ይህ ጠልሰም በመፅሐፈ ቱላዳን እንዲሁም በሌሎች መፃሕፍት ውስጥ ይገኛል። ቱላዳን የተሰኘው መፅሐፍ የኢትዮጵያውያን አባት ታላቁ ሊቀ ሰማእት ቅዱስ ጊዮርጊስ አረማውያን ፈተና ሲያፀኑበት ፈተናውን ለመታገስ፣ ለመቋቋም፣ ለማሳለፍ እንዲሁም ታላላቅ ተአምራትን ለመፈፀም ወደ አምላኩ ያቀረበውን ፀሎትና ምስጋና እንዲሁም ሌሎች ጥበባትን የያዘ መንፈሳዊ መፅሐፍ ነው።
ከስር የሰጠኸን ጠልሰም ላይ የሚታዩት ሁለት ዘንዶዎች ሌዋትን እና ብሔሞት ይሰኛሉ። እነዚህ ሁለት ዘንዶዎች እስከ ምፅአት ምድርን ከበው እንደሚገኙ አባቶች ያስተምራሉ። በተጨማሪ ሌዋታን እና ብሔሞት ከምድራችን ጋር ስላላቸው ቁርኝት በመፅሐ አክሲማሮስና በስነፍጥረት አንድምታ መፅሐፍት ላይ ሰፊ እውቀት ስላለ እነርሱን እንድታነብ እንመክርሃለን።
በክብ ቅርፁ መሀል ያሉት የእግዚአብሔር መለኮታዊ ስሞች ሲሆን እንደየ መፃሕፍቱ ልዩነት ስላለው በሌሎች መፅሐፍት ላይ የቅዱሳን መላእክት ስም ተጠልስሞ ይነበባል!
እግዚአብሔር አገራችንን ኢትዮጵያን እና ሊቃውንቶቿን ይጠብቅልን። አሜን

No comments:
Post a Comment