Friday, December 20, 2019

የዘመኗ ቤተክርስቲያን መልክ

የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁንን :: ዛሬ በፊታችሁ ይህንን ርዕስ ወደ እናንተ ይዤ የቀረብኩበትን ምክንያት እንደሚከተለው አብራራለሁ :: የዘመኗ ቤተክርስቲያን መልክ የሎጥና የአብርሃም ዘመን መልክ እየሆነ ከመጣ ሰንበትበት ብሎአል :: እንዴት ለሚለው ጥያቄ ምላሼን እነሆ ብያለሁና ተከታተሉኝ ::
ሎጥና አብርሃም በመጽሐፍቅዱሳችን ቃል መሠረት ዘመዳሞችና ሎጥም የአብርሃም የወንድሙ ልጅ እንደሆነ ከቃሉ እናነባለን ኦሪት ዘፍጥረት 12 : 5 :: ይሁን እንጂ አብራም የእግዚአብሔር ጥሪ ደርሶት ከሀገሩና ከዘመዶቹ ተለይቶ በወጣ ጊዜ ሎጥ አብሮት አልተጠራም ፣ ማለትም የእግዚአብሔር ጥሪ አልደረሰውም ፣ እንዲሁ አብርሃምን ተከትሎ የወጣ መሆኑን አሁንም ቃሉ በግልጥ ይነግረናል ኦሪት ዘፍጥረት 12 ፥ 4 ፤ ኦሪት ዘፍጥረት 13 ፥ 1 :: ታድያ በእግዚአብሔር ተጠርቶ የወጣው አብራም በከብት ፣ በብርና በወርቅ እጅግ በበለጠገበት ወራት ፣ ከአብራም ጋር የሄደው ሎጥ ደግሞ የላምና የበግ መንጋ ድንኳንም ነበረው በአንድነትም ይቀመጡ ዘንድ ምድር አልበቃቸውም ፣ የነበራቸው እጅግ ነበረና በአንድነት ሊቀመጡ አልቻሉም የአብራምንና የሎጥን መንጎች በሚጠብቁት መካከልም ጠብ ሆነ በዚያም ዘመን ከነአናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር ይለናል ቃሉ ዘፍጥረት 13 ፥ 2 - 8 :: ይሁን እንጂ ይህ ጠብ ሲጀመር የሎጥና የአብራም እንጂ በሁለቱም በኩል ያለ የጠባቂዎቹ ጠብ አለመሆኑን አብራም በትክክል ጠንቅቆ ያወቀ ነውና አብራም ሎጥን እንዲህ አለው :: እኛ ወንድማማች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ አለው ይለናል ::
ውድ ወገኖቼ ሆይ የዘመኗ ቤተክርስቲያን መልክ ያልኩት እንግዲህ ከዚህ ታሪክ ተነስቼ ነው :: ሎጥ ከአብራም ጋር በፈጠረው ግጭት የአብራምንና የሎጥን መንጎች በሚጠብቁት መካከል ጠብ እንደሆነ ሁሉ ዛሬም በዘመናችን ባለች ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ሎጥ ብቻ ሳይሆን ብዙ ችግር ፈጣሪ ሎጦች አሉና እነዚህ ሎጦች አብራምን ከመሰሉ በእግዚአብሔር ተጠርተው የእግዚአብሔርን ጥሪ ተግባራዊ ከሚያደርጉና ወደ ፍጻሜም ከሚወስዱ ሰዎች ጋር በሚፈጥሩት ግጭት አንድ መንጋና አንድ ሕዝብ ሆኖ በሚኖረው በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ትልቅ የሆነ መበጣበጥና ጦርነት ይፈጠራል :: ታድያ ሎጥ ሰላማዊ መስሎ አብራምን ተከትሎ እንደወጣ ሁሉ እነዚህም በአሁን ዘመን ላለች ቤተክርስቲያን የጠብ መንስዔ የሆኑ ሎጦች አብራምን ከመሰሉ የእግዚአብሔር ጥሪ ከደረሳቸው ሰዎች ኋላ ኋላ ተከትለው የወጡ ሰዎች ቢሆኑም ሰላማዊነታቸው ግን የሚፈልጉትን እስኪያገኙ ድረስና ቢያገኙም የማይጠግቡም ሆነ በቃኝ የማይሉ በመሆናቸው ያሻቸውን ሁሉ ሊያገኙ በወደዱት መጠን ማግኘት እስከ ቻሉ ድረስ ብቻ ነው :: ድንገት ቀና ያሉ እና ቀናም የሚሉ በመሆናቸውም የሚያነሱት ረብሻ መጠን የሌለውና ገደቡንም የሳተ ስለሆነ መቋጫም ሆነ እልባት ልናበጅለት አይቻለንም :: እነዚህን የመሰሉ ሰዎችን መገላገል የሚቻለው ቀኝና ግራ ሳይሉ ሁሉንም ዕድል ለእነርሱ አሳልፎ በመስጠትና የወደዱትንም እንዲያደርጉ በመፍቀድ ብቻ ነው :: ቊሳዊና ማቴሪያሊስት ስለሆኑ ወንድምነት የሚባለው ቋንቋ እንዲህ ላሉ ሰዎች ግልጽ አይደለም አይገባቸውምም :: ከወንድምነት ይልቅ ገንዘብን ጥቅምንና ክብርንም ጭምር ያስቀደሙ በመሆናቸው ወንድምነት ለተባለው የቤተሰብነት ሕይወት የታወሩ ናቸው :: ከእነርሱ ሳይሆን ከመንጋው መካከል በሚነሳው ብጥብጥ በጥባጭነታቸው የሚታወቅ መሠርይ ሰዎች ናቸው :: የዘመኗ ቤተክርስቲያን ሎጦች ላማራቸው ፣ ለመረጡትና ለለመለመው ነገር ካልሆነ በስተቀር ለመንፈሳዊው ነገር ዓይኖቻቸው የማይነሳና ማየትም የማይችሉ ምድራዊና ሥጋውያን ሰዎች ናቸው ::
ሎጥ ዓይኑን ያነሳውና እንደ እግዚአብሔር ገነት አምሳል የሆነችውን ዞአርን የመረጠው አብራም ቀኝና ግራ ሳይል ሁሉንም ምርጫ ለእርሱ ከሰጠውና ከተወለት በኋላ ነው :: እስከዚያ ድረስ ግን ሰላማዊ መስሎ በእረኞች መካከል እየገባ ጠብን የሚጭርና የሚያቀጣጥል ጉድጓድንም መንፈሳዊ ለሆነው ለአጎቱ ለአብራም የሚምስ ሰው ሆኖ የተገኘ ነው :: ስለዚህ የጠብ መነሻና መገኛ የሆነው ሎጥ በእውነተኛው በእግዚአብሔር ሰው በአብራም ካልሆነ በስተቀር በሌላው ሰው በፍጹም የሚታወቅ አይደለም :: የዘመናችን ሎጦችም እንደዚህ ናቸው :: በእውነተኞቹ በእግዚአብሔር ሰዎች ካልሆነ በስተቀር ጠብን የጀመሩም ሆነ የቀሰቀሱ እነርሱ መሆናቸው ጨርሶ አይታወቅም :: ይልቁንም መንፈሳዊና የሚጸልዩልን ናቸው ብለን ምስጢራችንንም ሁሉ ዝክዝክ አድርገን ልንነግራቸው እንችላለን :: እነርሱ ግን ዓይን ያወጡና በእግዚአብሔርም ስም መነገድን የለመዱ ስለሆኑ እኽ ብለውም ሆነ ተቆርቋሪ መስለው ይሰሙናል ፣ ነገር ግን ከቀናት በኋላ ለሞታችን የሚሆንን ጉድጓድ ሲምሱብን እናገኛቸዋለን :: የዘመናችን የቤተክርስቲያን ሎጦችም ታድያ እንዲህ በመሆናቸው ዓይን ያውጡ ሌቦች ናቸው :: ተከትለው ወጥተው ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ባነሱት ረብሻና ብጥብጥ ምክንያት ዋናና ፊተኛ መሆንን የሚፈልጉ በመሆናቸው ዓይናችንን ከፍተን ልናያቸውና እንደሚገባም ልናውቃቸው ይገባል እላለሁኝ ::
ሎጥ አብራም ዕድሉን ሁሉ ለእርሱ ሰጥቶትና ለቆለት በመረጠው ምርጫ ምክንያት አንዱ ከሌላው እርስ በእርሳቸው ተለያዩ በማለት የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል ኦሪት ዘፍጥረት 13 : 11 :: የዘመናችን የቤተክርስቲያን ሎጦች ግን እንዲህ አይደሉም እናንተ እንኳ ማንነታቸውን አውቃችሁ ጠብን ከመጥላት የተነሳ ወንድምነት ይበልጣልና እስቲ ዕድሉን ሁሉ ልስጠው እርሱም የወደደውን ያድርግ ስትሉ ሁሉንም ነገር ብትተዉላቸው ፣ እነዚህ ሰዎች ግን እጅግ የተለዩ ፣ በአብራምም ዘመን ዓይነት እንደነበረው ሎጥ ያይደሉ በመሆናቸው ኃጢአታቸው ገጦና ፈጦ የወጣ ሆኖ ሳለ በኃጢአታቸው ተጸጽተው ንስሐ የማይገቡ መንፈስቅዱስም የማይወቅሳችው ናቸው :: ከዚህም ሌላ የመረጡትን ዞአር የያዙ እንኩዋ ቢሆኑም እጅግ በጣም ራስ ወዳዶችና ጥቅመኞች እንዲሁም ሃይማኖት ለበስ ፖለቲከኞች በመሆናቸው እንደ አብርሃሙ ዘመን ዓይነቱ ሎጥ በቀላሉ የሚፋቱአችሁ አይሆኑም :: እራሳቸውን ሎጦች ሳይሆን አብራሞች አድርገው የሚቆጥሩ በመሆናቸውም እናንተን የሎጥ ያክል ቆጥረው በሄዱበት መንገድ ሁሉ ተከትላችኋቸው እንድትሔዱ ፣ የራሳችሁ ምርጫ ቢኖራችሁም እንኳ ከእናንተ ምርጫ ይልቅ የእነርሱ ምርጫ እንደሚበልጥ አምናችሁና ተቀብላችሁ ምርጫቸውንም ምርጫዬ ነው ብላችሁ አጽድቃችሁ እንድትከተሏቸው መጣላታቸውንና መናከሳቸውን ባለማቆም የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ :: ይህንንም የሚያደርጉት አንድ ዓይነቶችና አንዱም ከሌላው የማይሻል ፣ የማይለይም ስለሆኑ ነው መጽሐፍቅዱሳችን በመጽሐፈ ምሳሌ 27 ፥ 17 ላይ ብረት ብረትን ይስለዋል ሰውም ባልንጀራውን ይስላል እንደሚል ፣ በእነርሱ ዘንድ አንዱ ከሌላው የተሻለ ሆኖ ባልንጀራውን የሚስል አይደለም :: በአጠቃላይ ሁሉም የማይሳሳሉ ዱልዱሞችና ከእጅ አይሻል ዶማዎች ናቸው :: እንደነዚህ ካሉ ፈጣጦች ፣ በሚሰሩት መልካም ያልሆነ ሥራም ከሚጸጸቱ ይልቅ ዓይኔን ግንባር ያርገው ሲሉ በከተሞች ሁሉ ከሚንቀሳቀሱ አወናባጅ ሎጦች እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ ይጠብቀን ተባረኩልኝ ::
አባ ዮናስ ጌታነህ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባ ነገሥታትን ገደለ ወይስ እነርሱ ገደሉት ?ክርስትናችን የሚያስተምረን መግደልን ነው ወይስ መገደ...

