Wednesday, June 9, 2021

የመስቀል በዓል

በአገራችን በየአመቱ መስከረም 17 ቀን የመስቀል በዓል ተከብሮ ይውላል። ይህ በዓል ምንም አይነት የመፅሐፍ ቅዱሳዊ ትዕዛዝ ኖሮት አይደለም ሚከበረው። የመስቀል በአል መስከረም 17 እንዲከበር ያዘዘው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ነው። እንዳለመታደል ሁኖ ዛሬም ድረስ የአገራችን አማኞች የደመራን በአል ሚያከብሩት በሱ ትዕዛዝ ነው።

«ወአመ ፲ወ፯ ለመስከረም ግበሩ በዓለ መስቀል»
መስከረም 17 ቀን በዓሉን(የመስቀልን) አክብሩ

«መፅሐፈ ጤፉት ምዕራፍ 4 ገፅ 135»

በዓሉን ለማክበር የሚያቀርቡት ምክኒያት ንግስት ኢለኒ ኢየሱስ የተሰቀለበትን መስቀል ለመፈለግ እሳት አቃጥላ በጭሱ በመመራት መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ስላገኘቸ በዛ ምክኒያት ነው የሚል እሳቤ አለ። ሆኖም ግን ይህ ታሪክ በዋናዎቹ የክርስትና መዛግብት ውስጥ አይገኝም። ከዚህ የተለየ ሌላ ታሪክ ግን በስንክሳር ላይ ሰፍሮ እናገኛለን።

ንግስት ዒለኒ ልጇ ክርስትናን ከተቀበለ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ መስቀሉን እንደምትፈልግና ቤተ ክርስቲያንም እንደምትገነባ ስለት ተሳለች ልጇ አምኖ ከተጠመቀ በኃላ ብዙ ሰራዊት አስከትላ ኢየሩሳሌም በመሄድ ቦታውን መፈለግ ጀመረች ቦታውን ማግኘት ስላልቻለች አንድ የአይሁድ ሽማግሌ በማገት አስራ በረሃብና በጥማት እየቀጣች ቦታውን እንዲያሳያት አደረገች

ከዚያም መጋቢት 10 ቀን #ሶስት #የተቀበረ መስቀል አግንታ አንደኛውን መርጣ ለልጇ እንደላከችለትና ቤተክርስቲያን እንዳነፀች ይናገራል።
(መፅሐፈ ስንክሳር ዘወርሐ መጋቢት 10 )

ትክክለኛው ታሪክ ይህ ከሆነ ዛሬ በየአመቱ የሚከበረው ንግስት ኢለኒ ኢየሱስ የተሰቀለበትን መስቀል ለመፈለግ እሳት አቃጥላ በጭሱ በመመራት መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ስላገኘቸ ነው ከሚለው አመለካከት ጋር ይፋለሳል።

ብዙ ግዜ እንደምንሰማው በክርስትና ሃይማኖት "መስቀል ሃይላችን ነው" "መስቀል ቤዛችን የነብሳችን መዳኛ ነው" ወዘተ ይሉናል። ታዲያ የነብስ መዳኛ የሆነው መስቀል የሚቃጠለው ለምንድን ነው?

በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/orthox

No comments:

Post a Comment