Monday, May 31, 2021

ቅዋሜ እንዲህ በጥበብ ሲገለጽ ደስ ይላል!
"አደም ፋራህ ያጫወተኝን የሶማሌ ተረት ላጫውታችሁ። ልጅቷ በሚስጥር ይዛው የነበረው ፍቅረኛዋ ለትዳር ሽማግሌ ሳይልክ በድንገት ይሞታል። ፍቅራቸው የሚስጢር ስለነበር ቀብሩ ላይ ተገኝታ ማልቀስ አልቻለችም። ትንሽ ቆይቶ አንድ ፍየላቸው ይሞትና ተመልካችን እስኪደንቅ ታለቅሳለች። እናቷ ይሄን አይተው 'ይኼ ለቅሶ ከፍየሏም በላይ ነው' አሉ ይባላል። ዛሬ በትግራይ ጉዳይ ፣ በመጪው ምርጫ አሳበው ከፍየሏ በላይ የሚጮሁ አሉ። በቅን አስበው ለሚጨነቁት አይዟችሁ ችግሩን እንፈታዋለን እንላቸዋለን ፤ ከፍየሏ በላይ ለሚጩኹት ግን የተደበቀ ፍላጎታቸው ጥቂት ቆይቶ ገሀድ ሲወጣ የምናየው ይሆናል።"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በኢትዮ ጅቡቲ ምዕራፍ - 1 አዳማ - አዋሽ የፍጥነት መንገድ ማስጀመርያ መርሀ ግብር ላይ ከተናገሩት ።

No comments:

Post a Comment