Thursday, December 12, 2019


እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደሆነ እወቁ 
እርሱ ሰራን እኛም አይደለንም 
እኛስ ሕዝቡ የመሠማርያውም በጎች ነን 

መዝሙር 99 ( 100 ) 3

የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን 

የምንባቡን ክፍል ስንመለከት እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደሆነ እወቁ እርሱ ሰራን እኛም አይደለንም ማለቱ ሰሪነቱን ፣ ፈጣሪነቱን ያመለክታል :: ከዚህ እውነት አንጻር ዛሬ ላይ ቆመን የእግዚአብሔርን ፈጣሪነትና ሰሪነት ስናስብ ከሰዎች አስተሳሰብና የምልልስም ሆነ የሕይወት ሥርዓት ብልሽት አንጻር  የእግዚአብሔር ፈጣሪነቱም ሆነ ሰሪነቱ ያልተከበረበት ደረጃ ላይ እንደደረስን እናስተውላለን :: መጽሐፍቅዱሳችንም ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ በማለት ይገልጽልናል ::  የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና ፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው ፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት ሞላባቸው፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚያንገላቱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ የማያስተውሉ፥ ውል የሚያፈርሱ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት ያጡ ናቸው እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም ይለናል  በሮሜ 1 21 - 32 )የተጻፈውን እንመልከት:: 

