Monday, May 31, 2021
ቅዋሜ እንዲህ በጥበብ ሲገለጽ ደስ ይላል!
"አደም ፋራህ ያጫወተኝን የሶማሌ ተረት ላጫውታችሁ። ልጅቷ በሚስጥር ይዛው የነበረው ፍቅረኛዋ ለትዳር ሽማግሌ ሳይልክ በድንገት ይሞታል። ፍቅራቸው የሚስጢር ስለነበር ቀብሩ ላይ ተገኝታ ማልቀስ አልቻለችም። ትንሽ ቆይቶ አንድ ፍየላቸው ይሞትና ተመልካችን እስኪደንቅ ታለቅሳለች። እናቷ ይሄን አይተው 'ይኼ ለቅሶ ከፍየሏም በላይ ነው' አሉ ይባላል። ዛሬ በትግራይ ጉዳይ ፣ በመጪው ምርጫ አሳበው ከፍየሏ በላይ የሚጮሁ አሉ። በቅን አስበው ለሚጨነቁት አይዟችሁ ችግሩን እንፈታዋለን እንላቸዋለን ፤ ከፍየሏ በላይ ለሚጩኹት ግን የተደበቀ ፍላጎታቸው ጥቂት ቆይቶ ገሀድ ሲወጣ የምናየው ይሆናል።"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በኢትዮ ጅቡቲ ምዕራፍ - 1 አዳማ - አዋሽ የፍጥነት መንገድ ማስጀመርያ መርሀ ግብር ላይ ከተናገሩት ።
Sunday, May 30, 2021
Saturday, May 29, 2021
Friday, May 28, 2021
Thursday, May 27, 2021
Wednesday, May 26, 2021
Tuesday, May 25, 2021
Monday, May 24, 2021
Sunday, May 23, 2021
Saturday, May 22, 2021
ድርሳነ ጽዮን ማርያምና ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ"
ለምን እንደሆነ ባላውቅም አንዳንድ የኦርቶዶክስ ጥንታዊ ድርሳናት በፁሁፎቻቸው በግልፅ ነብዩ ሙሐመድን "ﷺ" መሳደብ የተለመደ አድርገው ይመለከቱታል። መጽሀፍቶችን በግሌ ማጥናት ከመጀመሬ ከሶስትና ከአራት አመት በፊት ሰው ነግሮኝ ቢሆን በዚህ ደረጃ ድፍረት ይኖራቸዋል ብየ ማመን የሚቸግረኝን ፁሁፎች አይቸ ደንግጫለሁ። የምወደው የፌስቡክ ወንድሜ ቢላል ሀበሽ ጋር በመሆን ከአራት አመት በፊት ከመቶ በላይ የተለያዩ የተቀባይነት ደረጃ ያላቸውን የቀኖና ገድላትና ድርሳም መጽሀፍትን በሶፍት ኮፒ ከተለያዩ ኦርቶዶክሶች በማግኘት ማጥናት ከጀመርን በኃላ ግን ማመን የማንችላቸውን ብዙ ትርክቶች ማስተዋል ጀመርን። በመሀሉም አንድ ራሱን የቻለ ቴሌግራም ከፍተን የምናገኛቸውን ፁሁፎች ከአስተያየታችን ጋር ለሌላው አስተማሪ እንዲሆን ማስፈር ጀመርን (ቻናሉን በዚህ ሊንክ ያገኙታል t.me/orthox ) የማልረሳውና ከሁሉም በላይ ያሳመመን የነበረው ግን አንድ ስለ ነብዩ "ﷺ" በአስፀያፊ መልኩ የሚያወራውን ክፍል ነበር። ሰው የጥላቻ ደረጃው ምን ያክል በዚያ መልኩ ቢገን ነው በሳቸው ላይ እንዲያ አይነት ነውር ፈጥሮ የሚቀጥፈው? የሚለው ግን ሁሌ ይገርመኝ ነበር። ለማንኛውም ያንን ከመንፈሳዊ ድርሳን የማይጠበቅ አስፀያፊ ታሪክ ወደናንተ አላመጣውም። ዛሬ ከዚያ ውጭ እሳቸውንና አንድ የሳቸውን ተከታዮች አስመልክቶ የሚያወራ አስቂኝ ተረት ግን አካፍላችኃለው።
