Wednesday, June 9, 2021

ስለ ምናባዊው ሰለሞናዊ መንግሥት እንደ አንደኛ መረጃ የሚቆጠረው ክብረ ነገሥት የተባለው ተረት ከቤተ ክርስቲያን መጽሐፍት ጋር ያለው መፋለስ ክብረ ነገሥት በጥበቡ ተማርካ ንጉሥ ሰለሞንን ለማየት የሄደችው ንግሥት ኢትዮጵያዊ ናት ከሰለሞን ጋር ዝሙት ፈጽማ ምኒልክ የሚባል ልጅ ወልዳለች ልጁ አድጎ ወደ ሰለሞን ተመልሶ በመሄድ የሙሴን ጽላት ሰርቆ አመጣ ከእርሱ በኃላ ኢትዮጵያ ውስጥ መንገሥ የሚችሉት የእርሱ ዘሮች ብቻ(ሰለሞናዊያን) ናቸው የሚል ምናባዊ ድርሰት ነው እንደ ክብረ ነገሥት ገለጻ ንግሥተ ሳባ ሰለሞንን ልትጎበኝ የሄደችው ሰለሞን ቤተ መንግሥቱን ገንብቶ ካጠናቀቀ ከ7 ዓመት በኃላ ነው① የቤተ መንግሥቱ ግንባታ 7 ዓመት የፈጀ ሲሆን② ግንባታው የተጀመረው ሰለሞን በነገሠ በ4ኛ ዓመቱ ነው③ የተጠናቀቀው ደግሞ በነገሠ በ11ኛ ዓመቱ ነው ④ አጠቃላይ የሰለሞን ዕድሜ 52 ነው⑤ ሰለሞን የነገሠው በ12 ዓመቱ ነው⑥ የቤተ መንግሥቱ ግንባታ የተጀመረው በነገሠ በ4ኛ ዓመቱ 12+4 = 16 ግንባታው የፈጀው ጌዜ 7ዓመት 16+7 = 23 ንግሥቷ ልትጎበኘው የመጣችው ቤተ መንግሥቱ ከተጠናቀቀ ከ7 ዓመት በኃላ ነበር 23+7= 30 ሰለሞን ከንግሥተ ሳባ ጋር በተገናኘበት ወቅት ዕድሜው 30 ነበር ። ንግሥቲቱ ከሰለሞን ጋር ለ6 ወራት ተቀመጠች⑦ አስቂኝ ቀመር ቀምሮ ከንግሥቷ ጋር ዝሙት ሰራ እንዴት? ከታች በስፋት እናየዋለን ☺ 9ወር የእርግዝና ጊዜ አለ 6ወር + 9ወር = 1 ዓመት ከሦስት ወር ልጁ አድጎ 22 ዓመት ሲሞላው ታምሪን በተባለው ነጋዴ ወደ አባቱ ሰለሞን ሄደ ከሰለሞን ጋር ተገናኘ⑧ ከአባቱ ጋር ለሦስት ዓመታት ቆየ ስለዚህ ከላይ ጀምሮ ሒሳቡ ሲሰላ የሰለሞን ዕድሜ 30+1ዓመት ከሦስት ወር + 22 = 53 ዓመት ከሦስት ወር ሆነ ማለት ነው እንደ መጽሐፈ ስንክሳር ደግሞ የሰለሞን አጠቃላይ ዕድሜ 52 ነበር ምኒሊክ ሰለሞን ጋር ሄደ በተባለበት ሰዓት ሰለሞት ከሞተ ዓመት አልፎታል እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሰለሞንም ምኒልክን እስራኤል ላይ አነግሠዋለሁ እንጅ ወደ እናቱ መልሸ አልሰደውም አለ⑨፣ ምኒልክም እስራኤል አገር መንገሥ አልፈልግም ብሎ የሙሴን ጽላት ሰርቆ መጣ ①0፣አገሪቱ ላይ መንገሥ የሚችለው የእርሱ ዘር ነው የሚለውንና ሌሎች ተረቶችን የያዘው ክብረ ነገሥት አፈር በላ ማለት ነው ። ሰለሞን ከንግሥቷ ጋር ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ቀመረው የተባለው ቀመር ☺ " በብልሃት የሚያስጠሙ ምግቦች አስጋብዟት ነበርና በነቃች ጊዜ አፏ በጥማት ደረቀ እጅግም ተጠማች አፏም ደርቆ ነበረና ልምላሜን አላገኘችም ካገኘችውም ውሃ ልትጠጣ አስባ ታወጣና ታወርድ ጀመር ወደ ንጉሡም ተመለከተች ከባድ እንቅልፍ የተኛ መሰላት እሱ ግን ለጥሟ ውሃን ለመስረቅ እስክትነሳ ይጠብቅ ነበር እንጅ አልተኛም " (ክብረ ነገሥት ምዕራፍ 23 ገጽ 23) ልብ በሉ ሰለሞን ማለት በዘመኑ የተከበረ ታላቅ ጥበበኛ ንጉሥ ነበር ይህች ንግሥትም በጥበቡ ተማርካ አገሯን ለቃ እሱን ለማየት ሄደች የተባለው የሴት ችግር የለበትም በመጽሐፍ ቅዱስም ወይዛዝርት የሆኑ 700 ሚስቶችና 300 እቁባቶች እንደነበሩት ተጠቅሷል (1ኛ ነገሥት 11:3) ታዲያ ይህ ሰው ከአንዲት ሴት ጋር ግብረ ስጋ ለመፈፀም ብሎ ቅመም የበዛበት ውሃ የሚያስጠማ ምግብ አብልቶ ውሃ ለመጠጣት እስክትነሳ ድረስ ሳይተኛ ሌሊቱን ሙሉ አጮልቆ ሲጠብቃት አደረ መባሉ የሚያስገርም የፈጠራ ተረት አይደለም ? ዋቢ መጽሐፍት ፦ ¹ክብረ ነገሥት ገጽ 32 ቁጥር 5 ² መጽፈሐ ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ 23 ³ያለፈው ምንጭ ⁴ ያለፈው ምንጭ ⁵ያለፈው ምንጭ ⁶ያለፈው ምንጭ ⁷ክብረ ነገሥት ገጽ 20 ቁጥር 7 ⁸ክብረ ነገሥት ገጽ 25—26 ⁹ክብረ ነገሥት ገጽ 31 ቁጥር 9 ¹⁰ክብረ ነገሥት ገጽ 56 ለተጨማሪ በቴሌግራም ያግኙን http://telegram.me/orthox
1 996
8

No comments:

Post a Comment