Sunday, February 28, 2021
Friday, February 26, 2021
Monday, February 22, 2021
Sunday, February 21, 2021
Saturday, February 20, 2021
Friday, February 19, 2021
የድንጋይ ቆብና ክታብ /የጋት ሚካኤል
የጋት ሚካኤል በደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት ከስማዳ ዋና ከተማ ወገዳ በምስራቅ አቅጣጫ 20 ኪ/ሜ ተጉዞ የሚገኝ በጥንት ጊዜ ቁሳዊና መንፈሳዊ ታሪክ የተፈጸመበት ቦታ ነዉ፡፡የጋት ሚካኤል በአብርሃ ወአጽብሃ /ከ1253-1268/ዘመን በአባ ዙል እንደተተከለ ይነገራል፡፡
በዘመኑ የአካባቢው አቅኝ የነበሩት አዛይ አስፍ የሚባሉ ከየጋት አጋሚዶ እስከ ወፍጌ በነበረዉ የቅኝ ክልላቸዉ የተፈጥሮ ደን ዉስጥ ከሚገኝ ዋሻ አባ ዘመንፈስና አባ ጋቶ ከሰሜን አቅጣጫ ታቦተ ሕግ ይዘው መጥተው ከዋሻው ውስጥ እንደተቀመጡአዛይ አስፎ ወገን ሲያሰማራ በጫካ ውስጥ የተለያዩ መናንያን እንደተቀመጡ ይታያሉ፡፡
በዚህ ጊዜ የቦታው አቅኝና አባ ዙል ሲያነጋግሯቸው ታቦታቱን ይዘው እንደመነኑ ሲገልጹ በአካባቢው ቤተክርስቲያን እንዲተክሉ ሲፈቀድላቸው ምን ያህል ቦታ ይበቃወታል ሲባሉ”ጋት ሙሉ”ቢፈቀድልኝ ይበቃኛል፡በማለታቸዉ የተተከለዉ ደብር የጋት ሚካኤል ተባለ፡፡
አባ ጋቶ በቀን 9 ቁና ባቄላ እንደሚበሉ የሚነገርላቸው 50 ኪ/ግ የሚመዝን የምንኩስና የድንጋይ ቆብ 25 ኪ/ግ የሚመዝን ክታብና የድንጋይ መቁጠሪያ አጥልቀዉ በቀን 900 ጊዜ መስገድ እንደሚችሉና አባ ጋቶ የጋት ሚካኤልን አባ ዘመንፈስ የጉንጅ ማርያምን በተመሳሳይ ምሳርና መጥረቢያ እንደሰሩ ይነገራል፡፡
እንደ አባቶች አባባል ሁለቱም የበቁ ስለነበሩ አንዱ ሲሰራ ውሎ ሲወረውር ከአንደኛው የሥራ ቦታ በቀጥታ እንደሚደርስላቸው ይነገራል፡፡አባ ጋቶ የተፈቀደላቸውን 9 ቁና መብላት እንዲቀንሱ በተጠየቁት መሰረት ቢቀንሱ የስግደት አቅማቸውም በመቀነሱና መጥረቢያውንም ቢወረውሩ ከመካከል ቦታ አጋሚዶ ጻድቃኔ ከተባለ ቦታ በማረፍ ሁለቱም የቀጠሮ ሰዓት ሲያልፍባቸው ባጋጣሚ አንዱ ወደ ሌላው ሁለቱም ከየቦታው ተነስተው ሲሄዱ ሳይቀጣጠሩ መጥረቢያው ካረፈበት ቦታ ላይ ተገናኙ ፡፡
ሁለቱም ባንድ ላይ ተቀምጠው የተወያዩበት ቦታ ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ እንደሚባለው አባባል ጻድቃን ተባለ፡ከዚህ ቦታ ላይም ውኃ ፈልቆ እስካሁን አለ ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ፡፡ የጋት ሚካኤል የሚገኘውታምራዊ የድንጋይ ቆብና ክታብ አሁንም አስደናቂ ቅርስ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
የድንጋይ መቁጠሪያው በግራኝ ወረራ ዘመን ወደ ጎጃም ድማ ጊዮርጊስ ሂዶ እንደቀረ ይነገራል፡፡ይህ የድንጋይ ቆብና ክታብ በዘመነ ደርግ የወረዳውዋና ከተማ ተክሉ /ኮሽ/ በነበረበት ጊዜ ታሪካዊ ቆቡንና ክታቡን ለጉብኝት ወደ ጎንደር ክፍለ ሀገር ከተማ ጎንደር ለመውሰድ ታስቦ ኮሽ ድረስ እንዲመጣ በማድረግ በበቅሎ ተጭኖ ለመውሰድ ሲሞከር በቅሎዎች እየተኙ መሄድ እንደተሳናቸው በኋላ የመኪና መንገድ ሲሰራ ደግሞ በመኪና ተጭኖ ሲሞከር መኪናው ሸረፍ ጎዴ ሲደርስ ባልታወቀ ምክንያት ሞተሩ እየጠፋ እምቢ ሲል እነዚህን ቅርሶች ከመኪና በማውረድ መኪናው ብቻውን መሄድ እንደቻለ የሚነገርለት ይህ የታላቁ አባት የአባ ጋት ቆብና ክታብ መንፈሳዊ ታሪክ እንደሰራ ይነገራል፡፡ይህ አስደናቂ ቆብና ክታብ አሁንም ድረስ የቱሪስት መዳረሻ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
ምንጭ፡- ከስማዳ ወረዳ /ባ/ቱ/ጽ/ቤት