Tuesday, May 4, 2021

💖💛💚ገድለ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ላይ የሚነሱ የተለመዱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው 💖💛💚
====>1)ቅዱስ ተክለሃዮማኖት አለም አቀፍ ቅዱስ ናቸው ስለሚባለው ምን ማለት እንችላለን????
★★★**ድል፡የነሳው፡ከጎኔ፡በዙፋን፡አነግሰዋለው፤አለም(አህዛብ)ላይ፡ስልጣን፡እሰጠዋለው**@ራዕይ2:26-27@ራዕይ20:4
♦♦አባታችን ተክለሃይማኖት እንደ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ እየተጋዘ በድፍን አለም የሚገኙ ገዳማትን ባርከዋል ስለዚህ አጽማቸው (2ነገ13:20-21) ክርስትና ዋና ማዕከላት ወደሆኑት ዓለማት ለበረከት ፈልሷል።
♦♦በግብጽ ኮብቲክ ቤተክርስትያን(Plant Of Religion)ብለው ይጠሯቸዋል፤በአረብኛ ገድላቸው ይገኛል። በስማቸው ገዳማት አብያተክርስቲያናት ሰይማ በክርስቶስ በተሰጣቸው ታላቅ ቃል ኪዳን ቅዱሱ እየተጠቀመች ነው ።ሳርያ ሮም ማላናካ ዳጊስታን ወ.ዘ.ተ.ረ.ፈ ፤ አብያተክርስትያናት ቅዱስነታቸውን ይቀበላሉ።አባታችን አለም አብያተክርስትያናት ሁሉ አምድና ቅዱስ ናቸው። ከኢንሳይክሎፒዲያ ያረጋግጡ (en.wikipedia.org/wiki/Tekle_Haymanot)
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
====>2)ተክለሐይማኖት በደነታችን ውስጥ ያላቸው ድርሻ ምንድን ነው??
★★★**በሰማይ፡በሚገኙት፡ፍጹም፡ቅዱሳን፡ነፍሳት፡ምልጃ፡መጸለይ፡አለባችው፤ሰማያዊ፡ቅዱሳን፡የማይገዛ፡ክርስቶስ፡ተቃዋሚ፡ነው**@ ሮሜ13:1-7@1ጢሞ2:2@ዕብ12:23)
★★★**እነዚህ ወደ ሰማይ አርገው አምላክ ፊት የቆሙና በምድር ላይ ስልጣን የተሰጣቸው ቅዱሳን ናቸው**@ራዕ11:12 @ራዕ11:4-6
♦♦ተክለሃይማኖት በተጋድላዊ ውስጥ ለሚገኙ ክርስትያኖች ያማልዳል..ስማቸው ለታመኑ አጸደ ነፍስ አጸደ ስጋ ትምክት ይሆናሉ።
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
====>3)ቅዱስ ተክለሃይማኖት ወንዝ አጠገብ በመስቀል አማትቦ የያዘውና ያጠመቀው <<የዛር ውላጅ ሰው>>ማን ነው???
★★★** ስለ ምድራዊ ነገር ስነግራችው ካላመናቸው ስለ ብዙ ወገን ስላሉት መንፈሳዊ ዓለም ቢነግራችው እንዴት ታምናላችው??** @ዮሐ3:12@ማር9:29)
★★★**ንጉስ ናቡከደነፆር በከፋ ኀጢያቱ በመርገም ተመታ ፥ የሰው ተፈጥሮውን ቀየረ ፥ ፤ የሰው አይምሮው ተቀይሮ የእንስሳ ወገን ሆነ፥ የበሬ ጸጉር የንስር ጥፍር አወጣ ከሰው ተለይቶ ሰባት ዓመት ሙሉ ከእንስሳት ወገን ኖረ ፥ ሳር በላ ፥ አምላክ በምህረቱ በጎበኘው ግዜ እንደ ገና ወደ ሰው ተፈጥሮው ተቀየረ ነገሰም ልዑሉንም አመሰገነ ** @ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 4 ቁጥር 30-34
★★★**ይህን የከፋ ኀጢያት በሰራው ላይ ስጋው ለሴጣን እንዲሰጥና ደግሞ ይድን ዘንድ አሁን ፈርጄበታለሁ**@1ቆሮ5:3-5