በእናቶቻችን የቡና አጠጣጥ የምናውቃቸው አቦል፣ ቶና እና የበረካ ስያሜዎች በሀገራችን ደብተራዎች ድርሰት በሆነው በድርሳነ ጽዮን ማርያም ውስጥ በነብዩ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم የሚያምኑ ሙስሊሞች ናቸው ተብለው እናገኛቸዋለን። ነብዩ ሙሐመድም "ﷺ" ቡና እየጠጡ ይሰግዱ ነበር ብሎ ግልፅ ያለ ቅጥፈት ያስነብበናል።
ከፁሁፎች ውስጥ የሚከተሉትን ንግግሮች እናገኛለን፦
"ሁለተኛ ፀሎት
1 የሰማያዊት እናታችን ፅዮን ተአምር ይህ ነው ጸሎቷና በረከቷ ከሁላችን የጥምቀት ልጆች ጋር ይሁን ዛሬም ዘውትርም ለዘልአለሙ ይደረገውልን
2 መሐመድም እፀ ኩስራ የተባለችውን ቡናን በሚያፈላና በሚሰግድ ጊዜ ፍርቃን የተባለውን መፅሐፍ ከመውደዱ የተነሳ ዲያብሎስ ወደሱ ይመጣና በምዕራፍ 28 ላይ የሚገኘውን ቃላት ጻፈው ነገር ግን እንዳያነቡት አጠረው ወገኖችህ የታጠረውን እንዳያነቡት የታጠረውን አታንብቡ ሌላ ያልታጠረውን ግን አንብቡ ብለህ አስተምራቸው ይለዋል"
ከላይ ባየነው ፁሁፍ ውስጥ እንግዲህ አስቡት ነብዩ "ﷺ" ቡና እያፈሉ ይሰግዱ ነበር ይለናል
ለዚህ ፀሀፊው ስለ ማስረጃ የሚጠይቀው አማኝ ስለሌለው ነብዩ ﷻ ስለነበሩበት የበረሀ ምድርና ስለአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ እንኳን ሳያጠራ እንዲሁ መንጋው ላይ ይጫወትበታል። የቡና አፈላልን የተከተለው ዘየ በዚያ ጊዜ እንደነበረ እንኳን የሚገልፅ ምንም አይነት ሀይማኖታዊም ታሪካዊም ሰነድ የለም። ደብተራው ምን አስጨንቆት? ሰፈሩ ላይ ያየው አንድ ሙስሊም ካናደደውም ከመሬት ተነስቶ ይፅፈዋል። ማን ከልካይ አለበት?
ወደ ኢትዮጵያ ቡና እንዴትእንደገባ ሲተርክ ደግሞ እንዲህ ይለናል።
7 ወደ ኢትዮጵያ እንዴት እንደመጣ እንነግሯቹኃለን በመሐመድ ስርዓትና ህግ የሚጓዙ #አቦልና #ቶና #በረካ #የሚባሉ #ሶስት ሰዎች ለንግድ የመጡ መስለው ከአምስት መተንብላን (ከአማኞች) ጋር እነዚህን ዕፅዋት ይዘው ይመጣሉ እነዚህ ሶስት ዕፅዋት #ጫትና #ቡና #ጥንባሆ አህዛብ ለሰይጣን የሚያቀርቧቸው የጣኦት መሰዋት ናቸው
8 ለክርስቲያን ግን እነዚህን መብላት መጠጣት አይገባም እነዚህን #የበሉና #የጠጡ #ካልተጠመቁ #ሰዎች #ጋር #በገሀነም #ይፈረድባቸዋል መፅሐፍ የተናገረውን አልሰማችሁም በአምሳሉ እግዚአብሔር የፈጠረው የመጀመሪያው አዳም አትብላ የተባለውን ክፉ እፀ በለስ በልቶ ከልብስ ብርሀሰን እንደተራቆተና ከተድላ ገነት ወጥቶ የፍዳ የመርገም የፍርሃት የስቃይ ቦታ ወደምትሆን ወደዚህች ምድር ተሰደደ ክፉዎች እፅዋትና መልካሞች ዕፅዋት እንዳሉ ጌታችን በወንጌል ነግሮናል እነዚህን ዕፅዋት በመብላት በመጠጣት አትሳቱ ይህንም አድርጋችሁ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሔዳችሁ አታርክሱ
