1- ድንግል ማርያም የአዳም ልጅ አይደለችምን? ከሆነችስ ያለ ልዩነት "በአንዱ አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች ሆኑ" የሚለው ቃል እንዴት አይመለከታትም?
2- የጌታ መሞትና ማዳን እርስዋን የማይመለከት ነውን? ጌታ ለእርስዋም ካልሞተ "መድኃኒቴ" ለምን አለችው?
3- እርስዋን ጥንተ አብሶ ካለባት እናቷ ያለ ጥንተ አብሶ እንድትወለድ ካደረገ ክርስቶስስ ጥንተ አብሶ ካለባት እናቱ ንፁህ ሆኖ መወለድ አይችልምን?
1- ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በመመረቂያ ፅሁፋቸው እንዲህ አሉ፦ "እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ድንግል ማርያም ለእግዚአብሔር የመታዘዝና የእምነት አርኣያና ምሳሌ ናት።በሁለት ወገን ድንግል ናት።በሥጋም በነፍስም።#የተፀነሰችው_ያለ_ጥንተ_አብሶ ወይም #ከጥንተ_አብሶ_ነፃ_ናት" #ባንልም ቅሉ ቅድስተ ቅዱሳን ንፅህት በእግዚአብሔር የማዳን ሥራና በሥጋዌው ሱታፌ ያላት ናት።" ወልታ ፅድቅ.ገፅ.192-193
2- መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የተባሉ ሊቅ በ "መሰረተ ሃይማኖትና የካህናት ተልእኮ" በሚለው መፅሐፋቸው ገፅ.29 ላይ፦ "አንዳንዶች እመቤታችን አድፎ የነበረው የአዳም ጠባይ ወይም #ጥንተ_አብሶ_እንደሌለባት_ያስተምራሉ፤ነገር ግን ይሄ ትምህርት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን #ተቀባይነት_የለውም።ምክንያቱም እመቤታችን ከኢያቄም ከሐና በሕጋዊ ሩካቤ የተገኘች ናት። #ካሣ_የማያሳስፈልጋትም_ሳትሆን_ክርስቶስ_በደሙ_ከዋጃቸው_ካሣም_ከተከፈለላቸው_ወገን_ናት፤ሆኖም እንደ አዳምና ሔዋን የምኞት የመናገርና የገቢር ኃጢአት ፈፅሞ የለባትም።" ብለዋል።
3- አሥራት ገብረማርያም በትምህርተ መለኮት መፅሐፋቸው #1983ቱ እትም ገፅ.96 ላይ ፦ "በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነት መሰረት በሉቃ.1:38 ላይ የመልአኩን ብሥራት ተቀብላ "እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" ብላ እምነቷን በእግዚአብሔር ላይ ባሳረፈች ጊዜ ጌታን ከመውለዷ በፊት መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን ቀድሶና #አንፅቶ_የጥንቱን_የአዳምን_ኃጢአት አስወግዶላታል።……በሌላ በኩል ደግሞ የቀድሞው የአዳም ኃጢአት የሚወረሰው በወንድ ዘር አማካኝነት ልጅ በሚወለድበት ጊዜ ከአባት ወደ ልጅ በመሆኑና ጌታ ግን የተወለደው መንፈስ ቅዱስ #የጥንቱን_ኃጢአት_ካስወገደላት ከእናት ብቻ ስለሆነ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የጥንቱን የአዳም ኃጢአት አልወረሰም።"
የአቡነ ሺኖዳንና የምሥራቃውያንን እንዲሁም የኢትዮጵያን ጥቂት ሀሳብ በክፍል ሁለት እጨምርበታለሁ።
ሻሎም!!



No comments:
Post a Comment