Wednesday, December 23, 2020

ZemruTube Ethiopia Orthodox Tewahido mezmur
«መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሠ እማ» ሳዊሮስ ሊቅ
«ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም»መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4፡7 በማለት ጠቢቡ ሰሎሞን ከመዝሙራት ሁሉ በሚበልጥ መዝሙሩ የዘመረላትን እመቤታችንን «ጥንተ አብሶ» /የቀደመ በደል/ እንዳልደረሰባት ቤተክርስቲያናችን መፅሐፍ ቅዱስን እና የጥንታውያን አባቶችን ትምህርት መሰረት አድርጋ ታምናለች ፡፡
«እመቤታችን አዳም በጥንተ ተፈጥሮው ሳለ /ከመበደሉ በፊት/ የተቀዳች ዘር ናት፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ...»ኢሳ 1፡9 እንዲል፡፡ ጌታችንም ይህን ንጹሕ ሥጋ ነው የተዋሐደው፡፡ የተአምረ ማርያም መቅድም «እመቤታችን አስቀድማ በአምላክ ሕሊና ትታሰብ ነበረ» ማለቱም ምክንያተ ድኂን ያደረጋት ንጹሕ ዘር መሆኗን ነው የሚገልጠው፡፡
አነጻት፣ ቀደሳት የሚሉት ቃላት የሚገልጡት አሳብ አንድ ነው፡፡ አስቀድሞ ያዘጋጃት የመረጣት እናት መሆኗን ብቻ፡፡ ቅዱስ ያሬድ «ማርያምሰ ተሃቱ እምትካት ውስተ ከርሡ ለአዳም ከመባሕርይ ፀዐዳ፤ ማርያም አስቀድሞ በአዳም አካል /ባሕርይ/ ውስጥ እንደ ዕንቁ ታበራለች፡፡» እንዲል፡፡ አዳምና ሔዋን በጥንተ ተፈጥሮ ሳሉ ካልበደለ ዘር የተቀዳች ንጹሕ መሆኗን በነጭ እንቁ መስሎ ተናግሮላታል፡፡
ሊቁ ቅዱስ ሳዊሮስ ደግሞ በሃይማኖተ አበው «መንፈስ ቅዱስ አቀባ እም ከርሠ እማ፤ መንፈስ ቅዱስ በእናቷ ማኅፀን ጠበቃት» ነው የሚለው፡፡ ሊቃውንቱ አንድ ትምህርት ያላቸው ናቸው፡፡ ቅዱስ ያሬድ «አንጺሖ ሥጋሃ ሃደረ ላእሌሃ» ያለውን ትርጉም ለመስጠት የቅዱሳን አባቶችን ትምህርትና እምነት መረዳት ያሻል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከላይ በዕንቁ መስሎ በአዳም ባሕርይ ውስጥ ታበራለች ያላትን እናት ደርሶ ሌላ ይላታል ማለት አይቻልም፡፡ ብዙዎቹን ወደ ስህተት የከተተው የቋንቋ ችግር ነው፡፡ ቋንቋ ንባብ እንጂ ምስጢር አይደለም፡፡ ፊደል ይገድላልና፣ ትርጓሜ /ምስጢር/ ግን ሕይወትን ይሰጣል፡፡ «አንጺሖ ሥጋሃ ሀደረ ላእሌሃ» መረጠ፣ አከበረ፣ ቀደሰ፣ ለየ እና አደረባት የሚል ነው፡፡ ሊቁ ስለ ሰንበተ ክርስቲያን ክብር የተናገረው ለዚህ አስረጅ ይሆናል፡፡ «ቀደሳ ወአክበራ ወዐልዓላ እምኩሎን መዋእል» ምን ማለት ነው፡፡ ሰንበተ ክርስቲያንን ለያት፣ አከበራት ማለት ነው፡፡ «ንጹሕ አነ እምደሙ ለዝ ብእሲ፤ እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ» ስንልስ ልዩነኝ አይመለከተኝም ማለታችን ነው፡፡ ስለዚህ ሊቁ «አንጺሖ ሥጋሐ» ያለው «ሥጋዋን ከአዳም ለይቶ አነጻ ቀደሰ ለየ» ማለት እንደሆነ ቤተክርስቲያናችን ታምናለች፡፡
በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው መጽሐፍ የእመቤታችንን ንጽሕናና ቅድስና አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያናችን ያላትን አስተምህሮና አቋም እንዲህ ያስረዳል፡፡ «አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጢአት /ጥንተ አብሶ/ ያላገኛት፤ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት፤ ገና ከመውለዷ አስቀድሞ በአምላክ ሕሊና ታስባ ትኖር የነበረች፤ በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ አሳብና ፈቃድ ሁሉ የተጠበቀች፤ ከተለዩ የተለየች ንጽሕት ቅድስተ ቅዱሳን ናት ይላል፡፡ /መሐል. 4፥7/፡፡» /የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና የውጪ ግንኙነት፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ድርጅት፣ 1988 ዓ. ም./፡፡
ቀደም ባሉት ዓመታት በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሊቃውንት ጉባኤ አባል እና ጸሐፊ በመሆን ያገለግሉ የነበሩት መምህር ሀብተ ማርያም ተድላ፤ የወላዲተ አምላክን ቅድስና እና ንጽሕና የበርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ጠቅሰው ባስረዱበት መጽሐፋቸው እንዲህ ብለዋል፡ «አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኀጢአት /ጥንተ አብሶ/ ያላገኛት ለመሆኗ በቅዱሳት መጻሕፍት የተረጋገጠ ነው፡፡ «መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው፣ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት...» /ሉቃ. 1፥28-38/ ይህ አባባል፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እርሷ ከመላኩ በፊት ጸጋን የተሞላችና የተባረከች መሆኗን በማያጠራጥር ሁኔታ ነው የሚገልጸው፣ ምክንያቱም መልአኩ ሰላምታውን በኃላፊ እንጂ በትንቢታዊ ግሥ አላቀረበምና፤ ወደፊት ጸጋ ይመላብሻል ከሴቶችም ሁሉ የተባረክሽ ትሆኛለሽ አላላትም፡፡ እንደገና መልአኩ በሰላምታ መደንገጧን አይቶ... «ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን /ባለሟልነትን/ አግኝተሻልና አትፍሪ...» አላት፡፡ አሁንም የመልአኩ ማረጋጊያ ዐረፍተ ነገር እንደ ኃላፊ እንደ ትንቢት አይደለም፤አግኝተሻል አላት እንጂ ወደ ፊት ታገኛለሽ አላላትም፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየው እመቤታችን ከመፀነሷ በፊት ወይም ወደዚህ ዓለም ከመምጣቷ በፊት ጀምሮ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያልነበረባት መሆኑን ነው፡፡» /ነጭ ዕንቁ በአዳም ገላ፤ በመምህር ሀብተ ማርያም ተድላ፤ አዲስ አበባ 2002 ዓ.ም፤ ገጽ. 43/፡፡
ልበ ብርሃኑ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ /ሊቀ ጠበብት/ «ምልጃ እርቅና ሰላም» በተሰኘው መጽሐፋቸው፤ «ለእናትነት የመረጣትን ማደሪያውን ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ ከኀጢአት ከርኩሰት ከእድፈት ሁሉ ጠብቋታል፡፡ የሰው ልጆች በተያዙበት በአዳም በደል ወይም በራሳቸው በደል ምክንያት የረከሱበት የኀጢአት ቅሪት መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የለባትም፣ አላገኛትም፤ ምክንያቱም እርሱ ራሱ ማደሪያ አድርጎ ስለመረጣት» በማለት አብራርተዋል፡፡ /ምልጃ እርቅና ሰላም፤ አለቃ አያሌው ታምሩ፤ አዲስ አበባ፤ ገጽ 49/፡፡
ወላዲተ አምላክ የውርስ ኃጢአት አለባት ማለት ጽርፈት ሆኖ ሳለ፤ ጥንተ አብሶ /መርገመ ሥጋ ወነፍስ/ በመልአክ ብሥራት ራቀላት ማለትም ከፍተኛ የሆነ የነገረ ሃይማኖት ስሕተት ውስጥ የሚጨምር ነው፡፡ የመልአክ ብሥራት የቀደመ በደልን /ጥንተ አብሶን/ የሚያርቅ ከሆነ በብሥራተ መልአክ የፀነሱ እመው /እናቶች/ የሶምሶን እናት፣ የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ... ምነው ከጥንተ አብሶ ያልነጹ ? በዚያውስ ላይ የወልደ እግዚአብሔርን ሞት ከንቱ አያደረገውምን ? የኑፋቄ ትምህርቶች መሠረታዊ ችግር አንዱን ጥቅስ ብቻ መዞ መነሣት ብቻ አይደልም፡፡ አንዱ ስሕተት ማለቂያ ወደ ሌለው ክህደት የሚጨምር መሆኑ ነውና ራሳችንን በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ጠብቀን ልናቆይ ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ አባል የሆኑት መልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን የወላዲተ አምላክን ንጽሕና በመሰከሩበት ቃል፡- «... ከዚህ ዓለም ቅዱሳንና ቅዱሳት መካከል እንደ እመቤታችን ያለ፤ በእርሷ መጠን ጸጋን የተመላ፤ በንጽሕናና በቅድስና የተዋበ፤ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነና በልዑል ኃይልም የተጠበቀ ሰውነት ያለው /ሉቃ. 1፥28-36/ የለም፡፡ ይኸውም እመቤታችን ለአምላክ እናትነት የተመረጠች ድንግል በመሆንዋና እንዲሁም የአምላክ እናት እንደ መሆንዋ መጠን በሐልዮ፤ በነቢብና በገቢር ሁሉ ንጽሐ ጠባይዕ ያላደፈባት ቅድስትና ቡርክት በመሆንዋ ነው፡፡ ስለዚህ ራስዋ አስቀድማ በወንጌል ቃል እንደተናገረችው፤ ትውልድ ሁሉ «ቅድስት ወብፅዕት» እያለ ሲያመሰግናት ይኖራል፡፡ ሉቃ. 1፥48፡፡»/ ሰአሊ ለነ ቅድስት የነገረ ማርያም ትምህርት፤ ክፍል አንድና ሁለት፤ የማእዶት መጽሔት ልዩ እትም፤ 1993 ዓ. ም. 2ኛ እትም፤ ገጽ 48/፡፡
«ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌል ቢሰበክላችሁ የተረገመ ይሁን፡፡» እንደተባለ፡፡ /ገላ.1፥8 እና 9/፡፡ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲ ያናችን ካስተማረችን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትምህርት ውጪ አዲስ /የተለየ፣ የኑፋቄ/ ትምህርት የሚያስተምሩ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ለይተን በማወቅ የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርት ጠንቅቀን ልንጠብቅ ያስፈልጋል፡፡ የተለየ የኑፋቄ ትምህርትን ከሚዘሩ መስሕታን /አሳቾች/ ርቀን በሃይማኖት ጸንተን ምግባር ትሩፋት ሠርተን መንግሥቱን ለመውረስ ስሙን ለመቀደስ የእግዚአብሔር ቸርነት የወላዲተ አምላክ አማላጅነት አይለየን፡፡
ይቆየን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Saturday, December 19, 2020