ከላይ ያነብብነው ፁሁፍ የሚገኘው "ድርሳነ ጽዮን ማርያም" በሚል በሀገራችን ደብተራዎች የተደረሰ ባዶ ተረት ውስጥ ነው። ማንም ህሊና ያለው ሰው እንደሚረዳው ታሪኩ ከአለማት ሴቶች የተመረጠችውን ንፁህ ሴት ማርያምን ፈጽሞ አይወክልም። እነዚህ ደብተራ ፀሀፊዎች ባገኙት አጋጣሚ ለኢስላምና ለአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم ያላቸውን ጭፍን ጥላቻ በዚህ አይነት በሬ ወለደ ተረት ይገልፁታል። አማኙ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ የማርያምን ስም በማከናነብ እሷ እንደተናገረችው አድርገው ያቀርቡታል። የዋሁ ህዝብ ደግሞ "ቃለ ህይወት ያሰማልን እልልልል" ብሎ ከመቀበል ውጭ ሊጠይቃቸው ይፈራል።
አሏህ ﷻ ሒዳያውን ይስጣችሁ..!
______
ተጨማሪ ንጽጽራዊ ትምህርቶችን ለመከታተል
❐ ዩቲዩብ || http://bit.ly/2ZPzYTI
❐ ቴሌግራም || t.me/yahya5
❐ ፌስቡክ || http://bit.ly/2QYG9CV
❐ ድረ ገጽ || www.ethio-islamic.org
ለምን እንደሆነ ባላውቅም አንዳንድ የኦርቶዶክስ ጥንታዊ ድርሳናት በፁሁፎቻቸው በግልፅ ነብዩ ሙሐመድን "ﷺ" መሳደብ የተለመደ አድርገው ይመለከቱታል። መጽሀፍቶችን በግሌ ማጥናት ከመጀመሬ ከሶስትና ከአራት አመት በፊት ሰው ነግሮኝ ቢሆን በዚህ ደረጃ ድፍረት ይኖራቸዋል ብየ ማመን የሚቸግረኝን ፁሁፎች አይቸ ደንግጫለሁ። የምወደው የፌስቡክ ወንድሜ ቢላል ሀበሽ ጋር በመሆን ከአራት አመት በፊት ከመቶ በላይ የተለያዩ የተቀባይነት ደረጃ ያላቸውን የቀኖና ገድላትና ድርሳም መጽሀፍትን በሶፍት ኮፒ ከተለያዩ ኦርቶዶክሶች በማግኘት ማጥናት ከጀመርን በኃላ ግን ማመን የማንችላቸውን ብዙ ትርክቶች ማስተዋል ጀመርን። በመሀሉም አንድ ራሱን የቻለ ቴሌግራም ከፍተን የምናገኛቸውን ፁሁፎች ከአስተያየታችን ጋር ለሌላው አስተማሪ እንዲሆን ማስፈር ጀመርን (ቻናሉን በዚህ ሊንክ ያገኙታል t.me/orthox ) የማልረሳውና ከሁሉም በላይ ያሳመመን የነበረው ግን አንድ ስለ ነብዩ "ﷺ" በአስፀያፊ መልኩ የሚያወራውን ክፍል ነበር። ሰው የጥላቻ ደረጃው ምን ያክል በዚያ መልኩ ቢገን ነው በሳቸው ላይ እንዲያ አይነት ነውር ፈጥሮ የሚቀጥፈው? የሚለው ግን ሁሌ ይገርመኝ ነበር። ለማንኛውም ያንን ከመንፈሳዊ ድርሳን የማይጠበቅ አስፀያፊ ታሪክ ወደናንተ አላመጣውም። ዛሬ ከዚያ ውጭ እሳቸውንና አንድ የሳቸውን ተከታዮች አስመልክቶ የሚያወራ አስቂኝ ተረት ግን አካፍላችኃለው።
በእናቶቻችን የቡና አጠጣጥ የምናውቃቸው አቦል፣ ቶና እና የበረካ ስያሜዎች በሀገራችን ደብተራዎች ድርሰት በሆነው በድርሳነ ጽዮን ማርያም ውስጥ በነብዩ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم የሚያምኑ ሙስሊሞች ናቸው ተብለው እናገኛቸዋለን። ነብዩ ሙሐመድም "ﷺ" ቡና እየጠጡ ይሰግዱ ነበር ብሎ ግልፅ ያለ ቅጥፈት ያስነብበናል።
