ማተብ ማሰር የጣዖታዊያን መገለጫ ነው!
የአገራችን ኦርቶዶክስ አማኞች ከመጽሐፍ ቅዱስ ትዕዛዝ ይልቅ ተራ የፈጠራ ድርጊቶችን ለእምነታቸው እንደዋነኛ መሠረት አድርጎ የመውሰድ አባዜ በብዛት ይታያባቸዋል፥ ሆኖም ግን እነዚህ ድርጊቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ያልታዘዙ እና በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የማይታወቁ የፈጠራ ድርጊቶች ናቸው።
ከነዚህ አንዱ አንገት ላይ ክር ማሰር ነው፥ አንገት ላይ ክር ማሰር መቼ እና እንዴት እንደተጀመረ በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ብንፈትሽ፦ "ምዕመኑ አንገታቸው ላይ ክር ይሰሩ" ብሎ አያዝም፥ ሆኖም ግን አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ያለ ዐውዳቸው ጠምዝጦ፦" ክር ማሰር የተፈቀደ ነው" ለማለት ሲሞክሩ እናያለን። ከዛ ውስጥ አንዱ በመጽሐ ምሳሌ ምዕራፍ ስድስት ላይ ያለን ጥቅስ ነው፦
እዚህ ክፍል ላይ በጭራሽ፦ "አንገት ላይ ክር እሰሩ" የሚል ትዕዛዝ የለም፥ «በአንገትህ እሰረው» ሚለውን ቃል መዞ አውጥቶ ከክር ጋር ለማገናኘት መሞከር ተገቢ አይደለም። ቃሉ የሚያወራው ሕግ እና ትዕዛዝን ስለመጠበቅ ነው «በአንገትህ እሰረው» ከሚለው በፊት «በልብህ አኑረው» የሚል ቃል እናገኛለን፥ እና በአንገታችሁ ከሚታሰረው በተጨማሪ በልባችሁም ውስጥ ክር ታኖራላችሁ ማለት ነው?
በተጨማሪም ፦
ምሳሌ 3፥3:“ምሕረት እና እውነት ከአንተ አይራቁ! በአንገትህ እሰራቸው! በልብህ ጽላት ጻፋቸው!።”
"ምጽዋትና ሃይማኖት ከአንተ አይራቁ በአንገትህ አሰራቸው በልብህ ጽላትም ጻፋቸው" ( የኦርቶዶክሱ 81 የ2000 እትም )
እነዚህ ጥቅሶች በሙሉ መልዕክታቸው ሕግና ትዕዛዝን ጠበቅ እውነተኛና መሐሪ ሁን እንጅ አንገትህ ላይ ክር እሰር የሚል ትርጉም የላቸውም ።
መጽሔተ አሚን ፦ « የኦርቶዶክስን ሃይማኖት ባህልና ታሪክ አምስቱ አዕማደ ሚስጥር በዓለም ውስጥ የሚገኙ ሃይማኖቶች ስልቶችና ባህላቸው፣ ከኒቂያ ጀምሮ ስለ ሃይማኖት የተሰበሰቡት ጉባኤዎችን፣ በኢትዮጵያ ስለ የተሾሙትን ጳጳሳት እና እጨጌዎችን ተራ ቁጥር የሚያሳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ነው። በዚህ መጽሐፍ ገጽ 61 « ስለ ምንኩስና አጭር ታሪክ » በሚለው ክፍል ላይ፦
« ብራህማዎች የህንድ ካህናት የተባሉት #ሶስት #አማልክት #አሉ #ብለው #ያምናሉ #ከሙሴ #በፊት #ሶስትነትን #መጀመሪያ #የገለጹ #እነርሱ #ናቸው ይባላል፥ የበራህማ ወገኖች የሚለዩበት ምክኒያት ከአንገታቸው ላይ ነጭ ክር(ማተብ) ያስራሉ። ይህም ልምድ በአገራችን በኢትዮጵያ የተለመደ ነው፥ መነኮሳቱ የክር ማተብ ወይም ቅናት የሚባለውን ያስራሉ። በሕዝቡም ዘንድ የተለመደ የክርስቲያን ምልክት ሆኖ ይኖራል፥ በዚሁ ሥራቸው የህንድ መናኒያንና ናዝራዊያን ለክርስትና ምንኩስና ፊታውራሪ ሆኑ ይባላል»
በዚህ መጽሐፍ ላይ ከሙሴ በፊት በሥላሴ(ሦስት አማልክት) አለ ብለው ያምኑ የነበሩ የህንድ ጣዖታዊያን ራሳቸውን የሚለዩት እንደዛሬው የአገራችን ኦርቶዶክስ አንገታቸው ላይ ማተብ በማሰር ነበር፥ ይህን የጣዖታዊያን መገለጫ የሆነን ተግባር የአገራችን የኦርቶዶክስ አማኞች ልክ እንደ የሃይማኖታቸው መሠረት አድርጎ ሲጨነቁ ማየተ ያስገርማል። ልምዱ የጣዖታዊያን እንጅ የመጽሐፍ ቅዱስ ትዕዛዝ አይደለም ።
No comments:
Post a Comment