ይህንን
አስመልክቶ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው ላይ ሲናገር ‹‹በእንተ
ሔዋን ተዐፅወ ኆኃተ ገነት ወበእንተ ማርያም ድንግል ተርኃወ ለነ
ዳግመ›› በቀዳሚት ሔዋን ምክንያት የገነት ደጃፍ ተዘጋብን
ዳግመኛም ሰለዳጋሚት ሔዋን ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን
በማለት አስገንዝቧል፡፡
ይህንንም ምሥጢር ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አሞንዮስ
አውሳቢዮስ በቅድመ ወንጌል ሲገልጡ ‹‹ወበከመ ተኃብአ ሰይጣን
በጉሕሉቱ ውስተ ሥጋ ከይሲ ከማሁ ኮነ ድኅነትነ በተሰውሮተ ቃል
እግዚአብሔር በዘመድኀ›› ሰይጣን በስጋ ከይሲ ተሰውሮ አዳምን
እንዳሳተው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስም በሥጋ
ብእሲ ተሰውሮ መጥቶ አለምን እንዳዳነ፡፡ (ትርጓሜ ወንጌል ገፅ
28) በማለት ተናግረዋል
በቀዳሚት ሔዋንና በዳግሚት ሔዋን መካከል ያለውን ምስጢራዊ
ንጽጽር አስመልክቶ ‹‹ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ›› በመባል
የሚታወቀው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲገልጽ ዳግሚት ሔዋን
የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍሬ የሕይወት
መድኃኒት የሆነው ጌታ የተገኘባት አማናዊት ዕፀ ሕይወት በመሆኗ
የዕፀ በለስን ፍሬ በልታ ሞትን ላመጣችብን ለቀዳሚት ሔዋን ካሣ
ናት፡፡ ምክንያቱም ከዳግሚት ሔዋን ከድንግል ማርያም
የተወለደው የማህፀኗ ፍሬ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስን የሚያርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ
ነፍስን የሚያድል ሕይወተ ሥጋ ሕይወተ ነፍስን የሚሰጥ ቀዳሴ
ሥጋ ወነፍስ (ወመንፈስ) የሆነ ብሩክ አምላክ ነውና፡፡ (አባ
ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ አርጋኖን ገጽ 328-329)፡
‹‹ተፈስሒ ኦ ቅዱስት አሞሙ ለኩሎሙ ሕያዋን ናንቀዐዱ ኃቤኪ
ትሰዕሊ በእንቲአነ›› በመንፈስ ልደት የከበሩ ቅዱሳን ሕያዋን
የሆኑበት ማየ ገቦ የተገኘብሽ የሕያዋን ፃድቃን እናታቸው ንዕድ
ክብርት እመቤታችን ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም በቅዱስ ዮሐንስ
አንጻር ልጆችሽ የምንሆን እናታችን ድንግል ማርያም ሆይ ደስ
ይበልሽ፡፡ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ
ትለምኚልን ዘንድ ዓይነ ኅሊናችንን ወደ አንቺ እናነሣለን እያሉ
ዘወትር ያከብሯታል ያመሠግኗታል ይማጸኑባታልም፡፡ (ውዳሴ
ማርያም ትርጓሜ ገጽ 58፡59)፡
ይህንን አስመልክቶ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ሲናገር "" በእንተ ሔዋን ተዐጽወ ኖኅተ ገነት ወበእንተ ማርያም ድንግል ተርኅወ ለነ ዳግመ : በቀዳሚት ሔዋን ምክንያት የገነት ደጃፍ ተዘጋብን ዳግመኛም ስለ ዳግሚት ሔዋን ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን "" በማለት አስገንባል :: ከዚህም ሌላ ሰፊና ጥልቅ በሆነው የነገረ ማርያም አስተምህሮው የዜና አበው ሊቃውንት "" የነገረ ማርያም አባት "" እያሉ የሚጠሩት ታላቁ የቤተክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ሔኔሬዎስ ከላይ የገለጥነውን ኃይለ ቃል መሠረት በማድረግ እመቤታችን "" የሔዋን ጠበቃ አለኝታ "" ብሏታል :: በዜና አበው ክፍለ ትምህርት እንደሚታወቀው ይህ አባት የነበረበት ዘመን "" የነገረ ማርያም ዘመነ ልደት "" በመባል ይታወቃል ::
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለነገር ድኅነት መሠረት መሆኗን በመግለጥ የተአምሯ መጽሐፍ "" እግዝእትነ ማርያም ነበረት እምቅድመ ዓለም በኅሊና አምላክ "" ይላል
No comments:
Post a Comment