ከፁሁፎች ውስጥ የሚከተሉትን ንግግሮች እናገኛለን፦
"ሁለተኛ ፀሎት
1 የሰማያዊት እናታችን ፅዮን ተአምር ይህ ነው ጸሎቷና በረከቷ ከሁላችን የጥምቀት ልጆች ጋር ይሁን ዛሬም ዘውትርም ለዘልአለሙ ይደረገውልን
2 መሐመድም እፀ ኩስራ የተባለችውን ቡናን በሚያፈላና በሚሰግድ ጊዜ ፍርቃን የተባለውን መፅሐፍ ከመውደዱ የተነሳ ዲያብሎስ ወደሱ ይመጣና በምዕራፍ 28 ላይ የሚገኘውን ቃላት ጻፈው ነገር ግን እንዳያነቡት አጠረው ወገኖችህ የታጠረውን እንዳያነቡት የታጠረውን አታንብቡ ሌላ ያልታጠረውን ግን አንብቡ ብለህ አስተምራቸው ይለዋል"
ከላይ ባየነው ፁሁፍ ውስጥ እንግዲህ አስቡት ነብዩ "ﷺ" ቡና እያፈሉ ይሰግዱ ነበር ይለናል
7 ወደ ኢትዮጵያ እንዴት እንደመጣ እንነግሯቹኃለን በመሐመድ ስርዓትና ህግ የሚጓዙ #አቦልና #ቶና #በረካ #የሚባሉ #ሶስት ሰዎች ለንግድ የመጡ መስለው ከአምስት መተንብላን (ከአማኞች) ጋር እነዚህን ዕፅዋት ይዘው ይመጣሉ እነዚህ ሶስት ዕፅዋት #ጫትና #ቡና #ጥንባሆ አህዛብ ለሰይጣን የሚያቀርቧቸው የጣኦት መሰዋት ናቸው
8 ለክርስቲያን ግን እነዚህን መብላት መጠጣት አይገባም እነዚህን #የበሉና #የጠጡ #ካልተጠመቁ #ሰዎች #ጋር #በገሀነም #ይፈረድባቸዋል መፅሐፍ የተናገረውን አልሰማችሁም በአምሳሉ እግዚአብሔር የፈጠረው የመጀመሪያው አዳም አትብላ የተባለውን ክፉ እፀ በለስ በልቶ ከልብስ ብርሀሰን እንደተራቆተና ከተድላ ገነት ወጥቶ የፍዳ የመርገም የፍርሃት የስቃይ ቦታ ወደምትሆን ወደዚህች ምድር ተሰደደ ክፉዎች እፅዋትና መልካሞች ዕፅዋት እንዳሉ ጌታችን በወንጌል ነግሮናል እነዚህን ዕፅዋት በመብላት በመጠጣት አትሳቱ ይህንም አድርጋችሁ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሔዳችሁ አታርክሱ
ከላይ ያነብብነው ፁሁፍ የሚገኘው "ድርሳነ ጽዮን ማርያም" በሚል በሀገራችን ደብተራዎች የተደረሰ ባዶ ተረት ውስጥ ነው። ማንም ህሊና ያለው ሰው እንደሚረዳው ታሪኩ ከአለማት ሴቶች የተመረጠችውን ንፁህ ሴት ማርያምን ፈጽሞ አይወክልም። እነዚህ ደብተራ ፀሀፊዎች ባገኙት አጋጣሚ ለኢስላምና ለአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم ያላቸውን ጭፍን ጥላቻ በዚህ አይነት በሬ ወለደ ተረት ይገልፁታል። አማኙ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ የማርያምን ስም በማከናነብ እሷ እንደተናገረችው አድርገው ያቀርቡታል። የዋሁ ህዝብ ደግሞ "ቃለ ህይወት ያሰማልን እልልልል" ብሎ ከመቀበል ውጭ ሊጠይቃቸው ይፈራል።
አሏህ ﷻ ሒዳያውን ይስጣችሁ..!
