Wednesday, April 21, 2021

ገላ:3:21 "እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚቃወም ነውን?" አይደለም::

ሕግ የተስጠው ሕይወትን ለማስገኘት አልነበረም ::
የሙሴ ሕግ የአይሁድን ሕዝብ ሕይወት ይቆጣጠር እንደነበር እውነት ቢሆንም ለሕዝቡ መንፈሳዊ ሕይወት አልስጠም: ሊስጥም አይችልም ነበር: ገላ:3:21 ይህንን ክፍል ካየን በኍላ (ገላ:2:21) ስናመሳክረው

"የእግዚአብሔርን ፀጋ አልጥልም ፅድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ::

ሕይወትና ጽድቅ በሕግ በኩል የሚገኙ ቢሆን ኖሮ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞት አያስፈልገውም ነበር::
ነገር ግን ኢየሱስ ሞቷልና ስለዚህ ሕግ ለኃጢአተኞች ሕይወትና ጽድቅ ሊሰጥ ጨርሶ አይችልም ማለት ነው::

እስራኤላውያንን ራስን ወደሚያጸድቅ ሃይማኖታዊ ሥነ-ምግባር የመራቸው"የሕግ አምልኮ" ነበር::
ክርስቶስን እንዳይቀበሉ ያደረጋቸውም ይህ ነበር:.

(ሮሜ:9:30)"እንግዲህ ምን እንላለን?ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም::"

ሕግ የተስጠው ኃጢአትን ለመግለጥ ነበር: ገላ.3:19)
ገላ:3:23-29) [color=blue]

"እምነት ሳይመጣ ሊገለጥ ላለው እምነት ተዘግተን ከሕግ በታች እንጠበቅ ነበር::

እንደዚህ በዕምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኗል :ዕምነት ግን መጥቷልና ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም:: በእምነት በኩል ሁላችሁ በከርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ
ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኍልና::

አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም ወንድም ሰትም የለም ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና::

እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሐም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ::


አንድን ኃጢአተኛ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለማምጣት ሕግና ጸጋ ሲተባበሩ የምናየው እዚህ ላይ ነው::

ሕግ ለአንድ ኃጢአተኛ ጥፋተኛ መሆኑን ሲያሳየው ጸጋ ደግሞ በክርስቶስ ሊያገኘው የሚችለውን ይቅርታ ያሳያዋል::

"ሕግ ቅዱስ ነው:ተዕዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት" (ሮሜ:3:2) ሕጉ የቆሽሽውን ፊታችንን የሚያሳየን መስተዋት ነው(ያዕ:1:22-25)::
የቆሽሽውን ፊታችንን ግን በመስተዋት አንታጠብም:: በኢየሱስ ክርስቶስ ደም በኩል መንጻትን የሚሰጠን ግን ጸጋ ነው (1ኛ ዮሐ:1:7)

ስለዚህ ሕጉን ትክክለኛውና ተገቢው መንገድ የስዎችን ኃጢአት ሲያሳያቸውና አዳኝ ወደሆነው ጌታ ሲመራቸው ነው::

የተሳሳተውና የማይገባው መንገድ ደግሞ ሕግን በመጠበቅ ደህንነትን ለማግኘት መሞከር ነው::
ሕግ አሕዛብም ሆኑ አይሁድ(ጠቅላላ የሰው ዘር) "ከኃጢአት በታች ሁሉን ዘግቶታል"(ገላ:3:22) ሁሉም ኃጢያተኞች ስለ ሆኑ ሁሉም በጸጋ ሊድኑ ይችላሉ:: እግዚአብሔር አንድ እንጂ ሁለት የደህንነት መንገድ የለውም:: ይኽውም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው::[/color]


ገላ:3:28 "ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናች ሁና" የሚለው አባባል እንዴት ግሩም ነው!ሕግ በግለስቦችና በሕዝቦች መካከል ብቻ ሳይሆን በተለያዮ የምግብ ዓይነቶችና እንስሳት መካከል እንኳ ልዮነት አድርጓል::
ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ለመከፋፈል ሳይሆን አንድ ለማድረግ መጣ::

በገላትያ ኅብረተስብ ውስጥ ባሪያዎች እንደ ዕቃ ይቆጠሩ ነበር ሴቶችም ምንም ክብር አልነበራቸውም አይሁዳውያን ደግሞ አሕዛብን ይንቋቸው ነበር ስለሆነም ይህ የገላትያ ክርስቲያኖች ደስ የማያስኝ ታሪክ ነበር::

ፈሪሳውያን በየቀኑ ጥዋት እንዲህ እያሉ ይጸልዮ ነበር: "እግዚአብሔር ሆይ!አይሁድ እንጂ አህዛብ ስላልሆንኩ: ወንድ እንጂ ሴት ስላልሆንኩ: ነጻ ሰው እንጂ ባሪያ ስላልሆንኩ አመስግንሀለሁ":: በክርስቶስ ግን እነዚህ ሁሉ ልዮነቶች ተወግደዋል::ይህ ማለት በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን መንፈሳዊ ግንኙነት በተመለከተ
እነዚህ ነገሮች ዋጋ አይኖራቸውም ማለት ነው::

ሕግ ይህንን ልዮነት ቢያጠናክረውም እግዚአብሔር ግን በጸጋው ለሰዎች ሁሉ ምህረትን ያደርግ ዘንድ በእርሱ ፊት ሁሉም እኩል መሆናቸውን አወጀ (ሮሜ.11:25-32)::

በመጨረሻ ሕግ የእግዚአብሔር ወራሾች ሊያደርገን ፈጽሞ እንደማይችል እናያለን (ገላ:3:29)::እግዚአብሔር የተስፋ ቃል የስጠው ለአብርሐም ዘር ነበር:: ያም ዘር ክርስቶስ ነው::


ጸጋ: "ካሪስ" የሚለውን የግሪክ ቃል የሚተረጉም ሲሆን ሦስት የዕብራይስጥ ቃላን አሳብ ይይዛል እነርሱም "ሞገስ" "ፍቅር" እና "ምሕረት" ወይም "ቸርነት" በተስኙት የአማርኛ ቃላት ይተረጎማሉ::

የእግዚአብሔር ጸጋ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ቀርቧል (ዮሐ:1:16:17)የዘላለም ሕይወት የጸጋ ስጦታ ነው(ሮሜ:6:23)::

ስለዚህ ጸጋ እግዚአብሔር በተለይ ያለው መልካም አስተያየትና የሚያፈልቀው ፍጹም ፍቅር ነው: (ሉቃ:1:28;ቲቶ:2:11::

ጸጋ ለሰው ሁሉ የሚገለጠው ከእግዚአብሔር ቸርነት የተነሳ እንጂ ማንም ሰው የተገባው ሆኖ አይደለም (ሮሜ:4:4-5; 5:6; ኤፌ 2:4)::

እግዚአብሔር በጸጋው ደህንነትን ፈጽሞልናል (ኤፌ:2:6-8
የእግዚአብሔርን ጸጋ የምንቀበለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ
በማመን ነው(ዕብ:4:16)

ያለ ክርስቶስ በሕግ ወይም በሥራ እንጸድቃለን ብንል የጸጋው ተቀባዮች ልንሆን አንችልም (ገላ.5:4-5;
ሮሜ.8:1-2:

ክብር ለአብ ክብር ለወልድ ክብር ለመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን::

No comments:

Post a Comment