Wednesday, June 5, 2024
በመልካም ሁኔታ ተመሥርታ መልካም ጐን የነበራት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በግብጻውያን ጳጳሳት መሪዎች ምክንያት ውድቀቷ የጀመረበት ጊዜ ክፍል ሦስት
በመልካም ሁኔታ ተመሥርታ መልካም ጐን የነበራት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በግብጻውያን ጳጳሳት መሪዎች ምክንያት ውድቀቷ የጀመረበት ጊዜ ክፍል ሦስት
በመልካም ሁኔታ ተመሥርታ መልካም ጐን የነበራት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በግብጻውያን ጳጳሳት መሪዎች ምክንያት ውድቀቷ የጀመረበት ጊዜ
ክፍል ሦስት
ሰላም ሰላም የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንዴት ናችሁ ተባረኩ የዛሬው ትምህርት እንዲያመልጣችሁ አያስፈልግምና የተለቀቀውን ቪዲዮ ከፍታችሁ ደጋግማችሁ ስሙ ይህ ትምህርት ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን በዋናነት የሚመለከት ቢሆንም ከዚያ መልስ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ተጠርተው ላሉ አማኞች የምሥራቹን ቃል ለሚሰብኩ ለሚያስተምሩና ለሚመሩ አብያተክርስቲያናት መሪዎች እንዲሁም አገልጋዮቻቸው ጭምር ጥሩ ማስገንዘቢያና ማስተዋልን የሚሰጥ ወቅታዊ ፣ አስፈላጊም የሆነ ትምህርት ነው
በደገኛው መሪ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ተቋቁማ ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት የሚል ስያሜ ይዛ በነገሥታቱ ፈቃድ ብሔራዊነትን አግኝታ አገር አቀፍ እንቅስቃሴ የጀመረችው ቤተክርስቲያን መልካም በሆኑ ተግባሮችዋ እና በጥሩ ጐንዋ ያስደመመችን ቢሆንም ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ሥራውን በክብር አጠናቆ ካረፈ በኋላ ከእርሱ በመቀጠል የተነሱት ሰዎች ማንም ከማንም አይበልጥም አያንስምም ማን ማንን ሊመራ ይችላል ? የማን ቤት ጠፍቶ የማን ይበጅ ቀረርቶ በሚል ተረታዊ ባሕልና እኔነት ፣ የእበልጥ ባይነትና የውድድር አተካሮ ውስጥ ገብተው ግብጾች ይምሩን ፍሬምናጦስን የሾሙ እነርሱ ናቸውና በሚል ደካማ ሃሳብ የዝሆን ጥርስ ፣ ወርቅ ፣ አልማዝ ፣ ብርና የመሣሠሉትን ይዘው በመሄድ ቤተክርስቲያኒቱን አሳልፈው ለግብጻውያን ሰጡ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ የቤተክርስቲያኒቱ ውድቀት የጀመረው ግብጻውያኑ መልካም አባቶችና እውነተኛም መንፈሳዊ መሪዎች ሆነው የክርስቶስ ኢየሱስን ወንጌል በመስበክ ቤተክርስቲያኒቱን ለተሻለ ክብር ቢያበቁ እንዴት መልካም በሆነ ነበር ነገር ግን ያ ሳይሆን ቀርቶ መንፈሳዊነቱ በሥጋዊ ጥቅም ተቀየረ ግብጻውያኑም ከተረከቡት ሃላፊነትና ሥልጣን ይልቅ በኢትዮጵያውያኑ በኩል በየጊዜው የሚገበርላቸው ወርቅና ብር እንዲሁም የዝሆን ጥርስ በልጦባቸው ለአንድ ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት ያክል ቤተክርስቲያኒቱን ለከፋ ውድቀት ዳረጓት ይህ ብቻ አይደለም በፍትሐ ነገሥት መጽሐፍ ላይ ኢይሲሙ ጳጳሳተ እማዕምራኒሆሙ በማለት በስርዋጽ አስገብተው ትርጉሙም ከሊቃውንቶቻቸው መካከል ጳጳሳትን አይሹሙ ማለት ነውና ከላይ ከሐዋርያት በመለኮታዊ ኃይል የወረደ ድንጋጌ በማስመሰል አኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ሹመቱን ቢጠይቁም ለዚህ ነገር የማይበቁና መጠየቃቸው እንኩዋ ሳይቀር ትልቅ ኃጢአትን የሚያወርድና መቅሰፍትንም ጭምር የሚያመጣብን መሆኑን በመንገር የኢትዮጵያው ንጉሣችን የግብጽን ቤተክህነት ይቅርታ እንዲጠይቅ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንቱም ጥፋተኞች ነን ሲሉ እንዲሸማቀቁ ዝቅ ብለውም እንዲያደገድጉም ሆነ እንዲያጎበድዱ አድርገዋቸዋል ይህንና የመሣሠሉትን ሁሉ ማድረጋቸው ኢትዮጵያውያን የነቁብን እንደሆነ ዓባይን ይገድቡብናል ቤተክርስቲያኒቱንም ከእኛ እጅ አውጥተው የራሳቸው በማድረግ የለመድነውን ወርቅ ብር አልማዝና የመሣሠሉትን ሁሉ ያስቀሩብናል በማለት አስበው ነው ቤተክርስቲያናችንንም እንደራሳቸው አጥቢያ አድርገው ይመለከቷት ነበርና እነዚህን ነገሮች ሁሉ ቢያስቡና ቢያደርጉ አይደንቅም ነገር ግን በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እገዛና