______
ተጨማሪ ንጽጽራዊ ትምህርቶችን ለመከታተል
❐ ዩቲዩብ || http://bit.ly/2ZPzYTI
❐ ቴሌግራም || t.me/yahya5
❐ ፌስቡክ || http://bit.ly/2QYG9CV
❐ ድረ ገጽ || www.ethio-islamic.org
See Less
11
Friday, May 21, 2021
Thursday, May 20, 2021
Wednesday, May 19, 2021
Tuesday, May 18, 2021
Sunday, May 16, 2021
"ጣውላ በሚስማር ተማረረና ወጋኸኝ እኮ ቢለው ራሴ ላይ የሚያርፈውን መዶሻ ብታይ አይዞህ ትለኝ ነበር" አለው ይባላል።

ጥያቄ ነው..........
እንደ ዶክተር አብይ በውስጥና በውጪ ጠላቶች ተከቦም ቢሆን በቆራጥነት የሚሰራ፣ ስራ ጀምሮ የሚጨርስ፣ የማይዘርፍ፣ ሆደ ሰፊ፣ ዘረኛ ያልሆነ፣ በዲሞክራሲ የሚያምን፣ ሰው የመናገር መብት አለው ብሎ የሚያምን፣ በውጪ ሀይሎች የማይጠመዘዝ፣ ባለራዕይ መሪ፣ አገሩን የሚወድ፣ የማይወላውል፣ ለሀገርና ለህዝብ ስጋት የሆኑ ትዕቢተኞችን እንደሁኔታው እያየ የሚያስተነፍስ....ወዘተ መሪ ካለ ጠቁሙኝና እኔም ዶክተር አብይን ልክዳው። ካልሆነ ግን ለሀገርና ለህዝብ የምታስብ ከሆነ ከጎኑ ሆነህ አግዘው፣ እርዳው የመዶሻውን ሳታይለት ጣውላ ሆነህ አትውቀሰው።
Via tilahun tadesse
ቴሌግራም ላይ በዚ ይቀላቀሉን
2020
1 Comment
8 Shares
Like
Comment
Share
Saturday, May 15, 2021
Friday, May 14, 2021
Thursday, May 13, 2021
Wednesday, May 12, 2021
Tuesday, May 11, 2021
Sunday, May 9, 2021
Saturday, May 8, 2021
Thursday, May 6, 2021
መጽሐፈ ሲራክ
Jump to navigationJump to search
መጽሐፈ ሲራክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ከብሉይ መጻሕፍት የሚፈረጅ ነው። ለማንበብ እታች ይጫኑ።
«እግዚአብሔር መድኃኒትን ከምድር ፈጥሯልና አዋቂ ሰው ባለ መድኃኒትን አይንቀውም። ታምራቱን ያወቁ ዘንድ ውሃ በእንጨት የጣፈጠ አይደለምን? በታምራቱ ይከበሩ ዘንድ እግዚአብሔር ለሰዎች ጥበብን ሰጣቸው። በመድኃኒቱ ያድናቸዋል በሽታቸውንም ያርቅላቸዋል። በሚያድኑ ገንዘብ ከነሳቸው መድኃኒት ያደርጋሉ እሱም ለሀገር ፍቅርን ያመጣል።» ፴፰፡፬-፰።
እግዚአብሐር ፈጠረ ሥራያተ እምነ ምድር ወብእሲሰ ጠቢብ ኢይሜንኖ። አኮኑ ብዕፅ ጥዕመ ማይ ከመ ያእምሩ ኅይሎ። ወውእቱ ወሀቦሙ ለእጓለ እምሕያው ጥበበ፤ ከመ ይከበሩ በሰብሐቲሁ። ወቦቱ ይፌውሶሙ ወያሴስል ኲሎ ሕማሞሙ። እምውስቴቱ ይገብሩ ሥራያተ በዘ ይፌውሱ ወውእቱ ያመጽእ ስላመ ለብሔር።
የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ [1] በመጫን የመጽሐፉን ገጾች ማንበብ ይችላላሉ
የተዋህዶ ልጅ
አዋልድ መጻሕፍት በመጽሐፍ ቅዱስ