ውድ ወገኖቼ ሆይ ይህ የተጻፈው ቃል እንዳለ ሆኖ በሰዎች ሕይወት ላይ ተግባራዊ እየሆነ መምጣቱ ሲገርመን ከዚህ የመገረምና የሃዘኔታ ሕይወት ሳንወጣና ሳናገግም  ደግሞ ይባስ ተብሎ  ሕዝቡና የመሠማርያውም በጎች ነን የተባልነው እኛ  በዚህ በሮሜ 1 21  - 32 ባለ ክፉ ሃሳብ ተጠልፈን  የእግዚአብሔርን ፈጣሪነቱንም ሆነ ሰሪነቱን በመዘንጋት የመሠማርያው በጎች ልንሆን እግዚአብሔርም ሊያሰማራን የተቸገረብን ፍየሎች መሆናችን በእጅጉ ያሳዝናል :: ዛሬ ላይ እኛስ ሕዝቡ የመሠማርያውም በጎች ነን የተባልን ቅዱሳን ከዚህ ይልቅ የዓመጻን መንገድ መርጠን ራሳችንን በራሳችን መንገድ ላይ ያሰማራን ብልጣብልጥ ፍየሎች ሆነናል :: በብሉይ ኪዳኑ የመሥዋዕት ሥርዓት ደንብ የነበሩትን ሁለት ፍየሎች ብንመለከት እነዚህ ሁለት ፍየሎች በማስተስረያ ስነ ሥርዓት ቀን ይቀርቡ ነበር :: ታድያ አንዱ ይታረድ ሁለተኛው ግን ይለቀቅ እንደነበረ መጽሐፍቅዱሳችን ይጠቁመናል :: ( ዘሌዋውያን 16 7 - 22 ) ታድያ ከእነዚህ ከሁለቱ ፍየሎች መሃል አንዱ ታርዶ ሌላኛው መለቀቁ ትልቁን  ትምህርት የሚሰጠን ነው :: ታድያ ለእነዚህ ለሁለት ፍየሎች የመታረድም ሆነ የመለቀቅ ፈቃድ የተገኘው ከአራጁም ሆነ ከለቃቂው በተገኘ ፈቃድ ነው እንጂ ከፍየሎቹ አለመሆኑን ልናስተውል ይገባል :: ይህንን ስል ታድያ ራሱን ያረደም ሆነ የለቀቀ ፍየል አለመኖሩን ልጠቁማችሁ  ነው :: ይህንን ሁኔታ እንግዲህ እንደብሉይ ኪዳኑ ሥርዓት አስተውለን ከተመለከትነው መሥዋዕት ሊሆን የሚታረደው በጉ ብቻ ሳይሆን ፍየሉም ነው እያልኩ ነው ፣ ስለዚህ አንደኛው  ይታረዳል  ሌላኛው ፍየል ደግሞ ይለቀቃል :: ይህንን እውነታ ዛሬ ላይ  ታድያ ወደ እኛ ዘመን ስናመጣው  ሁሉም ብልጣብልጥ ሆኖና በየራሱም ምክንያት ተሸፍኖ ራሱን የለቀቀ ፍየል እንጂ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖ የሚታረድም ሆነ የሚለቀቅ ፍየል ግን አሁን በእኛ ዘመን አይገኝም ::  ለዚህም ነው ጴጥሮስ ይህንን ቃል የጠቀሰልን ቃሉም እንዲህ ይላል :: በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ ( 1ኛ ጴጥሮስ 2 15 - 17 ) :: ፍየሎች በባሕርያቸው ጠንካሮች ሆነው በድርቅ ሀገር ሊኖሩ ቢችሉም ፍየሎች አሁንም ክርስቶስን ያልተከተሉ ሰዎች ምሳሌ ናቸው (ማቴዎስ 25 33 ) ታድያ የዛሬውም ክርስቲያን እንደ እኔ ያለ አገልጋዩንም ልትሉት ትችላላችሁ ከአነጋገሩ ከአሰባበኩና ከሰላምታው ተነስታችሁ አሁን ላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አውቆ ክርስቶስን የተከተለ የክርስቶስ በግና የእግዚአብሔር ባሪያ ነው ብትሉትም ጠጋ ብላችሁ ሕይወቱን ስትመረምሩ ግን አርነቱን ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን ያደረገ በቃሉ መሠረት ሁሉን  ከማክበር ይልቅ ማዋረድን ገንዘቡ ያደረገ ፣ ወንድሞችንም ከመውደድ ይልቅ መጥላትን እግዚአብሔርን ከመፍራትና  ንጉሥንም ከማክበር ይልቅ እግዚአብሔርን መዳፈርና ሹማምንትንም መዘርጠጥ ተግባሩ ያደረገ አለሌ ፍየል ነው :: እግዚአብሔር ሳይለቃቸው  ራሳቸውን ኤፍታ ሲሉ የለቀቁ ጻድቃን መሳይ ፍየሎች ደግሞ ከዓመጻ ብዛት የተነሳ ዛሬ ላይ ባለ ሕይወታቸው ሊሰሙንና ሊቀበሉን ባይወዱም መጨረሻቸው ግን የሚሆነው እንዲህ ነው ትንቢተ ኤርምያስ 2 2 20 - 37 የተጻፈውን ያንብቡ :: 

ውድ ወገኖቼ ሆይ ጌታ እግዚአብሔር ያስበን :: በመንገድ ላይ እንደተለቀቀ እንደ ፈጣል ግመል ሆነንም  ሰዎች ሳይደክሙ በወራታችን የሚያገኙንና እኛም በስንፍናችንም ሆነ በሌብነታችን ብዛት የምናፍር እንዳንሆን ቀን ሳለ ዛሬ እግዚአብሔር እግሮቻችንን ከሻካራው መንገድ ይመልስልን 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ተባረኩ 

አባ ዮናስ ጌታነህ 

በመንፈስቅዱስ የሆነ የቤተክርስቲያን ውሳኔ በዛሬዋ ቤተክርስቲያን እንዴት ይታያል ( ክፍል አራት )

Sunday, December 8, 2019


ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም


የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች ሰላም ለእናንተ ይሁን


እነሆኝ እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም ይላል ( ዕብራውያን 2 ፥ 12 )


