Saturday, May 22, 2021

ድርሳነ ጽዮን ማርያምና ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ"

ለምን እንደሆነ ባላውቅም አንዳንድ የኦርቶዶክስ ጥንታዊ ድርሳናት በፁሁፎቻቸው በግልፅ ነብዩ ሙሐመድን "ﷺ" መሳደብ የተለመደ አድርገው ይመለከቱታል። መጽሀፍቶችን በግሌ ማጥናት ከመጀመሬ ከሶስትና ከአራት አመት በፊት ሰው ነግሮኝ ቢሆን በዚህ ደረጃ ድፍረት ይኖራቸዋል ብየ ማመን የሚቸግረኝን ፁሁፎች አይቸ ደንግጫለሁ። የምወደው የፌስቡክ ወንድሜ ቢላል ሀበሽ ጋር በመሆን ከአራት አመት በፊት ከመቶ በላይ የተለያዩ የተቀባይነት ደረጃ ያላቸውን የቀኖና ገድላትና ድርሳም መጽሀፍትን በሶፍት ኮፒ ከተለያዩ ኦርቶዶክሶች በማግኘት ማጥናት ከጀመርን በኃላ ግን ማመን የማንችላቸውን ብዙ ትርክቶች ማስተዋል ጀመርን። በመሀሉም አንድ ራሱን የቻለ ቴሌግራም ከፍተን የምናገኛቸውን ፁሁፎች ከአስተያየታችን ጋር ለሌላው አስተማሪ እንዲሆን ማስፈር ጀመርን (ቻናሉን በዚህ ሊንክ ያገኙታል t.me/orthox ) የማልረሳውና ከሁሉም በላይ ያሳመመን የነበረው ግን አንድ ስለ ነብዩ "ﷺ" በአስፀያፊ መልኩ የሚያወራውን ክፍል ነበር። ሰው የጥላቻ ደረጃው ምን ያክል በዚያ መልኩ ቢገን ነው በሳቸው ላይ እንዲያ አይነት ነውር ፈጥሮ የሚቀጥፈው? የሚለው ግን ሁሌ ይገርመኝ ነበር። ለማንኛውም ያንን ከመንፈሳዊ ድርሳን የማይጠበቅ አስፀያፊ ታሪክ ወደናንተ አላመጣውም። ዛሬ ከዚያ ውጭ እሳቸውንና አንድ የሳቸውን ተከታዮች አስመልክቶ የሚያወራ አስቂኝ ተረት ግን አካፍላችኃለው።

በእናቶቻችን የቡና አጠጣጥ የምናውቃቸው አቦል፣ ቶና እና የበረካ ስያሜዎች በሀገራችን ደብተራዎች ድርሰት በሆነው በድርሳነ ጽዮን ማርያም ውስጥ በነብዩ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم የሚያምኑ ሙስሊሞች ናቸው ተብለው እናገኛቸዋለን። ነብዩ ሙሐመድም "ﷺ" ቡና እየጠጡ ይሰግዱ ነበር ብሎ ግልፅ ያለ ቅጥፈት ያስነብበናል።

ከፁሁፎች ውስጥ የሚከተሉትን ንግግሮች እናገኛለን፦

"ሁለተኛ ፀሎት

1 የሰማያዊት እናታችን ፅዮን ተአምር ይህ ነው ጸሎቷና በረከቷ ከሁላችን የጥምቀት ልጆች ጋር ይሁን ዛሬም ዘውትርም ለዘልአለሙ ይደረገውልን

2 መሐመድም እፀ ኩስራ የተባለችውን ቡናን በሚያፈላና በሚሰግድ ጊዜ ፍርቃን የተባለውን መፅሐፍ ከመውደዱ የተነሳ ዲያብሎስ ወደሱ ይመጣና በምዕራፍ 28 ላይ የሚገኘውን ቃላት ጻፈው ነገር ግን እንዳያነቡት አጠረው ወገኖችህ የታጠረውን እንዳያነቡት የታጠረውን አታንብቡ ሌላ ያልታጠረውን ግን አንብቡ ብለህ አስተምራቸው ይለዋል"