በመምህራኖቻችን እልህ አስጨራሽ ትግል ቤተክርስቲያናችን ከግብጻውያን እጅ ወጥታ የራስዋን ሥልጣን የራስዋ ማድረግ ቻለች በገዛ ልጆችዋም መመራት ጀመረች ይሁን እንጂ በእነዚህ አስከፊ የጨለማና የባርነት ዓመታት ውስጥ እነዚህ ደበሎ ለባሽ የኮፕቲክ መነኮሳት ድሪንቶአቸውንና አቧራቸውን ያራገፉብን በመሆናቸው ቤተክርስቲያናችን እስከ ዛሬ ድረስ ከወንጌሉ እውነት ወጥታ ወደ ተመሠረተችበት የእግዚአብሔር ቃል መሠረትና የእምነት መግለጫዋ እንዳትመለስ ዓይነተኛ የጥፋት ምክንያት ሆኑ ከዚህ የተነሣ እስካሁንዋ ሰዓት እስከ እኛ ዘመን ድረስ እነዚሁ ግብጻውያን የታሪክ ተወቃሽ ሆነው ይኖራሉ በፍጻሜውም ዘመናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ከተጠያቂነት አያመልጡም
የተወደዳችሁ ወገኖች መሪነት ምሳሌነት ነው ለዚህም ነው በ2ኛ ጢሞቴዎስ 3: 10 ላይ አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ ያለው ስለዚህ አንድ ሰው በሃላፊነት ተመድቦ ከመሥራቱና ይህንንም ሃላፊነት ከመውሰዱ በፊት ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ማየት አለበት መሪ የምንሆነው እንደ ኮፕቲክ መነኮሳት ባለ አፍቅሮ ንዋይ ውስጥ ተዘፍቀንና ተጠምደን ፣ ሥልጣናችንን በመጠቀም ወርቅና ብር ለማጋበስ ከሆነ ወርቅና ብሩ አልቆ ወይንም ቀርቶብን በምትኩ ሌላ ነገር ሲመጣ መቆም ያቅተንና ጥለን እንፈረጥጣለን ግብጻውያኑ ደበሎ ለባሽ መነኮሳት ያደረጉት ይህንኑ ነበር የጣሊያን ወረራ ሲመጣ ወንበራቸውን እስከ ጊዜውም ድረስ ቢሆን ሊጠብቅላቸውና ሊያስጠብቅላቸው የሚችለውን ጊዜያዊና ተጠባባቂ ሰው መድበው ጥለውን ፈረጠጡ ዛሬም ታድያ በኦርቶዶክሳዊቷ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በወንጌላውያኑም አብያተክርስቲያናት ጭምር ይሄ ስሕተት እንዳይደገም ሥጋቴ ነው ለምን ብትሉኝ ዛሬ ላይ ከእኔ ወዲያ ሲል አላስይዝ ብሎ መድረኩን የሞላው ፓስተር ሁሉ በነገው የመከራ ዘመን አሳማኝ በሚላቸው ልዩ ልዩ ምክንያታዊ ጥቅሶቹ የየራሱን የምቾት ቀጠና በማዘጋጀትና በማደላደል መንጋውንም በትኖ ለአውሬ በመስጠት እግሬ አውጪኝ ሲል ሲኮበልልም እንዳይገኝ ይልቁንም እንደ ሐዋርያው እንደ ጳውሎስ በመከራም ጭምር ጸንቶ በመቆም ምሳሌ የሆነውን የተፈተነ ሕይወቱን ለሕዝቡ እንዲያሳይ ጽኑ የሆነውን ምክሬን ለማስተላለፍ እወዳለሁ 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2 : 15 እንደገናም ግብጻውያን መነኮሳት ከጣልያን ወራራ መልስ ተመልሰው መጥተው ወንበራቸውን በመያዝ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የባጣ ቆዪኝ ቤት ሊያደርጓት እንደ ሞከሩት ሁሉ ዛሬም ኦርቶዶክሳዊት ብቻ ሳትሆን ማንኛዋም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የባጣ ቆዪኝ ቤት አይደለችምና ቤተክርስቲያንን የባጣ ቆዪኝ ቤት ሊያደርጉ እንዲህ ዓይነቱን አስነዋሪ ተግባር ለሚፈጽሙ አሁንም ቤተክርስቲያን የራስዋ የሆነን ፈጣን የዲሲፒሊን እርምጃ ልትወስድ ይገባታል እንጂ ጉዳዩን እንዲሁ በቸልታ ልታየውና ልታልፈው አያስፈልግም የሚል መልዕክት አለኝ ቤተክርስቲያንን ደግሞ እኛ አገልጋዮችዋና መሪዎቿ ብንተዋት የሞተላት ኢየሱስ ግን ፈጽሞ አይተዋትም የራሱ የሆኑ ታማኝ ሎሌዎቹን በማስነሳት እስከ ፍጻሜው ድረስ ይጠብቃታል በመጨረሻም ቤተክርስቲያን ለሌላ ላትሆን አንዴ ለእርሱና ለራሱ ስለሆነች ከራሱ ጋር ለዘላለም ሊያኖራት እርሱ ራሱ መጥቶ ይወስዳታል ወገኖች ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን ተከታተሉ በተረፈ በክፍል አራት ትምህርታችን እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑ የምላችሁ
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
Advertisements
Occasionally, some of your visitors may see an advertisement here,
as well as a Privacy & Cookies banner at the bottom of the page.
You can hide ads completely by upgrading to one of our paid plans.
UPGRADE NOW DISMISS MESSAGE
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment