Скопійовано!
አማልክትና ትንሣኤያቸው...
ብዙ አማልክት ተሰቅለዋል፥ ተነሥተዋል (ተረት ቢኾንም) ። ከኢየሱስ በፊት ተሰቅለው ከሞት ስለተነሡ አማልክት እስኪ እንመልከት።
1. የፍሪግያው አቲስ (1170 ቅ.ኢ)
ይህ አምላክ ተብዬ ለኀጢአት ስርየት ነፍሱን የሰጠ ነው ይባልለታል። ላቲኑ “suspensus lingo” ይለዋል፤ “በዕንጨት የተንጠለጠለ” ማለት ነው። ከሞተ በዃላ ተቀበረ፥ ከሞት ተነሣ፥ ዐረገ።
2. የግብጹ ቱሊስ (1700 ቅ.ኢ)
ይህ ግብጻዊ አዳኝ (አምላክ ተብዬ) ልክ እንደ ኢየሱስ ከተሠቃየ በዃላ ሞተ፥ ተቀበረ። ነገር ግን ሞት ሊይዘው አልቻለም። ከሞት ተነሣ፥ ወደ ሰማያትም ዐረገ።
3. (ኤስኺሉስ) ፕሮሜቴዉስ (547 ቅ.ኢ)
ይህ አምላክ ነኝ ባይ እንደ ኢየሱስ በዕንጨት ላይ ተቸነከረ። ሲሞት ተፈጥሮ ተዘባረቀ። መሬት ተናወጠች፥ ዐለቶች ተሠነጠቁ፥ መቃብሮች ተከፈቱ። ይህ አምላክ ተብዬ የተሠቃየበት ምክንያት “ለሰው ልጅ ፍቅር” የሚል ነበር። ግና ርሱም ተነሣ።
4. የሮሙ ቊሪኑስ (506 ቅ.ኢ)
ይህ አምላክ ተብዬ እንዲህ ተብሎለታል፡—
1. ከድንግል ተፀነሰ፤
2. እናቱ ከነገሥታት ዘር ትወለዳለች፤
3. በእኩያን እጅ ተሰቀለ፤
4. ሞቶ ነፍሱን በሰጠ ጊዜ ምድር መላዋ በጨለማ ተዋጠች።
ይህ አምላክ ተብዬ ታዲያ ከሙታን ተነሣ፥ ወደ ሰማያትም ዐረገ።
5. የሶርያው ታሙዝ (1160 ቅ.ኢ)
ይህ አምላክ ተብዬ ለኀጢአት ስርየት የተሰቀለ ነው ይባልለታል። ዩልዩስ ፊርሚኩስ “ለዓለም ድኅነት ሲል ከሙታን የተነሣ” ይለዋል። በ400 ቅ.ገደማ ክቴሲያስ የተባለ ገጣሚ ተቀኝቶለታል፡—
“ታመኑ ቅዱሳን፥ ተመልሷል ጌታችኹ
ታመኑ በጌታ፥ በተነሣላችኹ
ታሙዝ በታገሰው ሕማማት
አግኝተናል እኛ ድኅነት።”
(ተመሳስሎ የተተረጐመ)
6.የህንዱ ክሪሽና (1200 ቅ. ኢ)
ይህን አምላክ ተብዬ ሳታውቁት አልቀራችኹም። በዕንጨት የተሰቀለ ነው። እግሮቹ ኹሉ የተበሱ ናቸው። ታሪኩም የሚከተለው ነው፡—
1. ከድንግል ተወለደ፤
2. ርሱና እናቱ በእረኞች፥ በጠቢባንና በመላእክት ተጐብኝተዋል፤
3. ጨቋኙ ገዥ ካንሳ የበኵር ልጆች ኹሉ ይገደሉ አለ፤
4. በበረሓ ተፈተነ፤
5. በጋንጅስ ወንዝ ተጠመቀ፤
6. አርድእት (ደቂቆች) ነበሩት፤
7. በምሳሌ ያስተምር ነበር። ማሃብሃራታ የተባለ የህንድ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያትተው ይህ ከአምላክ ተብዬ ከሞት ተነሣ። ከዚያም ወደ ሰማያት ዐረገ።
እንግዲህ እኒህ ኹሉ አምላክ ተብዬዎች ሞተው የተነሡ መኾናቸው ነው። ከእነዚህ ኹሉ ተረቶች መኻል ግን ኢየሱስ አስከነዳ። ለምን? አይሁዳዊ ነውና። (ናምሩድ)
https://t.me/orthox
1 947
28
No comments:
Post a Comment