 ጸሎተ ሃይማኖት (የሃይማኖት ጸሎት)

Read in PDF
ነአምን በ፩ዱ፡ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኲሉ ገባሬ ሰማያት
ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ።
ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ
በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።
መቅድም
ሀ. ስሙ
1. ጸሎተ ሃይማኖት
2. የኒቅያ የሃይማኖት መግለጫ (ውሳኔ ሃይማኖት፤ አንቀጸ ሃይማኖት)
Nicene Creed
3. የኒቅያ ቁስጥንጥንያ ውሳኔ ሃይማኖት Nicene-
Constantinopolitan Creed
ለ. ለምን አስፈለገ?
1. « መለኮታዊውንና ሐዋርያዊውን እምነት ጠቅልሎ ያስቀመጠ
ስለሆነ።» ቅዱስ አትናቴዎስ
2. ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ግልጥ
በማድረግ ከክህደት ምእመናን ለመጠበቅ ነው።
3. እያንዳንዱ ቃልና ሐረግ የክርስቲያንን እምነት የሚያጠነክር ስለሆነ
ነው።
4. ቤተ ክርስቲያን ልትሆነውና ልታደርገው የሚገባትን ነገር
የሚያመለክት ነው።
ሐ. በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ያለው ልዩ ቦታ
1. በመላው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ተቀባይነት ያለው አንቀጸ
ሃይማኖት ነው።
2 የክርስቶስን አምላክነት የመንፈስ ቅዱስ አምላክነት በማብራራት ቤተ
ክርስቲያንን ከታላቅ አደጋ የታደገ ነው።
3. በኒቅያ በ325 ዓ.ም ላይ እንደገና በ381 ዓ.ም ላይ
በቁስጥንጥንያ በተከናወነው ኢኩሜኒካል ጉባኤ ላይ ተጨማሪ አንቀጾች
( መንፈስ ቅዱስን የሚመለከቱ) ገብቶለት ቤተ ክርስቲያንን በቀጥተኛ
ሃይማኖት (ኦርቶዶክስ) የመራ ነው።
መ. በቤተ ክርስቲያን የአምልኮ ሕይወት ያለው ቦታ
1. በጸሎት ማለትም በቅዳሴ ጊዜ በካህናትና በምእመናን ይደገማል።
2. የሚጠመቁ ሰዎች እምነታቸውን የሚገልጡት ጸሎተ ሃይማኖትን
አሰምተው በመድገም ነው። (የክርስትና አባትና እናት ስለሕፃኑ ፈንታ
ሁነው በጸሎተ ሃይማኖት እምነታቸውን መመስከር አለባቸው።
3. የክርስትና መለያ ምልክት ስለሆነ በምኩራብ የእምነት መግለጫ
የሆነው « እስራኤል ሆይ ስማ (ሼማ)በሚለው የአይሁድ አንቀጸ
ሃይማኖት ትይዩ ሊታይ የሚችል ነው።
መ. ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያለው ግንኙነት
1. ጸሎተ ሃይማኖት በተደነገገ ወቅት ገና የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ገና
አልተቋጨም ነበር።
2. ጸሎተ ሃይማኖት ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን የያዘ ስለሆነ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ለመወሰን ማለትም የትኞቹ መጻሕፍት
በቅዱሳት መጻሕፍት ቁጥር መግባት እንዳለባቸው
ለመወሰን አገልግሎአል።
ክፍል አንድ
ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአብሔር አብ
ሀ. እናምናለን። (ነአምን)
እምነት ደረቅ የሆነ የመረጃ ጥርቅም ሳይሆን በሕይወታችን ውስጥ
ለውጥ የሚያመጣ የመዳን መንገድ ነው። እናምናለን የምንለው
እውነት በጸሎታችን፥ በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ እንዴት ባለ
መንገድ መመራት እንዳለብን የሚያሳስብ ነው። የሰውን ሁለንተና
የሚነካ ነው።
• እምነት አእምሮን ይዛል፤ በመሆኑም « ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን
የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን» ብለን
ስንናገር፥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዓለምን የምናየው በተለየ መንገድ ነው።
• እምነት ፈቃድን ይይዛል፤ እምነት ማለት በፈቃዳችን ወደ እኛ ለቀረበው
