አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የማርያምን ሥዕል አቅፎ ጡቷን ጠባ፥ ከጡቶቿም ጣዕሙ ድንቅ የሆነ ወተት ፈሰሰለት።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በልጅነቱ ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ አባቱ እንዲማር ለአንድ መምህር ይሰጠዋል፥ ሰባት ዓመት ሙሉ ተምሮ 4ና ፊደል ቁጥር ማጥናት ስለተሳነው መምህሩ ለአባቱ ወስዶ ልጁን መለሰለት። አባቱም በስዕለት ስለወለደው እንደማይቀበለውና ከእሱ ጋር እያገለገለ እንዲቆይ ነገረው፥ አባ ጊዮርጊስም ለመነኮሳት እህል እየፈጨ እዚያው ያገለግል ጀመር።
ታዲያ አንድ ቀን ከማርያም ሥዕል ፊት እየሰገደ ትምህርቱን እንድትገልጥለት ካልሆነ እንድትገድለው ሲለምናት ማርያምም ከመልአኩ ዑራኤል ጋር መጥታ ጽዋ ብርሃን እንዳጠጣችውና የሰማይና የምድር ሚስጥር እንደተገለጸለት ለክብሯ የምስጋናና የውዳሴ መጽሐፍትን እንደጻፈ ይነገራል። ከነዚያ ውስጥ አንዱ የሆነውን « ኆኅተ ብርሃን » የተባለውን መጽሐፍ እንዴት እንደ ደረሰላት ምክኒያቱን በገድሉ ሲናገር እንዲህ ይላል፦
«ዳግመኛም ከዕለታት አንድ ቀን እንደልማዱ ለስም አጠራርዋ ስግደት ይሁንና ከእመቤታችን ሥዕል ፊት ሲጸልይ በፍቅሯ ጣዕም ኅሊናው ተመሰጠ፥ ወደ ሥዕልዋም ሔደ አቀፋትም። በሃይማኖትም #የሥዕልዋን #ጡቶች #ጠባ፥ ከጡቶቿም ጣዕሙ ድንቅ የሆነ ወተት ፈሰሰለት አጠገበችው አረካችውም። ያን ጊዜም በመንፈስ ቅዱስ ደስ ተሰኘ ለምስጋናዋ ክብር የሚገባ ኆኅተ ብርሃን የተባለ መጽሐፍንም ደረሰላት » (ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ምዕራፍ 4 ቁጥር 1—2)
ምሥል ፦ በተመሳሳይ በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የነበረውና ከማርያም ጡት እንደጠባ የሚናገረው ቅዱስ በርናንድ አባ ጊዮርጊስ በ13 መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ እንደነበሩ ልብ ይሏል።
ለተጨማሪ በቴሌግራም ያግኙን
http://telegram.me/orthox
No comments:
Post a Comment