ውድ ወገኖቼ ሆይ ይህንን ቃል ልብ ብለን ተመልክተነዋል ? ከኢየሱስ በላይ ሐዋርያ ፣ ከኢየሱስ በላይ ነቢይ ፣ ከኢየሱስ በላይ እረኛ  ሊያውም ትልቅ እረኛና የእረኞችም አለቃ የሆነ ፣ ከኢየሱስ በላይ ወንጌላዊ ፣ ከኢየሱስ በላይ መምህር  ፣ ከኢየሱስ በላይ ሊቀ ካህን ሊያውም በሰማያት ያለፈና በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ትልቅ ሊቀ ካህን ፣ ከኢየሱስ በላይ ንጉሥ ሊያውም የእሾህ አክሊል ብቻ ሳይሆን  የክብርና የምሥጋናን ዘውድ ተጭኖ የታየ ንጉሥ እንደ እርሱ ያለ ማንም የለም :: ይሁን እንጂ ታድያ እንዲህ ያለው ጌታ ነው እንግዲህ ብዙዎቹ ሐዋርያ ፣ ነቢይ ፣ እረኛና የመሣሠሉትን ተብለው ስለተጠሩ ብቻ ወንድሞች ሊሉን ባፈሩበት በዚህ ዘመን ወንድሞች ብሎ ሊጠራን ያላፈረው :: ከዚህ የተነሣ እንግዲህ ዛሬ ዘመናችን ነው ወይንም በሌላኛው አባባል ዘመን መጥቶልናል ሲሉ  በእንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ ተጠምደው ላሉ የዘመኑ እረኛ ፣ ነቢይ ፣ ሐዋርያና የመሣሠሉትን ሲባሉ ለተጠሩ ሰዎች እኛም የምንሰጣቸው ምላሽ  ከኢየሱስ ጋር ልትፍቁት የማትችሉት ወንድምነት ውስጥ የገባን ስለሆነ ወንድምነታችን ቀረባችሁ እንጂ አልቀራችሁብንም ነው ::  ደግሞም ክርስቶስ ወንድሞች ብሎ በመጥራት የሰጠን ወንድምነት የማያሳፍርና በመቤዠት ውስጥ የመጣ  የዘላለም  ወንድምነት ስለሆነ እናንተ ደግሞ ይህ ምስጢር ሳይገባችሁ ነውና ሐዋርያ ፣ መጋቢ ፣ ነቢይና የመሳሰሉትን የተባላችሁት ወንድሞች ብለን ስንጠራችሁ የሚያሳፍራችሁ ፣ የምትበሳጩ  ፣ የምታኮርፉና  የምትቆጡ ከዚህ የተነሳም ወንድምነታችንንም ጭምር ልትቀበሉት የምትቸገሩ ብትሆኑም  የተቤዠን ጌታ ግን ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራን እኛም ወንድማችን ልንለው አያፍርብንም ፤ ደግሞም  ይሄ ጉዳይ ለእርሱ ደስታው እንጂ ችግሩ አይደለም :: በተለይ በወንጌላውያን ቤተክርስቲያን አንድን ፓስተር ወይንም አንድን ሐዋርያ አንድ አማኝ ድንገት እንኩዋን አፉን አዳልጦት ወንድም እገሌ ቢለው ፓስተሩ ፣ ሐዋርያውም በሉት ሌላው የሚሰማውን ስሜት በተለይ በዚህ ዘመን ሁላችንም እናውቀዋለን :: አንዳንዱማ  ሐዋርያ ፣ ነብይ እና የመሣሠሉትን ተብዬ ተጠርቼ ሳለ ለምን ወንድም ብላችሁ ጠራችሁኝ ? ሲል ከመጠን በላይ ያኮርፍና ላያገኘን ምሎና ተገዝቶ ፣ መንገዱንም አሳብሮ ይሄዳል በየከተማችን ያለ የመጋቢዎች ኩርፍያማ ከዚህም የባሰ ነው :: እግዚአብሔር ያስበን ወገኖቼ :: ከእኛ በፊት የአገልግሎት ቅድሚያና ብልጫም የነበረው ጳውሎስ እኮ ፣ ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ ተብሎ እስካሁን እስከ እኛ ዘመን ድረስ ይነገርለታል 2ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 15 እና 16 :: ታድያ ወንድማችን ጳውሎስ ወንድማችን ስለተባለ ወንድም ተብዬ ተጠርቻለሁና ተዋርጃለሁ ያዙኝ ልቀቁኝ አለ እንዴ አላለም :: ሐዋርያነቱንም ቢሆን እኮ ይገባኛል ብሎ በይገባኛል መንፈስ ያልተቀበለ በመሆኑ ወንድም ተብሎ መጠራቱ ለእርሱ ደስ ያሰኘው እንጂ የቆረቆረው አልሆነም 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ፥ 9 – 11 ::  ደግሞም ከሐዋርያነት ይልቅ ወንድምነት እንደሚበልጥ በትክክል የተረዳና የገባው ስለሆነ እንደ እኛ አይደለም :: እኛ ብንሆን ግን እንደዚህ  ጳውሎስ እንደተጠራበት አጠራር ቅንነትንና ወዳጅነትን ተላብሶ  ወንድማችን ሲል በአደባባይ የጠራንን ሁሉ ልናጠፋው እንቅልፍ አይወስደንም :: እንደገናም ቤተክርስቲያንዋም የእኛ እንጂ የእርሱ ስለልሆነች ኮንትራቱ እንዳለቀ ሠራተኛ ከቤተክርስቲያን ምክንያት ፈጥረን አስፈንጥረን እናባርረዋለን :: ጌታ ዓይኖቻችንን ይክፈትልን ይህንን ያክል በአጭሩ ካልኩ እንግዲህ ይበቃኛል :: በዚህ ምንባብ ተጠቀሙ ተባረኩ ::


…..ጳውሎስም፦ ወንድሞች ሆይ፥ ሊቀ ካህናት መሆኑን ባላውቅ ነው፤ በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር ተብሎ ተጽፎአልና አላቸው
የሐዋርያት ሥራ 23 : 1 – 5


አባ ዮናስ ጌታነህ

Friday, December 6, 2019

ከዳተኛይቱ ይሁዳ አንድ ቀን በሙሉ ልብዋ ተመልሳ


የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ከቪዲዮው መልዕክት በተጨማሪ ይህንን ጽሑፍ በማስተዋል እንድታነቡ እጋብዛለሁ ተባረኩልኝ
ከዳተኛይቱ ይሁዳ አንድ ቀን በሙሉ ልብዋ ተመልሳ እግዚአብሔርን እንደምትወድ ከጌታ ቤት በአንድም በሌላም መንገድ የከዱና የኮበለሉ ሰዎች እንደዚሁ አንድ ቀን ተመልሰው እግዚአብሔርን ይወዳሉ :: ይህም የሚሆነው በእኛ ቀን ሳይሆን በእግዚአብሔር ቀን ነው :: ይህን ስል ግን እያንዳንዳችን ክርስቲያኖች ማድረግ የሚገባንን የበኩላችንን ነገር ሁሉ አናድርግ አንምከር አናስተምር አንገስጽ ማለቴ አይደለም ፣ ነገር ግን ያ ሁሉ እንዳለ ሆኖ እግዚአብሔር ደግሞ ብቻውን በሚያደርገው ነገር ከዳተኛይቱ ይሁዳ በሙሉ ልብዋ ወደ እግዚአብሔር እንደተመለሰች ከመንግሥቱም ሆነ ከቤቱ የጠፉና የኮበለሉ ሰዎች ደግሞ እንዲሁ በእግዚአብሔር ክህሎት ወደ ቤቱ ይመለሳሉ :: ለዚህም ነው ጌታ እግዚአብሔር በትንቢተ ኤርምያስ 31 ፥ 22 ፤ በትንቢተ ኤርምያስ 3 ፥ 14 – 22 ላይ ከዳተኛ ልጆች ሆይ እኔ ባለቤታችሁ ነኝና ተመለሱ ፣ በእውቀትና በማስተዋል የሚመሯችሁን እረኞች እሰጣችኋለሁ ያለው :: እንደገናም እኔም የተመረጠችውን ምድር የትኛውም ሕዝብ ያላገኘውን የተዋበች ርስት ልሰጥሽ እንደ ወንዶች ልጆቼ ምንኛ በደስታ ልቊጠርሽ አልሁ :: አባቴ ብለሽ የምትጠሪኝ እኔንም ከመከተል ዘወር የማትዪ መስሎኝ ነበር :: የእስራኤል ቤት ሆይ ለባልዋ ታማኝ እንዳልሆነች ሚስት ስታታልሉኝ ኖራችኋል ይላል እግዚአብሔር በማለት ይህንን መልዕክት በነቢዩ በኤርምያስ ለከዳተኛዋ ይሁዳም ሆነ ለእስራኤል ቤት ተናገረ :: ታድያ ይህንን መልዕክት በነቢዩ በኩል ማምጣቱ እስራኤል ዘወትር አምላኩዋ ያደረገላትን ሁሉ ማስታወስ ነበረባት :: በእርሱ ብቻ በመታመን እርሱንም ማምለክ ነበረባት ፣ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ረስታዋለች ከልብዋም አውጥታ ጥላዋለች ከዚህ የተነሳ በትንቢተ ኤርምያስ 2 ፥ 32 ላይ ጌታ እግዚአብሔር በውኑ ለእስራኤል ምድረበዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንሁበትን ? ሕዝቤስ ስለምን እኛ ፈርጥጠናል ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል ? በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን ? ሕዝቤ ግን የማይቆጠር ወራት ረስቶኛል በማለት ሲናገር እንመለከታለን :: እንግዲህ ሕዝቤ ተብላ ወደ አንተ አንመለስም ስትል የማይቆጠር ወራት አምላኳን የረሳች እስራኤል ናት በሙሉ ልብዋ ወደ እግዚአብሔር ተመልሳ በዚሁ በትንቢተ ኤርምያስ 3 ፥ 21 መሠረት እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት መንገዳቸውን አጣመዋልና የእስራኤል ሕዝብ ጩኸት አሳዛኝ ልቅሶ ባድማ ከሆኑት ኮረብታዎች ተሰማ የሚለን ::
ይህንን መልዕክት በተለቀቀው ቪዲዮ የሰማችሁም ሆነ ለማንበብ ፈቃደኛ ሆናችሁ መልዕክቱን የምታነቡ ሁሉ በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥምና ለጠፉ ሰዎች በፍቅር ሆናችሁ የመናገርም ሆነ የመመስከር ፋይላችሁን አትዝጉ ደግሞም ፈራጁ እያለ እናንተንም ሆነ ሁላችንን ስላልተቀበሉን ፣ ስላልተቀበሏችሁ ፣ ስላላስተናገዱን ስላላስተናገዷችሁ መጸለይ አለበለዚያም እነርሱን በግል ሄዶ ማነጋገርና ማመካከር መጨረስ የሚገባንንም እዚያው በግል መጨረስ ነው እንጂ ከብስጭትም ሆነ ከመመረር የተነሳ እንዲሁ መድረኩ ስለተገኘ ብቻ እነዚሁኑ ሰዎች በየሶሻል ሚዲያው ገበናቸውን አውጥተን የውይይት አጀንዳ ባናድርጋቸው ፣ ደግሞም እንደ ጳውሎስና በርናባስም እስከ መከፋፋት ደርሰን ባንለያይባቸው እንደገናም ነገ የሚሆነውን አናውቅምና ከዚህም ሌላ ከጌታ ዘንድ ምን ዓይነት መንፈስ እንደሆነላችሁ አታውቁም እንባላለንና በችኮላ ተናደን የፍርድን ቃል በላያቸው ባንናገር የተሻለ ነው የሚሆነው :: እነዚህን ጥቅሶች በማስተዋል አንብቧቸው የሉቃስ ወንጌል 9 ፥ 51 – 56 ፤ የሐዋርያት ሥራ 15 ፥ 36 – 41 ፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 4 ፥ 11 ፤ ፊልሞና ቊጥር 8 – 25 :: ዛሬ ላይ ሁላችንም ማለት ይቻላል ብለን ብለን ተስፋ የቆረጥንባቸውን ሰዎች በነገው ሕይወታቸው እግዚአብሔር ወደ ቤቱ በምን ዓይነት መንገድ ጠርቶና መልሶ እንደሚጠቀምባቸው ከአንዳንዶች በቀር አብዛኞቻችን ላናውቅ እንችላለን :: ይህ ሲባል ግን የተግሳጽም ሆነ የዘለፋ እንዲሁም የምክር መልዕክቶችን ጌታ እንደሰጠን መጠን አንናገር አናስተላልፍ እያልኩ አለመሆኔን በግልጽ ልትረዱልኝ ይገባል :: እንደውም መጽሐፍቅዱሳችን የሚለን በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር ነው የሚለን ትንቢተ ኢሳይያስ 58 ፥ 1 እንመልከት :: ከዚህ በመቀጠል መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ የእስራኤልም ሆነ አሁን ላይ ያለ የሐዲስ ኪዳን ሕዝብን አሳዛኝ ጩኸትና የመመለስ ልቅሶ እንዲህ በማለት አስደናቂ በሆነው የመዝሙር ስንኞቹ እና ዜማው ገልጾታልና እርሱን እጋብዛችኋለሁ ተከታተሉ ::
አዝ፦ ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x)
በመዳኑ ፡ ምክንያት ፡ መላዕክት ፡ ፈንጭተው
በአገልግሎቱም ፡ ብዙ ፡ ሰዎች ፡ ረክተው
ያንን ፡ ሰው ፡ በቃሉ ፡ እንቅፋት ፡ እግኝቶት
ወድቆ ፡ የነበረው ፡ አዳኙንም ፡ ከድቶ
አዝ፦ ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x)
መርዶውን ፡ እየሰሙ ፡ ሰዎች ፡ አልቅሰውለት
ጌታ ፡ እንዲያስነሳው ፡ ከልብ ፡ ጸልየውለት
በመራራ ፡ ጩኸት ፡ ለአምላኩ ፡ ነግረውለት
መልሶ ፡ እምጥቶታል ፡ እግዚአብሔር ፡ አዝኖለት
አዝ፦ ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x)
የውድቀቱን ፡ ምክንያት ፡ ነግሮ ፡ አስጠንቅቆታል
ወንድሞቹ ፡ ቀድሞ ፡ ጌታ ፡ አምጥቶለታል
ተስፋን ፡ እየናቀም ፡ በወጥመድ ፡ ቢገባም
ጌታ ፡ ቸር ፡ ነውና ፡ አይጨክንበትም
አዝ፦ ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x)
ያን ፡ ጨካኝ ፡ አንበሳ ፡ በግልጽ ፡ አሳፍሮ
በብረቱ ፡ በትር ፡ መንጋጋውን ፡ ሰብሮ
ዳግም ፡ አምጥቶታል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
ሙሾው ፡ ተለውጧል ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን
አዝ፦ ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x)
አባ ዮናስ ጌታነህ