✍ የተሃድሶ መናፍቃን አዋልድ መጻህፍትን አይቀበሉም መጽሐፍቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት እንዳላቸውም አይቀበሉም እንደውም እንደ ልብ ወለድ ድርሰቶች ቆጥረውት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ይሳለቃሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ግን መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርጋ አዋልድ መጻሕፍትን ትቀበላለች እስቲ ለተሃድሶ መናፍቃኑ ምላሽ ይሆን ዘንድ አዋልድ መጻሕፍትን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንመልከት።
✞ "አዋልድ መጻሕፍት" የሁለት ቃላት ጥምር ውጤት ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ "የመጻሕፍት ልጆች" ማለት ነው መጻሕፍት የተባሉትም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተለይተውና ተቆጥረው የምናውቃቸው ሰማንያ አንዱ መጽሐፍተ ብሉያተና ሐዲሳት ናቸው አዋልድ መጻህፍት የአስራው መጻሕፍት ምስጢር ትርጓሜ ተብራርቶ የሚገኝባቸው መጻሕፍት ናቸው ቅዱሳን ነቢያት እንዲሁም ሐዋርያት፤ በየዘመናቱ የተነሱ መምህራንና ሊቃውንት አዋልድ መጻሕፍት መጠቀማቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል መጽሐፍ ቅዱስን ለማብራራት አዋልድ መጽሐፍት አስፈላጊ ናቸውና።
✞ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ነገር የሚናገሩ መጻሕፍትን ቁጥር አልገደበም እንደውም በ 2ኛ ጢሞ 3፥15-16 ላይ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። ነው የሚለው እነዚህ የቅዱስ ጳውሎስ ትምህርቶች ስለ መጻሕፍቱ መመዘኛ እንጂ ቁጥር አይነግሩንም ቅዱስ ጳውሎስ "የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ" አለ እንጂ ይህንን ያህል መጽሐፍ አላለም።
☞ መጽሐፍ ቅዱስ ሌሎችንም ቅዱሳት መጻሕፍት እንድናነብ መክሮናል እስራኤል ወደ ከነዓን ሲጓዙ በእግዚአብሔር ረዳትነት ከአሕዛብ ጋር ያደረጓቸውን ጦርነቶች የያዘ "የእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ" የሚባል መኖሩን ሙሴ በዘኁ 21፥14 ላይ ነግሮናል።
☞ ኢያሱ ፀሐይን አቁሞ፣ ጨረቃን አዘግይቶ አሕዛብን የረታበት ድንቅ ታሪክ የተጻፈበት "የያሻር መጽሐፍ" የሚባል አለ ይህም ☞በኢያ 10፥13 ላይ ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም። ተብሎ ተጽፎልናል እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በዚህ በያሻር መጽሐፍ የዳዊት መዝሙርም ተጽፎአል ☞ በ2ኛ ሳሙ 1፥17 ላይ ዳዊትም ስለ ሳኦልና ሰለ ልጁ ስለ ዮናታን ይህን የኀዘን ቅኔ ተቀኘ፥ የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ፥ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፎአል።
☞ የእስራኤል የነገስታት ታሪክ መጽሐፍ /2ኛ ነገ 1፥18/፣ የይሁዳ ነገስታት ታሪክ መጽሐፍ /2ኛ ነገ 8፥23/፣ የሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ /1ኛ ነገ 11፥41/፣ የሚባሉ አያሌ መጻሕፍት መኖራቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ይመሰክራል መኖራቸውን ብቻ ሳይሆን የቀረውንም ታሪክ ከእነዚህ መጻሕፍት እንድናነብም ይጋብዘናል።
