Tuesday, May 4, 2021

May 7, 2018
April 23, 2019
May 3, 2019
May 4, 2019
May 10, 2019
May 12, 2019
May 15, 2019
May 17, 2019
May 26, 2019
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
June 2, 2019
June 5, 2019
June 10, 2019
June 12, 2019
June 13, 2019
July 2, 2019
† † እግዚአብሔር የቅዱሳንን ነፍስ ይጠብቃል ከሃጢአት እጅም ያድናቸዋል::† መዝ.96፡10
✝️† እንኳን ለታላቁ ጸድቅ ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም በዓል በሰላም በጤና አደረሰ ን †✝️

አምላከ ሀብተ ማርያም ማረን
የጻድቁ ሀብተ ማርያም ረድኤት በረከት ይደርብን በቃልኪዳናቸው ይጠብቁን 🤲🤲🤲

መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያምን ያድምጡ👇👇👇👇
https://myvideo.cc/movies/aU9xdy95VXU4Q1ZWMzNpc0ltenZNd2ZMMkI2TkdKdEJmQ2lUMENEZzNZUT0
August 1, 2019
August 16, 2019
September 1, 2019
October 6, 2019
October 15, 2019
November 6, 2019
November 14, 2019
December 5, 2019
December 6, 2019
January 4, 2020
January 5, 2020
February 4, 2020
March 4, 2020
March 16, 2020
March 18, 2020
March 20, 2020
March 21, 2020
4_6037194434293008483.pdf
3.7 MB
March 28, 2020
April 4, 2020
ጠላቶችህ አጋንንትን ያጠፋልህ እና ይጠብቅህ ዘንድ ቅዱስ ሚካኤል ካንተ አይለይም የሰጠሁህን ቃል ኪዳን እንዳልነሳ በራሴ ማልኩልህ ከእናትህ ማህፀን ጀምሮ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ አድርጌ መረጥኩህ እንጂ በብዙ ገድልህና በድካምህ ብቻ የወደድኩህ አይደለም፡፡ ይህን ቃል ኪዳን ከሰጠው በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር፣ በብርሃን፣ በቅዳሴ፣ በስልጣን ወደ ሰማይ አረገ፡፡
ቅድስት ዮስቴናም ባሏ ከሞተ በኋላ ለራሷ ምንም ሳታስቀር ገንዘቧን እናት አባት ለሞቱባቸው፣ ለባልቴቶች፣ ለጦም አዳሪዎች፣ ለድሆች ጨርሳ ሰጠች፡፡ በጾም በፀሎትና በስግደት ሰውነቷን አደከመች፡፡ እንዲህ ባለ ገድል ሳለች ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል ወደ እሷ መጣ እኔን ለማገልገል ሴቶች ወንዶች ባሮችሽን፣ ወንድሞችሽን እህቶችሽን ቤትሽን ስለ ተውሽ ሰማንያ ርስት ከተሞችን ሰባት አክሊሎችን እነሆ አዘጋጀሁልሽ አላት ደጋግ ስራን ሰርታ ከፈፀመች በኋላ አረፈች፡፡ መዝ 115/116 ፡ 6 እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ ተስፋውን እንደነገራት ሰባቱን አክሊላት ሸለማት ሰማንያውን አህጉራት ገነት አወረሳት፡፡

ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ወደ ቤተክርስቲያን በሄደ ጊዜ ወንጌል ሲነበብ የክርስቶስ ጌትነቱን የሚናገር ወንጌል ሲነበብ "ወዮሴፍ ብእሊሃ ለማርያም ፃዲቅ ውእቱ" የሚል ከቄሱ አፍ ይህን ንባብ ሲሰማ ደንግጦ ወንጌል ወደ ሚነበብበት ስፍራ ሄደ የሚያነበውን ቄስ ገሰጸው "ወዮሴፍሰ ፈሃሪሃ ለማርያም ጽድቅ ውእቱ" በል እንጂ ብእሲሃ አትበል ብሎ መከረው ቄሱም አቡነ ሀብተማርያም እንዳዘዘው ከስህተቱ ወደ ቀና ንባቡ ተመለሰ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገልጾ ወዳጄ አመሰገንኩህ እናቴን ድንግል ማርያም ስለ አከበርክ እኔም በመንግስተ ሰማያት ፈጽሜ አከብርሃለሁ አለው፡፡
ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ከጌታ ጋር በተነጋገረ ጊዜ እንደ ነብዩ ሙሴ በፊቱ ብርሃን ተሳለ፡፡ ሰዎችም የፊቱን ብርሃን አይተው መቅረቡን ፈርተው አደነቁ፡፡ አቡነ ሀብተማርያምም ጌታ ሆይ ከንቱ ውዳሴ እንዳይሆንብኝ በፊቴ ላይ የተሳለውን ብርሃን ሰውርልኝ ብሎ ፀለየ፡፡ ጌታም ፊቱን እንደቀድሞው አደረገው፡፡ በጾም በፀሎት ላይ ሳለም በሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ወደ ሰማይ ተነጥቆ ቅዱሳን የሚኖሩባቸውን ዓለማት መንግስተ ሰማያትንና ሲኦልን ተመለከተ፡፡

ሰይጣንም መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ በሀብተማርያም ላይ መከራ አፀናበት ዘንድ ፍቀድልኝ ብሎ ጮኾ፤ ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም በሰይጣን ላይ ተቆጥቶ በነፍሱም በስጋውም መከራ ታፀናበት ዘንድ አልፈቅድም ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ መርጨዋለሁና በንፅህናና በቅድስና ኃጢአት እንዳይሰራ ዘወትር እጠብቀዋለሁ በእርሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሀብተማርያም ፀሎት በተማፀነኝ ሁሉ ላይ እንኳን አላሰለጥንህም ብሎ አሰናበተው ሰይጣንም ይህን ቃል ሰምቶ አፍሮ እያዘነ ሄደ፡፡ ያዕ 1፡12
አባታችን አቡነ ሀብተማርያም እንዲህ ባለ ስራ ላይ ሳለ ሰውነታቸው እንደ መርግድ የሚያሸበርቅ ዘጠኙ ክቡራን ሰዎች ወደ እርሱ መጡ፡፡ አብሯቸው ያለውን መልአክ ይህን ያህል ብርሃን የከበበው ይህ ሰው ማን ነው ብሎ ጠየቀው መልአኩም አባትህ ተክለሃይማኖት ነው አለው፡፡ ክቡር የሆነ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ጠርቶ ልጄ ሀብተማርያም ሆይ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ስለወደደህ ብዙ ምርኮ እንዳገኘህ በአንተ ፈጽሞ ደስ ይለኛል፡፡ ነገር ግን የምለምንህ ነገር አለና እሺ በለኝ አለ፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም ጌታዬ ነገሩ ምንድን ነው አለ? ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትም ከተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀበር ቃል ኪዳን ግባልኝ አለው፡፡
✝️አቡነ ሀብተማርያምም ይህንን አደርግ ዘንድ ስለምን ትወዳለህ አለው አቡነ ተክለሃይማኖትም በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች አሉና ነው፡፡
እነሱም፡-
1. መብረቅ፣
2. ቸነፈር፣
3. ረሃብ፣
4. ወረርሽኝ፣
5. የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡

የአንተም አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደሆነ አጥንቴ የተቀበረባት ሀገሬ ከነዚህ መቅሰፍታት ትድናለችና ልጄ ሀብተማርያም ሆይ አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ስለዚህ ነው ቃል ኪዳን ግባልኝ ብሎ ማለደው፡፡ ይህን ሲባባሉ እንዲህ የሚል ቃል መጣ፡፡ ከወዳጄ ከሀብተማርያም አንደበት ይህ ቃል ኪዳን አይወጣም እርሱ በወደደው የሚቀበር አይደለም፡፡ እንዲህም ብለህ የምታስገድደው ለምንድን ነው እኔ በወደድሁት ቦታ ይቀበራል እንጂ የሚል ቃል ተነገረ፡፡ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትም እየለመነና እየሰገደ ሶስት ጊዜ ከስላሴ ዙፋን ተንበረከከ፡፡ይሁን ይደረግ የሚል ቃል ከሰማይ ሰማ በወዳጄ በሀብተማርያም አጥንት ቦታህ የምትድን ስለሆነች ፈቃዴ ነው ብሎ ጌታ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም በፀሎት ላይ ሳለ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ የቆምክባትን ቦታ ምስራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን ባርክ አለው፡፡ ሲባርክም ሶስት አጋንንት በፀሎቱ ስልጣን ታስረው በፊቱ ታዩት፡፡ እነዚህም አጋንንት ከኖህ ጀምሮ ሰውን በማሳት ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋር ምን ፀብ አለን አሉ አባታችንም አቡነ ሀብተማርያም በትዕምርተ መስቀል ሲያማትብ ሁለቱን አጋንንት ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው አንዱ ጊዜዬ ስላልደረሰ አታጥፋኝ አለው፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይህንን ተወው ጊዜው አልደረሰም አለው፡፡ የጌታ ቃል እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ሰይጣን ከአባታችን ተለይቶ ጠፋ፡፡ ማር 9፡23
ከዚህም በኋላ ዕለተ ሞቱ በደረሰ ጊዜ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር ያዘው፡፡ ጌታችንም በምስጋና ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ዛሬ ወደአንተ የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት እወስድህ ዘንድ ነው ሰባት የጽድቅ አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ፡፡
1. ስለ ንፁህ ድንግልናህ፣
2. አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣
3. ስለ ፍፁም ምንኩስናህ፣
4. ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ፣
5. ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው፣
6. በጾም ስለተጋደልክ፣
7. ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
በተጨማሪም እኔ የሰጠሁህን ቃል ኪዳን ተስፋ አድርጎ መጽሐፈ ገድልህን ለሚጽፈው ስሙን በመንግስተ ሰማያት በእውነት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፣ ለቤተክርስቲያንህ ዘይትን፣ ወይንን፣ ዕጣንን፣ ህብስትን እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ በአንተ ስም መብዓ የሰጠውን የወደደውን ሁሉ አደርግለታለሁ፡፡ በመንግስተ ሰማያትም ከወዳጆቼ ከቅዱሳን ጋር በደስታ አኖረዋለሁ፡፡ የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው በኋላ ጌታችን አፉን ሶስት ጊዜ ሳመው፡፡ ያን ጊዜም ከመድኃኒዓለም ጣዕም ፍቅር የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች መዝ 115/116 ፡ 6 በሰማያዊ መልአክት በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ ህዳር 26 ቀን አረፈ፡፡ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በፃዲቁ መቃብር ቀበሩት፡፡

🤲ኦ አምላከ አቡነ ሀብተ ማርያም ዕቀቦ ወአድኅኖ ወባልሆ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ወእምኩሉ ተቃራኒ ወእምኩልነ ክቡር ሀብተ ማርያም ለዓለም ዓለም አሜን ለይኩን ለይኩን::

https://t.me/AbuneHabtemariyamtsdik
April 18, 2020
May 3, 2020
May 15, 2020
June 2, 2020
🕊†† † እንኳን ለታላቁ ጸድቅ ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የልደት (#ግንቦት 26 )በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደሰችሁ† † †

🌼የጻድቁ አባታችን የሀብተማርያም ልጆች ሆይ በማስተዋል እና በማገናዘብ በዓላቶቹን አክብሩ በጠዋት እና በማታም ያለመታከት ምስጋናን አቅርቡ የእግዚአብሔር ክብር ሁሌ በሱ ላይ ይገለጻል እና ቃል ኪዳኑም ለዘለዓለም ተስፍ ይሁነን ::

🌼ሰላም ለልደትከ እማህፀነ ቅድስት ዮስቴና
በብሥራተ ጻድቅ ባሕታዊ ሠናየ ዜና
ሐብተ ማርያም ጴጥሮስ ሐዋርያ ወልደ ዮና
መሐረኒ ምግባረ ጽድቅ ወጸግወኒ ልቦና
አፍቅሮ ቢጽ እኃሥሥ ዘምስለ ፍጽምት ትሕትና::

