Wednesday, April 21, 2021


ጸጋ ማለት ምን ማለት ነው? ስፋ ባለ መልኩ ብታብራሩት..

ጸጋ ማለት ምን ማለት ነው? ነጻ ስጦታ ከሚለው የተለየ ማለት ነው?
 May 31, 2011 በ መንፈሳዊ  BINIYAM (120 ነጥቦች) የተጠየቀ

3 መልሶች

 
0ድምጾች
ሮሜ 3 ፡23-24 ቲቶ 2፡11
- ፀጋ በጣም እጂግ ብዙ ትርጉም ያለው ሲሆን በጥቅሉ ግን ፍፁም የሆነ የእግዚያብሄር ስጦጣ ሲሆን የሰጪውን እንጂ የተቀባዩን ማንነት የማያሳይ የማይገባውን ሰው እንደሚገባው አድርጎ የሚቆጥር ሃጢያጠኛን በእምነት ምክንያት ጻድቅ ይሚያደርግ አንድን አማኝ በመንፈስ ብቁ የሚያደርግ ብቃትን የሚሰጥ የእግዚያብሄር የፍፁም ደግነቱ መገለጫ የሆነ ሙሉ ምህረት ስጪ መነሻው መስቀል የሆነ ለክርስቶስ መምጣት የሚያዘጋጅ… መገለጫውና ስራው ብዙ ቢሆንም ማንነቱ ግን አንድና አንድ ብቻ የሆነ እርሱም ኢይሱስ ክርስቶስ መልካሙ አዳኛችን ነው።
 Jun 19, 2011  ስም-አልባ የተመለሰ
 
 
0ድምጾች
ይህን ለሚያነቡ ሁሉ የጌታ ሰላም ይሁን። አሜን!!!

ጸጋ ማለት ምን ማለት ነው? ማንም አማኝ ነኝ የሚል መለስ ለመስጠት የሚያስገድድው ጥያቄ ነው። ጌታ ይባርከውና ወንድም ቢንያም ይህን ጥያቄ ስላቀረበልን እኔ ለራሴ ሰፋ ያለ ትምህርት አገኛለሁ ብዬ አምናለሁ።

ስለ ጸጋ ከዘፍጥረት የሚጀምር ይመስለኛል። ምን ነካው ይህ ሰውዬ! ጥያቄው የአዲስ ኪዳን ጉዳይ ሲጠየቅ ወደ ቡልይ የሚወሰድን አትበሉኝና ትንሽ ላውጋችሁ።

በእግዚአብሔር መልክና በምስላቸው ስላሴ ስለ ፈጠሩን ትልቅ ክብር እና ትልቅ እድል ነው። ይህ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር በምስራቅ በኤደን ገነትን ተከሎ አዳም ይጠብቃትም ዘንድ ያበጃትም ጭምር ከአንድ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ጋር ሰጠው ይኸውም መልካሙንና ክፉን ከሚያስተውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና የሚል ነበር። እንዲህ ያለ ጠቃሚ ምክር አዘል ጉዳይ የፍቅር አባታቸው ነገረው እሱ ግን በወረት ከውሸት አባት ጋር የማይጠቅም ጓደኝነት አበጀ። የተከለከለው ፍሬ በመብላት አዳም ወደቀ። ፈጣርም ከገነት አባረራቸው በሞት ፈንታ ግረው ጥርው እንዲበሉ አዘዛቸው። ይህ በሰዎች ተስፋ የማይቆርጥ እግዚአብሔር በዘፍ 3፡15 እኛ ዛሬ ወንጌል የምንለውን "ቃል" ገባላቸው። ጸጋ እዚህ ላይ የጀመረ ይመስለኛል።

ይህ ብቻ አይደለም ትውልድ በትውልድ እየተተካ በዘላለማዊ ዙፋኑ ላይ ያለውን ፈጣሪ ኩሉ ዓለምን ሰው በመፍጠሩ እስኪጸጸትና በኖህና ቤተሰቡ ጊዜ በውሃ እስኪያጠፋት ድረስ እጅግ አሳዝነውታል። እውነቱን እንናገርና እኛስ እንዴት እንሆን? ወገኖቼ የጌታ ምጻት ብቻ ሳይሆን ምንም ምልክት ያልተሰጠን ምን ጊዜ ሊሆን የሚችል የቤተ ክርስቲያን መነጠቅም አለና እንደ ሌባ እንደሚመጣ አንርሳ። እግዚአብሔር ቃሉን የማያጥፈው ተስፋውን ለመፈጸም ጊዜው ሲደርስ አንዲት ድንግል ብጽእት መረጠና መልአኩን ልኮ አስታወቃት ድንግልም በተዓምር መንፍስ ስለ ጸለላት ወንድ ሳታውቅ አረገዘች የእግዚአብሔርም ልጅ ኢየሱስ የስሙ ትርጉም ሕዝቡን ከሃጢአታቸው ያድናቸዋል የሚባለው ጌታ ተወለደ (ዮሐ 3፡16)

አባዬ! ይህች ጽዋ ከኔ ትለፍ እያለ በገቴሰማኒ ላቡ እንድ ደም እስኪንጠባጠብ ድርስ ጨንቆት ነበር ግን ያባቱን ፈቃድ እንዲሆን የተቀበለ የእግዚአብሔር ልጅ ይባረክ። ሳይበድል በደልኛ ሆኖ ባላደረገው ወንጀል በውሸት ተከሶ በኛ ፈንታ በኛ ቦታ በጎልጎታ መሰቀል ክቡር ደሙን አፈስሶ ለያይቶን የነበረው የጥል ግድግዳ አፍርሶ ከአብ ጋር ለዘላለም አስታርቆናል። ጳውሎስ በእርሱ ሁነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት የማያውቀው አንድያ ልጁን ኃጢአት አደረገው ይላል (2 ቆሮ 5፡21)። አሁን አባቶች እንድ ሚሉት እንሆ ፈረስ እንሆ ሜዳ ሆኖልናል የቀረው የሰው ፈንታ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዲሁ በነጻ የሰጠን አንድያ ልጁ ነው ጸጋ ምክንያቱ በመንፈስ ቅዱስ በኩል እሱን በማመን በሱ በኩል ብቻ ነው ሁሉን ያለ ምንም ዋጋ ሳንከፈል የተሰጠን ያገኘነው። ሳይመሽ አሁኑኑ እንወስንና እጅ ለእጅ በፍቀር ተያይዘን በጨለማ ላሉት እንድርስላቸው። ለዚህ ነው የተጠራነው።

No comments:

Post a Comment