ባለፉት በአባቶቻችን ዘመንም ሆነ ዛሬ በእኛ ዘመን የእግዚአብሔር የምሕረቱ እርዳታ የማያስፈልገው ሰው ይኖር ይሆንን...__የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ከቪዲዮው መልዕክት በተጨማሪ ይህንን ጽሑፍ በማስተዋል እንድታነቡ እጋብዛለሁ ተባረኩልኝ ከዳተኛይቱ ይሁዳ አንድ ቀን በሙሉ ልብዋ ተመልሳ እግዚአብሔርን እንደምትወድ ከጌታ ቤት በአንድም በሌላም መንገድ የከዱና የኮበለሉ ሰዎች እንደዚሁ አንድ ቀን ተመልሰው እግዚአብሔርን ይወዳሉ :: ይህም የሚሆነው በእኛ ቀን ሳይሆን በእግዚአብሔር ቀን ነው :: ይህን ስል ግን እያንዳንዳችን ክርስቲያኖች ማድረግ የሚገባንን የበኩላችንን ነገር ሁሉ አናድርግ አንምከር አናስተምር አንገስጽ ማለቴ አይደለም ፣ ነገር ግን ያ ሁሉ እንዳለ ሆኖ እግዚአብሔር ደግሞ ብቻውን በሚያደርገው ነገር ከዳተኛይቱ ይሁዳ በሙሉ ልብዋ ወደ እግዚአብሔር እንደተመለሰች ከመንግሥቱም ሆነ ከቤቱ የጠፉና የኮበለሉ ሰዎች ደግሞ እንዲሁ በእግዚአብሔር ክህሎት ወደ ቤቱ ይመለሳሉ :: ለዚህም ነው ጌታ እግዚአብሔር በትንቢተ ኤርምያስ 31 ፥ 22 ፤ በትንቢተ ኤርምያስ 3 ፥ 14 - 22 ላይ ከዳተኛ ልጆች ሆይ እኔ ባለቤታችሁ ነኝና ተመለሱ ፣ በእውቀትና በማስተዋል የሚመሯችሁን እረኞች እሰጣችኋለሁ ያለው :: እንደገናም እኔም የተመረጠችውን ምድር የትኛውም ሕዝብ ያላገኘውን የተዋበች ርስት ልሰጥሽ እንደ ወንዶች ልጆቼ ምንኛ በደስታ ልቊጠርሽ አልሁ :: አባቴ ብለሽ የምትጠሪኝ እኔንም ከመከተል ዘወር የማትዪ መስሎኝ ነበር :: የእስራኤል ቤት ሆይ ለባልዋ ታማኝ እንዳልሆነች ሚስት ስታታልሉኝ ኖራችኋል ይላል እግዚአብሔር በማለት ይህንን መልዕክት በነቢዩ በኤርምያስ ለከዳተኛዋ ይሁዳም ሆነ ለእስራኤል ቤት ተናገረ :: ታድያ ይህንን መልዕክት በነቢዩ በኩል ማምጣቱ እስራኤል ዘወትር አምላኩዋ ያደረገላትን ሁሉ ማስታወስ ነበረባት :: በእርሱ ብቻ በመታመን እርሱንም ማምለክ ነበረባት ፣ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ረስታዋለች ከልብዋም አውጥታ ጥላዋለች ከዚህ የተነሳ በትንቢተ ኤርምያስ 2 ፥ 32 ላይ ጌታ እግዚአብሔር በውኑ ለእስራኤል ምድረበዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንሁበትን ? ሕዝቤስ ስለምን እኛ ፈርጥጠናል ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል ? በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን ? ሕዝቤ ግን የማይቆጠር ወራት ረስቶኛል በማለት ሲናገር እንመለከታለን :: እንግዲህ ሕዝቤ ተብላ ወደ አንተ አንመለስም ስትል የማይቆጠር ወራት አምላኳን የረሳች እስራኤል ናት በሙሉ ልብዋ ወደ እግዚአብሔር ተመልሳ በዚሁ በትንቢተ ኤርምያስ 3 ፥ 21 መሠረት እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት መንገዳቸውን አጣመዋልና የእስራኤል ሕዝብ ጩኸት አሳዛኝ ልቅሶ ባድማ ከሆኑት ኮረብታዎች ተሰማ የሚለን :: ይህንን መልዕክት በተለቀቀው ቪዲዮ የሰማችሁም ሆነ ለማንበብ ፈቃደኛ ሆናችሁ መልዕክቱን የምታነቡ ሁሉ በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥምና ለጠፉ ሰዎች በፍቅር ሆናችሁ የመናገርም ሆነ የመመስከር ፋይላችሁን አትዝጉ ደግሞም ፈራጁ እያለ እናንተንም ሆነ ሁላችንን ስላልተቀበሉን ፣ ስላልተቀበሏችሁ ፣ ስላላስተናገዱን ስላላስተናገዷችሁ መጸለይ አለበለዚያም እነርሱን በግል ሄዶ ማነጋገርና ማመካከር መጨረስ የሚገባንንም እዚያው በግል መጨረስ ነው እንጂ ከብስጭትም ሆነ ከመመረር የተነሳ እንዲሁ መድረኩ ስለተገኘ ብቻ እነዚሁኑ ሰዎች በየሶሻል ሚዲያው ገበናቸውን አውጥተን የውይይት አጀንዳ ባናድርጋቸው ፣ ደግሞም እንደ ጳውሎስና በርናባስም እስከ መከፋፋት ደርሰን ባንለያይባቸው እንደገናም ነገ የሚሆነውን አናውቅምና ከዚህም ሌላ ከጌታ ዘንድ ምን ዓይነት መንፈስ እንደሆነላችሁ አታውቁም እንባላለንና በችኮላ ተናደን የፍርድን ቃል በላያቸው ባንናገር የተሻለ ነው የሚሆነው :: እነዚህን ጥቅሶች በማስተዋል አንብቧቸው የሉቃስ ወንጌል 9 ፥ 51 - 56 ፤ የሐዋርያት ሥራ 15 ፥ 36 - 41 ፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 4 ፥ 11 ፤ ፊልሞና ቊጥር 8 - 25 :: ዛሬ ላይ ሁላችንም ማለት ይቻላል ብለን ብለን ተስፋ የቆረጥንባቸውን ሰዎች በነገው ሕይወታቸው እግዚአብሔር ወደ ቤቱ በምን ዓይነት መንገድ ጠርቶና መልሶ እንደሚጠቀምባቸው ከአንዳንዶች በቀር አብዛኞቻችን ላናውቅ እንችላለን :: ይህ ሲባል ግን የተግሳጽም ሆነ የዘለፋ እንዲሁም የምክር መልዕክቶችን ጌታ እንደሰጠን መጠን አንናገር አናስተላልፍ እያልኩ አለመሆኔን በግልጽ ልትረዱልኝ ይገባል :: እንደውም መጽሐፍቅዱሳችን የሚለን በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር ነው የሚለን ትንቢተ ኢሳይያስ 58 ፥ 1 እንመልከት :: ከዚህ በመቀጠል መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ የእስራኤልም ሆነ አሁን ላይ ያለ የሐዲስ ኪዳን ሕዝብን አሳዛኝ ጩኸትና የመመለስ ልቅሶ እንዲህ በማለት አስደናቂ በሆነው የመዝሙር ስንኞቹ እና ዜማው ገልጾታልና እርሱን እጋብዛችኋለሁ ተከታተሉ :: አዝ፦ ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን 
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን 
ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን 
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x)