★★★**ለሴይጣን በሥጋ አሳልፌ የሰጠኃቸው ሄማኔዎስና እስክንድሮስ ናቸው**@1ጢሞ1:20
★★★**ክርስቶስም ጴጥሮስን ዞር በል አንተ ሴጣን አለው**@ማቴ16:23
♦♦መንፈሳዊው ዓለም ብዙ የመናፍስት ወገን እንዳሉ ይተናል ፥ ሴጣን በእብራይስጥ ጥሪ ትርጉሙ <<ተቃዋሚ>> እንደ ሆነ ኢየሱስ ቅዱስ ጴጥሮስን በተናገረው ንግግር በቀላሉ ማወቅ እንችላለን፡፡
♦♦ሰው በመርገም ከተፈጥሮው እንደ ሚቀየር ሥጋው ለሴጣን እንደ ሚሰጥና እንደ ገና ሊድን እንደ ሚችል ንጉስ ናብከደነፆር ሕይወትና ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ተመልከተናል።
♦♦በገድለ ተክለሃይማኖት የተገለጸው የዛር ውላጅ እንደ ንጉስ ናቡከደነፆር በክፉ መርገም የሰው ተፈጥሮውን ወደ<<ቡዳ ዛር ውላጅ>> ቀይሮ ይኖር የነበረ <<አዳም ዘር ነው>>የሰው ልጅ ነው።
♦♦ቅዱስ ጳውሎስ በመርገም ስጋው ለሴጣን ከተሰጠ በኃላ ይድናል ያለውን ቃል አባታችን ተክለሃይማኖት ሥጋው ለሴጣን ዛር ውላጅ ተሰጥቶ የነበረውን ሰው አድኖ ሲፈጽመው አናያለን....በዚህም ሰማያዊ መላአክ ደስስስስ ብሏቸዋል...ሲጣን እስከዛሬ ሲያስበው ቢበሳጭም።
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
====>4)<<ሐሙስና እሁድ እባብ የገደለ ይድናል>> የሚለው ተምሳሌት ምን ትርጉም ዓለው??
★★★**ዳዊት፡ኢየሩሳሌምን፡በያዘ፡ግዜ፡በዳዊት፡ቤት፡እውርና፡አንካሳ፡አይገባም፡የሚል፡ተምሳሌት፡ተነገረ**@2ሳሙ5:8
♦♦እንደ መናፍቃን የመንደር ተረታ ተረት ትርጉም ዳዊት አካለ ስንኩሎችን አይወድም ማለት ነው።ቃሉ እውነተኛ መልክት ግን ሌላ ነው።
♦♦ሲጀምር ንግግሩ ለዳዊት እንደ ተነገረው ተምሳሌት ነው ቀጥተኛ ትርጉም የለውም ፥ ተክለሃይማኖት ቀንዳሙን ዘንዶ በመስቀሉ የገደለው ቀን የተነገረ ነው፡፡
♦♦ሐሙስ ቁረባን የታወጀባት እሁድ ደግሞ የትንሳኤ ቀናት ናቸው። ቁርባን በትንሳኤም ዋጋ አላት የሚለውን ቃል (ዮሐ6:54) በተምሳሌት ሲያመሳጥር ነው።
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
♦♦ሌሎቹ መንደር ተሳዳቢ መናፍቃን ደግሞ፥ ከሐዋሪያት ጀምሮ ክርስትና መንፈሳዊ የተጋድሎ(Christian ascetic) መንገዶች የሚያቁ ይመስል ስለ ቅዱስ ተክለሃይማኖት
ተጋድሎ መንገድ ሲተቹ ማየት የተለመደ ነው።
ቅዱስ ስሞኦን ዘአልፖ፤ አይነት ጥንታዊ ቅዱሳን ካለምግብ 37 አመት እግራቸው ቆመው ለዓለም ጸልየዋል።፡፡
♦♦(((Simeon Stylites - Wikipedia
https://en.m.wikipedia.org › wiki › Sime...)))
2 September 459) was a Syriac ascetic saint who achieved notability for living 37 years on a small platform on top of a pillar near Aleppo (in modern Syria).
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
DEBR II
====>5)ቅዱስ ተክለሃይማኖት የክርስቶስን ሞት<<ንዳድ ሞት>>የተካፈለው እንዴት ነው?
★★★**እኔ፡ክርስቶስን፡ሞቱንም፡በመስቀል፡ሞት፡ብካፈል፡ደስተኛ፡ነኝ**@ፊል3:10-11@1ጴጥ4:13
♦♦እንደ ጳውሎስ በክርስቶስ ፍቅር የነደደው ተክለሃይማኖት የክርስቶስን አካላዊ መስቀል ሞት እንደ ሐዋሪያት በመስቀል በመካፈል የሞቱ ፍጻሜ እንዲሆን ተመኝቶ ክርስቶስን ጠየቀው።
♦♦ክርስቶስም<<ወዳጂ ተክለሃይማኖት ሆይ!! በወንጌልና በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ሁሉን መከራዬን ተካፍለክ የጽድቅን ሥራ ሁሉ ፈጸምክ ምንም አልቀረኸምና በሰላም ሞት ትሞታለህ>>ዓለው።(ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፤ነሐሴ 1989ዓ.ም ፤ ምዕራፍ ፶፯፤ ገጽ. 195)
♦♦እሱ ግን እንደ ሐዋሪያት የመስቀል ሞትክን ልካፈል ብሎ አብዝቶ ለመነው። ክርስቶስም ለሱ ባለው ጥልቅ ፍቅር ተደስቶ
<< ንዳድ ሞት ትሞታለክ ፥ እሷንም ሐዋሪያት እንደ ተካፈሏት እንደ መስቀሌ ሞት መካፈል አስብልካለው፥ካንተም በኃላ በደብረ ሊባኖስ በተጋድሎ በቸነፈር በንዳድ የሚሞቱ እንዳንተ ይታሰብላቸዋል>>አለው
♦♦መናፍቃን ገድሉ ያላለውን ብዙ አጋንት ውሸት ቢለፈልፉም አባታችን ለክርስቶስ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ሞቱን በመካፈል ያሳየበት ነው።ማንም ሊረዳው የሚገባው ከ15በላይ ገድለ ተክለሃይማኖት ቅጂዎች በዓለም ላይ አሉ።
♦♦ኢ.ኦ.ተ.ቤ ዕውቅና የምሰጠው ደብረ ሊባኖሱን ግዕዝ ቅጂ ብቻ ነው።ከዛ ውጪ ማንም በግሉ ተነስቶ ያሳተመው ዕትሞች ሁሉ ተቀባይነት አለው ብሎ ማሰብ አላዋቂነት ነው።
♦♦መናፍቁ ፀረ ክርስቶሱ ጌታቸው አሳተሙት ዕውቅና በሌለው በአንድ የመንደር ገድል ላይ ተቅማጥ ትሞታል ተብሎ ተተርጉሞል።የተተረጎመበት የግዕዝ ቃሉ<<ሕማመ ብድብድ>>የሚለው ነው ይህም<<ንዳድ ቸነፈር መከራ>>የሚ ል ትርጉም አለው።በምንም ታምር <<ተቅማጥ ተብሎ>>ሊተረጎም አይችልም።
♦♦በምንም ታምር ሴራ የታሰበ ካልሆነ <<ሕማመ ብድብድ>>ተቅማጥ ተብሎ ሊተረጎም አይችልም።ቅ/ተክለሃይማኖት የሞቱት በንዳዳ ትንኝ ተነድፈው ነው፥ገድሉ ላይ አባታችን ትንኟን በእጁ ይዟታል፡፡ቅብጥ ቋንቋም በግብጽ በሚገኘው ገድላቸው ተመሳሳይ ነው።
♦♦ከዚህ የባሰ<<ሰገራህን ብላ>>ተብሎ ነብዩ ሕዝቅኤል መታዘዙን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ መጻፉን የማያቁት መናፍቃን አላማቸው ባይሳካም@ሕዝ4:12፥የመጨረሻው ጽድቅ ደረጃ13 ላይ የደረሰው አባታችን አይደለም ፥7ደረጃ ላይ የደረሱትም መናዮች አይበሉም አይጠጡም፥አይጸዳዱም።፡፡
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
====>6)ቅዱስ ተክለሃይማኖት ስዕለ አድኖ የመልአክት ክንፍ ተደርጎ የሚገለጸው ለምንድን ነው???
