በጸጋና በህግ መካከል ለቀረበው ጥያቄ ያለኝ ሀሳብ እንደሚከተለው ነው: መጽሀፍቅዱስ ህግ በሙሴ ጸጋ በጌታ እየሱስ በኩል እንደተሰጥ ይናገራል; ከመጀመርያው ሰው በህግ እንደማይድን እግ/ር ሳያውቅ አልቀረም ይሁን እንጂ ያለህይወት የተሰጠው ህግ የሚፈጽመው ስለጠፋ በሰው ላይ የሀጥያት ምስክር ሆኖ 1500 አመት ገደማ ከሳሽ ሆኖ ኖረ በመጨረሻ ላይ የሚፈጽመው ሰው ተገኘ እርሱም የሰው ልጅ የሆነው እየሱስ ነበር; በዚህ ሀጥያት ተሸነፈ ማለት ነው; በግልጽ ለማስቀመጥ ስለኛ ጌታ እየሱስ ህግን ፈጸመ ሀጥያት በመስቀል ላይ ተገደለ ማለት ነው: ስለዚህ ህግ አፉን ዘጋ ጸጋ እጁን ዘርግቶ ተቀበለን ማለት ነው: ስለዚህ በአዲስ ኪዳን ዘመን የምንጠብቀው አትንካ አትቅመስ የለም ወይንም ከዚህ ብታልፍ የሚባል ነገር የለም ማለት ነው:: የምንጠብቀው ህግ ቢኖር የመንፈስ ህግ ወይንም በፍቅር ላይ የተመሰረተ የመንፈስ ህግ እንጂ ለመዳን የምንጠብቀው ማለቅያ የሌለው ህግ የለንም:: ጸጋ የተባለው ቃል በራሱ የነጽ ስጦታ መሆኑ ነው ---ጌታ የሱስ ይባርካቺሁ::::
ሕግ አልተሻረም:: ኢየሱስ እንዲያሁም አጠነከረው:: ወንድሙን የሰደበ ነፍሰ ገዳይ ነው ተባለ::
ኢየሱስ አስርቱን ትእዛዝ በሁለቱ ፍቅር ትእዛዝ summerize አደረገው እንጂ አልሻረውም::
ሕግን የሚጠብቅ ከኢየሱስ በቀር አንዳች ጻድቅ የለም:: (ሮሜ)
በመስቀሉ ሞት በጸጋ ድነናል:: (ገላቲያ)
ጸጋ አጥያተኝነትን የሚያስክድና ሕግን የምንጠብቅበት ሀይል የሚሰጠን ነው:: (ቲቶ)
በጸጋ ድኛለሁ ብሎ ሕግን የማይጠብቅ አሁንም ከሕግ በታች ያለ ባሪያ ነው:: (ያእቆብ)
በኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጸጋ ከሕግ በላይ ያኖረናል:: ማለትም ሕግን እንድንጠብቅ ያስችለናል:: መዳናችን የሚታወቀው በውስጣችን የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ የእ/ርን ፍቃድ እንድናደርግ ሲያስችለን ነው:: አለበለዚያ ወሬ ብቻ ሆነን እንቀራለን:: ኢየሱስ ጌታ ጌታ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት አይገባም ይላል:: የአባቴን ፍቃድ የሚያደርግ እንጂ ይለናል:: የአባቱ ፍቃድ በእምነት በጸጋ ድነን በመንፈስ ቅዱስ ከሕግ በላይ እንድንኖር ነው::
No comments:
Post a Comment