አሁን ሃሳቤን ጨርሼአለሁ መልዕክቴንም በዚሁ እጠቀልላለሁ :: በዚህ መልዕክት ተጠቀሙ :: ለሌሎችም አድርሱልኝ ተባረኩ ሻሎም
አባ ዮናስ ጌታነህ ሐዋርያዊ አገልጋይ
ከኦርቶዶክስ ተሃድሶ
Thursday, January 25, 2024
Subscribe to:
Posts (Atom)