🌼ሰላም ለአራኅከ ነሣኤ ኅለት ዘአሚን::
ዘይትባሕዩ ቦቱ አባግዒከ ዝርዋን::
ሀብተ ማርያም መርስ ሀብተ ማርያም ዛኅን::
ይሱቀኒ እምትንታኔ ጸሎትከ በትረ ሐፂን::
ለቁረተ ነፍስየ ካዕበ ቃልከ ክዳን::

🙇‍♀️በአለም የተበተኑ በጏች የተባሉ ልጆችህ የሚጠበቅበት የእምነት ዘንግን ለጨበጠ መሐል እጅህ ሰላምታ ይገባል::ጻድቁ አባቴ ሀብተማርያም ሆይ የዚች አለም ጸጥታዋና ሰላሟ አንተ ነህ እኮ እኔን ለመውደቅ የተፍገመገምኩትን እንደብረት ዘንግ የሆነ ጸሎትህ ከወደቅኩበት መሬት ያንሳኝ ይደግፈኝ ሁለተኛም የጏሰቆለች ነፍሴን ቃልኪዳንህ አይለያት::(መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያም)

🛐ኦ አምላከ አቡነ ሀብተ ማርያም ዕቀቦ ወአድኅኖ ወባልሆ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ወእምኩሉ ተቃራኒ ወእምኩልነ ክቡር ሀብተ ማርያም ለዓለም ዓለም አሜን ለይኩን ለይኩን::

https://www.youtube.com/watch?v=_5APlmAq2MY&feature=share
#ዝማሬ
🛐ጽሩይእምወርቅ

ጽሩይ እምወርቅ ወእምብሩር ንጡፍ ወኅሩይ እምአእላፍ
ሐብተ ማርያም መልአክ ዘውገ ኪሩብ ቀሊለ ክንፍ
አማን ስሙዐ ዜና እስከ አጽናፍ፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=Lf1Dtjnx8Pk&feature=share
June 3, 2020
https://youtu.be/5zErmwzujGM
🥰በ ላዕከ ብፁአን አባ ተክለብርሃን
የ እሰበይ ደብረ ብፁአን አቡነ ሀብተ ማርያም አንድነት ገዳም አበምኔት
June 8, 2020
July 3, 2020
August 1, 2020
August 31, 2020
October 7, 2020
December 4, 2020
January 4
February 3
March 5
🤍 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ መንግስቱ ሲመጣ "ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን?" 1ቆሮ6:2

††እንኳን ለዓብይ ጾም እኩሌታ እንዲሁም ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደሰችሁ†

🤍"ሰላም ለከናፍሪከ ማዕፆ ትእግስት ዘሤማ ሀብተ ማርያም ሚናስ ሱታፌ መላእክት ዘራማ: ዓማዴ ሰማይ ክርስቶስ አመ ይመጽእ በግርማ:: ነፍሰ ዚአየ በትንባሌከ አስተሳልማ:: እስመ ሰሉሥ ቅድሜሁ ለፌማ::"

❤️ፍቅር ያገብረኒ ነጊረ ዜናሆሙ ለቅዱሳን❤️” አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

🕊በአለም የተበተኑ በጏች የተባሉ ልጆችህ የሚጠበቅበት የእምነት ዘንግን ለጨበጠ መሐል እጅህ ሰላምታ ይገባል::ጻድቁ አባቴ ሀብተማርያም ሆይ የዚች አለም ጸጥታዋና ሰላሟ አንተ ነህ እኮ እኔን ለመውደቅ የተፍገመገምኩትን እንደብረት ዘንግ የሆነ ጸሎትህ ከወደቅኩበት መሬት ያንሳኝ ይደግፈኝ ሁለተኛም የጏሰቆለች ነፍሴን ቃልኪዳንህ አይለያት::(መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያም)

🤲ኦ አምላከ አቡነ ሀብተ ማርያም ዕቀቦ ወአድኅኖ ወባልሆ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ወእምኩሉ ተቃራኒ ወእምኩልነ ክቡር ሀብተ ማርያም ለዓለም ዓለም አሜን ለይኩን ለይኩን::

መልክአ አቡነ ሀብተማርያም በዜማ 👉https://www.youtube.com/watch?v=_5APlmAq2MY&feature=share

No comments:

Post a Comment