ለእግዚአብሔር መስጠታችን ነው።
• እምነት ስሜትን ይይዛል፤ እምነት ማለት ላዳነን ለእግዚአብሔር
የምንሰጠው የፍቅር ምላሽ ነው። ይህ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር
ደግሞ ሌሎችን በመውደድ ይገለጣል።
በመሆኑም እምነት አራት መልካም ነገሮችን በክርስቲያን ሕይወት
ውስጥ ያከናውናል።
1. አንደኛው በእምነት በኩል ነፍስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት
ይኖራታል። ሆሴዕ 2፥2።
እምነት ሳይኖረው ማንም ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት
አይኖረውም። (ማር 16፥16)
ያለእምነት የሆነ ነገር ሁሉ ኃጢአት ነው። ሮሜ 14፥23
« ዘላለማዊውንና የማይለወጠውን እውነት ማወቅ በሌለበት ሥፍራ
በመልካም ምግባር የተጌጠ ሕይወት እንኳ ሐሰት ሊሆን ይችላል።»
አውግስጢኖስ።
2. ሁለተኛው የእምነት ውጤት የዘላለም ሕይወት ነው።
ያለ እግዚአብሔርን ማወቅ የዘላለም ሕይወት ምንም ማለት አይደለም።
ዮሐ 17፥3። ይህ እግዚአብሔርን ማወቅ የሚጀምረው በእምነት በኩሉ
አሁን በዚህ ምድር ሳለን ነው። ይህ እውቀት ፍጹም የሚሆነው ግን
እግዚአብሔርን በሙላቱ ስናውቀው ወደፊት ነው። እምነት ተስፋ
የምናደርገውን ነገር የሚያስረግጥ ነው። ዕብራውያን 11፥1።
በመጀመሪያ እግዚአብሔርን በእምነት በኩል ሳያውቀው ማንም ሰው
ፍጹም ወደሆነው ወደሰማያዊ ደስታ እርሱም ወደ እውነተኛው
እግዚአብሔርን ማወቅ መድረስ አይችልም። « ሳያዩኝ የሚያምኑኝ
ብፁዓን ናቸው። ዮሐንስ 20፥29።
3. ሦስተኛው ከእምነት የሚገኝ መልካም ነገር ለዛሬው ሕይወታችን
ትክክለኛውን አቅጣጫ ይሰጠናል ወይም ያመላክተናል።
አንድ ሰው መልካም ኑሮ ለመኖር፥ በትክክለኛ መንገድ ለመኖር
የሚያስፈልገው ነገር ምን እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነው ። ይህን
ለማወቅ ደግሞ በራሱ ጥረት ብቻ የሚደገፍ ከሆነ፥ ይህን እውቀት
ሊያገኝ አይችልም ወይም ብዙ ድካም ይጠይቅበታል። እምነት ግን
መልካም ሕይወትን እንዴት መኖር እንደሚቻል ያስተምረናል። « ጻድቅ
በእምነት ይኖራል።» ያዕቆብ 2፥4።
4. አራተኛው የእምነት ውጤት በእምነት ፈተናን ድል እናደርጋለን።
« በእምነት ቅዱሳን መንግሥታትን ድል ነሡ» ዕብራውያን 11፥33።
ማናቸውም ፈተና ከዓለም ወይም ከሥጋ ወይም ከዲያብሎስ ነው።
ዲያብሎስ ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ እንድናምጽበት ይሻል። 1
ጴጥሮስ 5፥8። ዓለም ደግሞ በብልጥግናዋ ከእርሷ ጋር እንድንጣበቅ
በማድረግ ወይም ደግሞ በባላጋራነት በማስፈራራት ትፈትነናለች። ነገር
ግን እምነት ግን የሚመጣውን እና የተሻለውን ሕይወት በማመን ይህን
ድል ያደርገዋል። « ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችሁ ነው። 1
ዮሐንስ 5፥4። ሥጋ ደግሞ በአንጻሩ የሚፈትነን ቶሎ ወደሚያልፉት
የአሁኑ አለም እርካታዎች እንድንሳብ በማድረግ ነው። ነገር ግን እምነት
ደግሞ በእነዚህ ጊዜያዊ ነገሮች ላይ ብንጠለጠል ዘላለማዊውን
ደስታችንን እንደምናጣ ያሳየናል። « በሁሉም ነገር የእምነትን ጋሻ
ውሰዱ።
ለ. በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ (በአሐዱ አምላክ
እግዚአብሔር አብ )
በክርስትና እምነታችን ውስጥ ዋናውና ማዕከላዊው ነጥብ ምሥጢረ
ሥላሴ ነው።
አንድ ሊቅ ሲናገር « ምሥጢረ ሥላሴን ካድ፥ መዳንህን ታጣለህ፤
ምሥጢረ ሥላሴን ጠቅልለህ ለማወቅ ሞክር አእምሮህን ታጣለህ።»
ብሎአል።
1. ምሥጢረ ሥላሴን በሚገባ መረዳት የምንችለው እግዚአብሔር
በቃሉ ማለትም በቅዱሳት መጻሕፍት ራሱን የገለጠበትን መንገድ
በመረዳት ነው።
• የእግዚአብሔር አንድነት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተብራርቶ ተጠቅሶአል።
ዘዳግም 6፥4-5፤ 2 ሳሙኤል 7፥22፤ ኢሳይያስ 45፥18።
የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት በአዲስ ኪዳን
ጸሐፊዎች ተብራርቶ ተገልጧል። ዮሐንስ 1፥1፤
20፥28፤ ሮሜ 9፥5፤ ቲቶ 2፥13፤ቅ
• ቃል በመጀመሪያ እንደነበረ፤ (ዮሐንስ 1፥1፤ ቃልም በእግዚአብሔር
ዘንድ እንደነበረ ዮሐንስ 1፥1፤ ቃልም እግዚአብሔር እንደሆነ (ዮሐንስ
1፥1) ቃልም ሥጋ እንደሆነ (ዮሐንስ 1፥14) ያ ቃል (ልጁ) በአባቱ
ዘንድ ያለውን እንደተረከልን (ዮሐንስ 1፥18) ያስተምረናል።
• መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ባመኑት ላይ ማደሩና ቤተ ክርስቲያንን
መምራቱ በሰፊው በአዲስ ኪዳን ተገልጧል። ዮሐ 14፥15-17።
1. ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተገለጠው እውነት የሚያሳየን እውነት
ምንድነው።
• እግዚአብሔር በአንድነቱ አለ።
• እግዚአብሔር በሦስትነቱ አለ። ይህ አንዱ እግዚአብሔር ሦስት አካላት
ማለትም አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ ነው። ሦስቱም አካላት በመለኮት
አንድ ስለሆኑ አብ እግዚአብሔር ነው፤ ወልድ እግዚአብሔር ነው።
መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። በአንድነቱ ውስጥ ሦስትነቱ አለ።
በሦስትነቱ ውስጥ አንድነቱ አለ።
• እነዚህ ሦስቱ አካላት በሥማቸው እና በግብራቸው አንዳቸው
ከሌላቸው ልዩ ናቸው።
አብ በአባትነቱ አብ ተብሎአል። ወልድ በልጅነቱ በልደቱ ወልድ
ተብሎአል። መንፈስ ቅዱስም ከአብ የወጣ በመሆኑ ከአብ የወጥ
( ሠራፂ) ተብሎአል።
ቤተ ክርስቲያን በጸሎቱዋ « ለአብ፥ ለወልድ፥ ለመንፈስ ቅዱስ
እሰግዳለሁ፤ አንድ ሲሆኑ ሦስት፤ ሦስት ሲሆኑ አንድ፥ በአካል ሦስት
ሲሆኑ በመለኮት አንድ ለሚሆኑ» በማለት ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ
እውነት በእምነት ትመሰክራለች። (ጸሎት ዘዘወትርን ተመልከት።
1. ቤተ ክርስቲያን ጸሎትዋ የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርቷን
የሚያመለክት ነው።
• ጸሎታችንን የምናቀርበው ወደአብ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በመንፈስ
ቅዱስ አማካኝነት ነው።
___ አባታችን ሆይ ብለን እንጸልያለን።
___ በእንድ ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ብለን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ
ስም እንጸልያለን።
___ በመንፈስ ቅዱስ ተመልተንና ተመርተን እንጸልያለን።
1. ቤተ ክርስቲያን ሕይወቷ ምሥጢረ ሥላሴን የሚያመለክት ነው።
• ምሥጢረ ሥላሴ የሚያስተምረን የመጀመሪያው እውነት የእኛ ማንነት
ያለው ከክርስቶስ አካል ጋር ባለን ሕይወት እንጂ በግለኝነት በሚኖረን
ሕይወት አይደለም።
• ሁለተኛው ትምህርት እግዚአብሔር ፍቅር ነው። የእግዚአብሔር
ፍቅርም በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ መካከል እንዲሁም ለፍጥረቱ
በሙሉ እግዚአብሔር ባለው ፍቅር ታይቶአል። ይህ ፍቅር በሥላሴ
የምናምን እኛም ለፍጥረት ሁሉ ፍቅርን እንድገልጥ ያስተምረናል።
ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ስጡ
1. ጸሎተ ሃይማኖት በስንት ዓ. ም ተወሰነ?ለምንስ ጸሎተ ሃይማኖት
ተባለ? ሌላ ስሙስ ማን ይባላል?
2. የጸሎተ ሃይማኖት አከፋፈል እንዴት ነው?
3. እምነት በሕይወታችን ውስጥ ምን ዓይነት ፍሬ ያፈራል?
4. ስለ ምሥጢረ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
5. ስለ እግዚአብሔር ወልድ ወይም ስለእግዚአብሔር ቃል በተብራራ
መልኩ የምናገኘው በየትኛው ወንጌል ነው። ምዕራፍና ቁጥር ጥቀሱ።
6. ሥላሴን መርምረን በምልዓት ልንረዳ እንችላለን ወይ? አብራሩ።
5
3 Shares
Like
Comment
Share

