Wednesday, April 23, 2025

ወልድኪ ነፍሳተ ሶበ አርአየኪ በእሳተ ኵነኔ ዘሐሙ ማርያም ትብሊ በእንቲኣሆሙ ቅትለኒ ለቤዛሆሙ። - ልጅሽ በፍርድ እሳት የሚሠቃዩ ነፍሳትን ባሳየሽ ጊዜ፥ ማርያም ስለ ቤዛቸው (ስለ መዳናቸው) ግደለኝ አልሽ።”

ወልድኪ ነፍሳተ ሶበ አርአየኪ በእሳተ ኵነኔ ዘሐሙ ማርያም ትብሊ በእንቲኣሆሙ ቅትለኒ ለቤዛሆሙ። - ልጅሽ በፍርድ እሳት የሚሠቃዩ ነፍሳትን ባሳየሽ ጊዜ፥ ማርያም ስለ ቤዛቸው (ስለ መዳናቸው) ግደለኝ አልሽ።” "ማርያም የሞተችው ያለ ፈቃዷ መኾኑን፥ የሞቷን ታሪክ ይዘናል የሚሉ አንዳንድ መጻሕፍት ይመሰክራሉ። ከእነዚህም መካከል አንዱ የኾነው “ነገረ ማርያም” የተባለ መጽሐፍ እንደሚተርከው፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ማርያም የምትሞትበት ቀን ሲደርስ፥ ከዚህ ኀላፊ ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ትኼጂ ዘንድ ሙቺ ይላታል፤ ርሷ ግን፥ እኔ አንተን ወልጄ የአንተ እናት ኾኜ እንዴት ልሙት? ብላ አሻፈረኝ ትላለች። ጌታም፥ “በፈቃዷ እንዳልሞተችለት ዐውቆ፥ ዘጠኝ እልፍ ዘጠኝ ሺሕ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ (99,999) ነፍሳት በአንድ ቀን ተኰንነው ገሃነመ እሳት ሲወርዱ ያሳያታል።” እነርሱም ወደ ርሷ እየጮኹ እንድታድናቸው ይማፀኗታል። በዚህ ጊዜ ጌታን፥ ‘ልጄ ወዳጄ ሆይ፥ እነዚህን ነፍሳት እባክኽ ማርልኝ’ ትለዋለች። ርሱም ‘እኔ የአዳምን ልጆች ከገሃነመ እሳት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያስገባኹት፥ መከራ ተቀብዬ፥ ሞቼ፥ ተነሥቼ ነውና፥ አንቺም ለነዚህ ነፍሳት ስለ ኀጢአታቸው ካልሞትሽላቸው ዘላለም ገሃነመ እሳት ወርደው ይቀራሉ’ ይላታል። በዚህ ጊዜ ርሷ ‘እነዚህ ነፍሳት በእኔ ሞት የሚድኑ ከኾነ እንኳን አንድ ጊዜ ሰባት ጊዜም ልሙት’ ብላ ለመሞት ፈቃደኛ ኾነች ይላል። "የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መምህር የነበሩት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ጸሎተ ሰብዐቱ ጊዜያት (ሰላምታ) በተሠኘ ድርሰታቸው፥ ይህንኑ ታሪክ በግእዝ ግጥም አቅርበውታል። “ወልድኪ ነፍሳተ ሶበ አርአየኪ በእሳተ ኵነኔ ዘሐሙ ማርያም ትብሊ በእንቲኣሆሙ ቅትለኒ ለቤዛሆሙ። - ልጅሽ በፍርድ እሳት የሚሠቃዩ ነፍሳትን ባሳየሽ ጊዜ፥ ማርያም ስለ ቤዛቸው (ስለ መዳናቸው) ግደለኝ አልሽ።” ይህም ግጥም “ማርያም የሞተችው ቤዛ ለመኾን” ነው የሚለው ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትረካ፥ እውነት መስሎ በአምልኮተ ማርያም ውስጥ በዜማ እንዲቀርብ አድርጓል። "ወደ ፊት እንደምናየው ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ በማርያም ስም ለሚያስፋፋው ትምህርት እንዲያግዘው በያሬድ ስም ወደ መጽሐፈ ድጓ የጨመራቸው የያሬድ ያልኾኑ ሐሳቦች አሉ፦ ለምሳሌ፦ “ዮም ፍሥሓ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም… ከመ ትቤዙ ነቢያተ ወጻድቃነ አማን ተወልደት እመ ብርሃን። - በማርያም መወለድ ምክንያት ዛሬ ደስታ ኾነ … ነቢያትንና ጻድቃንን ትቤዥ (ታድን) ዘንድ የብርሃን እናት በእውነት ተወለደች” የሚል እናነብባለን። መቼም ይህ በያሬድ ስም ወደ ድጓ ከገቡ ባዕዳን ድርሰቶች መካከል እንደሚመደብ አያጠራጥርም፤ ምክንያቱም በክርስቶስ ላይ ሌላ ቤዛ የሚጨምር ትምህርት የተስፋፋው በተለይ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን መኾኑ ግልጥ ነው። “መልክአ ፍልሰታ” የተሠኘውን፥ ስለ ሥጋዋ መፍለስ ልዩ ልዩ ሐሳቦችን የሚያቀርበውንና ማርያምን የሚወድሰውን ድርሰት የደረሰው፥ ርሱ ወይም ደብተራዎቹ መኾናቸው ከዚህ በፊት ተጠቅሷል። ይህ ድርሰት የማርያምን ሞትና ትንሣኤ የሚተርከውን ትረካ፥ በአምልኮት ጭምር ለማድመቅ የተሰናዳ ድርሰት መኾኑ ከይዘቱ ይታወቃል። ድርሰቱ የማርያም ፍልሰታ በሚታሰብበት በጾመ ፍልሰታ በሰዓታት ጸሎት ላይ በዜማ ይባላል።

No comments:

Post a Comment