Thursday, February 11, 2021
መጋቤ ሐዲስ እሸቱን ምን አበሳጫቸው ? እግዚአብሔርስ ተሳደቡልኝ ብሎ አዞናልን ? ( ክፍል አንድ )መጋቤ ሐዲስ እሸቱን ምን አበሳጫቸው ? እግዚአብሔርስ ተሳደቡልኝ ብሎ አዞናልን ? ግጭቱ የተነሳው ታክሲ ውስጥ ነው :: ድንግል ማርያም እንደኛ ሰው ናት የሚሉ የወንጌላውያን ቤተክርስቲያን አማኞች የሆኑ ሦስት እህቶች ከአንዲት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኝ ጋር ባደረጉት ውይይት ኦርቶዶክሳዊትዋ አማኝ መልስ ያልነበራት በመሆኑ እኚሁ መጋቢ ሐዲስ እሸቱ በገዛ አንደበታቸው እንዲህ ሲሉ ስለዚህች እህት ተናግረው ነበር :: ብዙ ጥቅስ የሌለው ሰው ብስጭት ይቀናዋልና በጣም ተናደደች አሉን :: አያይዘውም በዚህ ጉዳይ እርሳቸውም ሳይቀሩ የባሱ ሆነው የተገኙ መሆናቸውን በመግለጽ << እውነት ለመናገር እኔ ራሴ እነዚህ ሰዎች ድንግል ማርያምን እንደኛ ሰው ናት ሲሉ መቋቋም አልቻልኩም ነበር >> አሉን :: ታድያ የትኛውን ጉዳይ መቋቋም እንዳልቻሉ ግልጽ ባያደርጉልንም አያይዘው የሰነዘሩአቸው የስድብ ቃሎችና ጽርፈቶች ግን ተናደደች ቃል ስላጣች ያሉአትን ብቻ ሳይሆን እርሳቸውንም ጭምር ውይይቱ ያናደደ ፣ መልስ ያሳጣና ለሽንፈት ሳይቀር የዳረገ መሆኑን እርሳቸው ራሳቸው በገዛ አፋችው ተናደው ከሰነዘሩአቸው የስድብና የዘለፋ ኃይለ ቃሎች መረዳት ችያለሁ :: የመጣው የእውነት ቃል ደግሞ በማንም ይምጣ በማን ፣ ማንም ይናገረው ፣ የትኛውም ሰው ይስበከው ቢያሸንፈን ለጥቅማችን የተነገረ በመሆኑ ምንም የሚያበሳጨን ነገር ሊኖር አይገባም ነበር :: መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ግን ከልጅትዋ በላይ ተበሳጩ ፣ የስድብና የዘለፋ ቃሎችንም በልጆቹ ላይ ሰነዘሩ :: እንደገናም ቁጣው አልበርድላቸው ብሎ ዩቲዩብ ላይ ሳይቀር መጥተው ገነፈሉ ተንተከተኩ :: ለዚህም ነው ከላይ ያሉትን ሁለት መጠይቆች በማንሳት የትምህርቴ መነሻ ሃሳብ ያደረኩት ፤ መጋቢ ሐዲስ እሸቱን ምን አበሳጫቸው ? እግዚአብሔርስ ተሳደቡልኝ ብሎ አዞናልን ? መልሱን በተከታዩ ትምህርቶች ይከታተሉ ተባረኩ ሼር ሼር ሼር ይደረግ ቅዱሳን ጠቃሚ መረጃ ስለሆነ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ተበሳጭተው የተናገሩበትና የተዛለፉበት የዩቲዩብ ሊንክ ሰምተው እርስዎም እንዳይደግምዎት ይጠንቀቁ https://youtu.be/Ofwl7tit5QU
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment