የተዋህዶ ልጅ
አዋልድ መጻሕፍት በመጽሐፍ ቅዱስ
✍ የተሃድሶ መናፍቃን አዋልድ መጻህፍትን አይቀበሉም መጽሐፍቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት እንዳላቸውም አይቀበሉም እንደውም እንደ ልብ ወለድ ድርሰቶች ቆጥረውት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ይሳለቃሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ግን መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርጋ አዋልድ መጻሕፍትን ትቀበላለች እስቲ ለተሃድሶ መናፍቃኑ ምላሽ ይሆን ዘንድ አዋልድ መጻሕፍትን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንመልከት።
✞ "አዋልድ መጻሕፍት" የሁለት ቃላት ጥምር ውጤት ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ "የመጻሕፍት ልጆች" ማለት ነው መጻሕፍት የተባሉትም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተለይተውና ተቆጥረው የምናውቃቸው ሰማንያ አንዱ መጽሐፍተ ብሉያተና ሐዲሳት ናቸው አዋልድ መጻህፍት የአስራው መጻሕፍት ምስጢር ትርጓሜ ተብራርቶ የሚገኝባቸው መጻሕፍት ናቸው ቅዱሳን ነቢያት እንዲሁም ሐዋርያት፤ በየዘመናቱ የተነሱ መምህራንና ሊቃውንት አዋልድ መጻሕፍት መጠቀማቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል መጽሐፍ ቅዱስን ለማብራራት አዋልድ መጽሐፍት አስፈላጊ ናቸውና።
✞ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ነገር የሚናገሩ መጻሕፍትን ቁጥር አልገደበም እንደውም በ 2ኛ ጢሞ 3፥15-16 ላይ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። ነው የሚለው እነዚህ የቅዱስ ጳውሎስ ትምህርቶች ስለ መጻሕፍቱ መመዘኛ እንጂ ቁጥር አይነግሩንም ቅዱስ ጳውሎስ "የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ" አለ እንጂ ይህንን ያህል መጽሐፍ አላለም።
☞ መጽሐፍ ቅዱስ ሌሎችንም ቅዱሳት መጻሕፍት እንድናነብ መክሮናል እስራኤል ወደ ከነዓን ሲጓዙ በእግዚአብሔር ረዳትነት ከአሕዛብ ጋር ያደረጓቸውን ጦርነቶች የያዘ "የእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ" የሚባል መኖሩን ሙሴ በዘኁ 21፥14 ላይ ነግሮናል።
☞ ኢያሱ ፀሐይን አቁሞ፣ ጨረቃን አዘግይቶ አሕዛብን የረታበት ድንቅ ታሪክ የተጻፈበት "የያሻር መጽሐፍ" የሚባል አለ ይህም ☞በኢያ 10፥13 ላይ ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም። ተብሎ ተጽፎልናል እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በዚህ በያሻር መጽሐፍ የዳዊት መዝሙርም ተጽፎአል ☞ በ2ኛ ሳሙ 1፥17 ላይ ዳዊትም ስለ ሳኦልና ሰለ ልጁ ስለ ዮናታን ይህን የኀዘን ቅኔ ተቀኘ፥ የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ፥ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፎአል።
☞ የእስራኤል የነገስታት ታሪክ መጽሐፍ /2ኛ ነገ 1፥18/፣ የይሁዳ ነገስታት ታሪክ መጽሐፍ /2ኛ ነገ 8፥23/፣ የሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ /1ኛ ነገ 11፥41/፣ የሚባሉ አያሌ መጻሕፍት መኖራቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ይመሰክራል መኖራቸውን ብቻ ሳይሆን የቀረውንም ታሪክ ከእነዚህ መጻሕፍት እንድናነብም ይጋብዘናል።
☞ ሐዋርያው ይሁዳም በኦሪት ዘዳግም የማናገኘውን የሙሴን ታሪክ "ዜናሁ ለሙሴ" ከሚባለው መጽሐፍ ወስዶ ነግሮናል ከሰማንያ አንዱ አሥራው መጻሕፍት ውጪ ያሉት መጻሕፍትን መቀበል የማይገባን ቢሆን ኖሮ ሐዋርያው ይሁዳ "ዜናሁ ለሙሴ" ከተሰኘው መጽሐፍ ባልጠቀሰ ነበር በይሁ 1፥8 ላይ።
✍ አዋልድ መጻሕፍት ጌታችን ለሐዋርያት የገባው ቃል ኪዳን አማናዊ መሆኑን የሚመሰክሩ ናቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለሐዋርያት በማቴ 28፥20 ላይ "እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ" ብሏቸዋል ይህ ማለት ግን ሐዋርያት እስከ ዓለም ፍጻሜ ይኖራሉ ማለት ሳይሆን ለሐዋርያት የተሰጠው ጸጋ እስከ ዓለም ፍጻሜ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ይቀጥላል በእነርሱ እግር የሚተኩትም የጸጋው ተሳታፊ፣ የክብሩ ባለቤት ይሆናሉ ማለት ነው እንጂ ታዲያ ለሐዋርያት የተሰጠው ክብር፣ ጸጋና በረከት እስከ ዓለም ፍጻሜ ከቤተ ክርስቲያን ጋር መሆኑን ከምናረጋግጥባቸው መንገዶች አንዱ በቅዱሳት መጻሕፍት በተጻፉት የቅዱሳን ታሪኮችና ሥራዎች ነው።
✍ በሐዋርያት ዘመን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በ90 ዓ/ም አካባቢ በተጻፈው በዮሐንስ ራእይ የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ላይ ያበቃል ከዚያ በኃላ በወንጌል አምነው፣ በሐዋርያት እግር ተተክተው የተጓዙት የቤተ ክርስቲያን ልጆች ታሪክና ተጋድሎ የት ይገኛል? በአዋልድ መጻህፍት ነው።
✍ እነ ልበ አምላክ ዳዊት፣ እነ ምናሴ፣ እነ ሕዝቅኤል፣ እነ ዳንኤል፣ ሐና፣ ሰሎሞን... የጸለዩት ጸሎት ለእነርሱ ዋጋ በማሰጠቱ፣ እግዚአብሔርም ስለ ተቀበላቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል እግዚአብሔር ጸሎታቸውን የተቀበላቸው የሌሎች ቅዱሳት እናቶችና ቅዱሳን አባቶች ጸሎት ተጽፎ ምእመናን ቢጠቀሙበት እንዴት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ይሆናል?
✍ ዛሬ የተሃድሶ መናፍቃኑ ለስም የሚቀበሏቸው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን መጻሕፍት ቅድስና አረጋግጣ፣ አማናዊ መሆናቸውን ፈትና፣ በጉባኤ የወሰነችው ቤተ ክርስቲያን ናት እኛም ኦርቶዶክሳውያን እነዚህን መጻሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አድርገን የተቀበልናቸው እርሷ በጉባኤያቷ ወስና ስለሰጠችን ነው ታዲያ የተሃድሶ መናፍቃኑ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን የሰጠችንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከተቀበሉ እርሷ የሰጠችንን ሌሎች መጻሕፍትስ ለምን አይቀበሉም??? መልስ የሌለው ጥያቄ።
✞ ብቻ የተሃድሶ መናፍቃኑን ልብ ሰጥቶ ወደ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን ይመልስልን!!! አሜን!!! ✞

No comments:
Post a Comment