ከተለመዱ አገር በቀል ተረቶች መካከል « የአዳም ቋንቋ ግእዝ ነው» የሚለው ተረት በብዛት በክርስቲያን ወገኖች በተለይ ደግሞ የኦርቶዶክሶች አማኞች ሲደጋግሙት ይሰማል እውነታው ግን "ሁሉም የኔ" የሚል የልጅ አስተሳሰብና ተራ ምኞት ብቻ መሆኑን በራሳቸው የእምነት መጽሐፍት መረዳት ይቻላል ።
ግእዝ አናባቢ ፊደላት እንኳን እንኳን ያልነበሩት ምሉዕ ያልሆነ ቋንቋ ነበር። አናባቢ የተጨመረበት ከሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ በኃላ ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያ ይዞት በገባው በአባ ሰላማ እንደሆነ የቋንቋ ምሁር የሆኑት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወሐዲስ ላይ እንደዚህ ገልጸውታል
«አባ ሰላማ (ከሰቴ ብርሃን) የእብራይስጥና አረብኛን አናባቢ ፊደላት በማዳበሪያነት በመጠቀም የአናባቢ ቅጥያዎችን በመጨመር ያደገ ነው»
(( ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መፅሐፈ ሰዋሰው ወግስ መቅደም 4ኛ ክፍል))
ግእዝ ከአባ ሰላማ (ፍሬምናጦስ) በፊት ያለ አናባቢ በግእዝ ብቻ ነበር አገልግሎት ሚሰጠው « ከካብዕ እስከ ሳብዕ » ያሉት አናባቢዎች አልነበሩም
« ከሣቴ ብርሃን ሰላማ በዘመነ ሐዲስ መጻሕፍትን ከጽርእ ወደ ግእዝ ሲመልስና ሲያስመልስ በግእዝ ቃል ብቻ ለመተርጎም አልመችህ ቢለው የአይሁዶችን ፣የአረቦችንና የጽርእዎችን እንደ ቋንቋው ስርዓት ድምጡን እየለወጠ በሚያስኬድ በነቁጣና በዋየል ከካብዕ እስከ ሳብዕ ያሉትን ስድስቱን አፅጹቅ አግብቶ በጽርእ ቋንቋ ሸ የሚሉ ፊደል ስለሌለ ሸን ሠ ብሎ ከሸነቱ አውጥቶ በንባቡና ባገባቡ ከጽርእ ፊደል አስማምቶ እንደ እብራይስጥ አድሶታል #ለብሉይና ለሐዲስ የበቃና የተቀደሰ ብርሃን የለበሰ #ከዚያ #ወዲህ ነው » (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወሐዲስ ገጽ 29 « ስለ ፊደላት ፯ ነት » የሚለው ክፍል ላይ )
ለምሳሌ፦ አበባ ፣ አበቡ ፣ እባብ የሚሉ ቃላት ቢኖሩ እና ያለ አናባቢ ብንጽፍቸው ሶስቱም በተመሳሳይ
« አበበ » ነው ሚሆኑት በዚህ ኹኔታ የተጻፈን ነገር ይኸ ነው ብሎ መግለፅና ቋንቋው ሙሉ ነበር ብሎ አፍ ሞልቶ መናገሩ ትልቅ ስህተት ነው
በተጨማሪ «አማርኛ ከግእዝ ፣ ግእዝም ከእብራይስጥና ዐረብኛ የተመሰረተ ነው »
(( አማርኛ መጽሔተ ቃላት በመስፍን ልሳኑ 1952 አርትስቲክ ማተሚያ ቤት መሰረታዊ የአማርኛ ፊደል ከሚለው ክፍል ገጽ 15))
እነዚህን መረጃዎች መሠረት አድርገን የአዳም ቋንቋ ግእዝ ነበር መላእክትና ሌሎች ፍጥረታት ግእዝን እንደመግባቢያ ይጠቀሙ ነበር የሚለውን የወገኖቻችን ሙግት ስንፈትሸው ምኞት ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ እነሱ ብቻ በሚያምኑበት የብሉይ ኪዳን ተጨማሪ መጽሐፍ በሆነው መጽሐፈ ኩፍሌ ላይ ፍጥረት ሁሉ የተፈጠረው በእብራይስጥ ቋንቋ እንደሆነና እግዚአብሔርም ከፍጥረቱ ጋር ለመግባባት ይጠቀምበት የነበረው ይህ ቋንቋ እንደሆነ ይገልጻል
መፅሐፈ ኩፍሌ 11 ፣13 1980 ዕትም
ምሥጢርን ገለጥሁለት ዕዝን ልቡናውም እንዲሰማ አንደበቱም እንዲናገር አደረግሁ #ፍጥረቱ #በተፈጠረበት #በእብራይስጥም ቋንቋ ከእርሱ ጋር እናገር ጀመርሁ የአባቶችን መጽሐፎች ወሰደ። እነዚያም የእብራይሰጥ ቋንቋ የተጻፈባቸው ናቸው።
ፍጥረቱ ሁሉ የተፈጠረው በእብራይስጥ ቋንቋ ከሆነና መግባቢያቸው ይኸው ቋንቋ ከሆነ የኦርቶዶክስ ወገኖቻች እናንተ ወይስ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተብሎ ሚታመነው የትኛው ነው ?
✍️ http://t.me/orthox

No comments:
Post a Comment