☞ ሐዋርያው ይሁዳም በኦሪት ዘዳግም የማናገኘውን የሙሴን ታሪክ "ዜናሁ ለሙሴ" ከሚባለው መጽሐፍ ወስዶ ነግሮናል ከሰማንያ አንዱ አሥራው መጻሕፍት ውጪ ያሉት መጻሕፍትን መቀበል የማይገባን ቢሆን ኖሮ ሐዋርያው ይሁዳ "ዜናሁ ለሙሴ" ከተሰኘው መጽሐፍ ባልጠቀሰ ነበር በይሁ 1፥8 ላይ።
✍ አዋልድ መጻሕፍት ጌታችን ለሐዋርያት የገባው ቃል ኪዳን አማናዊ መሆኑን የሚመሰክሩ ናቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለሐዋርያት በማቴ 28፥20 ላይ "እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ" ብሏቸዋል ይህ ማለት ግን ሐዋርያት እስከ ዓለም ፍጻሜ ይኖራሉ ማለት ሳይሆን ለሐዋርያት የተሰጠው ጸጋ እስከ ዓለም ፍጻሜ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ይቀጥላል በእነርሱ እግር የሚተኩትም የጸጋው ተሳታፊ፣ የክብሩ ባለቤት ይሆናሉ ማለት ነው እንጂ ታዲያ ለሐዋርያት የተሰጠው ክብር፣ ጸጋና በረከት እስከ ዓለም ፍጻሜ ከቤተ ክርስቲያን ጋር መሆኑን ከምናረጋግጥባቸው መንገዶች አንዱ በቅዱሳት መጻሕፍት በተጻፉት የቅዱሳን ታሪኮችና ሥራዎች ነው።
✍ በሐዋርያት ዘመን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በ90 ዓ/ም አካባቢ በተጻፈው በዮሐንስ ራእይ የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ላይ ያበቃል ከዚያ በኃላ በወንጌል አምነው፣ በሐዋርያት እግር ተተክተው የተጓዙት የቤተ ክርስቲያን ልጆች ታሪክና ተጋድሎ የት ይገኛል? በአዋልድ መጻህፍት ነው።
✍ እነ ልበ አምላክ ዳዊት፣ እነ ምናሴ፣ እነ ሕዝቅኤል፣ እነ ዳንኤል፣ ሐና፣ ሰሎሞን... የጸለዩት ጸሎት ለእነርሱ ዋጋ በማሰጠቱ፣ እግዚአብሔርም ስለ ተቀበላቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል እግዚአብሔር ጸሎታቸውን የተቀበላቸው የሌሎች ቅዱሳት እናቶችና ቅዱሳን አባቶች ጸሎት ተጽፎ ምእመናን ቢጠቀሙበት እንዴት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ይሆናል?
✍ ዛሬ የተሃድሶ መናፍቃኑ ለስም የሚቀበሏቸው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን መጻሕፍት ቅድስና አረጋግጣ፣ አማናዊ መሆናቸውን ፈትና፣ በጉባኤ የወሰነችው ቤተ ክርስቲያን ናት እኛም ኦርቶዶክሳውያን እነዚህን መጻሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አድርገን የተቀበልናቸው እርሷ በጉባኤያቷ ወስና ስለሰጠችን ነው ታዲያ የተሃድሶ መናፍቃኑ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን የሰጠችንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከተቀበሉ እርሷ የሰጠችንን ሌሎች መጻሕፍትስ ለምን አይቀበሉም??? መልስ የሌለው ጥያቄ።
✞ ብቻ የተሃድሶ መናፍቃኑን ልብ ሰጥቶ ወደ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን ይመልስልን!!! አሜን!!! ✞

·
Subscribe to:
Posts (Atom)