Wednesday, June 9, 2021

ይመጣል የተባለው ምናባዊው ንጉሥ « ቴ » ከቅርብ ግዜ ወዲህ በብዛት እየሰማናቸው ካሉ የቆረፈዱ የምኞት ተረቶች መካከል ንጉሥ ቴ የተባለ ኢትዮጵያን የሚገዛ ንጉሥ ይነግሣል ኢትዮጵያ የዓለም ገዥ ትሆናለች ሁሉም ነገር በቁጥጥሩ ስር ይሆናል የዓለም መንግስታት በሙሉ ይታዘዙታል ያለ ንጉሡ ፈቃድና ትዕዛዝ ዓለም ላይ ሚደረግ አንዳች ነገር የለም እና የመሳሰሉ የፈጠራ ተረቶችን መስማት የተለመደ ሆኗል ለዚህ ተረት አስረጅ ሆኖ የሚቀርበው ገድለ ፊቅጦር ፣ ራእየ ሳቤላ ፣ የማቴዎስ ወንጌል 24 ፣ 14 አንድምታ ፣ ራእየ ሲኖዳ እና ድርሳነ ዑራኤል ይገኙበታል ትንቢቱ እንዲህ ይላል « በኢትዮጵያ ሰዎች በአገራቸው ዘመን አቈጣጠር ዓለም በተፈጠረ በሰባት ሺ ሁለት መቶ ዘጠና ስምንት ዓመት በሰኔ ፲፯ ቀን በወንጌላዊው በሉቃስ ዘመን በዓለም ሁሉ ከሰማይ እንደ ብላጊ ዝናም አመድ ይዘንማል » (ድርሳነ ዑራኤል ዘጥቅምት ገጽ 328 ቁጥር 31) እንደ ቤተ ክርስቲያን የጊዜ አቆጣጠር ከአዳም እስከ ኢየሱስ መወለድ ያለው ዘመን 5500 ከልደቱ አሁን እስካለንበት የኛ የኢትዮጵያዊያን ጊዜ ሲቆጠር 2013 በአጠቃላይ 7513 ይሆናል ድርሳነ ዑራኤል በዓለም ሁሉ ላይ ከሰማይ አመድ ይዘንማል ያለን ዓለም በተፈጠረ በ7298 ወይንም በኛ ዘመን አቆጣጠር 1798 ዓ,ል ማለትም ከዛሬ 215 ዓመት በፊት ነበር ማለት ነው ሆኖም ግን የዘነበ አመድ የለም ስለዚህ የድርሳነ ዑራኤል ተረት አፈር በላ ማለት ነው ። «አመድ ከዘነመ ከአራት ዓመት በኋላ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስማዕት የሆነ በፊቅጦር በገድሉ መጽሐፍ እንደተነገረው የስሙ ምልክት «ቴ » ተብሎ የተመለከተው ይነግሣል ከወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ተሹሞ ከወጣ ጳጳሳቸው ጋር ቅዱሳን የሆነ የኢትዮጵያ ካህናት ይወጡና በግብጽ ምድር በአባ ሲኖዳ ደብር ውስጥ የሃይማኖት ጉባኤ ያደርጋል » (ድርሳነ ዑራኤል ዘጥቅምት ገጽ 330 ቁጥር 44_45) ሲቀጥል እንደ ድርሳነ ዑራኤል የስሙ ምልክት « ቴ » ተብሎ የተመለከተው ንጉሥ ይነግሣል የተባለው አመድ ከዘነመ ከአራት ዓመት በኃላ ነበር ከዛሬ 211 ዓመት በፊት 1794 ነበር በአገራችን የነገሥታት ታሪክ ከዛሬ 211 ዓመት በፊት የዘመነ መሳፍንት ጊዜ ነበር ጉልበት ኖሮት ማሸነፍ የቻለ ከነጋሲ ዘሮች መርጦ ለወጉ ንጉሥ ብሎ ሾሞ ያስቀምጣል እነዚህ ነገሥታቶች ንጉሥ ተብለው ከመጠራትና ግንብ ከመጠበቅ ውጭ በራሳቸው ሊወስኑ ሚችሉት አንዳች ነገር አልነበረም በዚህ ጊዜ ስሙ በቴ የሚጀምር ንጉሥም በጭራሽ አልነገሠም እዚሁ ድርሳን ገጽ 330 ላይ « ከወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ተሹሞ ከወጣ ጳጳሳቸው ጋር ቅዱሳን የሆነ የኢትዮጵያ ካህናት ይወጡና በግብጽ ምድር በአባ ሲኖዳ ደብር ውስጥ የሃይማኖት ጉባኤ ያደርጋል » ይላል እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ተሹሞ ይመጣላት የነበረው ከማርቆስ ወንበር ( ከግብጽ ) ነበር በዚህም ለ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት ያህል ቤተ ክርስቲያኗ በግብጽ ቅኝ ግዛት ስር ነበረች ምክኒያቱም ፍትሐ ነገሥት « የኢትዮጵያ ሰዎች ከዐዋቂዎቻቸው ወገን በራሳቸው ፈቃድ ሊቀ ጳጳሳትን ለራሳቸው አይሹሙ » ብሎ ስለከለከለ ነው (ፍትሐ ነገስት ገፅ 30 ቁጥር 50 ) አሁን ላይ ግን ይህ ሐሰተኛ ቀኖና በመሆኑ ተወግዶ ኢትዮጵያዊያን በራሳቸው ፈቃድ ሊቀ ጳጳሳትን መሾም ከጀመሩ ከ50 ዓመት በላይ ተቆጥሯል ታዲያ ጳጳሳት ከግብጽ ሳይሆን ከራሳችን ከኢትዮጵያዊያን መሾም ከተጀመረ በኃላ ይመጣል የተባለው ንጉሡ «ቴ» በምን ሒሳብ ነው ከግብጽ ተሹሞ ከሚወጣ ጳጳስ ጋር የሃይማኖት ጉባኤ ያደርል ሚለን? ትንቢቱ ይፈጸማል የተባለው ከዛሬ 200 ዓመት በፊት ነበር የተፈጠረ ነገር የለም ይህን ያረጀ ተረት ተሸክሞ ዛሬም ድረስ ይመጣል እያሉ ማላዘን ተገቢ አይደለም ስለዚህ ይመጣል የተባለው ንጉሥ «ቴ» እውነት የሌለው ተራ ቅዥት መሆኑ ግልጽ ነው https://t.me/orthox

No comments:

Post a Comment