ከላይ ባየነው ፁሁፍ ውስጥ እንግዲህ አስቡት ነብዩ "ﷺ" ቡና እያፈሉ ይሰግዱ ነበር ይለናል 🙂 ለዚህ ፀሀፊው ስለ ማስረጃ የሚጠይቀው አማኝ ስለሌለው ነብዩ ﷻ ስለነበሩበት የበረሀ ምድርና ስለአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ እንኳን ሳያጠራ እንዲሁ መንጋው ላይ ይጫወትበታል። የቡና አፈላልን የተከተለው ዘየ በዚያ ጊዜ እንደነበረ እንኳን የሚገልፅ ምንም አይነት ሀይማኖታዊም ታሪካዊም ሰነድ የለም። ደብተራው ምን አስጨንቆት? ሰፈሩ ላይ ያየው አንድ ሙስሊም ካናደደውም ከመሬት ተነስቶ ይፅፈዋል። ማን ከልካይ አለበት?

📌 ወደ ኢትዮጵያ ቡና እንዴትእንደገባ ሲተርክ ደግሞ እንዲህ ይለናል።

7 ወደ ኢትዮጵያ እንዴት እንደመጣ እንነግሯቹኃለን በመሐመድ ስርዓትና ህግ የሚጓዙ #አቦልና #ቶና #በረካ #የሚባሉ #ሶስት ሰዎች ለንግድ የመጡ መስለው ከአምስት መተንብላን (ከአማኞች) ጋር እነዚህን ዕፅዋት ይዘው ይመጣሉ እነዚህ ሶስት ዕፅዋት #ጫትና #ቡና #ጥንባሆ አህዛብ ለሰይጣን የሚያቀርቧቸው የጣኦት መሰዋት ናቸው

8 ለክርስቲያን ግን እነዚህን መብላት መጠጣት አይገባም እነዚህን #የበሉና #የጠጡ #ካልተጠመቁ #ሰዎች #ጋር #በገሀነም #ይፈረድባቸዋል መፅሐፍ የተናገረውን አልሰማችሁም በአምሳሉ እግዚአብሔር የፈጠረው የመጀመሪያው አዳም አትብላ የተባለውን ክፉ እፀ በለስ በልቶ ከልብስ ብርሀሰን እንደተራቆተና ከተድላ ገነት ወጥቶ የፍዳ የመርገም የፍርሃት የስቃይ ቦታ ወደምትሆን ወደዚህች ምድር ተሰደደ ክፉዎች እፅዋትና መልካሞች ዕፅዋት እንዳሉ ጌታችን በወንጌል ነግሮናል እነዚህን ዕፅዋት በመብላት በመጠጣት አትሳቱ ይህንም አድርጋችሁ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሔዳችሁ አታርክሱ

ከላይ ያነብብነው ፁሁፍ የሚገኘው "ድርሳነ ጽዮን ማርያም" በሚል በሀገራችን ደብተራዎች የተደረሰ ባዶ ተረት ውስጥ ነው። ማንም ህሊና ያለው ሰው እንደሚረዳው ታሪኩ ከአለማት ሴቶች የተመረጠችውን ንፁህ ሴት ማርያምን ፈጽሞ አይወክልም። እነዚህ ደብተራ ፀሀፊዎች ባገኙት አጋጣሚ ለኢስላምና ለአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم ያላቸውን ጭፍን ጥላቻ በዚህ አይነት በሬ ወለደ ተረት ይገልፁታል። አማኙ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ የማርያምን ስም በማከናነብ እሷ እንደተናገረችው አድርገው ያቀርቡታል። የዋሁ ህዝብ ደግሞ "ቃለ ህይወት ያሰማልን እልልልል" ብሎ ከመቀበል ውጭ ሊጠይቃቸው ይፈራል።

አሏህ ﷻ ሒዳያውን ይስጣችሁ..!

______

ተጨማሪ ንጽጽራዊ ትምህርቶችን ለመከታተል

❐ ዩቲዩብ || http://bit.ly/2ZPzYTI
❐ ቴሌግራም || t.me/yahya5
❐ ፌስቡክ || http://bit.ly/2QYG9CV
❐ ድረ ገጽ || www.ethio-islamic.org 
See Less
1

No comments:

Post a Comment