Monday, January 18, 2021

🗣በብርሃኑ(ምሕረት የበዛለት)
👉በሁለት ክፍል በፃፍኩት ፅሁፍ አንዳንዶች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከአዳምና ከሔዋን የኃጢአታቸውን ውጤት እንጂ ኃጢአታቸውን አንወርስም ብላ ነው ምታምነው ላሉኝ ጥቂት ምላሽ ለመስጠት ያክል አባቶች የፃፉትን እጠቅሳለሁ።
1- አቡነ መልከ ፄዴቅ ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ትምህርት በሚለው መፅሐፋቸው ገፅ.142-143 "የኃጢአተኛ ልጅ ኃጢአተኛ ነው፤ የጥንተ አብሶ ኃጢአት ከዘር ጋር አብሮ እንደሚወረስ "እስመ ናሁ በኃጢአት ተፀነስኩ፥ወበዓመፃ ወለደተኒ እምዬ…እነሆ በኃጢአት ተፀንሼ በዓመፃ ተወለድኩ" ብሎ ንጉሥ ዳዊት አረጋግጧል፤ከውኃና ከመንፈስ የሆነ ዳግም ልደት ያስፈለገውም ከወላጅ በሆነው ልደት #ኃጢአት_በዘር_ስለሚተላለፍ እርሱን ለመደምሰስ ነው" ብለዋል።
2- ሊቀ ጉባኤ አበራ በቀለ፦ ትምህርተ ሃይማኖት እና ክርስቲያናዊ ሕይወት በሚለው መፅሐፋቸው ገፅ.90 ላይ እንዲህ ብለዋል፦ "የመጀመሪያው ሰው አዳም የፈፀመው በደልና የደረሰበት መርገም ሁለቱም አይለያዩም።ሁለቱም ወደ አዳም ልጆች ከትውልድ ወደ ትውልድ ተላልፈዋል"
3- የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም እንዲህ ብላ ተናግራለች፦ #We_are_born_with_Adam's_sin and its Consquence, which is death; for death is the wage of sin. Adam's sin has infected all his posterity; and the corrupt nature inherited from Adam drags all his posterity into sin…………#ከአዳም_ኃጢአትና_ከኃጢአቱ_ውጤት ይኸውም ሞት ጋር #ተወልደናል፤የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና።የአዳም ኃጢአት ከእርሱ ሚወለዱትን ሁሉ አጉድፏል፤ከአዳም የተወረሰው የጎደፈ ተፈጥሮ የእርሱን ዘሮች ሁሉ ወደ ኃጢአት ስቧቸዋል" በማለት ኃጢአቱንም ውጤቱንም ወርሰን እንደምንወለድ ያትታሉ።(ወልታ ፅድቅ. ገፅ.153)
4- ቅዱስ አትናቴዎስም በቅዳሴው አዳምና ሔዋንን " #እናንተ_እኛን_ናችሁ#እኛም_እናንተን_ነን" ይላል ይሄውም ትርጉሙ በደላቸው በደላችን መሆኑን ለማመላከት ነው።ቅዳሴ አትናቴዎስ.ገፅ.255. ወልታ ፅድቅ.ገፅ.159-160
5- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ኃጢአትን እንደምንወርስ ማስተማር የተለመደ መሆኑ ቢታወቅም አሁን አሁን የሚነሱ የማህበረ ቅዱሳን ትውልዶች ግን ውጤቱን እንጂ ኃጢአቱን አንወርስም ወደሚል ትምህርት ቢያዘነብሉም ወደ ሊቃውንቱ ግን ገና ያልገባ መሆኑን ከላይ የጠቀስኳቸው ሊቃውንት ምሥክር ናቸው።እስከዛሬም ብዙ ሰዎች ከቤተክርስቲያኒቱ ብዙ መምህራን በማኅበረ ቅዱሳን አነሳሽነት ተሐድሶ እየተባሉ ሚሰደዱት "ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ(የውርስ ኃጢአት) ነበረባት" ብለዋል እየተባሉ ነበር።ኃጢአት ካልተወረሰ የደኅንነት ትምህርት እንደሚናጋ ያስተዋሉት አይመስልም።የሆነ ሆኖ ከላይ ሌሎች ፀሀፊዎች የፃፉትን መጥቀሴ ለእነርሱ ከእነርሱ ሰዎች መጥቀሴ እንጂ መፅሐፍ ቅዱስ በቂዬ መሆኑን ዘንግቼ አይደለም።
❤️“#በአንዱ ሰው #አለመታዘዝ ብዙዎች #ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ #በአንዱ #መታዘዝ ብዙዎች #ጻድቃን ይሆናሉ።”
— ሮሜ 5፥19
ሻሎም!!
Image may contain: 2 people

No comments:

Post a Comment