Sunday, December 13, 2020

Useful Bible Studies > 1 Corinthians Commentary > chapter 15

Be careful about your friends

1 Corinthians 15:33-34

We have seen that the Christians in Corinth were doing many wrong things. Let us think about the cause of this wrong behaviour.

Clearly, the basic cause was wrong attitudes. Those Christians cared too much about their own desires, their own feelings, and their own gifts. That is, they cared too much about themselves. That was why they were not showing love towards each other. The result was that they were not obeying God.

Clearly, those wrong ideas did not come from their knowledge of God. The Bible did not teach them to do such things. There had to be another cause, and in 1 Corinthians 15:33, Paul mentions that cause. Those Christians had chosen friends who were evil.

We may ask whether Paul has mentioned this problem earlier. Perhaps he has. In 1 Corinthians 8:10, he said that they were joining people from evil religions, to eat together. In 1 Corinthians 1:18-23, he urged them not to care whether other people approved of them.

However, perhaps these wrong friends were other church members, who belonged to the powerful groups in their church (1:11-13). These groups were causing the Christians to argue fiercely, and even to take other Christians to the judges (3:3; 6:6).

The people who had no knowledge of God in 1 Corinthians 15:34 were church members. Otherwise, there would be no reason for the Christians to be ashamed. Perhaps those people knew about God, but they knew nothing about his character. They had not learned from him how they should live.

It is not wrong to have friends who do not know God (10:27). However, it is very wrong and foolish for a Christian to copy their evil behaviour.

Next part: How can a dead body live again? (1 Corinthians 15:35-36)

 

Please use the links at the top of the page to find our other articles in this series. You can download all our articles if you go to the download page for our free 450 page course book.

 

© 2014, Keith Simons.

 

"# ፍቅርህ # Yared Maru Remix "" Protestant Mezmur #

መስቀልን ለምኑ ያሉን ዶክተር ዘበነ ልመናቸውን የሚያቀርቡት ወደማን ነው ወደ መስቀሉ ወይንስ ወደ እግዚአብሔር መ...

Tuesday, December 8, 2020


 

 ግሩም ምክር ነው እባካቹ አንብቡት ትጠቀሙበታላቹ

========
"ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡
እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች፡፡ በአስራ ስምንተኛዉ ወር ዉሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት “እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርጉዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡
ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነዉ ልጅ በልጅ ሆኛለሁ፡፡ አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ...ችግር አለ??”
ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታዉቂልኝ የምፈልገዉ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡
ልወልድ የምችለዉ በሁለት አመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል...የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ሃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ነዉ”
የዚህ አጭር ተረት መሰል ታሪክ ጭብጡ፡
ሰዎች ለጥያቄዎቻቸዉና ለጸሎቶቻቸዉ መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ፡፡ በሌሎች ምስክርነት አትቅና፡፡
የራስህን የጸሎት መልስ ካላገኘህ ዉስጥህ አይሰበር ይልቅ ለራስህ እንዲህ በለዉ "ጊዜዬ እየደረሰ ነዉ ተወልዶ መሬት የረገጠ እለት ሰዎች በአድናቆት የተወለደዉን ይመለከቱታል " እናም እግዚአብሔርን እንጠብቅ በጊዜው ውብ አድርጎ ይሰራዋል የተናገራችሁን ፣ የገባላችሁን ኪዳን አካል ለብሶ እስክታዩ ድረስ የእግዚአብሔርን ጊዜ ጠብቁ።"
(የወንጌል ድምፅ)
25
7 Shares
Like
Comment
Share