 በመዳኑ ፡ ምክንያት ፡ መላዕክት ፡ ፈንጭተው
 በአገልግሎቱም ፡ ብዙ ፡ ሰዎች ፡ ረክተው
 ያንን ፡ ሰው ፡ በቃሉ ፡ እንቅፋት ፡ እግኝቶት
 ወድቆ ፡ የነበረው ፡ አዳኙንም ፡ ከድቶ

 አዝ፦ ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
 መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን
 ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
 መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x)

 መርዶውን ፡ እየሰሙ ፡ ሰዎች ፡ አልቅሰውለት 
ጌታ ፡ እንዲያስነሳው ፡ ከልብ ፡ ጸልየውለት 
በመራራ ፡ ጩኸት ፡ ለአምላኩ ፡ ነግረውለት
 መልሶ ፡ እምጥቶታል ፡ እግዚአብሔር ፡ አዝኖለት 

አዝ፦ ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
 መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን 
ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
 መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x) 

የውድቀቱን ፡ ምክንያት ፡ ነግሮ ፡ አስጠንቅቆታል 
ወንድሞቹ ፡ ቀድሞ ፡ ጌታ ፡ አምጥቶለታል
 ተስፋን ፡ እየናቀም ፡ በወጥመድ ፡ ቢገባም
 ጌታ ፡ ቸር ፡ ነውና ፡ አይጨክንበትም 

አዝ፦ ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን 
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን
 ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን 
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x)

 ያን ፡ ጨካኝ ፡ አንበሳ ፡ በግልጽ ፡ አሳፍሮ
 በብረቱ ፡ በትር ፡ መንጋጋውን ፡ ሰብሮ
 ዳግም ፡ አምጥቶታል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
 ሙሾው ፡ ተለውጧል ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን

 አዝ፦ ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን
 መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን 
ያ ፡ ተከራታቹ ፡ ኮብላይ ፡ ወገናችን 
መቷል ፡ እንደገና ፡ እሰይ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x) አባ ዮናስ ጌታነህ

Monday, December 2, 2019

እነዚህን መልዕክቶች በማስተዋል ይመልከቷቸው
የኃጢአተኛውን ፡ ጥፋት ( Yehatiategnawn Tefat ) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
አዝ፦ የኃጢአተኛውን ፡ ጥፋት
እግዚአብሔር ፡ መቼ ፡ ይወዳል?

የተጣለ ፡ ሰው ፡ እንኳን ፡ ፈጽሞ ፡ እንዳይጠፋ
በምክሩ ፡ ያስባል ፣ በምክሩ ፡ ያስባል


ምሕረትና ፡ ዕውነት ፣ ፍቅርና ፡ ቸርነት ፡ የሞላው ፡ ጌታ

ኃጥዕ ፡ በንስሐ ፡ ይቀበል ፡ ይቅርታ

ማንም ፡ እንዳይጠፋ ፡ መድህን ፡ ሞቶልናል

ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤዛ ፡ ሆኖልናል


አዝ፦ የኃጢአተኛውን ፡ ጥፋት
እግዚአብሔር ፡ መቼ ፡ ይወዳል?