★★★**ከትንሣኤ ሙታን በን በኃላ ፥ የሠው ልጅ እንደ መልእክት ፥ በሰማይ ይኖራል** @ማቴ22:30
★★★**እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ እንደ ንስር ክንፍ ይወጣሉ ይወርዳሉ ፥ አይደክሙምም**@ኢሳ40:31
★★★**ከዘንዶውም ታመልጥ ዘንድ ለሴቲቱ ሁለት ክንፎች ተሰጣት** @ራዕ12:14
♦♦ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቅድስና ጫፍ ከደረሰ በኃላ ፥ ድፍን ዓለምን ሁሉ የተጋዘው ፥ እንደ ነብዩ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ነው። ሰማያዊ ክንፍ የተጋዘው ፥ ከደብረ ዳሞ ገመድ ሲወርድ ፥ ሴጣን ገመዱን በመበጠስ ፥ ሊገለው በመከረ ግዜ ፥ ያመልጥ ዘንድ ለአንድ ግዜ ብቻ ነው ።
♦♦ሰው ለጽድቅ በቅቶ ፥ለዘላለማዊ ሕይወት ሲበቃ ፥ በሰማይ እንደ መልአክ ይኖራሉ ብሎ ክርስቶስ ተናግሯል ። ቅዱስ ተክለሃይማኖት ግን ፥ ገና በምድር ፥ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ መልአክ፥ ተጋድሏዊ ሕይወት እንዳሳለፉ ፥ ለማስገንዘብ ሲባል መንፈስ ቅዱስ ምስለ አድኖው ክንፍ እንዲኖረው ፈቅዷል።
♦♦መጥምቁ ዮሐንስ ቅድስት ባርባራ ፥ በክርስቶሰሠምራና ሌሎችም ብዙ ቅዱሳን ምስለ አድኖን ተመሳሳይ ክንፍ እንመለከታለን
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
====>7)ተክለሃይማኖት ለፍርድ ቀን ከቅዱሳ ጋር ለፍርድ ሲቀመጥ በኪዳኑ ታምነው በስሙ በጽዋ ዝክር መልካም ለሰሩ የልጆቹ ነፍሳት ትምክት የሚሆናቸው እንዴት ነው???
★★★**በኔ፡ባላቸው፡መመካት፡ታላቅ፡እንደሆነ፡አቃለው፤ጌታ፡ለፍርድ፡ቀንም፡የምትመኩበት፡ነው**@ፊል1:25-26@2ቆሮ1:13-14
★★★**በአንዱ፡ቅዱስ፡ሥም፡ጽዋ፡ያጠጣ፡በሰማይ፡ዋጋው፡ተጽፏል**@ማቴ10:39-42
★★★**እናንተ ዓለምን ትታችሁ የተከተላችሁ የፍርድ ቀን ዙፋን ላይ ተቀምጣችው ትፈርዳላችው** @ማቴ19:27-28
♦♦አንድ፡ክርስትያን፡ከአምላክና፡ከእመቤቴ፡በተጨማሪ©ቤተክርስትያን፡አምድ፡የሆኑትን፡ቅዱሳን፡ሁሉ፡ይወዳል(ራዕ3:12)©ነገር፡ግን፡በተለያየ፡ምክያት፤ወደ፡አንዱ፡ቅዱስ፡ዘንበል፡ማለቱና፡የተጋድሎው፡ተመራጭ፡ቅዱስ፡አባት(እናት) (Favorite Saint)ማረጉ፡አይቀርም።
♦♦በቅዱሱም:ሥም፡ጽዋ፡ዝክር፡ያወጣል©ቅዱሱም፡ለፍርድ፡ቀን፡ለዚያች፡የኃጥኡ፡ነፍስ፡በምልጃው፡ትምክት፡ይሆንላታል©ክርስቶሥም"በጻድቅ፡ሥም፡ጽዋ፡ያጠጣ፡..."ብሎ፡እንደተናገረ፡የቅዱሱን፡ምልጃ፡ሰምቶ፡መንግስተ፡ሰማይንም፡ያወርሳታል።
♦♦ቅዱስ ተክለሃይማኖት ለልጆቹ የፍርድ ቀን የሚኖረው ትምክት በዚህ ወንጌል ቃል ላይ የተመሠረተ መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል።፡
♦♦በገዳሙ ዙሪያ የሚኖሩ ሕዝቦች ★★አገሩን አለቃ አትናቅ★★2ነገ17:25-31 ፥በሚለው ወንጌል ቃል መሰረት ክርስትያን ሆነ አልሆነ ቅዱሱን ዓመታዊ መታሰብያ ቀን ክብር ሊሰጥ ይገባዋል ቢንቅ ግን በኑሮውም በነፍሱ ኩነኔ ያፍሳል ፍርድ ቀን ገዳሙ ዙሪያ ያሉት ሰዎች ሁሉ ጻድቁ ፊት ይቀርባሉ።
♦♦ገድሉ ይህን ከመጀመሪያ ገጹ ጀምሮ ቢናገርም ጠላት<<ነፍስ፡ሁሉ>>እምትለውን ቃላት ብቻ በማጣመም ብዙ በሬ ወለደ ውሸት ቢያወራም ገድሉ በመንፈስ ቅዱስ ስለተጻፈ ፍጹም ነው።፡
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
@By Orthodox Activist Master kiya
🌿❤️💛🌹💖💛❤️💚🌹♥🌿🌹
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን!!!!
No photo description available.
Birtukan Bekele, Melat A. Bultumee and 45 others
41 Comments
8 Shares

No comments:

Post a Comment