Tuesday, December 1, 2020

 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለመልአኩ ዜና ብስራት በሰጠችው ቃለ ተአምንሮ ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር ከጥንት ያሰበውና የፈቀደው ያድህነተ ዓለም ሥራ እንዲፈጸምና አማናዊ እንዲሆን አድርጋለች :: ይህም ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ታላቅ ሱታፌ በጉልህ ያሳያል :: ይህንን ምሥጢር በተመለከተ ኢትዮጵያዊው ሊቅ በድርሰቱ "" ዘበቃለ ጉሕሎቱ ለሰይጣን መልአክ ስሕተት ተሰፍሐ ግላ ጽልመት ውስተ ኩሉ ዓለም :ወበቃለ ብሥራቱ ለገብርኤል መልአክ ጽድቅ ተሰፍሐ ብርሀነ ሕይወት ውስተ ኩሉ ዓለም : የስሕተት አለቃ በሆነው በሰይጣን የክፋትና የጥፋት ቃል ምክንያት የጨለማ መጋረጃ በዓለም ሁሉ እንደተዘረጋ : የእውነት መልአክ በሆነው በቅዱስ ገብርኤል የምሥራች ቃል ደግሞ የሕይወት ብርሀን በዓለም ሁሉ ተዘረጋ በማለት መስክሯል :: ኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም እመቤታችን በነገረ ድህነት ውስጥ ያላትን ልዩ ሥፍራ ሲናገር "" በእንተ ተሠግዎቱ ለወልደ አምላክ እምኔኪ ቀሩባነ ኮነ እምድር ውስተ አርያም :ብኪ ወበከመ ወልድኪ "" ብሏል :: የዚህ ኃይለ ቃል ትርጉዋሜ ምሥጢርም ቃለ እግዚአብሔር ወልድ ከሥጋሽ ሥጋ :ከነፍሥሽ ነፍስን ነሥቶ ካንቺ ሰው በመሆኑ ከምድር ወደ ሰማይ :ከሞት ወደ ሕይወት : ከመርገም ወደ በረከት : ከኃሳር ወደ ክብር : ከሲኦል ወደ ገነት የተሸጋገርንብሽ ማለት ነው :: ከላይ የተጠቀሰውን በቃዲምት ሔዋንና በዳግሚተ ሔዋን መካከል ያለውን ምሥጢራዊ ንጽጽር አስመልክቶ


'' ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ ""በመባል የሚታወቀው ሊቁ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲገልጽ "" ለእመ ኃሠሥላ ለሔዋን ትረክባ በህየ እንዘ ትትፌሣሕ በወለታ ዘእምጽአት ፈውሰ ለቁስሊሀ : ለእመ ኃሠሦኮ ለአዳም ረክቦ በህየ እንዘ ይትፌሣሕ ወይገብር በዓለ ምስለ ዳግማዊ አዳም "" በማለት በንጽጽሩ ውስጥ ያለውን ጥልቅና ረቂቅ ምሥጢረ ድህነት አስተምሯል :: እንደ ሊቁ አገላለጽ ዳግሚት ሔዋን የተባለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍሬ ሕይወት ወመድኃኒት የሆነው ጌታ የተገኘባት አማናዊት ዕጸ ሕይወት በመሆኗ የዕጸ በለስን ፍሬ በልታ ሞትን ላመጣችብን ለቀዳሚቷ ሔዋን ካሣ ናት :: ምክንያቱም ከዳግሚት ሔዋን ከድንግል ማርያም የተወለደው የማኅጸኗ ፍሬ ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሚያርቅ :በረከተ ሥጋ :በረከተ ነፍስን የሚያድል ሕይወተ ሥጋን ሕይወተ ነፍስን የሚሰጥ : ቀዳሴ ሥጋ ወነፍስ ወመንፈስ የሆነ ቡሩክ አምላክ ነውና ::


††† አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በአምስት ሺ አራት መቶ ሰማንያ አምስት ዓመት ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ ኢያቄም ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7)
"ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ:: (ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ )

ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለሦስት ዓመታት ቆይታ ወደ ቤተ መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለአሥራ ሁለት ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና እያገለገለች: እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ: ጽዋዕ ሰማያዊ እየመገቧት ኑራለች:: አሥራ አምስት ዓመት በሞላት ጊዜ ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::
በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማኅጸንዋ ጸነሰችው:: ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር: ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ:: (ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ለብሐዊ)
ወልደ እግዚአብሔርን ለዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ጸንሳ: እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14) "ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በናዝሬት ገሊላ ለሁለት ዓመታት ቆዩ::
ይህንን
አስመልክቶ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው ላይ ሲናገር ‹‹በእንተ
ሔዋን ተዐፅወ ኆኃተ ገነት ወበእንተ ማርያም ድንግል ተርኃወ ለነ
ዳግመ›› በቀዳሚት ሔዋን ምክንያት የገነት ደጃፍ ተዘጋብን
ዳግመኛም ሰለዳጋሚት ሔዋን ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን
በማለት አስገንዝቧል፡፡