የተጣለ ፡ ሰው ፡ እንኳን ፡ ፈጽሞ ፡ እንዳይጠፋ
በምክሩ ፡ ያስባል ፣ በምክሩ ፡ ያስባል


ሰው ፡ ግን ፡ በውድቀቱ
ለምን ፡ ተስፋውን ፡ ይቆርጣል ፡ ቶሎ?

ለምን ፡ ይቀናዋል ፡ መውረድ ፡ አሽቆልቁሎ?

ጌታን ፡ እጠብቃለሁ ፣ ቢገድለኝም ፡ ብሎ

በዕምነት ፡ የሚቆም ፡ አይቀርም ፡ ጐስቁሎ


አዝ፦ የኃጢአተኛውን ፡ ጥፋት 
እግዚአብሔር ፡ መቼ ፡ ይወዳል?
የተጣለ ፡ ሰው ፡ እንኳን ፡ ፈጽሞ ፡ እንዳይጠፋ 
በምክሩ ፡ ያስባል ፣ በምክሩ ፡ ያስባል


የሚወደውን ፡ ልጅ ፡ እግዚአብሔር
ለጥቅሙ ፡ ይቀጣዋል

መክሮ ፡ ይገስጸዋል ፣ ያስተካክለዋል

በአባትነት ፡ ዓይኑ ፡ ይመለከተዋል

ሲፍገመገም ፡ ቢያየው ፣ ፍጥኖ ፡ ይደግፈዋል


አዝ፦ የኃጢአተኛውን ፡ ጥፋት
እግዚአብሔር ፡ መቼ ፡ ይወዳል?

የተጣለ ፡ ሰው ፡ እንኳን ፡ ፈጽሞ ፡ እንዳይጠፋ
በምክሩ ፡ ያስባል ፣ በምክሩ ፡ ያስባል
1ኛ ) እግዚአብሔር በደለኛውን ንጹሕ ነህ አይልም ኃጢአትን ይቀጣል ነገር ግን ይሄው እግዚአብሔር ተመልሶ በምሕረት ይረዳል ይቅርም ይላል
ለእነዚህ ዋና ዋና ሃሳቦች የተጻፈልንን የእግዚአብሔር ቃል አስረጂ አቀርባለሁ
እግዚአብሔር ትዕግስተኛ ኃይሉም ታላቅ ነው በደለኛውን ንጹሕ ነህ አይልም እግዚአብሔር በወጀብና በአውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው ( ትንቢተ ናሆም 1 ፥ 3 )
እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል መቅበዝበዝን ወደዋል እግራቸውንም አልከለከሉም ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አይለውም በደላቸውንም አሁን ያስባል ኃጢአታቸውንም ይቀጣል ( ትንቢተ ኤርምያስ 14 ፥ 10 )
ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች፤ ልጅ የአባቱን ኃጢአት አይሸከምም፥ አባትም የልጁን ኃጢአት አይሸከምም፤ የጻድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆናል፥ የኃጢአተኛውም ኃጢአት በራሱ ላይ ይሆናል ( ትንቢተ ሕዝቅኤል 18 ፥ 20 )
እንግዲህ፦ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው ( የዮሐንስ ወንጌል 8 ፥ 24 )
2ኛ ) ይህን አውቀው ለተመለሱና ለሚመለሱ ብቻ ሳይሆን መመለስም ያለው ከእግዚአብሔር እርዳታ የተነሳ ስለሆነ ሊመለሱ የእግዚአብሔርን እርዳታ ለሚናፍቁ ሁሉ የእግዚአብሔር ምሕረት እንደገናም የምሕረት እርዳታውም ሆነ ይቅር ማለቱ አለ

እግዚአብሔር የረዳኝ ባይሆን ነፍሴ ለጥቂት ጊዜ በሲኦል ባደረች ነበር እግሮቼ ተሰናከሉ ባልሁ ጊዜ አቤቱ ምሕረትሕ ረዳኝ አቤቱ ለልቤ እንደ መከራዋ ብዛት ማጽናናሕ ነፍሴን ደስ አሰኛት ( መዝሙር 93 ( 94 ) 16 _ 19 )
ገፋኸኝ ለመውደቅም ተንገደገድኩ እግዚአብሔር ግን አገዘኝ
መዝሙር ( 118 )፥ 13
አቤቱ አምላኬ እየኝ ስማኝም ጠላቴ አሸነፍኩት እንዳይል የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው ለሞትም እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ እኔ ግን በቸርነትሕ ታመንሁ ልቤም በመድኃኒትሕ ደስ ይለዋል የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ ( መዝሙር 12 ( 13 ) ፥ 3 _ 6 )
እኔ ግን በምሕረትሕ ብዛት ወደ ቤትሕ እገባለሁ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናሕ መቅደስ እሰግዳለሁ ( መዝሙር 5 ፥ 6 )
ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሳ ነው ርኅራኄው አያልቅምና ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ታማኝነትሕ ብዙ ነው ( ሰቆቃወ ኤርምያስ 3 ፥ 22 እና 23 )
ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለጸጋ ስለሆነ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ በበደላችን ሙታን እንኩዋ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሰጠን በጸጋ ድናችኋልና በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሳን እያለ ይቀጥላል ( ኤፌሶን 2 ፥ 4 _ 10 )
3ኛ ) የምሕረት ባለጸግነትና ፍቅሩ ስላላለቀ እግዚአብሔር የኃጢአተኛውን ጥፋትም ሆነ የሟቹን ሞት አይወድምና የወደቀ ይነሳል የሳተ ይመለሳል
እግዚአብሔርስ ሞገሱን ረሳን፧ በቍጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን፧ ( መዝሙር ( 77 ) ፥ 6 _ 11
ሁላችን እንሞታለን፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ ነን፤ እግዚአብሔርም የነፍስን ጥፋት አይወዽም፥ ነገር ግን የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል
( 2ኛ ሳሙኤል 14 ፥ 14 )
የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ ( ትንቢተ ሕዝቅኤል 18 ፥ 32 )
እንዲህም ትላቸዋለህ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የወደቁ አይነሡምን ? የሳተስ አይመለስምን ? ( ትንቢተ ኤርምያስ 8 ፥ 4 - 6 )
ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ 1ኛ ቆሮንቶስ 10 : 12
ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል
( 2ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 9 )
ተባረኩ
አባ ዮናስ