ይህንንም ምሥጢር ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አሞንዮስ
አውሳቢዮስ በቅድመ ወንጌል ሲገልጡ ‹‹ወበከመ ተኃብአ ሰይጣን
በጉሕሉቱ ውስተ ሥጋ ከይሲ ከማሁ ኮነ ድኅነትነ በተሰውሮተ ቃል
እግዚአብሔር በዘመድኀ›› ሰይጣን በስጋ ከይሲ ተሰውሮ አዳምን
እንዳሳተው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስም በሥጋ
ብእሲ ተሰውሮ መጥቶ አለምን እንዳዳነ፡፡ (ትርጓሜ ወንጌል ገፅ
28) በማለት ተናግረዋል

በቀዳሚት ሔዋንና በዳግሚት ሔዋን መካከል ያለውን ምስጢራዊ
ንጽጽር አስመልክቶ ‹‹ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ›› በመባል
የሚታወቀው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲገልጽ ዳግሚት ሔዋን
የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍሬ የሕይወት
መድኃኒት የሆነው ጌታ የተገኘባት አማናዊት ዕፀ ሕይወት በመሆኗ
የዕፀ በለስን ፍሬ በልታ ሞትን ላመጣችብን ለቀዳሚት ሔዋን ካሣ
ናት፡፡ ምክንያቱም ከዳግሚት ሔዋን ከድንግል ማርያም
የተወለደው የማህፀኗ ፍሬ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስን የሚያርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ
ነፍስን የሚያድል ሕይወተ ሥጋ ሕይወተ ነፍስን የሚሰጥ ቀዳሴ
ሥጋ ወነፍስ (ወመንፈስ) የሆነ ብሩክ አምላክ ነውና፡፡ (አባ
ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ አርጋኖን ገጽ 328-329)፡

‹‹ተፈስሒ ኦ ቅዱስት አሞሙ ለኩሎሙ ሕያዋን ናንቀዐዱ ኃቤኪ
ትሰዕሊ በእንቲአነ›› በመንፈስ ልደት የከበሩ ቅዱሳን ሕያዋን
የሆኑበት ማየ ገቦ የተገኘብሽ የሕያዋን ፃድቃን እናታቸው ንዕድ
ክብርት እመቤታችን ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም በቅዱስ ዮሐንስ
አንጻር ልጆችሽ የምንሆን እናታችን ድንግል ማርያም ሆይ ደስ
ይበልሽ፡፡ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ
ትለምኚልን ዘንድ ዓይነ ኅሊናችንን ወደ አንቺ እናነሣለን እያሉ
ዘወትር ያከብሯታል ያመሠግኗታል ይማጸኑባታልም፡፡ (ውዳሴ
ማርያም ትርጓሜ ገጽ 58፡59)፡

ይህንን አስመልክቶ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ሲናገር "" በእንተ ሔዋን ተዐጽወ ኖኅተ ገነት ወበእንተ ማርያም ድንግል ተርኅወ ለነ ዳግመ : በቀዳሚት ሔዋን ምክንያት የገነት ደጃፍ ተዘጋብን ዳግመኛም ስለ ዳግሚት ሔዋን ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን "" በማለት አስገንባል :: ከዚህም ሌላ ሰፊና ጥልቅ በሆነው የነገረ ማርያም አስተምህሮው የዜና አበው ሊቃውንት "" የነገረ ማርያም አባት "" እያሉ የሚጠሩት ታላቁ የቤተክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ሔኔሬዎስ ከላይ የገለጥነውን ኃይለ ቃል መሠረት በማድረግ እመቤታችን "" የሔዋን ጠበቃ አለኝታ "" ብሏታል :: በዜና አበው ክፍለ ትምህርት እንደሚታወቀው ይህ አባት የነበረበት ዘመን "" የነገረ ማርያም ዘመነ ልደት "" በመባል ይታወቃል ::

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለነገር ድኅነት መሠረት መሆኗን በመግለጥ የተአምሯ መጽሐፍ "" እግዝእትነ ማርያም ነበረት እምቅድመ ዓለም በኅሊና አምላክ "" ይላል

 ወበእንተ ማርያም ድንግል ተርህወ ለነ


ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዩ ተተክለ መድኃኒት መስቀል

በእንተ ሔዋን ተዐፅወ ኆኅተ ገነት ወበእንተ ማርያም ድንግል ተርህወ ለነ ዳግመ


ድንግል ማርያም ዕፀ ሕይወት በመሆኗ የዕፀ በለስን ፍሬ በልታ ሞትን ላመጣች ለቀዳማዊት ሔዋን ካሣ ናት፡፡


ሥርዓተ ማሕሌት ዘልደት

 Print  Email

 ረከብኪ ሞገሰ መንፈሰ ቅዱሰ ወኃይለ ሰአሊ አስተምህሪ ለነ ማርያም ወልድኪ ሳህሎ ይክፍለነ ።

ኀበ ተርህወ ገነት ወሃበ ተነጽፈ እረፍት ይክፍለነ ነሃሉ ውስተ በአቶሙ ለቅዱሳን (ሦስት ጊዜ በአራራይ በል) ።